የዘ ኢክኖሚስ ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የሥራ ፈቃድ ተሰረዘ
አርብ ግንቦት 5 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የዘ ኢኮኖሚስ መጽሔት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር በኢትዮጵያ የነበረው የሥራ ፈቃድ መሰረዙን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ለጋዜጠኛው በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው፤ ጋዜጠኛው ከሙያ ሥነ መግባር ውጭ በተደጋጋሚ ሲሰራ በመገኘቱ ተደጋጋሚ የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል።
በተጨማሪም ከጋዜጠኛው ጋር ውይይት በማድረግ ከስህተቱ እንዲታቀብ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ባለስልጣኑ ገልጿል።
ይሁን እንጂ ቶም ጋርድነር የሙያውን ሥነ ምግባር በማክበር ለመስራት ባለመቻሉ ከዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2014 ጀምሮ በኢትዮጵያ የነበረው የጋዜጠኝነት የሥራ ፈቃድ መሰረዙንና ከዚህ በኋላ በጋዜጠኝነት ሥራ በኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እንደማይችል ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ዘ ኢኮኖሚስት በዚህ ጋዜጠኛ ምትክ ሌላ የሙያውን ሥነ ምግባር አክብሮና ገለልተኛ ሆኖ መስራት የሚችል ሰው መድቦ ማሰራት እንደሚችልም ባለስልጣኑ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ገልጿል።
_______________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n