ጤናዎ በቤትዎ-Online Medicine


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified



Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: 😁 ፈገግታ እና ቁምነገር™🌍📚📖
👇👇CLICK👇👇
https://t.me/bulkservicebot?start=264936139

ከዛም ☞ START ☜ የሚለውን ይጫኑት

ሼር ያድርጉት✔


እንኳን ለ1441ኛው ኢደል አድሃ አረፋ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳቹ! ኢድ ሙባረክ!
عيد مبارك‎


Forward from: 😁 ፈገግታ እና ቁምነገር™🌍📚📖
የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከልና ህሙማንን ለማስታመም የሚከተሉ ነገሮችን እንጠቀም ይላሉ ዶክተሩ

1) ሻይ በዝንጅብል፣ በቀረፋ፣ በቁንፉድና በነዕናእ ኣፍልቶ በቀን ለሁለት ጊዜ ያህል መጠጣት

2) ነጭ ሽንኩርትና ጥቁር አዝሙድ መጠቀም

3) ሌሎች የመከላከያ መንገዶችንም ንፅህናን ከመጠበቅ አንጻር አለመዘናጋት

@worldfunfactsbot @worldfunfactsbot


ኢትዮ ያላቹ አትክልት ተራ የድንብላል ቅጠል ብላችሁ ግዙ
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg


ኩላሊት በሽታ አለቦትን?

ውድ ወንድምና እህቶቼ የሚከተለውን የኩላሊት መድሀኒት አዘገጃጀት ይከታተሉ ፦

የዌራ ዘይት 3 የሾርባ ማንከያ 2 ትልቁ ሲኒ የተፈጨ ቦግዶኒስ ይላወሳል 3 የሾርባ ማንከያ ቦግዶኒስ በ1 ሌትር ውሃ ማታ ማታ ሲተኛ በውሃው በጥብጦ መዋጥ ሲተኙ በሚያመው ኩላሊት በኩል መተኛት አከታትሎ ሳምንት ሳይረሳ ከተደረገ የኩላሊት ጠጠር አለ ተብሎ ኦፖራሲዮን ይሆናሉ ተብሎ ዶክተር የፃፈለት እንኳን ቢኖር በበጉዶኒሱ ሰበብ ጠጠሩ ይወጣል ።

መውጣቱ ሊታወቅም ይችላል የተለቀ ከሆነ ትንሽ ከሆነ ሳያቁት ይወጣል በተለይ አንድ ሌትር በቀን ከጠጡ ይጨመርና ቋቅ እስኪል ጥግብ ብለው መጠጣት አለቦት አደራ በሚያም ጎን መተኛቱ አይዘንጉ ከመዳኒቱ አላህ ያገናኛችሁ የሚባለው ይህን የመሰለ ሰበብ በተግባር የታየለት በግዶኒስ በመቀቀልም በረድ አድርጎ ውሃው ጠግቦ በመጠጣትም እንደ አትክልትም መብላት የተቀቀለውም መብላት ይመከራል።

የኩላሊት ህመም ያለበት ሰው ለመቆም የሚከለክል ለመንገድ ጉዞ የሚከለክል ጎን የሚወጋ ጠጠር ያለበት ፊት እንኳን እንዲገረጣ መልክ ቢቀይርም ሰበቡን በማድረስ በአሏህ እርዳታ በጉዶኒስ ይታከሙ ።

ለራሴም ሰበብ ሆኖኛል ውጪ የተፃፈለት የኩላሊት ጠጠር ያለበት ወጥቶለት በሶፍት ተይዞ ወደ ወጭ የፃፈው የነበረው ዶክተር ተይዞ ሲሄድ በአይኔ ያየሁት ከወንድ ልጅ ብልት ይወጣል ተብሎ የማይታሰበ በአይኔ በብሌኑ አይቻለሁ ወደ ዶክተሩ የተኬደው ቀሪ ካለ ተብሎ ቼክ ለመደረግና ዶክተሩ አዝኖ ሲመረምረው ወደ ሌላሃገር ሲፃፍለት የገንዘብ አቅም እንደሌለው ሲነግረው ሰውየው በጣም ያለ ውጪ እንደ ማይቻል በሃዘኔታ ስለሸኘው ለማበሰርም ጭምር ከአቶብስ ተራ ወደ ሾላ ሲሄድ በኩላሊት በሽታ ይሰቃያሉ ኩላሊት በሽታ ያለበት ካለ ይህን ጉድ ከኔ ነው የወጣው ስለዚ የተያዘ ካለ ብሎ አሰራሩ ነገረኝ።

ሁለት ሆነን ኩላሊታችን የሚያመን ሰራነው ሁለታችን ሰበብ ሆነን ቦግዶኒሱ እኛም ሰበብ ሆነን እናተም ተጠቀሙበት የነገርኳቸው ሁሉ እንደተዋቸው እየነገሩኝ ነው ወሊላሂል ሃምድ አላህ የሁሉም ነገር መድሃኒት ፈጠረ ለኩላሊት ከፈጠረው መድሃኒት አንዱ ብየዋለሁ ።

በግዶኒስ መልካም ተግባር ከሰሩ በትክክል ይድናሉ ሼር ሼር ሼር አድርጉት ለተሰቃየ ሰው ሰበብ ይሆናል እራሴም ተጠቅሜበት ድራሹ ጠፋ መቆምና ብዙ ጉዞ ማድረግ አልችልም ነበር ወሊላሂል ሃምድ ተሻለኝ ብዙ ሰው በዚ በሽታ የተጠቃ አለ አሰራጩት ለአንድ ሰው ሂወት ማዳን አጅሩ ከባድ ነው ምርጥ የኩላሊት ዶክተር ነው ተጠቀሙት ።

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg




ጤና ይስጥልኝ ውድ የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮቻችን ለዛሬ ስለ ደም ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ?
አብረን እንከታተል
ABO blood Group System
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

የደም ዓይነት በቀይ የደም ሴሎች ሽፋን(ገጽ) ላይ የሚገኝ በውርስ የወሰድነውን አንቲጅን(Antigen) መሠረት ያደረገ የደም ክፍፍል ነው፡፡
አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ እነሱም ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ ናቸው፡፡
የደም ዓይነት ከእናትና አባት በወረስነው ዘረመል(ጂን) ይወሰናል፡፡
ሰውነታችን በአማካይ ከአራት እስከ ስድስት ሊትር ደም ይይዛል፡፡
ደም ከቀይ የደም ሴል፣ ነጭ የደም ሴል እና ፕሌትሌትስ (በፈሳሽ መሰል ፕላዝማ) የተሰራ ወይም የተገነባ ነው፡፡
የፕላዝማ(Plasma) 90% ውሃ ሲሆን በተጨማሪ ፕሮቲን፣ ሆርሞንና ውጋጅ ቆሻሻዎችን ይዟል፡፡
የደማችን 60% የሚሆነው ፕላዝማ ሲሆን 40% የሚሆነው ደግሞ የደም ሴሎች ናቸው፡፡
የደም ሴሎቻችን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ተግባር አላቸው ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጂን ወደተለያየ የሰውነት ክፍል ያደርሳሉ ካርበን ዳይኦክሳይድ እና ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ያስወግዳሉ፤ ደም ቀይ ቀለም እንዲኖረው አድርገውታል፡፡
ነጭ የደም ሴሎች ሰውነታችን በሽታ የመከላከል ሥርዓት አንዱ ክፍል ሲሆን ኢንፌክሽንን በመዋጋት ይረዳናል፡፡
ፕሌትሌትስ ደም እንዲረጋ በማድረግ የደም መፍሰስን ይከላከላሉ፡፡
የደም ዓይነታችን የሚለየው/የሚታወቀው በደም ውስጥ በሚገኙ አንቲጅን(Antigen) እና አንቲበዲ(Antibody) አማካይነት ነው፡፡
አንቲበዲ(Antibody) ሰውነታችን ከውጪ ለሚገቡ ጀርሞችን ለመከላከል የሚጠቀምበት የበሽታ መከላከያ ሥርዓት ክፍል ነው፡፡
አንቲጅን በቀይ የደም ሴሎች ገጽ ላይ የሚገኙ ፕሮቲኖች ናቸው አንቲበዲዎች በፕላዝማ ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን ሲሆን ከውጭ ወደሰውነታችን የገቡ ማንኛውንም ነገሮች በመለየት እንዲወገዱ ለበሽታ የመከላከል ስርዓት ጥቆማ ያደርጋል፡፡
የኤ.ቢ.ኦ የደም ሥርዓት ክፍፍል ምን ይመስላል?
አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ፡፡
• ኤ(A)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ቢ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡
• ቢ(B)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ቢ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ኤ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡
• ኤቢ(AB)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ እና ቢ አንቲጅን ይገኛሉ (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ምንም ዓይነት አንቲበዲ አይገኝም)
• ኦ(O)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ምንም ዓይነት አንቲጅን አይገኝም (በፕላዝማ ውስጥ ሁለቱም ኤ እና ቢ አንቲበዲ ይገኛሉ)፡፡
የትኛው የደም ዓይነት ለየትኛው የደም ዓይነት መስጠት ይችላል?
✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ለማንኛውም ሰው ደም መለገስ ይችላል፡፡
✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡
✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ያለው ሰው ቢ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡
✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤቢ የደም ዓይነት ላለው ሰው ብቻ ደም መለገስ ይችላል፡፡
ከየትኛው የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ?
✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኤ(A) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ቢ(B) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ከማንኛውም የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ፡፡
ከኤ(A) እና ቢ(B) አንቲጅን በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ አንቲጅን አለ እሱም አር.ኤች ፋክተር(Rh factor) ይባላል፡፡

በደም ውስጥ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል በደም ውስጥ ሲገኝ ፖዘቲቭ (+) ይባላል በደም ውስጥ ሳይገኝ ሲቀር ደግሞ ነጌቲቭ(-) ይባላል፡፡

• ሌሎች መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንድደርስዎ ፔችንን ላይክ ሼር ያድርጉ
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ተጭነው የኛ ቤተሰብ ይሁኑ

ስለምትከታተሉን ከልብ አመሰግናለሁ መልካም ጤንነት

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg






رمضان مبارك
በመላው አለም ለምትገኙ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች እንኳን ለ1441ኛው የረመዳን ወር በሰላም አደረሰን አደረሳቹ! መጪው ረመዳን የሰላም የፍቅር እንዲሁም የጤና እንዲሆንላቹ ምኞታችን ነው።

መልካም የረመዳን ወር ይሁንላቹ

ʜᴀᴘᴘʏ ʀᴀᴍᴇᴅᴀɴ ᴛᴏ ʏᴏᴜ ᴀɴᴅ ʏᴏᴜʀ ғᴀᴍɪʟʏ 🌙






ስለ ዳማከሴ ይህን እናውቃለን?
በሀገራችን ወደ 85 ሺህ የሚጠጉ እጽዋት ለሕክምና አገልግሎት ይውላሉ። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ደማ ከሴ አንዱ ነው።
• ደማ ከሴ አገር በቀል ተክል ሲሆን በሳይንሳዊ ስሙ ኦሲመም ላሚፎለም(Ocimum lamiifolium) እየተባለ ይጠራል።
• ተክሉ ሁለገብ የሆነ የመድኃኒትነት ባህሪ አለው። በሀገራችን በአብዛኛው ቦታዎች የምች መድሀኒት በመባል ይታወቃል።
• በባህላዊ ሕክምና ከተክሉ የሚገኝ ጭማቂ ለተለያዩ የዐይን በሽታዎች፣ ለራስ ምታት፣ በተለይ ትኩሳት ሲያጋጥም በባሕላዊው አጠራር ‹‹ምች›› እየተባለ ለሚጠራው ሕመም ማስታገሻነት ይውላል።
• በተጨማሪም ለምለም ቅጠሉ ተጨምቆ ሲጠጣ ለተቅማጥ፣ ለአሜባ (ደም ያለው ተቅማጥ)፣ ለሳልና ለሌሎችም ሕመሞች ለማስታገሻነት ይውላል።
• በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ለቆዳ፣ ለአንጀት፣ ጨጓራና ተያያዥነት ላላቸው ሕመሞች ይወሰዳል።
• ተክሉ ለተለያዩ የጤና ችግሮች አስተማማኝ የሚባል የፈውስ ባህሪ አለው።
• የፀረ-ወባ ገቢርነት እንዳለውም ይታወቃል።
• ቅጠሉን በማጨስ የወባ ትንኞችን ከአካባቢ እንዲርቁ ማድረግ ይቻላል።
• በተጨማሪም ፀረ ፈንገስና ፀረ ነፍሳት ባህሪ አለው። እንዲሁም ትኩሳትን ያበርዳል።
• ደማ ከሴ በኢትዮጵያ የሚበቅል ዕፅ ሲሆን ለዕቃ ማጠኛ አገልግሎት ይውላል።
• አብዛኛውን ጊዜ ለመድኃኒትነት ጥቅም የሚውለው ቅጠሉን በመጭመቅና በማሽተት፣ ወይም ቅጠሉን በውሀ አፍልቶ በመታጠን ወይም በመጠጣት ነው።
• ለጉንፋን፣ ለራስ ምታት ጥቅም ላይ ይውላል።
• የቅጠሉ ጭማቂ በውሃ ወይም ከቡና ጋር ለትኩሳት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።
• የአንጎል ጥቃት (ስትሮክ)፣ የጀርባ አጥንት መጨፍለቅ፣ የጅማት መጨማደድን ለማከም ከፍተኛ ጥቅም አለው።

• በጥቅሉ ከነርቭና ከጡንቻ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለማከም ማለትም የጡንቻ መዛል፣ ከቀዶ ሕክምና በኋላ የሚደረጉ የአካል እንክብካቤዎች፣ ከስፖርት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን፣ ከእጅና እግር መቆረጥና ከአጥንት መሰንጠቅ ጋር ያሉ ችግሮችን በቀላሉ ለማከም አገልግሎት ላይ ይውላል።

• የቅጠሉ ወይም የልጡ አካል በቁስል ላይ በመለጠፍ ቁሰሎችን በቀላሉ ለማዳን አገልግሎት ይሰጣል።
ሼር ለወዳጅወ

https://youtu.be/GbCaoS3nw0w https://youtu.be/GbCaoS3nw0w


Forward from: 🇪🇹 ኮሮና ሰበር ዜና 🇪🇹 Corona Update🇪🇹
"የባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔም በኮሮናቫይረስ መያዜ ተነገረኝ " የ3 ልጆች እናት ወ/ሮ አበራሽ ኦሮሞ
"ከ 100 በላይ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ሀገር በኮሮና ሞተዋል! 👇ይመልከቱት👇
https://youtu.be/GbCaoS3nw0w https://youtu.be/GbCaoS3nw0w https://youtu.be/GbCaoS3nw0w
#ሼር #Share


ለናተ የሚጠቅም ጤና መረጃ ከማቅረብ መቼም ወደኋላ አንልም እርሶ ብቻ ይከታተሉን መረጃ ሼር ያድርጉ

እንቁላል በመጠቀም ፀጉራችንን በቀላሉ ማሳደግ እና መንከባከብ እንችላለን።

እንቁላል ለፀጉር እድገት አሰፈላጊ የሆነውን ፕሮቲን በውሰጡ በመያዙ ፀጉራችንን በቀላሉ ሊያሳድግልን ይችላል ተብሏል ።

አዘገጃጀት
-በጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ ሁለት እንቁላል
ሰብረን በመጨመር አዛ ውሰሁጥ
ሁለት የሾርባ ምንኪያ የወይራ ዘይት
ቀላቅለን በደንብ አንድ ላይ ማዋሃድ

አጠቃቀም
1~ፀጉራችንን በሻምፖ ወይም በሳሙና በማደረግ በደንብ መታጠብ ።

2~የታጠብነውን ፀጉር በፎጣ ተጠቅመን ማድረቅ።

3~በመቀጠልም የደረቀው ፀጉራችን ላይ የዘጋጀነውን የእንቁላል ውህድ ሙሉ በሙሉ መቀባት ±አዚህ ጋር ልብ ልንል የሚገባን ነገር ቢኖር የፀጉራችውን ጫፎች ሳይቀር ሙሉ በሙሉ የእንቁላል ውህድ ተዳርሶ መቀባት አለበት ።

4~የተቀባነውን የእንቁላል ውህድ በሻወር ኮፍያ ወይም በፔሰታል ጠቅልለን በማሰር ከ10-20 ደቂቃ ማቆየት ።

5~የመታጠቢያ ሰዓታቸን እንደደረሰም ፀጉራችንን ሙሉ በሙሉ በኮንዲሺኘር በማደርግ መታጠብ ይኖርብናል ።

ማሳሰቢያ :-
-የተቀባነውን እንቁላል ከ20 ደቂቃ በላይ በፀጉራችን ላይ ማቆየት የለብንም -ምክንያቱም እንቁላሉ በቆየ መጠን ፀጉራችንን ከመጥቀም ይልቅ ጉዳት ሰለ ሚያሰከትል።

_ይህንን የእንቁላል ውህድ በወር አንድ ጊዜ ብቻ መጠቅም በቂ ነው ።

እንቁላሉን በዚህ መልኩ በመጠቀም ፀጉራችን በቃሉ እንዳይበጣጠሰ፥ ወዙን የጠበቀ እና ቶሎ እንዲያድግ ማድረግ እንችላለን።


በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የሚያሳይ ምስል
በባዬ ተሻገር (ኢንጅነር) የተዘጋጀ

https://youtu.be/HUFqtcQbunA https://youtu.be/HUFqtcQbunA


Forward from: 🇪🇹 ኮሮና ሰበር ዜና 🇪🇹 Corona Update🇪🇹
Watch ወቅታዊውን ኮሮና ቫይረስን በማስመልከት የተከናወነ "የሰው ልጅ ክብር! ሰብዓዊነት ፍትህ ነፃነት እና እኩልነት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ምርጥ ውይይት👇 ተጋበዙልኝ👇Watch👇
https://youtu.be/HUFqtcQbunA https://youtu.be/HUFqtcQbunA https://youtu.be/HUFqtcQbunA
#ሼር ቢያደርጉት ብዙ ሰው ይማርበታል።


Forward from: 🇪🇹 ኮሮና ሰበር ዜና 🇪🇹 Corona Update🇪🇹
‼️ሰበር ዜና‼️
‼️9 ሰው ኮሮና ተገኘበት‼️
በኢትዮጵያ ተጨማሪ ዘጠኝ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
****************

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ አላቸው።

ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት።

አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል።

የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።

በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEOO1uT6Kz7kvX6Pmg

ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።
via Ministry of health


Forward from: 🇪🇹 ኮሮና ሰበር ዜና 🇪🇹 Corona Update🇪🇹
"❗️ሰበር ዜና❗Watch "❗️ሰበር ዜና❗
ስለ ኮሮና ቫይረስ ያልሰማናቸው ሚስጥሮች | ከ ቫይረሱ በስተጀርባ የነማን እጅ አለበት? መታየት ያለበት ድብቅ ቪዲዮ"👇

https://youtu.be/b6qGC6eDwig https://youtu.be/b6qGC6eDwig 👆Watch "❗️ሰበር ዜና❗


ሁሉም ሰዉ አንድ ስለኮሮና ስርጭት እንዲያዉቀዉ ምፈልገዉ ነገር አለ ። በተደጋጋሚ ስለሚጠየቅ ልናገረዉ ።
የኮሮና ስርጭት ሶስት ደረጃ አለዉ ።
http://T.me/ethiohagere

1. የልምምድ ግዜ (Lag time ) -: ይሄ ግዜ የመጀመሪያ ቫይረሱን የያዘ ሰዉ ለሌላዉ የሚያስተላልፍበት ግዜ ጀምሮ ፣ ቫይረሱ በተከሰተበት አዲስ ማህበረሰብ ዉስጥ ለመስፋፋት ራሱን የሚያመቻችበት ነዉ ። ይሄ ግዜ የቫይረሱ ስርጭት እና መተላለፍ ፈጣን አይደለም ። እንደየ ማህበረሰቡ ሁኔታ እና የአኗኗር ባህሪ ይወሰናል ።

2. ፈጣን የስርጭት ወቅት ነዉ። ይሄ ግዜ የቫይረሱ ተጠቂዎች ከ3-5 ቀናት ባለ ጊዜ በእጥፍ እየጨመሩ የሚመጡበት ፣ ተያያዥ ሞት ከቀን ወደ ቀን የሚጨምርበት ፣ አደገኛዉ ግዜ ነዉ ። በዚህ ግዜ የምንዋጋዉ ሁለት ነገር ነዉ ። ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ማድረግና (ብዙ ሰዉ እንዳይዝ ማድረግ )ና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ ሞት እንዳይደርሱ ህክምና ማመቻቸት ነዉ ።

3. ኮሮና በፍጥነት የጨመረዉ ስርጭቱ የሚገታበት ፣ የሞት ቁጥር የሚቀንስበት ብሎም ወደ አደጋዉ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ የሚወርድበት ነዉ ።
(ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል የሚል ሃሳብ ከልባችሁ አዉጡ )
***

አንዴ ኮሮና ሀገር ዉስጥ መከሰቱ ከታወቀ በሗላ የትኛዉ ደረጃ ላይ ነህ እንጂ ሌላዉ ሃተታ ጥቅም የለዉም ።
አሁን ኢትዮጵያ ያለችዉ የመጀመሪያው ደረጃ ላይ ነች ። ባለዉ የተረጋገጠ መረጃ መጠን ማለት ነዉ ።

** http://T.me/ethiohagere
ዳይ!ርቀትህን ጠብቅ !!!

20 last posts shown.

6 948

subscribers
Channel statistics