አስተያየት ስጡበት!
የTMH ዳይሬክተር እና "ጦርነት ለትግራይ ባህላዊ ጨዋታ ነው" በሚል የሚታወቀው አሉላ ሰለሞን ትናንት ምሽት ሶስት ልጥፎቹን በትግራይ ፌስቡከኞች ተቃውሞ ምክንያት አንስቷል።
መጀመርያ የለጠፈው የአማራና የትግራይ ህዝብ ውይይት እንደጀመረ ሲሆን ለመድረክ አዘጋጆቹ መልካም እድል ተመኝቶ ነበር። አንድ ሰዓት ባልበረጠ ጊዜ ውይይቱ ተደርጎ ህዝብ የወሰናቸው ብሎ ሌላ መረጃ ለጠፈ። በአማራ ተወያዮች በኩል የአማራ ታጣቂዎች ከወልቃይትና ራያ እንዲወጡ ስምምነት እንደተደረሰ አድርጎ አቀረበ። በሁለቱም ልጥፎቹ የትግራይ ፌስቡከኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ብለው ሲያጣድፉት በትግርኛ "በራሳችን ቻናል እንገናኝ። በአማርኛ ስፅፍ አትሳደቡ" ብሎ ፃፈ። በዚህ የትግርኛ ልጥፍ ስርም "ውሸት አትፃፍ" ተብሎ ተቃውሞ በረታበት። ሶስቱንም ፅሁፎች አጥፍቶ በትግርኛ አራተኛ ፅሁፍ ፃፈ። ፅሁፉ "የስድብ ክፍለ በዚህ ይበቃል። ወደ መደበኛ ስራችን" የሚል ነው። በዚህ ፅሁፍ ስርም ብዙ ስድብ ተፅፏል። አሉላ አሁንም ሌላ ፅሁፍ በትግርኛ ፃፈ። የአማራና የትግራይ ህዝብ ውይይት አድርጓል ያለውም ሆነ፣ የአማራ ህዝብ ወኪሎች የአማራ ታጣቂ ከወልቃይትና ራያ እንዲወጣ ተስማምተዋል ያለው እውነት ሳይሆን አስተያየት ለመሰብሰብ እንደሆነ ገለፀ።
አስተያየት ይስጡበት
1) አንድ የሚዲያ ኃላፊ መሰል እውነት ያልሆኑ መረጃዎችን ማስተላለፍ አለበት?
2) የአማራና የትግራይ ህዝብ መካከል መፍትሔ ለማምጣት መሰል የሀሰት መረጃዎች ምን ያህል እንቅፋት ይፈጥራሉ?
3) አሉላ እነዚህን ሶስት ልጥፎች ለምን ያጠፋቸው ይመስልዎታል?
4) በአማርኛ ስለ ህዝብ ውይይት እየፃፈ፣ በትግርኛ አስተያያት ለመሰብሰብ ነው ያለው እንዴት ያዩታል? የግሉስ ይመስልዎታል?
5) አሉላ የሀሰት መረጃ ሲለጥፍ ተቃውመው ያስነሱትን የትግራይ ፌስቡከኞች እንዴት ይገልፁዋቸዋል?