TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

24 Jan, 13:14

Open in Telegram Share Report

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ የእሳት አደጋ ደረሰበት

ማክሰኞ ጥር 16 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በትናንትናው ዕለት ምሽት 4፡48 ላይ ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ግብዓት የፈሰሰበት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንፃ የእሳት አደጋ ደርሶበት መሰረተ ልማቱ መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የህዝብ ፋይልና ዳታ እንዲሁም መረጃዎች ላይ የደረሰ አደጋ አለመኖሩን የጠቆው የከተማ አስተዳደሩ፤ የአደጋው ምክንያት እና መንስኤ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ አስታውቋል።

ህንጻው የኢትዮ ቴሌኮም፣ የአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ተቋማት የተሳተፉበት እና የዲጂታል አገልግት መስጠት የሚያስችል ሥራ ተሰርቶበት የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል ተብሎ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ባለ 7 ወለል ህንጻው ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ የተገመተ ንብረት ሲወድም በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ከተጎጂዎቹ መካከል ሦስቱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች መሆናቸውንም ገልጿል።

የእሳት አደጋዉ ከህንጻዉ ምድር ቤት የተነሳ ሲሆን እሳቱ እስከ ኹለተኛ ፎቅ ድረስ ጉዳት ማድረሱንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የአደጋው ምክንያት እና መንስኤ ምርመራ እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ የጠቆመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ የአካባቢው ማህበረሰብም መንግስት የጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ከዚህ አደጋ ጋር ተያይዞ ማንኛውንም መረጃዎች በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል ትላንት ከቀኑ 10:46 በሸገር ከተማ ቡራዩ በሹፋን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ300 ሺሕ ብር በላይ የተገመተ ንብረት የወደመ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ምሽት 3:55 ላይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስኮ መነሀሪያ በህዝብ ማመላለሻ አዉቶቢስ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 1 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
_______
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

3.5k 0 14 16
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot