በቦረና እና ሱማሌ የድርቁ ተፅዕኖ ተባብሶ ቀጥሏል ተባለ
እሁድ ግንቦት 20 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እንዲሁም በሱማሌ ክልል ያለው የድርቅ ተፅዕኖ ተባብሶ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ በኦሮሚያና ሱማሌ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ ባስከተላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ባለፈው ሐምሌ ወር ባቀረባቸው ምክረ ሐሳቦች አተገባበር ላይ ሲያደርግው የቆየውን ክትትል አስመልክቶ ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚሁ ሪፖርት በቦረና ዞን በሦስት ዓመት ውስጥ ባሉ አምስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለመዝነቡ የድርቁ ተፅዕኖ መጨመሩን አመላክቷል፡፡
በዞኑ 870 ሺሕ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እና 900 ሺሕ የሚጠጋ የኅብረተሰቡ ክፍል ደግሞ አስቸኳይ የውሃ ምላሽ ያስፈልዋል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ከምግብ እጥረት የሚመነጩ የጤና እክሎች በሕጻናት፣ በእርጉዝና በሚያጠቡ ሴቶች እንዲሁም በአረጋዊያን ላይ መከሰታቸውን አስገንዝቧል፡፡
በቦረና ዞን 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት እንስሳት በድርቁ ሳቢያ የሞቱ ሲሆን፤ ይህም በገንዘብ ሲተመን ወደ 33 ቢሊዮን ብር ይሆናል ተብሏል፡፡ ይህን ተከትሎም 60 ሺሕ የሚሆኑ አባወራዎች እንስሶቻቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
ኮሚሽኑ አክሎም በዞኑ የድርቁ ተፅዕኖ በመባባሱ ወደ 69 ሺሕ የሚሆኑ አባወራዎች ወይም ከ378 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን በመጥቀስ፤ በዚሁ ሳቢያ ሴቶች ለጾታዊ ጥቃቶች ይበልጥ ተጋላጭ ሆነዋል ነው ያለው፡፡
በሶማሌ ክልል ያለው ወቅታዊው የድርቁ ተፅዕኖም በኹሉም የክልሉ 11 ዞኖች ጨምሮ ይገኛል ብሏል፡፡
ለሦስት ተከታታይ የዝናብ ወቅት ዝናብ ባለመዝነቡ የድርቁ ተፅዕኖ በዳዋ፣ በሊበን፣ በአፍዳር፣ በኮራህይ እና በጀረር ዞኖች ይበልጥ የጸና መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቅሷል፡፡
አያይዞም በክልሉ ኹለት ሚሊዮን የሚደርሱ የቤት እንስሳት መሞታቸውን እና በሸበሌ ዞን ብቻ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 50 ሺሕ የሚሆኑ የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት እንደሞቱ አመላክቷል፡፡
በክልሉ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የውሃ ምላሽ እንዲሁም 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ የምግብ ድጋፍ የሚፈልጉ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
እንዲሁም ከ112 ሺሕ በላይ ሕጻናት ለምግብ እጥረት የተጋለጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ አኃዝ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ14 በመቶ ጭምሯል ነው የተባለው፡፡
የክልሉ ማኅበረሰብ አስቸኳይ እርዳታ ፍለጋ ይበልጥ ተፈናቅለው ወደ መጠለያ ጣቢያዎች እየገቡ እንደሚገኝ እንዲሁም በድርቁ የተነሳ ከ600 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል በመዘጋታቸው ከ90 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ተጎጂ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ሆኖም በኹለቱም ክልሎች በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች እየቀረበ ያለው ሰብዓዊ እርዳታ ከደረሰው መጠነ ሰፊ ጉዳት ጋር ተመጣጣኝ አለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በሳሙኤል ታዴ
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n