Zemedkun Bekele (ዘመዴ)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


• የምፈልገውን መረጃ በዚህ ፍጥነት አግኝቻለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን። ሁላችሁንም ስለ ፈጣን ምላሻችሁ አመሰግናለሁ… 🙏🙏🙏


እፈልጋለሁ…!

"…በኢትዮጵያ ያላችሁ የዘመዴ ቴሌግራም ቤተሰብ የሆናችሁና በሳተላይት ዲሽ ሥራ ላይ የተሰማራችሁ ቤተሰቦች ለአንድ መረጃ ተፈልጋችሁ ነውና እዚህ ግሩፕ ውስጥ ካላችሁ አንድ ጊዜ በውስጥ መስመር ብታናግሩኝ ደስ ይለኛል።

• በ +49 152 15070996 ላይ በኋትስአፕ ላይ አለሁ በሉኝ።

• ፍጠኑ…! 🙏


ዛሬም ይቅርታ…!

"…ምን የመሰለ እጅ የሚያስቆረጥም ርእሰ አንቀጽ ለማዘጋጀት ቅመማ ቅመሙን ሁሉ አዘጋጅቼ ነበር። ከኤርትራ፣ ከኦሮሙማው ምድር፣ ከኤምሬትስ፣ ከዐማራ ምድር፣ ከትግሬም ምድር አሉ የተባሉ ቅመማ ቅመሞችን አዘጋጅቼ ነበር። ሽንኩርቱን፣ ቲማቲሙን፣ ጎመኑን፣ ድንቹን ሁሉ ከትፌ ከታትፌ፣ ቃሪያ ሰንጌ፣ ዳጣና ሚጥሚጣ ሁሉ ደርድሬ፣ ዘይቱን፣ ጨዉን አዘጋጅቼ መከለሻው አልቀረኝ በቃ ልወጠውጠው ስል ነው የማልቀርበት ጉዳይ የገጠመኝና ሠርቼ ሳላቀርብላችሁ የቀረሁት። ኢንቂርታ🙏

"…በዚያ ላይ እየመጣ እና ጣጣውን ጨርሶ አየር ላይ ለመዋል እየተዘጋጀንበት በሚገኘው የዘመድ ሚዲያ የሳተላይት ስርጭት የሙከራ ቀን ስርጭት ላይ የሚቀርቡ መርሀ ግብሮችን መረጣና ዝግጅቶችን ማሰናዳቱም ሌላው የዘገየሁበት ምክንያት ነው።

"…የዘመድ ሚዲያ 120 ቤተሰቡም 3 ሰው ጨምሮ 123 ሆኖ ተጠናቅቋል። እኔ የፔጁ አዘጋጅ ከቁጥር ስወጣ 122 ሰው ቤተሰብ ሆኖ ተመዝግቧል። በሁሉ የረዳን እግዚአብሔር ይመስገን።

"…የግል ጉዳዬን ጨርሼ በጊዜ ከመጣሁ የሆድ የሆዳችንን እያወጋን ምሽታችንን አደማምቀነው እናሳልፋለን። ነገ ግን እንደበቀደም ዕለቱ በጠዋት ምስጋናችንን እንደጨረስን የዛሬውን ጉደኛ ርዕሰ አንቀጽ ወደናንተ አደርሳለሁ። የነገ ሰው ይበለን።

• እኔ ግን ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ። ዘመድ ሚዲያ እየመጣ ነው።

30.3k 0 2 359 1.7k

"…ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ። ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። ፊሊ 3፥ 16-19

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

38k 0 2 1.7k 1.5k

8 ሰው ብቻ ቀረን

"…እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በሚቀጥለው ሳምንት የዘመድ ሚዲያ የሳታላይት መርሀ ግብር ስርጭቱን ይጀምራል ብለን ተስፋ እንዳረጋለን። ሁሉም ነገር እጅግ ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ተሳክቷል። እግዚአብሔር ይመስገን።

• 318 ቱ ሠራዊተ ጌዴዎኖችን አመስግኑልኝ። ተረባረቡ አይገልጸውም።

• 318 ቱን የሚያግዙ 120 ቤተሰብ እፈልጋለሁ ብዬም ነበር። በጥሪው መሠረት 112 ሰዎች የዘመድ ሚዲያ ቤተሰብ ለመሆን ተመዝግበዋል።

• አሁን የሚቀረን 8 ሰው ብቻ ነው።

~ ኑ የዘመድ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ።

42.6k 1 5 11 1.4k

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
"…የዘመኑ የእግዚአብሔር ፍርድ ከዓይን ጥቅሻ በእጅጉ የፈጠነ ነው። እንደ ድሮው በልጅ ልጅህ ይደርሳል ብለህ አትጠብቅ።

• ፈጣን ፍርድ ⚖⚖⚖

44.1k 1 83 172 1.5k

ጊዜ ቂጣው…

"…ይሄ የምታዩት ትዕይንት እዚያው በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የካቲት 23/2017 ዓም በዕለተ እሑድ ሰንበት የታላቁ የዓድዋ የድል በዓል በሚከበርበት ዕለት የተፈጸመ ነው።

• ጊዜ የሰጠው ቅል…

"…ባለ ጊዜ ምኒሊካውያንን በየሱስ ስም አስሮ፣ በር ዘግቶ የፓስተር ዮናታንን ፎቶ በጨርቅ አሠርቶ አይደለም በምሽት በቀን በብርሃን የማይቻል፣ የማይሞከረውን ሰልፍ በምሽት…

"…ጣልያን በገዛን ኖሮ አላለም ልጁ። ትውልድ እንዲሆን የተፈለገው እኮ እንዲህ ነው። ተስፋ እንድትቆርጥ፣ ፈጣሪስ የታለ እንድትል፣ ነፃነት የሚኖርህ ጴንጤ ስትሆን ነው ብለው እያሳዩህ ነው። አባቴ ጽና… ጽና አልኩህ… ጊዜ ቂጣ ነው።

44.5k 1 37 96 1.6k

ከዓድዋ ድል በኋላ…

"…ከታላቁ የዓድዋ ድል በኋላ በግልጽ፣ እንዲረክሱ፣ በሀገሬው ሕዝብም እንዲጠሉ ጠላት በብርቱ የደከመባቸው።

ሀ፦ራሱ ዓድዋ የሚለው ስም
ሁ፦እምዬ ምኒልክ
ሂ፦የዐማራ ነገድ
ሃ፦የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሄ፦ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ህ፦ታቦት እና ማርያም
ሆ፦ሰንደቅ ዓላማ እና ሀበሻ

• ሀ፦ጠላት ኢትዮጵያን የሚያደሙ ባንዳዎችን በሙሉ ከዓድዋ ከተማ መረጠ። መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ወዘተ ከከዓድዋ ብቻ ተመረጡ። ከሌላኛው የትግሬ ክፍል እምብዛም ነው። ዓድዋ በእነሱ ምክንያት ተጠላ። ሁ፦በዓድዋ የጦር መሪ በእምዬ ምኒልክ ላይማ የሚዘንበው የጥላቻ ዶፍ ምኑ ይነገራል? ሂ፦ ጦርነቱን የመራው ነገደ ዐማራው ነውና በሚል ይኸው መቶ ዓመት ሙሉ ፍዳውን እያየ ነው።

• ሃ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ዋነኛዋ ጠላት ተደርጋ የምትሰቃየውም ለዚሁ ነው። ከመሃል አዲስ አበባ ዓድዋ ድረስ የዘመተው ታቦተ ጊዮርጊስንማ በደንብ ነው የተበቀሉት። ቢራ አድርገው ቅዱስ ሥዕሉ ተረገጠ፣ ሽንት ተሸናበት፣ ተረገጠ፣ ተዋረደ፣ ቄሶቹ ራሱ ጠጥተው እንዲሰክሩበት ተደረገ። ታቦት ቅርስ ነው እንዲል ብርሃኑ አድማስ፣ ለሦሰተኛው መቅደስ ታቦተ ጽዮን ትመለስ ዘንድ ኢትዮጵያውያን ታቦት እንዲጠሉ በሰፊው ተሠራ። ምኒልክ ማርያምን ብለው በመማላቸው ምክንያት ማርያም የሚለው ስምም ከምኒልክ በላይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ይጠላ ዘንድ በሰፊው ተሠራ። ሆ፦ የቀረው ሰንደቅ ዓላማዋና ሀበሻ ነበር። ሰንደቅ ዓለማው በዓድዋው ሾተላዮች ረከሰ፣ በኦሮሞ የወያኔ ገረዶች ተዋረደ፣ ተቃጠለም። ሀበሻ የሚለው ክቡር ስምም ነበር እሱም ቢራ አድርገው አመጡት። አሁን ላይ እሱም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ በየቦታው ይረገጣል። ሽንት ይሸናበታል። ቆሻሻም ተደረገ።

• አይገርምላችሁም?

• የረሳሁት፣ ያስቀረሁት ካለም ጨምሩበት…

42.4k 1 37 47 1.3k

"…ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰቆ ኤር 3፥ 22-23። “…እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው። መዝ 92፥1። እናም ተወዳጆች ሆይ “…ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ፤” ቆላ 4፥2።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

47.4k 0 11 1.6k 1.6k

"…ገብተናል ገባ ገባ በሉማ…

http://tiktok.com/@zemedkun.b


"…በቲክቶክ መንደራችን ሞቅ፣ ደመቅ፣ ሸብረቅ፣ የባንዳንና የባንዳ ልጆችን ወሽመጥ ቆረጥ፣ ጉምድ፣ ጉምድምድ እያደረግን እኛም ኮራ ጀነን፣ ቀብረር እያልን የታላቁን የዓድዋ የድል በዓላችንን ብናከብርስ ምን ይላችኋል…?

• ዘራፍ አካኪ ዘራፍ እያልኩ ልመጣ ነኝ…

49.2k 0 5 140 1.3k

• አትገቡም… አትወጡም…!

"…ዛሬ የካቲት 23/2017 ዓም የወሄጴኑ የኦሮሙማው አገዛዝ መሃል ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሠራዊቱን ልኮ በደቡብ በር በምኒልክ አደባባይ በኩል የቤተ ክርስቲያኑን በር በዚህ መልኩ በውስጥም፣ በውጪም ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ ውሏል። 😂

"…ወደ ገነተ ጽጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለማስቀደስ ለመግባት ከሰሜን ሆቴል፣ ከአፍንጮ በር፣ ከሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ፣ ከቸርቸር ማለፍ አይቻልም ነበር አሉኝ። ፍተሻው ለጉድ ነበር፣ ነጠላ ያልለበሰ ሰውም ማለፍ አይችልም ነበር አሉኝ።

"…የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ኦሮሞ ናቸው ያውም የወለጋ ኦሮሞ፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ትግሬ ነው። ዓድዋ ደግሞ… 😂😂 ኧረ ላሽ…

"…ቤተ ክህነቱ ዝም፣ ጭጭ፣ ነገ ቅዳሴ መግባት አትችሉም ቢላቸውም የሚተነፍሱም አይመስልም። አይ ኦሮሞ አለ አቢይ…!

"…በኮሪደር ልማት ሰበብ ያጸዱትና እንጨቆረር የከተቱት ምእመን አይመጣም፣ ቤተ ክርስቲያንን ያለ ምእመናን አስቀርተናል ብለው ቢያስቡም ሰዉ ከእንጨቆረርም ቢሆን በገፍ መምጣቱን አልተወም። ይሄም ለወሄጴኑ የእግር እሳት ነው።

"…በደብረ ዘይት የቅድስት ሥላሴን ካቴድራል አፍርሰው የሕዝቡን ሙቀት ለክተዋል። ዝም ጭጭ ነው ያለው ሕዝቡ፣ አሁን ተክለሃይማኖት መርካቶ፣ በዓታ፣ ግቢ ገብርኤል፣ አራዳ ጊዮርጊስ፣ ቅድስተ ማርያም፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን በቀጣይ ቢያፈርሱት እንኳ ቅዱስ ሲኖዶሱ አይተነፍስም።

• እየመዘገባችሁ… ይብላኝ ነገ አኬሩ የተገለበጠ ጊዜ…

43.4k 1 32 50 1.5k

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
~ የዘንድሮው የዘመነ ኦሮሙማው የ2017 ዓም የዓድዋ በዓል አከባበር… 😂😂😂 ጭው፣ ጭር፣ ዝም… ጮጋ…

"…ወዳጄ ጊዜ ቂጣ ነው… ይገለባበጣል…! እንዲህ እንደሆነ አይቀርም። እንደመሸም አይቀርም። ለዛሬ ግን እነ ወሄጴን መጣም፣ መጣም ደስ ብሏቸዋል። እምዬ ምኒልክን በአካል አግኝተው የተበቀሉ ያህል ነው የተሰማቸው አይገልጠውም።

• ከምር ጥልያን ራሷ ሳትደነግጥ አትቀርም። 😂

45.3k 1 29 72 1.3k

ድሮ ድሮ…

"…የታላቁ የዓድዋ የድል በዓል በሀገረ ኢትዮጵያ በዋና ከተማዋ በአዲስ አበባ በምኒልክ አደባባይ እንዲህ ባለ ከፍ ባለ ክብር ይከበር ነበር። ድሮ ነው ድሮ ከዛሬ ሁለት ሦስት ዓመት በፊት።

• የዘንድሮውን ደግሞ ቆይተን እናየዋለን።

43.8k 1 11 40 1.1k

• ቪቫ ምኒልክ…✊

"…የነፃነት ያይደለ የድል፣ የአሸናፊነት በዓላችንንና የድሉ መሪን የእምዬ ምኒልክን፣ የአርበኞቻችንን በዓል ሞቅ ደመቅ አድርገን እያከበርን ነው።

ከይቅርታ ጋር…

"…ይሄ የድል በዓል፣ የጠላት ባሪያ፣ አሽከር፣ ገረድ የሆናችሁ ጥቂት የትግሬ እና የኦሮሞም ስም የያዛችሁ፣ የምኒልክ ስም ሲነሳ የሚያስጓራችሁ፣ የሚነስራችሁም የባንዳና የባንዳ የልጅ ልጆች እንቁላል ቀቃይ መንገድ መሪ የአቃጣሪ ልጆችን፣ እንዲሁም የምኒልክ ኦርቶዶክስ መሆን የሚያበግናችሁ የዓረብ ገረድ የወሃቢይ እስላም እና ጆሌ ሚሽኖታን አይመለከትም።

• ዓለም በሦስት አቢዮቶች ተቀይራለች።

፩፦ በእሳት
፪፦ በኢንዱስትሪ
፫፦ በዓድዋ

"…እነዙህ ሦስት ክስተቶች የዓለምን ቋሚ ሥርዓት፣ የሰው ልጅን አኗኗር የለወጡ ናቸው። ከእነዚህ ውጪ የዓለምን ሥርዓት የለወጠ የለም። ወያኔም ኦነግም፣ ጴንጤም፣ የወሃቢ እስላሞችም ጊዜ ሰጠን ብለው ጊዜ የሰጠው ድንጋይ ሰባሪ ቅል መስለው ዊኒጥ ዊኒጥ ሊሉ ይችሉ ይሆናል እንጂ ታላቁን የዓድዋን ድል መቅበር አይቻላቸውምም።

"…ብዙ የትግሬዎችን እና የኦሮሞ ጴንጤ፣ የኦሮሞ የወሃቢይ እስላሞችን ገፆች ካየሁ በኋላ ነው ደስ ደስ እያለኝ ይሄን የጻፍኩት።

• ምኒልክ ለምን ማርያምን ብሎ ማለ? ይልልኛላ ወሄጰኑ… 😂

45.6k 1 18 115 1.7k

• የት ሀገር ነው አበባ ያስቀመጡት…? 😂

"…አቤት እግዚኦ… የምኒልክ ስሙ ለባንዳ፣ ለባንዳ የልጅ ልጅ፣ ለእንቁላል ቀቃይ፣ ለጠላት መንገድ መሪ ልጆች እኮ እሳት ነው። ፈጃቸው፣ ለበለባቸው፣ አቃጠላቸው። ትኩስ ድንች ነው የሆነባቸው። ጣልያንን ለማስደሰት ይህን ያህል መገረድ ለጉድ ነው። ራሷ ጣሊያን የኦሮሞን እንዲህ መገረድ አይታ ሽምቅቅ ሳትል የምትቀር አይመሰለኝም። ማርያምን አሽከር፣ ገረድ፣ ባርያማ አይንገስ። ባርያ አይንገስ፣ ገረድ…

• ቪ ቫ ምኒልክ…✌️

44.9k 1 10 103 1.6k

እንኳን አደረሰን

"…የዛሬ 129 ዓመት ልክ በዛሬው ዕለት የካቲት 23/1888 ዓም በዕለተ እሑድ በዓድዋ ሥላሴ ግብጻዊው ሊቀጳጳስ አቡነ ማቴዎስ በመሩት ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ንጉሠ ነግሥት ዳግማዊ ዐፄ ምንልክ እና ንግሥቲቱ እቴጌ ጣይቱ በተገኙበት ከሥርዓተ ከቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ተአምረ ማርያም ተነብቦ፣ የሊቀ ጳጳሱ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ተሰምቶ፣ በጦርነቱ ላይ የሚሰዉ ኢትዮጵያውያን ጀግኖችም እግዚአብሔር ይፍታህ ተብለው፣ ቁጥራቸውም ከሰማእታት ወገን እንደሆነ ተነግሮአቸው፣ በሁዳዴ በዐቢይ ጾም እህል እንኳ በአፋቸው ሳይቀምሱ ነው በቀጥታ በባዶ አንጀታቸው ወደ ጦርነቱ ሥፍራ ሄደው በግማሽ ቀን ያን ግዙፍ የአውሮጳ ጦር ድል ያደረጉት።

"…በዚህ ድል ዓለም በሙሉ ይደመማል፣ ይኮራልም። በዚህ ድል የማይኮሩት የእንቁላል ቀቃይ ልጅ የጠላት አድራሽ ፈረስ እስከ አምባላጄ ድረስ መንገድ መሪ የነበሩ ፀረ ኢትዮጵያ ባንዳ የባንዳ የልጅ ልጆች ብቻ ናቸው።

"…ዓድዋ ፀሐይ ነው። ፀሐይ የምትጋረደው ለጥቂት ጊዜ በደመና ብቻ ነው። ደመና ደግሞ ስስ ነው። ሲያዩት ተራራ፣ ባዘቶ ጥጥ ይመስላል እንጂ ይተንናል። ይበንናል። ፀሐይን የሚጋርድ፣ የሚደብቅ ምድራዊ ኃይል የለም። ወደፊትም አይኖርም። የክረምት ደመና ጥቂት ጊዜ ዊኒጥ ዊኒጥ ይላል ፀሐይን ለመጋረድ። በክረምት የደመናን ፀሐይን መጋረድ ያየ ሰው ፀሐይ መቼም የምትወጣ ላይመስለው ይችል ይሆናል። የክረምት ደመና የፀሐይን ሙቀት እንጂ ብርሃኗን መጋረድ አይቻለውም። ፀሐይ አዲስ አበባ ላይ ብትጋረድ ሌላ ቦታ አለች። መንጋቱ፣ ቀን መሆኑን ከደመናው ጀርባ በማትታየው ፀሐይ ብርሃን ይታወቃል።

"…ዓድዋም ፀሐይ ነው። ለጊዜው መቀሌና ሸገር፣ ትግራይና ኦሮሚያ እንደ ፀሐይ ደምቆ ላይገለጥ ይችላል። ደመና ወያኔ፣ ደመና ኦነግ ኦህዴድ ሲተንኑ ፀሐይ ዓድዋ በድምቀት ይከበራል።

45.1k 0 28 120 1.7k

“…ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።” ምሳ 21፥31 “…ጻድቃን ድል ባደረጉ ጊዜ ብዙ ክብር አለ፤ ኀጥኣን ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ ግን ሰው ይሸሸጋል።” ምሳ 28፥12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

47.4k 0 16 1.5k 1.9k

መረጃ አምስት

"…አርበኛ ዘመነ ካሤ ከሰባታሚት እስር ቤት ትፈታለህ ዕቃህን አዘጋጅ ይለዋል ፖሊስ። ዘመነም ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ሳለ የእስር ቤት ጓደኞቹ እነ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴም ወደ ዘመነ በመቅረብ እንኳን እግዚአብሔር ረዳህ። ሰላም ሁን። እንግዲህ ተመላልሰህ ባትጠይቀን እንኳ አንዳንዴ አትርሳን ይሉታል። ዘመነም ጠጋ ብሎ "ኮሎኔል አይዟችሁ፣ በቅርቡ ይሄን እስር ቤት ሰብረነው ነፃ ትወጣላችሁ! ብሏቸው ተሰነባበቱ።

"…የሆነ ቀን ላይ ዘመነ እዚያው እስር ቤት ደውሎ እነ ኮሎኔል ለመውጣት እንዲዘጋጁ ይነገሯቸዋል። ማንችሎት ወደ እስርቤቱ ኃይል እንዲያስጠጋ ሲጠየቅ "ኋላ በሕግ ብጠየቅስ?" ብሎ አንገራግሮ የነበረ ቢሆንም ኃይል ተጨምሮ ዘመነ ካሤም ቃሉን ጠብቆ እነ ኮሎኔል ታዴም ከሰባታሚት ወጡ።

"…ኮሎኔሉ መልካም ሰው ነበር። እነ ፓስተር ምስጋናው፣ እስክንድር ነጋና ፋፍህዴን፣ እነ ሀብታሙ ዘፍራሳ፣ አቤ እስክስ ናቸው ኮሎኔሉን የጠለፉአቸው። በሽምግልናው ወቅትም ከእነ ባዬ ጋር ነበሩ። ኋላ ላይ የዐማራ ፋኖ በጎንደር ውክልና ሳይሰጣቸው ዘመነ መመረጥ የለበትም ብለው እስክንድርን መረጡ። ዘመነም አዘነባቸው። ብዙም አልቆዩ ኮሎኔሉ በውጊያ ላይ በጥይት ተመተው ቆሰሉ። ቆስለውም ተኙ። እንግዲህ እኚህ ለሀገራቸው ብዙ ሠርተው መጨረሻ ላይ ቆስለው ሕክምና እንኳን አጥተው በስቃይ ላይ የነበሩ ኮሎኔል ናቸው የሚደርስላቸው አጋዥ ኃይል አጥተው በኦሮሙማው ጦር በግፍ የተሰዉት።

"…ለእኔም ወዳጄ ነበሩ። በሽምግልናውም ወቅት ክፋት አላየሁባቸውም። ልብ በሉ የዐማራ ፋኖ አንድ ባለመሆኑ ምክንያት ጭራቅ ቡልጉ ጅቡ ኦሮሙማ ተራ በተራ እየበላቸው ነው። የዐማራ ፋኖ አንድ እንዳይሆን የሠራችሁ እግዚአብሔር ይፍረድባችሁ። በተለይ አስረስ መዓረይ ግን እግዚአብሔር ይይልህ። ሌላ ምንም አልልም።

• ነፍስ ይማር ወዳጄ…

49.8k 1 20 107 2.2k


20 last posts shown.