በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ከ200 በላይ የናይጄሪያ እስረኞች ወደ አገራቸው እንዲዛወሩ ጠየቁ
ቅዳሜ ጥር 20 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት ቃሊት ማረሚያ ቤት የሚገኙ ከ200 በላይ የናይጄሪያ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲዛወሩ መጠየቃቸው ተሰማ፡፡
እስረኞቹ በአብዛኛው በአደገኛ እፅ እና በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀሎች ተይዘው ማረሚያ ቤቱ የገቡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ታራሚዎቹ በህክምና፣ በምግብ እና በውሃ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸውን በመግለጽ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙብን በመሆኑ ወደ አገራችን ማረሚያ ቤት እንዛወር ሲሉ የናይጄሪያን መንግስት እርዳታ መጠየቃቸው ነው የተነገረው፡፡
ስለሆነም ታራሚዎች ለናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ እና በኢትዮጵያ ለናይጄሪያ ኤምባሲ በጻፉት ድብዳቤ የተወሰኑት ለበሽታ መጋለጣቸውን አውስተው፣ ቀሪ የእርስ ጊዜያቸውን በአገራቸው ለመጨረስ የአገሪቱ መንግስት እርዳታ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
ታራሚዎቹ በደብዳቤ አቤቱታቸውን ሲገልጹ ይህ ለኹለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ባለፈው ጥቅምት ወርም ከ300 ያላነሱ የናይጄሪያ ዜጎች በቃሊቲ እስር ቤት በአስከፊ ሁኔታ እንገኛለን በማለት ወደ ናይጄሪያ እንዲዛወሩ ለአገራቸው መንግሥት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ይሁን እንጂ የታራሚዎቹን ጥያቄ ለመመለስ የናይጄሪያ መንግስት ከዲፕሎማቲክ ዘዴ በስተቀር አገራትን ማስገድድ እንደማይችል ገልጿል፡፡
እነዚህን እና ሌሎች መረጃዎችን በምስል እና በድምጽ ለማግኘት የአዲስ ማለዳን የዩ ቲዩብ ቻናል ይቀላቀሉ @addismaledanews' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@addismaledanews