አዲስ ሪፖርተር - NEWS


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ሰበር - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቢሮ በገቡ የመጀመሪያው ቀን ዩናይትድ ስቴትስን ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የመውጣት ሂደት የሚያስጀምረውን የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ (Executive Order) ፈረሙ።

አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገሮች ግንባር ቀደሟ እንደሆነች ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንቱ "ድርጅቱ ቻይናን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጠያቂ ማድረግ ሳይችል ቀርቷል" ካሉ በሗላ አክለውም ቻይን ለመቅጣት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ይፋ ሲያደርጉ “ቻይና የዓለም ጤና ድርጅትን ሙሉ በመሉ ትቆጣጠረዋለች” ማለታቸው ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


መረጃ ‼️

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቢሾፍቱ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ ተነሺ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያሰሙ መኾኑን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ድረገጽ ዘግቧል።

አርሶ አደሮቹ ቅሬታ ያሰሙት፣ ከካሳ እና ከሠፈራ ዕቅድ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

መንግሥት ለማስፋፊያው የቀጠረው የሊባኖሱ አማካሪ ኩባንያ፣ አርሶ አደሮች ይነሱባቸዋል ወደተባሉት ቦታዎች ቅድመ-ጥናት የሚያካሄድ የባለሙያዎች ቡድን መላኩንም ዘገባው አመልክቷል።

አኹን ከሚኖሩበት ቀያቸው 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዲሠፍሩ ይደረጋሉ የተባሉት አርሶ አደሮች እስከ 2 ሺሕ 500 ይደርሳሉ ተብሏል።

ተነሺዎቹ አርሶ አደሮች፣ በአንድ ስኩዌር ሜትር 322 ነጥብ 5 ብር ካሳ እንዲከፈላቸው እንደታሰነ ከአርሶ አደሮቹና ከአንድ ደብዳቤ ላይ መመልከቱንም የዜና ምንጩ አውስቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


☎ 📞📞0914280819
መርጌታ ውዴ ባህላዊ ህክምና 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
➡️ ለገበያ
➡️ ለመስተፍቀር
➡️ ለመፍትሄ ሀብት
➡️ ለበረከት
➡️ ለጥይት መከላከያ
➡️ ለስንፈተ ወሲብ
➡️ የተወሰደ ገንዘብ ለማስመለስ
➡️ ራዕይ የሚያሳይ
➡️ ለዓቃቤ ርዕስ
➡️ ለመክስት
➡️ ለቀለም(ለትምህርት)
➡️ ሰላቢ የማያስጠጋ
➡️ ለመፍትሔ ስራይ
➡️ ጋኔን ለያዘው ሰው
➡️ ለሁሉ ሠናይ
➡️ ለቁራኛ
➡️ ለአምፅኦ
➡️ ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
➡️ ለግርማ ሞገስ
➡️ ለቁማር
➡️ ለዓይነ ጥላ
➡️ ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
➡️ ለሁሉ መስተፋቅር
➡️ ጸሎተ ዕለታት
➡️ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
➡️ ለእጅ ስራ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለማንኛውም ነገር ያናግሩን መፍትሄ አለን!!!
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 📞📞0914280819
 
ባላቹህበት እንሰራለን


ተመሳሳይ ፆታ ❗️🔥

ዶናልድ ትራምፕ አስገራሚ ወሳኔ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ወሰኑ! ከደቂቃዎች በፊት ቃለመሃላ የፈጸሙት ትራምፕ ከተፈጥሯዊዉ የጋብቻ ስነስርዓት ውጪ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት ምንም ጋብቻ በአሜሪካ ተቀባይነት እንደማይኖረውና ይህንን የሚያደርጉ ሁሉ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የሰራተኛ ቅነሳ‼️

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የሰራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል። በኢትዮጵያ በግጭት፣ ተፈጥሯዊ አደጋዎች እና ሌሎች ሰው ሰራሽ ችግሮች የተፈናቀሉ ዜጎችን በመርዳት የሚታወቀው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ካሉት ቢሮዎች ውስጥ 600 ሰራተኞችን ለመቀነስ መወሰኑ ታውቋል። ድርጅቱ ሰራተኞቹን የሚቀንሰው በበጀት ዕጥረት ነው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የአዲስ አበባ ፖሊስ የባለሀብቱን ገዳዮች መያዙን አስታወቀ

መሰረት ሚዲያ ከሀያ ቀን በፊት ታዋቂው የአክሰስ ኮም ኩባንያ ባለቤት እና የሸበል በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢረሳው ምናለ ምሽት 1:30 ላይ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው እንደተገደሉ መዘገቡ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ ይፋ ባረገው መረጃ የባለሀብቱን ገዳይ እና አስገዳይን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።

ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረውን መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለውን ግለሰብ እና አብዩ አይተነው ፈንታ ጨምሮ ለወንጀሉ መፈፀም አካባቢውን በመቆጣጠር ተሳትፎ የነበረውን አቶ ወርቁ መለሰ ካሴ የተባሉትን ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጌዴዎን ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ላይ በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

"ምንም እንኳን ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመቀየር ከወንጀሉ ተጠያቂነት ለማምለጥ በሐሰተኛ ስም ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ለመጥፋት ቢያስቡም በተሰራው እረፍት አልባ ፖሊሳዊ ጥበብ በታከለበት የክትትልና የምርመራ ስራ በቁጥጥር ስር ውለዋል" ያለው ፖሊስ የወንጀሉ ፍሬ የሆነው ንብረትነቱ የአቶ አብዪ አይተነው ፈንታ የውግ ቁጥር  የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ እና ለማምለጥ የሞከሩበት እንዲሁም ሽጉጡን የደበቁበት ላንድክሩዘር ተሽከርካሪ በኤግዚቢትነት ተይዟል ብሏል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ቢቸና ወረዳ ተወላጅ የሆኑት እና የ 'ምናሉ ሆቴል' ባለቤት አቶ ቢረሳው ግድያ ከተፈፀመባቸው በኋላ ቀብራቸው በሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

ምንጭ:- መሰረት ሚዲያ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የጥምቀት በዓል በተከበረባቸው የተለያዩ ስፍራዎች ላይ የሥርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ዋሉ።
👉ከእነዚህ መካከል በተወሰኑት ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የበዓሉን ሠላማዊነት በቅርበት ለመከታተልና ለህብረተሰቡ ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራዎች ላይ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ በማቋቋም የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማዋቀር ከፍትህ እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ባከናወነው ተግባር ወንጀልን እና የወንጀል ስጋቶችን መቆጣጠር ችሏል፡፡ 

በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በእነዚሁ በጊዜያዊነት በተቋቋሙት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ምርመራ ተጣርቶባቸዋል፡፡ ከተያዙት መካከል የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው መኖራቸውም ታውቋል፡፡

ብርሀኑ አበበ የተባለው ተከሳሽ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አበበ ቢቂላ ስታዲዮም በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በርካታ ሰው መሰባሰቡን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ የስርቆት ወንጀል ፈፅሟል፡፡

ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ተከሳሹ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በግምት 3:00 ሰዓት ገደማ ከሁለት ግለሰቦች ኪስ ውስጥ 2 ሞባይል ስልኮችን ሰርቆ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ካጠናቀቀና አቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተ በኋላ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በበዓሉ ስፍራ በተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት በዚያው ዕለት ተከሳሽ ብርሃኑ አበበ በ2 አመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት የፖሊስ መምሪያው መረጃ ያመለክታል። 

በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ በነበረው የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል፡፡

ታዘበው ሞላ የተባለው ይኸው ተከሳሽ በበዓሉ ከታደሙ አንዲት ግለሰብ ላይ ሞባይል ስልክ ሰርቆ በድጋሚ ከሌላ ሰው ላይ ሊሰርቅ ሲሞክር በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በስፍራው በተቋቋመው ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ከተጣራበት በኋላ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ዛሬ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም የተከሳሽ ታዘበው ሞላን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ  ምድብ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን በተፋጠነ ችሎት በማየት ጥፋተኝነቱን በማስረጃ በማረጋገጥ በ6 ወር እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በጃን ሜዳ በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ስነ ስርዓት ላይ የታዳሚውን ብዛት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተመሳስለው ገብተው ወንጀል የፈፀሙ 21 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ ይገኛል፡፡

ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ተጠርጣሪዎቹ የስርቆት፣ የቅሚያ እና የራስ ያልሆነን ንብረት ይዞ መገኘት ወንጀል የፈፀሙ ናቸው ተብሏል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ  እጅ ላይ የወንጀል ፍሬ የሆኑ እና የተለያየ አይነት ሞዴል ያላቸው ዘጠኝ ሞባይል ስልኮች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter




በአማራ ክልል ያለው የመምህራን ደመወዝ አለመከፈል መምህራንን የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ማስገደዱ ተገለጸ

በአማራ ክልል ከመስከረም እስከ ታሕሳስ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን፤ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ የጉልበት ሥራ ለመስራት ተገደዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ያሉ መምህራን ለተማሪዎቻቸው ሲሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተቋቁመው እየሰሩ ነበር ያለው ማህበሩ፤ "አሁን ላይ ግን ያለው ሁኔታ ካቅማቸው በላይ እየሆነ ነው" ብሏል፡፡

"ለወራት ደመወዝ ያልተከፈሉ መምህራን ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ ባለመቻላቸው የጉልበት ሥራ የሚሰሩ አሉ" ያሉት፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበበ ናቸው፡፡

"በዚህም ቀጣዩ የመምህራኑ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ አይታወቅም" ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት የትምህርት ሥራውንም ወደ ኋላ ጎትቶታል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ትምህርት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ወደሚሰጥባቸው ቦታዎች ሄደው ለመማር ሲሞክሩ በተፈጠረ የቦታ ጥበት፤ በአንድ ክፍል ውስጥ 90 የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲቀመጡ አስገድዷል ነው የተባለው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያሉ መምህራንን የተመለከቱ ችግሮች በሁሉም አካባቢ አይነት እና መጠናቸውን እየቀያየሩ መቀጠላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

Via : አሐዱ ሬዲዮ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የዶናልድ ትራምፕ በዓል ሢመት ዛሬ ምሽት ይከናወናል

ባለፈው ኅዳር ወር የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው እለት በይፋ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ፡፡

በዓለ ሢመታቸውን ተከትሎ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ይመለሳሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሁለት የፍርድ ችሎት፣ በርካታ የወንጀል ክሶች፣ ሁለት የግድያ ሙከራዎች እና በርካታ ጫናዎችን አልፈው ነው የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ሽንፈታቸውን በመቀልበስ በዓለ ሢመታቸውን የሚፈፅሙት፡፡

በዓለ ሢመታቸው ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን÷ በዋሽንግተን ዲሲ ያለውን ከባድ ቅዝቃዜ ተከትሎ ከአደባባይ ይልቅ በአዳራሽ ውስኝ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ መቅረቡን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ Capital ዘገበ ።

የውጪ ምንዛሪ ለውጡን ተከትሎ ከግምት ውስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ ቀረበ ።

መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ የነበረውን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ቢያደርግም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋማት ግን ተጨማሪ ክለሳዎች እንዲደረጉ እየጠየቁ መሆኑን ካፒታል ተረድታለች።

የሚኒስትሮች ም/ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን ያፀደቀ ሲሆን ይህም ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

አገልግሎቱ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያዉ እስከ 200 ሜጋዋትስ ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ድጎማ እንደሚያደርግ ገልጿል ። ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል ቢባልም የተደረገው ጭማሪ በዓመት ውስጥ 122 በመቶ ደርሷል።

ይሁን እንጂ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር በተገናኘ እንደ ዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምን (አይ.ኤም.ኤፍ) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ አጋሮች የተለያዩ ድጋፍ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ መንግስት ያፀደቀውን የታሪፍ ጭማሪ በድጋሚ እንዲያጤነው መጠየቃቸውን ነው ለማወቅ የተቻለው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ሀማስ ሶስት ታጋቾችን መልቀቁን ተከትሎ 90 ፍልስጥኤማውያን ከእስር ተለቀቁ

የእስራኤል ባለስልጣናት ሃማስ በጦርነት ለተጎዳው የጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ሴት ምርኮኞች አሳልፎ መስጠቱን አረጋግጠዋል። የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ እሁድ አመሻሹ ላይ እንደተናገሩት የ24 ዓመቷ ሮሚ ጎነን፣ የ28 ዓመቷ ኤሚሊ ዳማሪ እና የ31 ዓመቷ ዶሮን ሽታይንብሬቸር ለቀይ መስቀል ተላልፈው በእስራኤል ውስጥ “ደህንነታቸው በተጠበቀ ስፍርል ውስጥ ናቸው” ብለዋል።

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት 90 የፍልስጤም እስረኞች ተለቀዋል። ከእስራኤል እስር ቤት የተፈቱት ፍልስጤማውያን 69 ሴቶች እና 21 ታዳጊ ወንዶች ከዌስት ባንክ እና እየሩሳሌም እንደተለቀቁ ሃማስ አስታውቋል። የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከተፈቱት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በቅርቡ የታሰሩ እንጂ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ወይም አልተፈረደባቸውም ብሏል።

በመጀመርያው የእርቅ ሂደት እስራኤል ወደ 1,900 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትፈታ ሲጠበቅ ሃማስ 33 የሚሆኑ የእስራኤል ታጋቾችን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።የመከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት በዚህ የመጀመሪያ ስድስት ሳምንት ሂደት "በየሳምንቱ ከሦስት እስከ አራት ተጨማሪ ታጋቾች ይለቀቃሉ"። የሐማስ ባለስልጣን ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ቀጣዩ የታገቱ ሰዎችን የማስፈታት እና የእስረኞች ቅያሬ ቅዳሜ ይካሄዳል።

ከ630 በላይ ሰብዓዊ ርዳታዎችን የጫኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች እሁድ እለት ጋዛ የገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 300 ያህሉ ወደ ሰሜናዊው ጋዛ ሰርጥ አቅጣጫ ማቅናታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ ቶም ፍሌቸር ተናግረዋል።በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በአማካይ 40 የጭነት ተሽከርካሪዎች ብቻ እየገቡ ነበር፣ ከግጭቱ በፊት ግን በየቀኑ 500 የሚጠጉ የረድኤት ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ ይገቡ ነበር። የተኩስ አቁም ስምምነቱ በየቀኑ 600 የእርዳታ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ የሚያስችል ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter




☎ 📞📞0914280819
መርጌታ ውዴ ባህላዊ ህክምና 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
➡️ ለገበያ
➡️ ለመስተፍቀር
➡️ ለመፍትሄ ሀብት
➡️ ለበረከት
➡️ ለጥይት መከላከያ
➡️ ለስንፈተ ወሲብ
➡️ የተወሰደ ገንዘብ ለማስመለስ
➡️ ራዕይ የሚያሳይ
➡️ ለዓቃቤ ርዕስ
➡️ ለመክስት
➡️ ለቀለም(ለትምህርት)
➡️ ሰላቢ የማያስጠጋ
➡️ ለመፍትሔ ስራይ
➡️ ጋኔን ለያዘው ሰው
➡️ ለሁሉ ሠናይ
➡️ ለቁራኛ
➡️ ለአምፅኦ
➡️ ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
➡️ ለግርማ ሞገስ
➡️ ለቁማር
➡️ ለዓይነ ጥላ
➡️ ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
➡️ ለሁሉ መስተፋቅር
➡️ ጸሎተ ዕለታት
➡️ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
➡️ ለእጅ ስራ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለማንኛውም ነገር ያናግሩን መፍትሄ አለን!!!
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 📞📞0914280819
 
ባላቹህበት እንሰራለን


#Update

ቲክቶክ በአሜሪካ ተመልሷል‼️

ቲክቶክ ከታገደ ከሰዓታት በኋላ በአሜሪካ ውስጥ እንደገና መስራት መጀመሩን አሜሪካ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን አረጋግጠውልናል።

መተግበሪያው የተመለሰው እግዱ ተነስቶለት አለመሆኑ ልብ ይሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ትራምፕ ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል ደርጋለው አሉ።

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ገጻቸው ላይ ዛሬ ባወጡት ፅሁፍ ፤ ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራቱን እንዲቀጥል እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

ለዚህም በስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያ ቀን (ነገ) ቲክቶክ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል የሚያስችል እርምጃ ይወስዳሉ / ልዩ የሆነ ትዕዛዝ ይሰጣሉ።

ትራምፕ በዚሁ ፅሁፋቸው አሜሪካ የማህበራዊ ድረ-ገፁን ግማሽ (50%) በባለቤትነት መያዝ እንዳለበት ጠቁመዋል።

ነገ ወደ ቢሮ ገብቼ ስራ ከጀምርኩ በኃላ "ቲክቶክ እንዲጨልም አልፈልግም" ሲሉ ገልጸዋል።

ትራምፕ እንደ ጋራ ሽርክና አሜሪካ በቲክቶክ ውስጥ የ50% የባለቤትነት ድርሻ እንድትወስድ ሀሳብ አቅርበዋል።

ይህ ማለት ከወላጅ ኩባንያው ባይትዳንስ ወይም ከአዳዲስ ባለቤቶች ጋር " በአሜሪካ እና በመረጠችው ግዢ መካከል ትብብር ሊፈጥር ይችላል።

ትራምፕ " ይህንን በማድረግ ቲክቶክን እንታደገዋለን ፣ በጥሩ እጆች ውስጥ እናቆየዋለን " ብለዋል።

ቲክቶክ ከዚህ ቀደም " ከምሸጠው ሙሉ በሙሉ ዘግቼ አሜሪካን ብለቅ ይሻለኛል " ማለቱ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


አሪፍ ፕሮጀክት ነው❗
በያዝነው የጥር ወር መጨረሻ ወደ ገንዘብ ይቀየራል።
ያለምንም ወጪ ይሄን ፕሮጀክት ብሰሩ መልካም ነው፣ሊንኩ ከስር ተቀምጧል፣start በሉት👇👇👇
https://t.me/tapswap_mirror_1_bot?start=r_5368904178 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift


እስራኤል ዞልፋካር በተሰኘ ተምዛግዛጊ ሚሳኤል ተመታች

በኢራን የሚደገፈው የየመኑ ሃውቲ ታጣቂ ቡድን የሚያደርስባት ዙሪያ መለስ ጥቃት ያንገሸገሻት ኢስራኤል፣ አሁን ይባስ ብሎ የየመን መንገስት ጥቃት ስለባ ሆናለች እየተባለ ነው፡፡

በዚህም የየመን መንግስት ጦር በቴል አቪቭ ከባድ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙ እየሩሳለምን ክው አድርጓታል፡፡

የየመን ጦር ሃይል ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሬ እንደተናገሩት፣ የየመን ጦር የእስራኤል መንግስት መከላከያ ሚኒስቴር ግቢን፣ ዞልፋካር በተሰኘ ተምዛግዛጊ ሚሳኤል መምታቱን እስታውቀዋል፡፡

የየመን ጦር ሃይል ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ እንዳመላከቱት፣ “በቴላቪቭ የሚገኘውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር፣ በሚሳኤል ጥቃት ኢላማ አድርገናል” ብለዋል።

ኦፕሬሽኑ የተካሄደው 'ዞልፋካር' በተሰኘ ባላስቲክ ሚሳኤል ሲሆን፣ ጥቃቱ በጥንቃቄ የተፈጸመ እና ግቡን የመታ ትክክለኛ ድብደባ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የጠላት መከላከያ ስርአቶች ሊመከቱት ያልቻሉትን፣ ከባድ ጥቃት ፈጽመናል ሲሉ ቃል አቀባዩ ፎክረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያገኘ አርቲስት ነበር፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


🇳🇬 በሰሜን ናይጄሪያ ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ ፈንድቶ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት የነዳጅ ጫኝ ታንከር ሹፌር ተሽከርካሪውን መቆጣጠር ባለመቻሉ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደተገለበጠ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ነዳጁ መንገዱ ላይ መፍሰሱን ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ በርካታ ነዋሪዎች ነዳጁን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በድንገት ፍንዳታው ተከስቷል።

እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፤ እሳቱ በአቅራቢያ የነበሩ መኪኖች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ሱቆችን በእሳት ነበልባል ገርፏል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሐመድ ኡማሩ ባጎ በክስተቱ ማዘናቸውን ገልፀው ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

20 last posts shown.