አል አኒስ ቁርአንና ሱና አካዳሚ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


👉የቻናሉ ትኩረትና አላም ቁርአን ማስተማር
👉ቅን ባለራእይ ዲኑን የሚወድ በእውቀት የበለፀገ ትውልድ መፍጠር ነው ሼር በማድረግ ለምታግዙንና ትምህርቶቻችንን ለምትከታተሉ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን አስተያየት በዚህ እንቀበላለን@Alanis166_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


አጭር መልክት የሸእባን ወር በተመለከተ

https://t.me/alanisquranacademy






👉የጀግኖች ተምሳሌት

ከታሪክ ማህደር

አስማ ቢንት አቡ በክር
ከታሪክ እንማር
🎤ትረካ አቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ
https://t.me/alanisquranacademy


👉ከሺ ወንዶች በላይ ጀግና ሴት
ከታሪክ ማህደር

✅ሊደመጥ የሚገባ ታሪኽ

ኑሰይባህ ረ.አ
የጽናት ተምሳሌት
ሼር

https://t.me/alanisquranacademy


ከታሪክ ማህደር ሊደመጥ የሚገባ 👆

የፊርአውን ሚስት አስያ የሚገርም ጽናት ድንቅ ታሪክ

🎤በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ
ሼር
https://t.me/alanisquranacademy


ከፈትዋ ማህደር ጥያቄ፡- ወደ አንዳንድ “ሽኽ” ነኝ ወደሚሉ በተለምዶ ኪታብ ገላጭ ወደሚባሉ ሠዎች መሄድ እንዴት ይታያል? አንዲት ሴት ፆመኛና ሰጋጅ ልትሆን ትችል ይሆናል ነገርግን ቤትዋን የዘረፉ ሠዎችን ማንነት ለማወቅ ወደነዚህ “ሸኾች” ትሄዳለች ይህ ነገር እንዴት ይታያል?



መልስ፡- በአሏህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በሆነው።

ማንም ሰው ቢሆን ሩቅን የሚያውቅ የለም። ሩቅን አውቃለሁ የሚል ካለ የጠንቋዮች ምድብ ውስጥ ይካተታል። ጥንቆላን ደግሞ ኢስላም እንደ ክህደት (ኩፍር) ይመለከተዋል። ጠንቋዮች አንዳችን ሩቅ ሊያውቁ ከቻሉ የሚያውቁትን ያወቁት በጂኒዎች አማካኝነት ነው። ከዚያች ጋር ቅጥፈታቸውን ይደራርባሉ።

ሙስሊም ከእነዚህ ሰዎች ደጃፍ መቅረብ የለበትም። በሸኸ አብዱረህማን ኢብኑ ናስር በራክ (የኢማም ሙሀመድ ኢብኑ ሱዑድ ዩንቨርሲቲ የትምህርት ክፍል አባል) እንዲህ ይላሉ፡- “የሙስሊሞች እምነት ውስጥ ከተረጋገጡ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከአላህ (ሱ.ወ) ውጭ ሩቅን የሚያውቅ አለመኖሩ ነው። አሏህ እንዲህ ብሏል፡-

قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ

 

“በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም። ግን አላህ (ያውቀዋል)። መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም በላቸው።” (አን-ነምል 27፤65)

የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንኳን ሩቅን አውቃለው ከማለት ተቆጥበዋል። “እኔ ሩቅን አላውቅም!” ሲሉም ተደምጠዋል። አሏህ አንዲህ ይላል፡-

قُل لَّا أَقُولُ لَكُمْ عِندِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ لَكُمْ إِنِّي مَلَكٌ

 

“ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም። ሩቅንም አላውቅም። ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም።” (አል-አንአም 6፤50)

ሩቅን አውቃለሁ የሚል ተሟጋች ካለ ሙስሊም አይደለም። ይሁንና ድግምተኞችና ጠንቋዮች ሩቅን እናውቃለን በሚል ይሞግታሉ። በእርግጥ አንዳንድ ነገሮችን ሊያውቁ ቢችሉም ብዙ ነገሮችን ግን ይስታሉ። በሀዲስ ውስጥ እንደተዘገበው ጠንቋዮች አንዳንድ ዘገባዎችን የሚቀበሉት የሰማይን ዜና ከሚያዳምጡ አጋንንት /ጅኖች/ ናቸው። እነርሱ የሚሰሟትም በመላኢካዎች ችቦ ከመመታታቸው በፊት የሰሟትን ነው። እዚሁ ላይ መቶ ውሽቶችን በማከል ጠንቋዮች ወደ ደንበኞቻቸው ጆሮ ያደርሳሉ። ደንበኞቻቸው ውሸቶቹን የሚያምኗቸው በእነዚህ ጥራዝ በሆኑ እውነቶች ሳቢያ ነው።

በጥቅሉ ወደ ጠንቋዮች መሄድ ክልክል ነው። በድብቅ የተሰረቀ ነገር የት እንዳለ አውቃለሁ ወደሚል ጠንቋይ ጋር ስለሚሄድ ሲናገሩ መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- “ጠንቋይ ጋር የመጣና የሚናገረውን ያመነ በሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ በወረደው የካደ ነው።”

እነዚህን የመሰሉ ሠዎች “ሸኽ” የሚለው ተቀፅላ አይገባቸውም። “ዓሊም”፣ “ኪታብ ገላጭ”… በሚሉ ሥያሜዎችም ሊጠሩ አይገባም። ሩቅን እናውቃለን የሚል ሰው አታላይ ነው። ሠዎች ሊርቁት ይገባል። ማንነታቸውን የተረዳ ሠውም ያጋልጣቸው። ሰዎችን ከዙሪያቸው ማራቅ ይገባል። ጥንቆላ አላህ (ሰ.ዐ) ዘንድ ውግዝ ከሆኑ ነገሮች መሀል ከዋናዎቹ ይቆጠራል። ወደ ጠንቋይ መሄድም እንዲሁ። አሏህ የተሻለ ያውቃል

https://t.me/alanisquranacademy


ከፈትዋ ማህደር
ጥያቄ፡- ሸሪዓን የሚጥስ ኃጢያተኛ ሰው ሙስሊሞችን ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል?

መልስ፡- አብዝሃኞቹ የአህሉ ሱና ዑለሞች ኃጢያተኛ (ዓሲ) የኢማምነት መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ኢማም ሆኖ ማሰገድ እንደሚችል ይስማማሉ። ነገርግን ኢማምነቱን ይጠሉበታል። ሰዎችን መልካም ሰው ቢያሰግድ ተመራጭ ነው።

የአውሮፓው የፈትዋና የምርምር ማዕከል (المجلس الأوربي للبحوث والإفتاء/European Council for Fatwa and Research) የሰጠው ፈትዋ እንዲህ ይላል፡-

ሶላቱ ለራሱ የበቃው ሰው ሌሎች ሰዎችንም ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይፈቀድለታል። ኢማምነት ላይ የተሻለውን ስርዐት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ገልጾታል። እንዲህ ይላሉ፡-

يؤم القوم أقرؤهم لكتاب الله ، فإن كانوا في القراءة سواء فأعلمهم بالسنة، فإن كانوا في السنة سواء فأقدمهم هجرة، فإن كانوا في الهجرة سواء فأقدمهم سنًا، ولا يؤمن الرجلُ الرجلَ في سلطانه، ولا يقعد في بيته على تكرمته إلا بإذنه 

“ሰዎችን የአላህን መፅሐፍ ይበልጥ ያነበቡት ያሰግዷቸው። በቂርኣት እኩል ከሆኑ ሱናን ይበልጥ ያወቀው ሰው ያሰግዳቸው። ሱናም ላይ እኩል ከሆኑ ቀድሞ የተሰደደው ያሰግድ። ሂጅራ ላይ እኩል ከሆኑ እድሜው ከፍ ያለው ያሰግድ። ሰውየው ሰውየውን በስልጣኑ ቦታ ላይ አይምራው። በቤቱ ውስጥም እርሱ በሚከበርበት ቦታ ላይ ያለፍቃዱ አይቀመጥ።”

ኃጢያተኛነት የሶላትን ተቀባይነት አያሳጣም። ማንኛውንም መልካምም ሆነ ጠማማ ሙስሊም ተከትሎ መስገድ መቻሉ ከአህሉ ሱና እምነት ውስጥ ይጠቀሳል።

አንዳንዴ ደግሞ ኢማሞች ይፈፅሟቸዋል የሚባሉት ስህተቶች ልዩነት የሚፈቀድባቸው ዑለሞች የተለያዩባቸው ሃሳቦች (ኢጅቲሃዳት) እንጂ ኃጢያቶች አይደሉም። በኢስላም ውስጥ ቁርጥ ተደርገው የተቀመጡ ልዩነት የሌለባቸው ነገሮች አይደሉም።

ለምሳሌ የሱብሂ ሰላት ላይ የቁኑት ዱዓ ማድረግ/አለማድረግ፣ ልብሱ ከቁርጭምጭሚት በታች የወረደ ሰውን ተከትሎ መስገድ፣ ጺሙን የሚላጭን ሰው ተከትሎ መስገድ እና መሰል ዓሊሞች የተለያየ አቋም የያዙባቸው እና ፈትዋዎች የተለያዩባቸው ነገሮች ናቸው ብዙ ጊዜ ኢመሞች ይሰሯቸዋል ተብለው የሚጠቀሱ ስህተቶቸች። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች መንቀፍ እና ማብጠልጠል አይቻልም። መገሰፅ እና መምከር ግን ይቻላል። ምናልባት በጉዳዩ ላይ ሰውየው ዘንድ የተሻለ ዕውቀት ልታገኝ ትችላለህ። ስለዚህ በእነዚህ መሰል ጉዳዮች ዙርያ ተቃራኒ የሆነ ሃሳብ ያለውን ሰው መንቀፍ አይቻልም ስንል በዋናነት ደግሞ እርሱን ተከትሎ መስገድ ይበቃል ማለት ይቻላል።

አላሁ አዕለም!

https://t.me/alanisquranacademy


ከፈትዋ ማህደር 
ጥያቄ: ጠንቋይ አሊያም ደጋሚ ሰው ዘንድ በመሄድ እገሌ ድግምት ተደርጎበታል ወይ? ብሎ መጠየቅ ይቻላልን? የተደገመን ድግምት በሌላ ድግምት ማስፈታት/ማከሸፍስ ይፈቀዳል ወይ?




መልስ:- በፈለስጢን የአልቁድስ ዩኒቨርስቲ የፊቅሂ መምህር የሆኑት ዶ/ር ሑሳሙዲን ኢብን ሙሳ ዐፋነህ እንዲህ ይላሉ:-

አዋቂዎች ወደሚባሉት፣ ጠንቋይ ቤቶችና ወደመሳሰሉት ቤቶች መሄድ በሸሪዓ የተከለከለ ነው። ሙስሊሞች እነርሱ የሚናገሩትንና የሚሉትን ሊያምኑ አይገባም። በሐዲሥ ዉስጥ እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)

من أتى عرافاً فسأله عن شيء لم تقبل له صلاة أربعين ليلة

“አዋቂነኝ ባይ ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ አንድን ነገር የጠየቀው ሰው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።” ብለዋል። (ሙስሊም ዘግበውታል)

በሌላ ሰሂህ ሐዲሥም እንደተገለፀው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-

من أتى كاهناً فصدقه فقد كفر بما أنزل على محمد

“ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የሚለውን ያመነ ሰው በሙሐመድ ላይ በወረደው ነገር ክዷል።” የሐዲሥ አጠናቃሪ (ሱነን) ኢማሞች እና ሌሎችም ዘግበውታል።

ድግምትን በድግምት መፍታት አይፈቀድም። ይህም ሲባል አንድን ድግምት ለማክሸፍ ሲባል ሌላ ድግምት መጠቀም ነው። የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ይህንኑ ከልክለዋል – እንዲህ በማለት፡-

ليس منا من تطير أو تطير له أو تكهن أو تكهن له أو سحر أو سحر له

“ገድ ያየ ወይም የታየለት፣ የጠነቆለ ወይም የተጠነቆለለት፣ ድግምት የሠራ ወይም የተሠራለት ከኛ አይደለም።” (ጦበራኒ ዘግበውታል።)

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ድግምትን በድግምት ስለመፍታት ድንጋጌ ተጠይቀው “የሸይጣን ሥራ ነው።” ብለዋል። (ኢማም አሕመድ እና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል።)

ድግምትን ለመፍታትና ለማክሸፍ የተፈቀደው መንገድ በተከበረው ቁርኣን እና ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በተፈቀዱና በተረጋገጡ ዱዓኦች ነው። ከነኚህም መካከል ከአልበቀራ ምዕራፍ ኣየት አል-ኩርሲይ እና ሌሎች የቁርኣን ምዕራፎች  “ቁል ያ አዩሀል ካፊሩን”፣ “ቁል ሁወላሁ አሐድ”፣ “ቁል አዑዙ ቢረብ አልፈለቅ” እና “ቁል አዑዙ ቢረብ አን-ናስ” ይጠቀሳሉ። እንዲሁም ሌሎች የሚከተሉት አንቀጾችም ሊጠቀሱ ይችላሉ-

وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ فَإِذَا هِيَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ*  فَوَقَعَ الْحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ*  فَغُلِبُوا هُنَالِكَ وَانقَلَبُوا صَاغِرِينَ

“ወደ ሙሳም፡- ‘በትርህን ጣል’ ስንል ላክን። (ጣላትም) ወዲያውኑም የሚቀጣጥፉትን (ማታለያ) ትውጣለች። እውነቱም ተገለጸ። ይሠሩት የነበሩትም (ድግምት) ተበላሸ። እዚያ ዘንድ ተሸነፉም። ወራዶችም ኾነው ተመለሱ።” (አል-አዕራፍ 7 ፤ 117-119)

እንዲሁም የዩኑስ ምዕራፍ 79-82 ሌላው ነው።

وَقَالَ فِرْعَوْنُ ائْتُونِي بِكُلِّ سَاحِرٍ عَلِيمٍ * فَلَمَّا جَاءَ السَّحَرَةُ قَالَ لَهُم مُّوسَىٰ أَلْقُوا مَا أَنتُم مُّلْقُونَ * فَلَمَّا أَلْقَوْا قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئْتُم بِهِ السِّحْرُ إِنَّ اللَّهَ سَيُبْطِلُهُ إِنَّ اللَّهَ لَا يُصْلِحُ عَمَلَ الْمُفْسِدِينَ*  وَيُحِقُّ اللَّهُ الْحَقَّ بِكَلِمَاتِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُجْرِمُونَ

“ፈርዖንም፡- ‘ዐዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ’ አለ። ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ሙሳ ለእነርሱ፡- ‘እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ’ አላቸው። (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ ሙሳ አለ፡- ‘ያ በርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው። አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል። አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና። አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡”

እንዲሁም የጣሃ ምዕራፍ 65-69

قَالُوا يَا مُوسَىٰ إِمَّا أَن تُلْقِيَ وَإِمَّا أَن نَّكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَلْقَىٰ* قَالَ بَلْ أَلْقُوا فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ * فَأَوْجَسَ فِي نَفْسِهِ خِيفَةً مُّوسَىٰ قُلْنَا لَا تَخَفْ إِنَّكَ أَنتَ الْأَعْلَىٰ * وَأَلْقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوا إِنَّمَا صَنَعُوا كَيْدُ سَاحِرٍ وَلَا يُفْلِحُ السَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ

“ሙሳ ሆይ! ወይ ትጥላለህ ወይም በመጀመሪያ የምንጥል እንኾናለን” (ምረጥ) አሉ። “ይደለም ጣሉ” አላቸው። ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ (እባቦች) ኾነው ወደርሱ ተመለሱ። ሙሳም በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ። “አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና” አልነው። “በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል። ያንን የሠሩትን ትውጣለችና። ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና። ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም” (አልን)።”

ድግምትን ለማከም/ለማክሸፍ በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከተላለፉ ዱዓኦች ዉስጥ ደግሞ፡-

اللهم رب الناس أذهب البأس واشف أنت الشافي لا شفاء إلا شفاؤك شفاء لا يغادر سقماً

“አሏሁማ ረቢ ናስ አዝሂብ አልበእሰ፣ ወሽፊ አንተ ሻፊ፣ ላ ሺፋአ ኢል-ላ ሺፋኡከ፣ ሺፋአን ላ ዩጋዲሩ ሰቀማ” የሚለው ይገኝበታል።

ትርጉሙ፡- “የሰው ልጆች ጌታ የሆንክ አላህ ሆይ! መከራን አስወግድ፣ አንተ ፈዋሽ ነህና ፈውስ። ካንተ ፈውስ ዉጭ ሌላ ፈውስ የለም። በሽታን የማያስቀር የሆነ ፈውስን ፈውስ።”

ሌላው ደግሞ መልኣኩ ጂብሪል (ዐ.ሰ) ነቢዩን ካከመበት ዱዓእ መካከል ይኸኛው ይጠቀሳል፡-

بسم الله أرقيك من كل شيء يؤذيك ، ومن شر كل نفس أو عين حاسد الله يشفيك ، باسم الله أرقيك

“በአላህ ሥም አክምሃለሁ፣ ከሚያስቸግርህ ነገር ሁሉ፣ ከመጥፎ ነፍስ ሁሉ እንዲሁም ከምቀኛ ሁሉ አላህ ይፈውስህ። በአላህ ሥም አክምሃለሁ።”

ይህንኑ ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ማለትና ሌሎችንም ዱዓኦችና ዚክሮች መጠቀም ያስፈልጋል። አላህ እጅግ አዋቂ ነው።

https://t.me/alanisquranacademy























20 last posts shown.