☞ጣዕረ—ሞት
ሞት የተጣደው ሰው ላይ መላእክቶች ይወርዳሉ። ከአጠገቡም ይቀመጣሉ። ወደ ሞት እየተጓዘ ያለው ሰውም በአይኑ ይመለከታቸዋል። እርሱ ዘንድ ያወራሉ። ከጀነት ወይም ከእሳት የሆነን ሐኑጥና ከፍን ይይዛሉ። ሟቹ ዘንድ ያሉ ሰዎች በክፉም በመልካምም የሚያደርጉትን ዱዓ ተቀብለው አሚን ይላሉ። ጣዕረ- ሞት ላይ ለሆነው ሰው ሰላምታን ያቀርቡለታል። ሰውዬውም ሰላምታውን በአንደበቱ አልያም በምልክት መናገርና ማመላከት ካልቻለ ደግሞ በቀልቡ ይመልስላቸዋል። በእርግጥም ጣዕረ-ሞት ላይ ካሉ ሰዎች ይህን አይነት ነገር ተከስቷል። "አህለን ወሰህለን እንኳን ደህና መጣችሁ! እነዚህ ፊቶች" ብለዋል። ሸይኻችን ጣዕረ ሞት ላይ ከነበሩ ሰዎች ተነግሮት ይሁን አይቶ አላውቅም እንዲህ ብሎ ነግሮኛል "ጣዕረ-ሞት ላይ ያለ ሰው "ዐለይከ ሰላም" እንዳለ ሰምቻለሁ።
ኢብኑ አቢ ዱንያ ይህን ጠቅሷል "ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዐዚዝ የሞተበት ቀን ላይ ቤተሰቦቹን "አስቀምጡኝ" አለ። ቤተሰቦቹም "አስቀመጡት"። እርሱም "እኔ ነኝ አዘኸኝ ትእዛዝህን ያጓደልኩ! እኔ ነኝ ከልክለኸኝ ያመፅኩ" እያለ ሶስት ግዜ ደጋገመ። ከዚያም "ነገር ግን ላ ኢላሃ ኢልለ ላህ" አለ። ከዚያም አይኑን ከፍ አድርጎ በአትኩሮት ወደ ላይ ተመለከተ። አጠገቡ ያሉ ቤተሰቦቹም "የአማኞች መሪ ሆይ! በጣም አፍጥጠህ በአትኩሮት እየተመለከትክ ነው ምንድነው?" አሉ። እርሱም "እኔ አሁን ሰውም አጋንንትም ያልሆኑ አካላቶች ቀርበው ይታዩኛል" አለና ሞተ።
ፈዳለቱ ኢብኑ ዲናር እንዲህ ብለዋል "ሙሐመድ ኢብኑ ዋሲዕን ጣዕረ ሞት ላይ ሆኖ አገኘሁት። እንዲህ እያለ ነበር "የጌታዬ መላእክቶች እንኳን ደህና መጣቹህ! ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ! ከዚህ በፊት አሽትቼው የማላውቀውን ጥሩ መኣዛ እያሸተትኩ ነው።" አለና ወዲያውኑ አይኑን አንጋጠጠና ሞተ።"
📚አ-ር'ሩሕ ኢብኑ'ል ቀይዪም
https://t.me/abdurezaq27