✅ወጣትነት❗️
👉ወጣትነት በሁለት ድክመቶች መሀል የሚገኝ ብርታት በመሆኑ ለብዙ ፈተናዎች የተጋለጠ እርከን ነው። ለማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ጌጥ እና ውበት ብሎም የጥንካሬው ሚስጥር ነው። በማንኛውም ህብረተሰብ ወጣቱ የአፍላ ጉልበት ፤ የብሩህ አእምሮና እምቅ ሀይል ባለቤት ነው። ስለሆነም ለወጣቱ ትኩረት የማይሰጥ ስርአት የወደፊት ህልውናው ለአደጋ የተጋለጠ ነው።
👉 ኢስላም የህይወት መንገድ ነው። ለአማኝ ሰዎች ምቹ እና የመንፈስ መርጊያ ጭምር ነው። ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ይህንን ዲን ለማስተማር እና ለማስፋፋት ከአላህ እርዳታ በመቀጠል የወጣቱ ሚና የጎላ እንደነበር በሀዲሳቸው ነግረውናል። ሁለንተናዊ ባህሪና ይዘት ያለው ኢስላም በወጣቶች ትከሻ ላይ በመሆን የምድርን ገላ ከእድፍ አጸዳው።
👉አሊይ ኢብኑ ጧሊብ፣ዘይድ ኢብኑ ሳቢት፣ሙአዝ ኢብኑ ጀበል፣ ሙስአብ ኢብኑ ኡመይር፣ ሰአድ ኢብኑ አቢ ወቃስ፣ዙበይር ኢብኑል አዋም፣ ጦልሀ ኢብኑ ዑበይዲላህ ረዲየላሁ አንሁም አጅመዒን እና ሌሎችም በርካታ ሰሀባዎች ከ 10 - 20 ባለው የእድሜ ክልላቸው እስልምናን በመቀበልና ለእስልምና እድገት ታላቅ ተጋድሎ የፈጸሙ ብርቅዬ ወጣት ሰሀቦች ነበሩ።
👉ወጣትነት ላይ አእምሮ በፍጥነት የሰጡትን ይቀበላል፤ ያስተነትናል።ልብ ደም ይረጫል ፤ ደም ይዘዋወራል ፤ አይኖች በሚገባ ያያሉ፤ ጆሮ ሁሉን ይሰማል፤ አግሮችና እጆች ሁሉን ይፈጽማሉ። እርጅና ለይ ግን አዕምሮን በቀላሉ መግራት ይከብዳል። አስቀድሞ የያዘውን ሙጥኝ ይላል። አዲስ ሀሳብን ተቀበል ቢሉት ወኔው ብዙም የለውም። ስለሆነም እርጅናህ ከመምጣቱ በፊት ወጣትነትህን አላህ በሚፈልገው መልኩ ተጠቀምበት።
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ምክር ይለግሱናል፦
"ከአምስት ነገሮች በፊት አምስት ነገሮችን ተጠቀም ወጣትነትህን ከእርጅናህ በፊት፤ ጤናህን ከህመምህ በፊት፤ ሰፊ ግዜህን ከውጥረትህ በፊት፤ ሀብትህን ከድህነትህ በፊት እና ህይወትህን ከሞትህ በፊት።👇👇👇
https://t.me/ebnuseid01