Acibadem Healthcare Services


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Telegram


http://t.me/AcibademChatBot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Telegram
Statistics
Posts filter


አዲስ ዘመን ሲለወጥ፣ ላልተለወጠው የእርስዎ ታማኝነት እና እምነት አመስጋኞች ነን። ዓመቱን በሙሉ ደስታን እና ስኬትን እንመኝልዎታለን። መልካም አዲስ ዓመት 2024!


ለ2024 የጤና ግቦች አለዎት? አጠቃላይ የጤና ግምገማ በማድረግ መጀመርዎ ለጉዞዎ ግሩም መነሻ ይሆናል። በአቺባደም ቀደም ብለን የማወቅ እና አስቀድሞ የመከላከል እርምጃዎችን እናስቀድማለን። ምኞትዎን ወደ ተግባራዊ እርምጃዎች ለመቀየር ጊዜው አሁን ነው! የእኛን ልዩ የአዲስ ዓመት የጤና ምርመራ ጥቅል ለመጠቀም አሁኑኑ እኛን ያግኙን። ጤናዎን እንጠብቅልዎ!

#newyear #resolution #health #checkup #acibadem #Turkey


ሴቶች፤ በአዲሱ አመት ለጤንነታችሁ ቅድሚያ ስጡ፡፡ የእኛ "የሴቶች የጤና ምርመራ ፕሮግራም" የእናንተን ልዩ የጤና ፍላጎቶች ለማሟላaት በጥንቃቄ የተነደፈ ነው። ከማሞግራም (አነስተኛ ጨረር በመጠቀም የሚካሄድ የጡት ኤክስሬይ) እስከ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ድረስ፣ የጤና ጉዞዎን እና እርስዎን ለማገዝ ተዘጋጅተናል። ጤናዎን በማስቀደም 2024ን ይጀምሩ!
ያሉትን ሁሉንም የጤና ምርመራ ጥቅሎች ዝርዝሮች ለማግኘት አሁኑኑ ያግኙን።

https://www.facebook.com/100076508177885/posts/pfbid032CqhfweDboRjMTjV8DVnufB1PBQMKAhrMpig6T73isJ4iMvQ8ceGgcFxSAfbULERl/

#newyear #resolution #woman #health #checkup #acibadem #Turkey


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ክቡራን፣ ይህ አመት ለጤንነታችሁ ቅድሚያ የምትሰጡበት ነው። የአቺባደም የወንዶች ጤና መርሃ ግብር lዘርፈ ብዙ የጤና ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው። በዚህም ከልብ ህክምና ምርመራዎች አንስቶ እስከ የአእምሮ ጤና ምዘናዎች ድረስ የእርስዎን ደህንነት ቅድምያ ሰጥቶ ይመለከታል። ወደ ጤናማ 2024 የመጀመሪያዎን እርምጃ ይራመዱ!
ያሉንን ሁሉንም የጤና ምርመራ አገልግሎት ዝርዝሮች ለማግኘት አሁን ያግኙን።

#newyear #resolution #man #health #checkup #acibadem #Turkey


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በኢስታንቡል ከተማ ውስጥ ከሚገኙት 10 የአቺባደም ግሩፕ ሆስፒታሎች አንዱ አቺባደም አልቱኒዛዴ ሆስፒታል ነው፡፡

የአልቱኒዛዴ ሆስፒታል የምርመራ ክፍል ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዶክተሮች እና ለታካሚዎች የተደራጀ እንዲሁም ምቹ የምርመራ ሂደት ለማደረግ የሚያስችሉ የተሟሉ መሠረተ ልማቶች አሉት። ለሙሉ የጤና ምርመራ የቀረቡላችሁን ሁሉንም የአገልግሎት ጥቅሎች ዝርዝሮች ለማግኘት አሁኑኑ ያግኙን።

#newyear #resolution #health #checkup #acibadem #Turkey


አቺባደም ዩሮሎጂክ ኦንኮሎጂ የህክምና ክፍል የሽንት ማስወገጃ ስርዓት ካንሰር ላለባቸው ታካሚዎች በዓለም ዝነኛው መዳረሻ ነው።
በአቺባደም ከቀዶ ሕክምና እስከ የጨረር ሕክምና፣ ከኬሞቴራፒ እስከ ኢሚውኖቴራፒ፣ እና ከፎካል ቴራፒ እስከ ኒውክሌር ሕክምና ድረስ ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶችን እናቀርባለን። የኛ የኡሮሎጂ ቡድን ለፕሮስቴት ፣ ለኩላሊት ፣ ለፊኛ እና ለቴስቲኪዩላር ካንሰር በአነስተኛ ሽንቁር ረቂቅ ቀዶ ሕክምናዎች በማድረግ ላይ የተካነ ነው።
እያንዳንዱ ታካሚ በአሲባደም ቡድን ውስጥ በኦንኮሎጂ መማክርት ቡድን ውስጥ በሚሳተፉ ሁሉም የቡድኑ አባላት በጋራ ይገመገማል።
የመማክርቱ ቡድን አባላት ታማሚውን ይገመግማሉ፡፡ በተጨማሪም የሕክምና ክትትል መርሃ ግብር ያዘጋጃሉ፡፡ ስለዚህም ለታካሚዎች በግል የሚዘጋጅ እና ከአንዱ ስፔሻሊስት ወደ ሌላ በመምራት ሳይጉላሉ ሁሉን አቀፍ የሕክምና የሚያገኙበት ነው፡፡ የእኛ የሕክምና አቀራረብ ለእያንዳንዱ ታካሚ ከፍተኛ ከህመም የመዳን ስኬት እና የተሻለ ህይወት ጥራት እንዲያገኙ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ለበለጠ መረጃ አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሮአችን ያግኙ።

#bluenovember #man #prostatecancer #bladdercancer #acibadem


እውነተኛ የሕይወት ታሪክ
የካንሰር ፊኛን ማስወገድ እና አዲስ ማበጀት

የ49 አመቱ ሰርቢያዊ ሚሮስላቭ የፊኛ ካንሰር እንዳለበት ታወቀ። በቤልግሬድ እና በዛግሬብ የተለያዩ ምርጥ ዶክተሮች እና የተሻሉ የተባሉ የሕክምና አማራጮችን ለማግኘት ቻሎ ነበር፡፡
አንድ ቀን፣ በአጋጣሚ በኢንስታራም ላይ ማስታወቂያ ተመለከተ፡፡ ማስታወቂያው በቱርኪዬ በሚገኘው የአቺባደም ሆስፒታል የዩሮሎጂ ፕሮፌሰር በሆኑት ሙስጠፋ ሶፊከሪም ላይ ነበር። ወዲያው ቅጹን ሞልቶ ከፕሮፌሰር ሶፊከሪም ጋር ምክር ለማግኘት ቀጠሮ ያዘ። "" ፕሮፌሰር ሙስጠፋ ሶፊከሪምን በአካል አግኝቼ ስሀመሜ እና ስለ ህክምናዬ ጥልቅ ውይይት ካደረግኩ በኋላ ኢስታንቡል ወደሚገኘው አቺባዳም ሆስፒታል ለመሄድ እንዲሁም ህክምና ለማድረግ balሙሉ ተስፈኛ ነበርኩ" ሲል ሚሮስላቭ ተናግሯል።

የሚሮስላቭ የህክምና ጉዞ በአቺባደም ሆስፒታል ተጀመረ። የታመመውን ፊኛውን ለማስወገድ ቀዶ ጥገና ተደረገ፡፡ ፊኛው ከተወገደለት በኋላ የትናንሽ አንጀት ክፍልን በመጠቀም አዲስ የሽንት ከረጢት ለማበጀት የቀዶ ጥገናው ሂደት ተከተለ። አጠቃላይ ሂደቱ 6 ሰዓት ያህል የወሰደ ሲሆን ቀዶ ጥገናውም በጣም የተሳካ ነበር:: “ከቀዶ ጥገናው በኋላ ያለውም ሂደት መልካም ነበር፡፡ ምንም ዓይነት ኬሞቴራፒ ወይም ራዲዮቴራፒ አንሰጠውም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ላሉት አይነት እጢዎች በጣም የተሳካው ህክምና ራዲካል ሳይስቴክቶሚ ነው:: እናም ፊኛው ከተወገደ በኋላ ሌላ ምንም ነገር ማድረግ አያስፈልግም" ያሉት የዩሮሎጂ ፕሮፌሰሩ ሙስጠፋ ሶፊከሪም ናቸው፡፡ ተጨማሪ የሕክምና አስተያየት በነጻ ለማግኘት አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ጽህፈት ቤታችንን ያነጋግሩ።

#bluenovember #man #prostatecancer #bladdercancer #acibadem


ተተኪ ፊኛዎን ያግኙ
ለፊኛ ካንሰር ታማሚዎች አብዮታዊ መፍትሄ

በካንሰር የተጠቃውን ፊኛ ካስወገዱ በኋላ ሽንትን ለማከማቸት እና ከሰውነት ውስጥ ለማውጣት ሌላ መንገድ ማበጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ሁለት አማራጮች አሉ:: እነዚህም (Urostomy) ሽንት በተፈጥሯዊው ቱቦ ሳይሆን በቀዶ ጥገና ማስወገድ እና (Neobladder) ተተኪ ፊኛ ማበጀት ናቸው፡፡
• Urostomy ሽንት ከሆድ ውጭ በሚገጠም ልዩ ከረጢት ውስጥ ይሰበሰባል:: ከከረጢት ጋር መኖር በታካሚዎች የዕለት ተለት ህይወት እና በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል::


• Neobladder በታማሚው አንጀት ውስጥ የሚገኙ ሕብረ ህዋሳት በመጠቀም አዲስ ፊኛ መገንባት ሲሆን ይህም ሰው ሰራሽ የሽንት ማጠራቀሚያ ከረጢት የግድ አስፈላጊ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ይህም ለታካሚዎች መደበኛ የሆነ የሽንት ማስወገድ (በተለመደው መንገድ መሽናት) ያስችላቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቀዶ ጥገና ውስብስብ በመሆኑ የባለሞያዎችን ከፍተኛ ችሎታ እና ልምድ ይጠይቃል፡፡ አዲስ ፊኛ መልሶ ማበጀት ከትንሹ አንጀት ውስጥ የተወሰነውን ክፍል በመጠቀም አዲስ ፊኛ መፍጠር እና ከዋናው ፊኛ ይልቅ በማስቀመጥ እንዲሁም የሽንት ቱቦዎችን ወደ አዲሱ ፊኛ የላይኛው ክፍል ጋር መስፋትን ያካትታል። ስለዚህ ሽንት ከኩላሊቶቹ ውስጥ በሽንት ቱቦዎች በኩል ወደ አዲሱ ከረጢት በመውጣት ተከማችቶ ታካሚው እንደተለመደው መሽናት ይጀምራል፡፡
በአቺባደም እንደ መጀመሪያ አማራጭ ለእያንዳንዱ ታካሚ እንደተገቢነቱ የአዲስ የሽንት ከረጢት መልሶ ግንባታን እንተገብራለን። በአለም ዙሪያ ላሉ የፊኛ ካንሰር ታማሚዎች የአዲስ ፊኛ መልሶ ግንባታ የሚያካሂዱ በቁጥር ውስን ማዕከላት አሉ። በዚህ ምክንያት፣ ብዙ ታማሚዎች ይህን ሕክምና ለማግኘት አቺባደምን ይጎበኛሉ። ስለ ህክምናው የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ የአቺባደምን በአዲስ አበባ የመረጃ ፅህፈት ቤት እንዲያነጋግሩ እናበረታታዎታለን።

#bluenovember #man #prostatecancer #bladdercancer #acibadem


የፕሮስቴት ካንሰር
ለፕሮስቴት የተለየ አንቲጂን (PSA)

ለፕሮስቴት የተለየ አንቲጅን (PSA) ምርመራ በደም ውስጥ ያለውን የ PSA መጠን የሚለካ የደም ምርመራ ነው። PSA በፕሮስቴት አመንጪ እጢ የሚመረት ንጥረ ነገር ነው። በደም ውስጥ ያለው የ PSA መጠን ከፍ ያለ ሆኖ ሲገኝ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎች በፕሮስቴት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሌሎች ሁኔታዎች የ PSA መጠን መጨመር ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ በተለምዶ ከፍ ያለ የ PSA ደረጃ ከፍ ያለ የፕሮስቴት ችግር መኖሩን ይጠቁማል። ሆኖም ዕድሜ እና የዘር ሀረግን ጨምሮ የተለያዩ ምክንያቶች በPSA መጠን ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ልብ ሊባል ይገባል። በተጨማሪም የPSA መጠን በግለሰቦች መካከል ሊለያይ ይችላል፡፡ አንዳንድ የፕሮስቴት እጢዎች ከሌሎች የበለጠ PSA ያመርታሉ። ተጨማሪ የህክምና አስተያየትን ለማግኘት የደም ምርመራ ውጤቱን ወደ ባለሙያዎቻችን ይላኩ።

#bluenovember #man #prostatecancer #bladdercancer #acibadem




https://bit.ly/467SR5M


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አቺባደም ኸልዝኬር ግሩፕ
ሰማያዊ ህዳር - ለሁላችሁም የተሰናዳ ግብዣ

ሁላችሁም በፈረንጆቹ ኖቬምበር ወር ባዘጋጀናቸው የቤት ውስጥ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፍ ከአገልግሎቶቻችን ጋር እንድትተዋወቁ ግብዣ ስናቀርብላችሁ በጣም ደስ ይለናል። ለወንዶች ጤና ያለንን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ከምናደርጋቸው ተግባራት አንዱ የሀኪሞችን አስተያየት በነጻ ማቅረብ ነው፡፡ እርስዎም አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ጽህፈት ቤታችንን እንዲጎበኙ እናበረታታዎታለን ወይም ለተጨማሪ እርዳታ እንያነጋግሩን እናሳስብዎታለን። የእርስዎን ደህንነት ማረጋገጥ የእኛ ቀዳሚ ጉዳይ ነው። በአዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሮአችንን ለማግኘት በስልክ ቁጥሮች 0980474747 ወይም 0116663142 በመደወል ወይም ቦሌ መድሃኒአለም አንበሳ ባንክ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ማግኘት ይችላሉ::

#bluenovember #man #prostatecancer #bladdercancer #acibadem


ለ30 አመታት ያህል በአቺባደም የጡት ካንሰር ማእከል ከአለም ዙሪያ የመጡ ታካሚዎች አክመናል። ለሁሉም ታካሚዎች ሁለገብ ዘዴን እንጠቀማለን፡፡ በሆስፒታሉ በአጠቃላይ በጡት ካንሰር ህክምና የተካኑ የቀዶ ጥገና፤ የሕክምና ኦንኮሎጂ፤ የጨረር ኦንኮሎጂ፤ የመዋቢያ እና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና፤ ራዲዮሎጂ፤ ፓቶሎጂ እና ጄኔቲክስ ባለሞያዎች በጋራ ይሰራሉ፡፡ የላቀ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው የስፔሻሊስቶች ቡድን ምስጋና ይግባቸውና በሁለገብ አሰራራችን የጡት ካንሰርን በመመርመር እና በማከም ረገድ በጣም ስኬታማ ነን። ለበለጠ መረጃ አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሮአችን ያግኙ።

#pinkoctober #woman #breastcancer #acibadem


የሦስት ዓመት ሴት ልጅ እናት የሆነችው እና የ33 ዓመቷ ኢትዮጵያዊቷ የሂሳብ መምህርት አናያ በድንገት ደረጃ 4 የጡት ካንሰር እንዳለባት አወቀች። በወቅቱ ለጡት ካንሰር ምርመራ ወደ ህክምና ማዕከላት በዝዎች የሚሄዱበት አልነበረም፡፡ የህመሙ ስርጭት መጠን ማሳያ የሆነው የምርመራ ውጤት ምልክቱ በጡትዋ ላይ እና በጉበቷ ሳይቀር መገኘቱን ጠቆመ። አናያ በቱርኪዬ የሚገኘውን አቺባደም ሆስፒታል አድራሻ አገኘች። ወዲያውኑ በድረ-ገጹ ላይ የኦንላይን ታካሚ ቅጽ ሞላች። የአናያ የሕክምና ሪፖርቶች ወደ ተባባሪ ፕሮፌሰር ወደሆኑት ኦዝጌ ጉሙሴይ ተላኩ። “በጣም ወጣት ታካሚ ነበረች። ሆኖም የጡት ካንሰር ወደ ጉበቷ በመዛመት ላይ ነበር፡፡ HER2-ፖዘቲቭ የጡት ካንሰር ነበረባት። እሷን በኬሞቴራፒ እና በፀረ-HER2 ዒላማ ያደረገ ሕክምና ጀመርን” ሲሉ ተባባሪ ፕሮፌሰር ኦዝጌ ጉሙሴይ ያብራራሉ።
አናያ ወደ አቺባደም እንደደረሰች በአስቸኳይ ጥብቅ ሂደት የሚከተለውን የኬሞቴራፒ ሕክምናን ጀመረች። ከ 4 ዑደቶች በኋላ በጉበት ውስጥ ያሉ ችግሮች ሁሉ ተወገዱ፡፡ ከ6 ዑደቶች የኬሞቴራፒ ሕክምና እንዲሁም ከታለመለት ሕክምና በኋላ ኬሞቴራፒዋን አቁማ በፀረ-HER2 ሕክምና ብቻ ቀጠለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ ከPET-CT ስካን ውጤቶች የተገኙ ሪፖርቶች ስለ ሁኔታዋ ይፋዊ መግለጫ ሰጡ፡፡ አናያ ነጻ ሆነች። አሁን ከህመሞ ነጻ ከሆነች ከ 2 አመት በላይ ሆኗታል፡፡ ከካንሰር ነፃ ሆና እየኖረች ነው፡፡ ይህም ድንቅ ነው። አናያ እንዲህ ትላለች፡፡ "ይህንን ሆስፒታል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ። ትክክለኛውን ዶክተር በማግኘቴም በጣም እድለኛ ነኝ። ህመሜን ተፋልመውታል፡፡ ተባባሪ ፕሮፌሰር ኦዝጌ ጉሙሴይን አመሰግነዋለሁ። እኔ አምናለሁ፤ መላው የአቺባደም ሰራተኞች የላቁ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ ለሚያደርጉት ነገር ትኩረት አላቸው። ሁሉንም አመሰግናለሁ።" ተጨማሪ ነጻ የሕክምና አስተያየት ለማግኘት አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ጽህፈት ቤታችንን ያነጋግሩ።
#pinkoctober #woman #breastcancer #acibadem




https://bit.ly/4085EUk


የጡት ካንሰር ደረጃዎች በሰውነት ውስጥ ያለውን የካንሰር መጠን እና ስርጭት ይገልፃሉ። ብዙውን ጊዜ በቁጥር ከ 0 እስከ 4 ባለው ደረጃ ይመደባል፡፡ ደረጃው ከፍ ሲል ቁጥሮች የበለጠ የተስፋፋ ካንሰርን መኖር ያመለክታሉ፡፡ ደረጃ 0 ደግሞ የማይጎዳ የጡት ካንሰር ወይም ቅድመ ካንሰር ተብሎም ይጠራል። ይህ ማለት ያልተለመዱ ህዋሶች ተገኝተዋል፡፡ ነገር ግን በወተት ማስተላለፊ ቱቦዎች ወይም እጢዎች ላይ ብቻ የተገደቡ እና በዙሪያው ያሉትን ሕብረ ሕዋሳት (carcinoma in situ) አልወረሩም ማለት ነው፡፡ የአራተኛ ደረጃ የጡት ካንሰር ግን ቲዩመር ወደ ሌሎች የአካል ክፍሎች ወይም አጥንቶች አልፎ በላቀ ሁኔታ መዛመቱን ይጠቁመናል። የጡት ካንሰርም የካንሰር ህዋሶች ከመደበኛ ሴሎች ምን ያህል እንደሚለያዩ እና እጢው ምን ያህል በዝግታ ወይም በፍጥነት እንደሚያድግ ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ደረጃ ይሰጠዋል። ዝቅተኛ ደረጃ ካንሰር ማለት ባዕዶቹ ህዋሶች ከተለመዱት ሴሎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው እና ምናልባትም እድገታቸው ዘገምተኛ ነው፡፡ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ካንሰር ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ማለት ነው፡፡ አዲስ ምርመራ ለተደረገላቸው ታካሚዎች የጡት ካንሰርን ደረጃ መስጠት እና የደረሰበትን ምዕራፍን መለየት፣ ከሆርሞን-ሪሴፕትር እና ከHER2 ሁኔታ ጋር በመሆን የህክምና ቡድኑ ምርጡን የህክምና አማራጮች እንዲወስን ለመርዳት አስፈላጊ ናቸው።

#pinkoctober #woman #breastcancer #acibadem


ከ 2016 አንስቶ አቺባደም ሴኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጡት ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ይዞት የመጣውን ፈተና በሳይንስ እና በምርምር ለመዋጋት ይሰራል። በቱርክ ውስጥ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የምርምር ማዕከሉ የጡት ህመምን በሚመለከት በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ማለትም በራዲዮሎጂ፣ የሕክምና ኦንኮሎጂ፣ የጨረር ኦንኮሎጂ፣ ቀዶ ጥገና፣ ፓቶሎጂ፣ ዘረመል ዙሪያ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የተመሰረተ ነው፡፡ የባለሞያዎቹ የጋራ ግብ የጡት ህመምን በመመርመር እና በማከም ዙሪያ ዝርዝር ጥናቶችን ማካሄድ ነው፡፡ ቡድኑ ያነሰ መርዛማነት፣ አነስተኛ ተስፋፊነት እና የተሻለ ውጤታማነት ያላቸውን የሕክምና አማራጮች በማጎልበት አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ የምርምር ስራው የሚከናወነት በአቺባደም ሆስፒታሎች በተገኙ ሰፊ ክሊኒካዊ ልምዶች ላይ በመመስረት ነው፡፡ ሆስፒታሉ በቱርክ ውስጥ ግንባር ቀደም የጤና እንክብካቤ መዳረሻ ሲሆን ከመላው አለም ለሚመጡ ታካሚዎች ሁሉን አቀፍ የካንሰር ህክምና ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሮአችን ያግኙ።
#pinkoctober #woman #breastcancer #acibadem






https://bit.ly/3QcXruZ


ሁላችሁም በፈረንጆቹ ኦክቶበር ወር ባዘጋጀናቸው የቤት ውስጥ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፍ ከአገልግሎቶቻችን ጋር እንዲተዋወቁ ግብዣ ስናቀርብላችሁ በጣም ደስ ይለናል። ለሴቶች ጤና ያለንን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ከምናደርጋቸው ተግባራት አንዱ የሀኪሞችን አስተያየት በነጻ ማቅረብ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በጡት ካንሰር ዙሪያ ተጨማሪ የህክምና አስተያየቶችን በመስጠት ላይ እንገኛለን። እርስዎም አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ጽህፈት ቤታችንን እንዲጎበኙ እናበረታታዎታለን ወይም ለተጨማሪ እርዳታ እንያነጋግሩን እናሳስቦታለን። የእርስዎን ደህንነት ማረጋገጥ የእኛ ቀዳሚ ጉዳይ ነው።

#pinkoctober #woman #breastcancer #acibadem


ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ በጤና ቴክኖሎጂዎች ውስጥ የተከሰቱት የማያቋርጡ እድገቶች የጨጓራና አንጀት ካንሰርን ለማከም አዲስ ዘመንን ወልደዋል፡፡. ስለዚህም ከዚህ ህመም የመዳን ምጣኔ ከአመት አመት እየተሻሻለ መጥቷል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የትልቁ አንጀት ካንሰር ታማሚዎች የአምስት ዓመት የመትረፍ ምጣኔ ወደ 65% ከፍ ብሏል፡፡ “ለምሳሌ ፣ ዛሬ በጣም የተለመደው የጨጓራና የአንጀት ካንሰር አይነት የሆነው የትልቁ አንጀት ካንሰር በከፍተኛ የስኬት ደረጃዎች ሊታከም ይችላል። አንዳንድ የትልቁ አንጀት ካንሰር ዓይነቶችን ለማከም የታለመ ሕክምናን እንጠቀማለን። የታለመ ሕክምና በካንሰር ሕዋሳት ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ የታመሙ ክፍሎችን ነጥሎ ማጥቃት ይችላል፡፡ ይህ ዘዴ የካንሰር ሕዋሳትን እድገትና መስፋፋት ለማስቆም ይረዳል፡፡” የሚሉት በሙያቸው የጨጓራና የአንጀት ካንሰር እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጠባቸውን ሰዎች በማከም ላይ የሚያተኩሩት የሜዲካል ኦንኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ዶክተር ሁሴይን ኢንጊን ። ፕሮፌሰር ሁሴይን ኢንጊንን ለማነጋገር አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሮአችንን ያነጋግሩ።

#digestion #cancer #turkey #treatment #acibadem


የትልቁ አንጀት ካንሰር ምልክቶች በሠገራ ላይ ለውጥ መታየት እና የፊንጢጣ መድማትን ያካትታሉ፡፡ ወይዘሮ ሚርጃና በ63 ዓመታቸው የትልቁ አንጀት ካንሰር እንዳለባቸው በታወቀ ጊዜ እነዚህ ምልክቶች ነበሯቸው። ከዚህም በላይ ዕጢው በቀዶ ሕክምና ሊወገድ አልቻለም። ከቀዶ ጥገናው በፊት የኬሞቴራፒ እና የጨረር ህክምና እንደሚያስፈልግ በተነገራቸው ጊዜ ልጃቸው ለህክምና ምክር በቱርክ ወደሚገኘው አቺባደም ሆስፒታል ስልክ ደወለ። የሚርጃና የህክምና መረጃዎች በሜዲካል ኦንኮሎጂ ፕሮፌሰር ለሆኑት ዶክተር ሁሴይን ኢንጊን ተላከ። በዚህም መሰረት የወይዘሮዋ የህክምና ጉዞ በአቺባደም ሆስፒታል ተጀመረ። ፕሮፌሰሩ ከበድ ያለ የትልቁ አንጀት ካንሰር ያለባቸውን ታካሚዎች ለማከም የሚመረጠውን የህክምናን ዘዴ Immunotherapy ለመተግበር ወሰኑ፡፡ ሕክምናው የካንሰር ሕዋሳትን ለማጥፋት የሚረዱ ልዩ መድሃኒቶችን መጠቀምን የሚያጠቃልል ነው፡፡ Immunotherapy የሰውነት የበሽታ መከላከያ ስርአቶችን በማንቃት ባዕድ ነገሮች መኖራቸውን ያስጠነቅቃል፡፡ ዘዴው የበሽታ መከላከያ ስርዓትን በመጠቀም ካንሰርን ለማጥፋት ያግዛል፡፡ የሕክምናው ውጤት የተሳካ ነበር፡፡ ከስድስት ወር ህክምና በኋላ እጢው ሙሉ በሙሉ ጠፋ፡፡ "ከህክምናው ሂደት በኋላ ዓይኖቼ በተስፋ እና በሰላም እንባ ተሞሉ። ወደ ትክክለኛው ቦታ እንደመጣሁ አውቅ ነበር። በመጨረሻ ላለፉት 2 ዓመታት ከካንሰር ነጻ ህይወት እየኖርኩ ነው። ለሁሉም የአቺባደም ሐኪሞች እና ሰራተኞች ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው” ይላሉ ሚርጃና። ነፃ የሕክምና ምክር ለማግኘት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሯችንን ያነጋግሩ።

#digestion #cancer #turkey #treatment #acibadem


የሁሉም የጨጓራና የአንጀት ካንሰር ሕክምናዎች የተደራጀ ልዩ የህክምና ቡድን መያዝን ይጠይቃሉ፡፡ በቱርክ ውስጥ በአቺባደም ሆስፒታሎች የሚከናወኑ ሕክምናዎች የታቀዱ፣ በተያዘላቸው ዕቅድ የሚከናወኑ እና ሁለገብ በሆነ የባለሞያዎች ቡድን ቁጥጥር የሚደረግላቸው ናቸው ። አቺባደም የጨጓራና የአንጀት ኦንኮሎጂ ህክምና ክፍል በዘርፉ ህክምና የሰለጠኑ እና ሙያውን ስፔሻላይዝ ያደረጉ የጋስትሮኢንተሮሎጂስቶች፣ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች፣ ሜዲካል ኦንኮሎጂስቶች፣ ራዲየሽን ኦንኮሎጂስቶች፣ ኢንተርቬንሽናል ራዲዮሎጂስቶች እና የስነ ምግብ ባለሙያዎችን ያቀፈ ነው። ለበለጠ መረጃ አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሮአችን ያነጋግሩ።
#digestion #cancer #turkey #treatment #acibadem


መልካም አዲስ ዓመት!

20 last posts shown.