📚 ከሰለፎች ምክር 📚


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


أبــو مـريـم عــبــدالــســلام
📝🎤አቡ መርየም🎤📝
https://t.me/abduselamabumeryem
👆ሊንኩን ነካ በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
አስተያየትም ይሁን ምክር ወይም ወቀሳ ካላቹህ ብትልኩልኝ ለኔ ትልቅ ስጦታ 🎁 ነው
👇👇
በቦት ለመላክ 👇
@Abumeryeem_bot
ወይም 👇
@Abumeryeem

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


👌 አትከራከር

{ وَلَا تُجَـٰدِلۡ عَنِ ٱلَّذِینَ یَخۡتَانُونَ أَنفُسَهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِیمࣰا }
[سُورَةُ النِّسَاءِ: ١٠٧]

ለእነዚያም ነፍሶቻቸውን በወንጀል ለሚበድሉ ሰዎች አትከራከር

አላህ ከዳተኛ ኃጢአተኛ የኾነን ሰው አይወድምና

{ هَـٰۤأَنتُمۡ هَـٰۤؤُلَاۤءِ جَـٰدَلۡتُمۡ عَنۡهُمۡ فِی ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَا فَمَن یُجَـٰدِلُ ٱللَّهَ عَنۡهُمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ
[سُورَةُ النِّسَاءِ: ١٠٩]

ዛሬ ዱንያ ላይ ብትከራከሩላቸው
ነጌ አላህ ፊት የሚከራከርላቸው ሰው ማን አለ ❓


ስለዚህ 👇
👉አባትህም ይሁን እናትህ
👉ልጅህም ይሁን ወዳጅህ
👉ሸይኽህም ይሁን ተማሪህ
ተሳሳተ ከተባልክ ከመከራከርህ በፊት ጥፋት ነው የተባለውን ነገር ቆም ብለህ ተመልከተው እውነትም ስህተት ነው ወይስ አይደለም

ስህተት ከሆነ አንተ ያልሰራሀውን ስህተት ለአጢፊው በመከራከርህ የወንጀሉን ተካፋይ አትሁን ትጎዳለህ

ስህተት ካልሆነ ስህተት አይደለም ብለህ አስረዳ

https://t.me/abduselamabumeryem/5429


☑️ በአዩብ ላይ የወረደው ወርቅ!

♻️ በሚል ርዕስ ገሳጭና መካሪ የሆነ መደመጥ ያለበት ሙሓደራ።

🕌 በፉርቃን መስጂድ አለም-ባንክ።

📅 ማክሰኞ 04/06/2017E.C 📅

🎙️ በኡስታዝ አቡ በከር አብድረህማን ቢን ሸምሱ አላህ ይጠብቀው።

🔗 https://t.me/fewaedabibekr/4498


👉 በረመዷን ወሳኝ ተግባሮች

1️⃣ፈርድ ሰላቶችን በጀመዓ መስገድ
2️⃣የለይል ሰላት መስገድ
3️⃣ቁርአን አብዝቶ መቅራት
4️⃣ሰደቃን ማብዛትና ምግብ ማብላት
5️⃣መስጂድ ውስጥ ቆይታን ማብዛት
6️⃣ኢዕቲካፍ ማድረግ
7️⃣ምላስን መጠበቅ

https://t.me/abduselamabumeryem/5427


اللهم صل وسلم على محمد

https://t.me/abduselamabumeryem/5426




በጣም በተቆጣህ እና በተደሰትክ ሰአት የምትወስናቸው ውሳኔዎች በብዛት ትፀፀትባቸዋለህ ይላሉ ።

https://t.me/abduselamabumeryem/5423


🫵 ካንተ ማን ተሽሎ

🔶 ዱንያ ላይ ከመከራና ከጭንቀት ከሀሳብና ከሀዘን ርቆ ሁሌም ደስተኛ ሆኖ የሚኖር ሰው አለ ብለህ የምታስብ ከሆነ እጅግ በጣም ተሳስተሀል

👌 ሰዎች አንዱን የአንዱን ልብ ማየት ቢችሉ ኖሮ ሀሰድ ወይም ምቀኝነት የሚባል ነገር ባልኖረ ነበረ ይላሉ ከፊሎች

እያንዳንዷ ልብ የራስዋ የሆነ ጭንቀትና ሀዘን መከፋትና መደሰት አላት

ግን የምናያው የውጪ ዲኮር ብቻ ስለሆነ አናውቅም

👉 አንድ ምርጥ የሚያምር ጫማ የለበሰ ሰው ጫማውን ብቻ አይተህ አቤት መታደል አትበል ምናልባትም እኮ ጫማው ጠቦት እየፋቀው አውልቆ የሚጥልበትን እድል እየተጠባበቀ ይሆናል የልብ ጥበት ከእግር ይብሳል

👌 በሀሰት ገፅታ አትሸወድ
👌 በምታየው ሳቅ ሁሉ አትታለል


የአላህ ኒዕማ ስታስታውስ ከእኔ የተሻለን ነገር የተሰጠው ሰው አለ ብለህ እንዳታስብ

ላንተ የሆነው ተሰጥቶሀል
ላንተ የሚሻልህን ተደርጎልሀል

፣ فَخُذْ مَا آتَيْتُكَ وَكُنْ مِنَ الشَّاكِرِينَ

የሰጠሁህን ያዝና ከአመስጋኞቹ ኹን

✍️ አቡ መርየም

https://t.me/abduselamabumeryem/5422


ጥሎብኝ ኢባዳ የሚያበዙ ሰዎችን እወዳለሁ ግን ከነሱ አያደለሁም

ሸይኻችን ዓድናን በኢባዳ የታወቁ ናቸው ።


✅ አዲስ ሙሓደራ ከፉርቃን
       መስጂድ።
⤵️⤵️

🎧  تسجيلات الفرقان الإسلامية السلفية في الحبشة يسرها أن تقدم لكم هذه المادة وهي عبارة عن محاضرة.......

🎧 አዲስ ሙሓደራ ከአል ፉርቃ ኢስላማዊ ስቱዲዮ.......

🔖 أسباب البركة في الدعوة

🔖  በዳዕዋ ላይ በረካን ማግኛ ሰበቦች!


🎙️ للشيخ الفاضل أبي اليمان عدنان بن حسين المصقري حفظه الله ورعاه

🎙️ በታላቁ ሸይኽ አቡል የማን አድናን ኢብኑ ሁሴይን አል-መስቀሪ አላህ ይጠብቀዉ።

🗓️ سجلت يوم يوم الثلاثاء في ٥ - شعبان ١٤٤٦هـ في مسجد الفرقان في الحبشة حرسها الله تعالى
🗓️ ሻዕባን {05-1446 ሂጅሪያ } ማክሰኞ በታላቁ ፉርቃን መስጂድ አላህ ይጠብቃት።

📎 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17843


✍
    የዕሮብ ውሎ በደርስ ተሞሽሮ!!

   በሰለፍዮች ኮከብ ደምቃ ያመሸችው ፉርቃን ውሎዋንም በመሻኢኾች እና በመድረሳ ልጆች ለማፍካት ቀጠሮ ይዛለች!!


  ነገ (ዕለተ ዕሮብ) ቀን ሙሉ በሁለቱም መሻኢኾች መስጂድ አል_ፉርቃን ላይ ለመድረሳ ተማሪዎች ለየት ያለ የደርስ ፕሮግራም ይደረጋል።



  ፕሮግራሙ ለየት ባለ መልኩ ለመድረሳ ተማሪዎች የሚደረግ የደርስ ፕሮግራም ሲሆን; ከወንድም ይሁን ከሴት መገኘት የሚችል ሁሉ መሳተፍ ይችላል!!

  ፕሮግራሙ የሚደረገው ቀኑን ሙሉ ሲሆን ቦታው መስጂድ አል_ፉርቃን ነው!!

  ለዚህም ሲባል በነገው ዕለት አጠቃላይ አዲስ አበባ ያሉ የሰለፍዮች መድረሳዎች ዝግ ይሆናሉ!!

  ረፋድ 🕰3:00 ሰዓት ሲሆን የሁሉም መድረሳ ተማሪዎች ፉርቃን መስጂድ ተገኝተው ፕሮግራማቸው መከታተል ይኖርባቸዋል!!



በነገው ፕሮግራም የሚቀሩ ኪታቦች ዝርዝር…………
🪑በሸይኽ አቡል የማን ዓድናን የሚጀመሩት
📚عقيدة سفيان الثوري
📚كتاب الصيام من كتاب عمدة الاحكام
📚فضائل القرآن للامام النجدي.


🪑በሸይኽ አቡ ዐብደላህ ኸዛእ አል_ዓንሲ የሚጀመሩት;
📚نواقض الإسلام
📚زاد الصغار
📚باب الاعراب من متن الاجرومية






💻ይህ የሰለፍዮች ልሳን የሆነው "አል_ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱድዮ" ነው!!
https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio
   


Forward from: አል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ኢንሻ አሏህ ሙሀደራው ከዝሁር ሰላት በኋላ የሚጀምር ይሆናል።


የረሳናው 99 ዲናር 👇

👉 ንጉስ ነው ደስታ ሸሽቶታል ቀኑ ሀሳብ ነው ለሊቱ ጭንቀት ነው እንቅልፍና እሱ እየቆዩ ነው የሚገናኙት

🔶አገልጋዩ ደሞ ሁሌም ደስተኛ ነው ጠዋት ይገባል ማታ ይወጣል ፈገግታና ደስታ ከፊቱ አይጠፋም

👉ንጉሱ በጣም ተገርሞ ለአማካሪው ኻዲሜ ሁሌም ደስተኛ ሆኑ ሳየው በጣም ተገረምኩኝ የሱን የደስታ ምንጭና የኔን የጭንቀት ምክንያት ምንድን ነው ትላለህ ይለዋል

🔶አማካሪውም እስኪ ዛሬ ወደ ቤቱ ሲሄድ 💯 ዲናር ነው በልና
99 ዲናር ስጦታ ስጠው ግን እንዳትረሳ 💯 ዲናር ነው በለው ይለዋል

👉ንጉሱም ምክሩን ተቀበለና 99 ዲናሩን ለኻዲሞ 💯 ዲናር ነው ብሎ ይሰጠዋል

🔶ኻዲሙም ቤቱ ደርሶ ሚስቱና ልጆቹ ፊት በደስታ የተሰጠውን ዲናር ሲቆጥረው 99 ይሆናል

🔶 ደጋግሞም ቆጠረው 99 ዲናር ነው አንድ ዲናር አሁን ማን አነሳብኝ ብሎ ከቤተሰቡ ግብግብ ፈጥሮ በኔዴትና በቁጭት ሳይተኛ ያድራል

🔶ጠዋት ገና ሲነጋለት ምናልባት መንገድ ላይ ስነካካው ወድቆ ይሆናል ብሎ ማታ በመጣበት መንገድ ወደ ንጉሱ ይመለሳል

👉ንጉሱ ላይ ሲገባ ያ የበፊቱ ፈገግታና ደስታ ጠፍቶ አይኑ ቀልቶ ተጨንቆ ያየዋል ንጉሱም ምን ሆንክ ይለዋል ኻዲሙ ሰይዴ ማታ ከሰጡኝ ዲናር አንድ ዲናር ጠፍቶኝ ሳልተኛ አደርኩኝ ይላል

👉የዚን ጊዜ ንጉሱ የደስታ ማጣቱና የጭንቀቱን ዋናው ምክንያት ምን እንደሆነ አወቀ


🔶ኻዲሙ የ 99 ዲናር ባለቤት መሆኑን ረስቶ ሀሳቡና ጭንቀቱ ስላጣት አንድ ዲናር ብቻ ሲሆን ደስታው በሀዘን ቀየረው

👉የንጉሱም የጭንቀት ምክንያት እጁ ላይ ያለውን ማየት ትቶ ወደ እጁ ያልገባውን ማሰብ ነበረና በቀላሉ ተማረ

🫵እኛም የረሳናቸው ስንትና ስንት 99 ዲናሮች አሉን የተሰጠንን ረስተን ነው እንጂ የጎደለን ነገር ወይም የለም
ወይም ከተሰጠን አንፃር የጎደለን በጣም ትንሽ ነው

⭕ የተሰጠህን ተቀብለህ አመስግን
⭕ ላልተሰጠህ አትጨነቅ
⭕ ሁሉም ለበጎ ነው

﴿لَا تَحْسَبُوهُ شَرًّا لَكُمْ بَلْ هُوَ خَيْرٌ لَكُمْ﴾
ለናንተ ክፉ ነገር ነው ብላችሁ አታስቡት እንደውም እሱ ለናንተ መልካም ነገር ነው

✍ አቡ መርየም

https://t.me/abduselamabumeryem/5413


ኢማም ኢብኑ ሙንዚር እንዲህ ይላሉ

ጠቃሚ የሆነን እውቀት ኮፒ የሚያደርግ የሆነን ሰው አጅር ምንዳ አለው ኮፒ ያደረጉውን ያነበበ፣ የፃፈና የሰራበትን ሰውም ምንዳ ያገኛል

ተመልከቱ 👇
ሁለት አጅር ነው የሚያገኘው

አንደኛ ኮፒ ያደረገበትን
ሁለተኛ ሰዎች የተጠቀሙበትን

ስለዚህ አንተ አንብበሀው ተፅኖ ያላሳደረብህን አንተ የላክለትን ሰውዬ ግን ወደ አላህ መመለሻ ሰበብ ሊሆነው ይችላልና ጠቃሚ ፁሁፎችም ይሁኑ ድምፆች ሼር ከማድረግ አትዘናጉ

እዚ ቻናል ውስጥ የሚለቀቅ ነገር
ከቻላቹህ ከነ ሊንኩን ሼር ብታደርጉ መልካም ነው ይሄ ሱቅ አይደለም ስለዲናችን የምንጠቃቀምበት ቻናል ነው

ካልፈለጋቹም ሊንኩን አስወግዳቹህ ሼር አድርጉ መጨረሻ ላይ ተጠቃሚዎቹ እኛው ነን

ብቻ ነብያችን ﷺ በሊغُو ዓኒ ወለው አያህ ያሉትን አንርሳ

قال الإمام ابن المنذر:
وناسخ العلم النافع له أجره وأجر من قرأه أو كتبه أو عمل به.

(الترغيب والترهيب (1/65))

https://t.me/abduselamabumeryem/5412


ኢብኑ ተይሚያ ይቀጥላሉ 👇

👌 እኔ ለሚቃረኑኝ ሰዎች ልቤ ሰፊ ነው በማክፈርም ይሁን በማፈሰቅ በቅጥፈትም ይሁን በወገንተኝነት
እኔ ላይ የአላህ ድንበር ቢተላለፉብኝም እኔ በእነሱ ላይ የአላህን ድንበር አልተላለፍባቸውም

እንደውም የምናገረውና የምተገብረውን በፍትህ ሚዛን እመዝነዋለሁ ይላሉ ።

• - قالَ شيخُ الإسلامِ أبو العباس ابن تيمية
• ‏أنا في سَعة صَدرٍ لمنْ يُخالفني، فإنه وإن تعدَّى حدود اللهِ فيَّ بتكفيرٍ، أو تفسيقٍ، أو افتراءٍ، أو عصبيّةٍ جاهلية. فأنا لا أتعدّى حدود الله فيه. بل أضبطُ ما أقولهُ وأفعلهُ، وأزِنهُ بميزانِ العدل، وأجعله مؤتمًا بالكتاب الذي أنزله الله، وجعله هدى للناس.
📜مجموع الفتاوى (٢٤٥/٣)


🤲 ያረብ ለባረያህ አቡ አልአባስ ኢብኑ ተይሚያ እዘንላቸው በፊርደውስ አንድ ላይ አድርገህ አኑረን

https://t.me/abduselamabumeryem/5411


በእኛና በሰለፎች መሀከል ያለው ልዩነት 👇

👉 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ

🔶 ከዋሸብኝ ፣ ከበደለኝና ድንበር ካለፈብኝ ሰው ማንንም ሊበቀልልኝ አልፈልግም

🔶 እኔ ለሁሉም ሙስሊሞች ኸይርን እመኛለሁ

🔶 ለራሴ የምወደውን ለሁሉም አማኞች እወድላቸዋለሁኝ

🔶 እነዚያ የዋሹብኝና የበደሉኝ በኔ በኩል ይቅር ብያቸዋለሁኝ ይላሉ ።

👇👇👇
👌ልዩነቱ አሁን በየ ሀገሩ የሰለፊያን ዳዕዋ ፍርክስስ ካደረጋት ምክንያቶች አንዱ ወገንተኝነት ነው

ሁለት ሸይኾች ወይም ሁለት ዳዒዎች ዲናዊ ባልሆነ ሰበብ እንኳ ቢሆን ይጣሉና ከዚያም ሰዎች ለሁለት ይካፈሉላቸዋል ይሄኛውም ለሙስሊም ወንድሜ ዲፋዕ እያረግኩኝ ነው ይላል ያኛውም ለሙስሊም ወንድሜ እየተከላከልኩኝ ነው ይላል


🔶 ግን ሀቁ መሆን የነበረበት ዋናው የጉዳዩ ባለቤት እንኳ እኔ ለራሴ አልበቀልም ይቅር ብያለሁ አትበቀሉልኝ ማለት ነበረበት

ምክንያቱም የነብያችን ﷺ ባህሪ ይሄው ነበረ ለራሳቸው ተበቅለው አያውቁም

ሰለፎችም በዚው መስመር ነው ያለፉት

👌ግን ዲን የግል ክብር ማስጠበቂያ በሆነበት ዘመን ነገራቶች ተቀያየሩ

• - قالَ شيخُ الإسلامِ أبو العباس ابن تيمية
• فَلَا أُحِبُّ أَنْ يُنْتَصَرَ مِنْ أَحَدٍ بِسَبَبِ كَذِبِهِ عَلَي،َّ أَوْ ظُلْمِهِ وَعُدْوَانِه،ِ فَإِنِّي قَدْ أَحْلَلْت كُلَّ مُسْلِمٍ .
• - وَأَنَا أُحِبُّ الْخَيْرَ لِكُلِّ الْمُسْلِمِين،َ وَأُرِيدُ لِكُلِّ مُؤْمِنٍ مِنْ الْخَيْرِ مَا أُحِبُّهُ لِنَفْسِي ، والذين كذبوا وظلموا فهم في حِلٍّ من جهتي".
📜مجموع الفتاوى (٥٥/٢٨)


https://t.me/abduselamabumeryem/5410


👉 ፣ أوصني لا تغضب
ምከሩኝ ሲላቸው
አትቆጣ አሉት ነብያችን ﷺ

🔶 በቁጣ ጊዜ ለአንድ ደቂቃ የሚደርግ ትእግስት ለብዙ ወራቶች ከፀፀት ያርቃል ይላሉ

🔶ለሰከንዶች ትእግስት አለማድረግ የስንቶችን ሂወት ቀጥፏል ስንቶችን ደግሞ ወደ ዘብጢያ አውርዷል

👌 ተቆጥተህ ምንም አይነት ውሳኔ አትወስን


https://t.me/abduselamabumeryem/5409


👉ተናድጄ ነው ❗
👇
👉 ያንተ ብስጭትና የውስጥህ ህመም አንተን ብቻ ነው የሚመለከተው

🔶 አንተ ቢደላህም ቢከፋህም ሌሎችን በስረአት ማውራትህ አንተ ላይ ያለ የነሱ ሀቅ ነው

⭕ በድለህና አስቀይመህ ስታበቃ እከሌ አናዶኝ ነው ወይም ራሴን አሞኝ ነው ማለትህ ኡዝር አይሆንህም

https://t.me/abduselamabumeryem/5408


👉 በሰዎች ጅልባብ ውስጥ አትደበቅ
👉 እንደሰዎች አመለካከት አትኑር
👉 ከአላህ በስተቀር ማንንም አትለምን
👉 ከማንንም ውዳሴ አትጠብቅ
👉 ሰዎች ተገረሙብህ ወይም ናቁህ አያስጨንቅህ

👌 ካልሆነ በሰዎች እጅ ያለህ አሻንጉሊት ትሆናለህ


https://t.me/abduselamabumeryem/5407


👌 ሂወታችን በአጭሩ

1⃣ 60 ወይም 70 አመት የዱንያ ቆይታችን

2⃣በሺ የሚቆጠሩ አመታት የቀብር ውስጥ ቆይታችን በቅርቡ የሞቱት ነብያችን ﷺ እንኳ ቀብር ውስጥ 1400 አመታት አስቆጥረዋል


3️⃣ የቂያማ ቀን ቆመን የምናሳልፈው ቆይታችን 50 ሺ አመታት

4️⃣ ዘላለማዊው ሂወት ጀነት ውስጥ ወይም ጀሀነም ውስጥ

ሂወት ይቺው ነች !

https://t.me/abduselamabumeryem/5406


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
https://t.me/abduselamabumeryem/5405

20 last posts shown.

4 929

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

👉 አል-ፉርቃን ቻናል የእንግዶች አቃባበልና መቀበያ ቦታ እንደ እንግዳው አይነት ሊለያይ ይችላል ወደ ሱና የሚመጡ ሙስሊሞችንም እንደ ሁኔታቸው የሚመጥና...
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ይድረስ ሳውዲ ለመምጣት ለሚያስቡ ወንድሞች በፍሪ ቪዛ ወደ ሳውዲ እናስመጣለን ብለው የሚሉ የወንድሞ...
⚠️ ባለትዳሮች አዳምጡት! ጥያቄ - አንዲት ሴት ባለቤቷ በዲኑ ጠንካራ, ለሷም መልካም ሆኖላት ልትወደው ስላልቻለች ብቻ ፍቺ መጠየቅ ትችላለች? ምንስ ት...
ፊሊስጢናውያን ህፃናቶች ሴቶች ወገኖቻችን ከነቤቶቻቸው ሲያጋይዋቸው ሰንብተዋሉ እነሱም በተራቸው የሀያሉ ጌታችን ጁንድ የሆነችውን እሳት 🔥 አይናቸው እ...
፡الحمد لله ፊሊስጤናዊያን ወገኖቻችን ከአስከፊው ጦርነት እርፍ ስላሉ ደስ ብሎናል የሙስሊሞች ደስታ ያስደስተናል ህመማቸው ያሳምመናል ከከፊሎች አባባ...