TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Sep, 10:43

Open in Telegram Share Report

አልሸባብ ባደረሰው ጥቃት በርካታ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች መግደላቸው ተገለጸ

👉የአማጺ ቡድኑ “167 ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን ገድያለሁ” ብሏል

ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአልሽባብ ታጣቂዎች ትናንት እሁድ መስከረም 6/2015 ጧት ላይ በሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት ባኮል በአጀብ ይሄዱ በነበሩ ኹለት የጭነት ተሽከርካሪዎች (ኮንቮይ) ላይ የደፈጣ ጥቃት ማድረሳቸውን የሶማልያ ባልስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ጥቃቱ ያነጣጠረው በኹለት የተሽከርካሪ ቡድኖች (ኮንቮዮች) ላይ ሲሆን፤ አንደኛው ከሶማልያ የይድ ከተማ ወደ ዋጂድ፣ ኹለተኛው ደግሞ ከኤል ባርዶ ወደ ሁደር ከተማ ሲጓዝ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደሮች በዋጂድ እና ሁደር የጦር ሠፈር ያላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣን እንደተናገሩት፤ ጥቃቱ በጦር ሠፈሮቹ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች የተላኩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በሚያጅቡ ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሁዱር ከንቲባ ኦማር አቡልዳሂ መሀመድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች ደፈጣውን ማክሸፋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ በተደረገው የተውኩስ ልውውጥ አማጺዎቹ 50 የሚደርሱ ተዋጊዎችን ያጡ መሆኑን ለቪኦኤ የሶማልኛው ክፍል አስታውቀዋል፡፡

አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱ የወሰደ ሲሆን፤ በጥቃቱ 167 ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን መግደሉን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማወደሙን በርካታ የጦር መሳሪዎችን መማረኩን አስታውቋል፡፡

በኹለቱ ወገኖች የተገለጸው አሃዝ በትክክለኛ ወገን አለመረጋገጡ ተመላክቷል፡፡

በሶማልያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ለቮኢኤ በሰጡት ቃል፤ አልሸባብ በማህበራዊ ሚዲያ የተናገረውን “ፕሮፖጋንዳ ” ነው ብለዋል፡፡

“ለማጥቃት (የኢትዮጵያን ኃይሎች) ይሞክሩ ይሆናል ይሁን እንጂ ግን ለአስር ደቂቃ እንኳ የኢትዮጵያን መከላከያ ኃይሎች ሊገጥሙ አይችሉም” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

አያይዘውም “ይህ በሚገባ የታጠቀ ፕሮፌሽናል ጦር ነው” አልሸባብን በተመለከተ ሁልጊዜም በሚገባ ይቀጣዋል፣ ስለዚህ ይሄ ጸረ ኢትዮጵያ እና ከጸረ ኢትዮጵያ መከላከያ ፕሮፓጋንዳነት የዘለለ አይደለም፡፡” በማለት የተባለውን አጣጥለዋል፡፡

የደህንነት ምንጮች ደፈጣው እውነት መሆኑን አመልክተው፤ “በአልሸባብ የተነገረው እጅግ የተጋነነ ነው፡፡” ማለታቸውንም ዘገባው አመላክቷል፡፡
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

6.4k 0 17 31
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot