በትምባሆ፣ በአልኮል መጠጦችና በሌሎች ጤናማ ባልሆኑ ምርቶች ላይ የተጣለው ግብር ዝቅተኛ ነው ተባለ
ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በያዝነው በ2015በሚኒስትሮች ምክርቤት ጸድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተመራው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ ላይ፤ በተለይም በትምባሆ፣ በአልኮል መጠጦች፣ በስኳር የጣፈጡ መጠጦች እና ትራንስ ፋት ላይ የተጣለው ግብር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ።
የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር በጤና ታክስ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ትላንት መጋቢት 8/2015 በኢንተርሌግዥሪ ሆቴል አከናውኗል።
በመድረኩም የተለያዩ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን፤ በአክሳይዝ ታክስ ማሻሻያው በትምባሆ፣ አልኮል መጠጦች፣ በስኳር የጣፈጡ መጠጦች እና ትራንስ ፋት ላይ የተጣለው ግብር ሕብረተሰቡን ከተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች በመከላከል ረገድ ሊኖረው የሚችለው ጠቀሜታ ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡
የጤና ታክስ ሕይወት አድን ከመሆኑም በላይ፤ በጤናው ሥርዓት ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ፣ ለሕብረተሰብ ጠቃሚ የሚሆኑ ፕሮግራሞችን ለመደጎም ለመንግስት ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝም ተጠቁሟል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች ማለትም እንደ ካንሰር፣ የልብና የልብ ደምስር ሕመሞች እንዲሁም የረጂም ጊዜ የመተንፈሻ አካል ሕመሞች የብዙ ወገኖችን ሕይወት ያለእድሜአቸው በመቅጠፍ ላይ እንደሚገኙ የተገለጸም ሲሆን፤ እነዚህ ሕመሞች በጤናው ሥርዓት ላይም ከፍተኛ ጫና እያስከተሉ እንደሚ ገኙ ተገልጿል።
ስለሆነም፣ የጤና ታክስ ጤናማ ባልሆኑ ምርቶች ላይ ሲጣል፤ የችርቻሮ ዋጋን በመጨመር የተጠቃሚ ሰዎችን የመግዛት አቅም በማዳከም የፍጆታ መጠናቸውን እንዲቀንሱ፣ እንዲያቋርጡ ወይም አማራጭ ጤናማ ምርቶችን እንዲጠቀሙ ያበረታታል የተባለ ሲሆን፤ ተላላፊ ላልሆኑ ሕመሞች ተጋላጭነትንም እንደሚቀንስ ተነግሯል፡፡
ኢትዮጵያ በ2012 የኤክሳይይዝ ታክስ አዋጅ ስታጸድቅ በተለይም ጤናማ ባልሆኑ ምርቶች ላይ የተጣለው ግብር ላይ ያገኘችውን ስኬት ማጎልበት ተገቢ መሆኑ በመድረኩ የተነገረ ሲሆን፤ በያዝነው በ2015 ግን በሚኒስትሮች ምክርቤት ጸድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ ሕብረተሰቡን ከተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች በመከላከል ረገድ ሊኖረው የሚችለው ጠቀሜታ ዝቅተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።
ረቂቅ አዋጁ የሚመለከታቸውን ወገኖች ባሳተፈ መልኩ በተዋረድ ተገቢውን ውይይት የተደረገበት አለመሆኑን የገለጸው ማኀበሩ፤ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አዋጁ ከማፅደቁ በፊት የውይይት መድረክ እንዲያመቻች ጠይቋል። በተጨማሪም ጤናማ ያልሆኑ ምርቶች በሕብረተሰቡ ጤና ላይ አሉታዊ ጉዳት እንዳያመጡ ለማድረግ በቀዳሚ አማራጮች ናቸው ያላቸውን የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን በዝርዝር አስቀምጧል።
በዚህም፣ የገንዘብ ሚኒስቴር በሲጋራ ምርቶች ላይ ያቀረበው ረቂቅ የኤክሳይዝ ግብር በ2012 ከወጣው ምንም ሳይለወጥ መሆኑን የገለጸው ማኀበሩ፤ ይህም አድ-ቫሎረም 30 በመቶ እና 20 ሲጋራ በሚይዝ ፓኮ ላይ ቁርጥ ግብር (specific rate) 8 ብር ብቻ መሆኑን ገልጿል፡፡
ይህ የግብር መጠን በ2013 በሰዎች የሲጋራ ፍጆታ ላይ ያመጣው ውጤት አበረታች የነበረ ሲሆን፤ ከዚያ ወዲህ ባሉት ዓመታት ያስከተላቸው ውጤቶች በግሽበትና በሕብረተሰቡ የመግዛት አቅም መጠንከር የተነሳ እየቀነሱ መምጣታቸውም ተነግሯል፡፡
ስለዚህም በጤና ላይ ኦዎንታዊ የሆነ ውጤት ለማምጣት በረቂቅ አዋጁ ላይ አድ ቫሎረም 30% እና በተጨማሪ 20 ሲጋራ በሚይዝ በእያንዳንዱ ፓኮ ላይ 25 ብር ቁርጥ ግብር መጣል ይኖርበታል ያለው ማኀበሩ፤ ይህ ግብር ከተጣለ የአጫሾችን የሲጋራ ፍጆታ በ12 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን፤ በትምባሆ ምክንያት ሊመጣ የሚችል የሞት መጠንን በ38 ሺኽ እንደሚቀንስ ግምቱን አስቀምጧል። በገቢ ረገድም ለመንግስ ተጨማሪ 2929 ሚሊዮን ብር እንደሚያመጣም ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በአልኮል መጠጦች ላይ የሚጣለው ግብር በመጠን (volume) እና በአልኮል ይዘት መጠናቸው መሰረት ሲሆን፤ በዚህም መሰረት በሚከተሉት የአልኮል መጠጥ ምርቶች ላይ የሚጣለው ቀዳሚ ተመራጭ የግብር አይነት፤- ለቢራ 300 ሚ.ሊ ይዘት ባለው በእያንዳንዱ የቢራ ጠርሙስ ላይ አድ-ቫለሮም 40 በመቶ ሲደመር ቁርጥ ግብር 25 ብር፣ ለወይን መጠጥ አድ-ቫለሮም40 በመቶ ሲደመር በአንድ ሊትር ብር 200 ብር፣ ጠንከር ላሉ የአልኮል መጠጦች (spiritis) በአንድ አድ ቫለሮም 80 በመቶ ሲደመር ቁርጥ ግብር ብር 400 ብር ቢጣል በጤና ላይ የሚያበረክተው አዎንታዊ ውጤት የተሻለ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል በስኳር የጣፋጡ መጠጦች ላይ የሚጣለው ግብር በመጠንና (volume) በስኳር ይዘት መጠናቸው መሰረት ሲሆን፤ በዚህም በ2012 የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ መሰረት ስኳር ወይም ጣፋጭ የሌላቸው የውሀ ምርቶች አድ-ቫሎረም 10 በመቶ፤ የስኳር ወይም ማጣፋጭ ቅመም ባላቸው ለስለሳ መጠጦች ላይ አድ-ቫሎረም 25 በመቶ ግብር እንዲጣል ይጠቅሳል፡፡ ይህም በጤና ላይ በጎ አስተዋጽኦ እንዲያመጣ ከተፈለገ፤ መጣል ያለበት ቀዳሚ ተመራጭ የፖሊሲ ግብር በሂደት ሊከሰት በሚችለውን ግሽበትና በሰዎች የመግዛት አቅም መጠንከር የማይሸረሸር መሆን ይኖርበታል ተብሏል፡፡
ስለሆነም በለስላሳ መጠጦች ላይ የሚጣለው ቀዳሚ ተመራጭ ግብር በሊትር 6 ብር እንዲሆን የሚመከር ሲሆን፤ ይህም የሚተገበረው የስኳር ይዘታቸው በ100 ሚ.ሊ. ውስጥ ከ4ግራም የበለጠ ስኳር ባላቸው ሲሆን፤ ይህ ታከስ ሥራ ላይ ከዋለ በእውነተኛው ዋጋ ላይ 4 ነጥብ 9-10ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ ሲያስከትል፤ የፍጆታ መጠንን ከ -13 በመቶ - (-6 በመቶ ) ባለው መጠን እንደሚቀንስ ተነግሯል፡፡
በኢንደስትሪ በከፊል የሚመረት የትራንስ ፋት መጠን በሁሉም ምግቦች በ100 ግራም ውስጥ ከሚገኝ የጠቅላላ ስባት ምርቶች ላይ ወይም በአገር ውስጥ በሚመረት ወይም በከፊል ሃይድሮጅን ተጨምሮባቸው የሚመረቱ ዘይቶች ላይ አስገዳጅ የሆነ የ2 ግራም ገደብ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ መውጣት እንዳለበት ማኀበሩ አሳስቧል፡፡
__
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n