Posts filter


🔑 Miiraa fi jaalala dhugaa karaalee ittiin adda baafannu,... Itti fufaa dubbisaa

➡️ See more
See more
🚨

▶️Jaalalli dhugaa akkamitti beekama?.... Itti fufaa dubbisaa


#68 ✍️

1. የሚበጀውን ባለቤት ያውቃል
2. ቅቤና ቅልጥም ወዴት ግጥምጥም
3. ሁሉም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋል

@Amharic_proverb 💬


#67 ✍️

1. የሞኝ ምስጋና የግንቦት ደመና
2. ሸኝ ቤት አይገባም
3. የአህያ "እቃው" ሆዱ ውስጥ ነው

@Amharic_proverb 💬


#66 ✍️

1. የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል
2. ሰውን ሰው ያሰኘው እቁብ ነው
3 እንዲያው ብትመለሺ የገንፎ እንጨት ላሺ

@Amharic_proverb 💬


#65 ✍️

1. ተው አትርሳ ተሰርቶልሀል የሳት ገሳ
2. እንኳን ለእህቴ ለሌላውም ይዘፍናል አንገቴ
3. የጨለማ አፍጣጭ የእውር ገልማጭ
4. ቅዠት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
5. የማይድን በሽተኛ በበጋ እሸት አምጡልኝ ይላል

@Amharic_proverb 💬


እንኳን ለገና በዓል  አደረሳችሁ

ግጥም ለኢየሱስ ቻናል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) አደረሳችሁ ይላል።

መልካም የገና በዓል!

SHARE @amharic_proverb


#64 ✍️

1. የሚያድግ ልጅ አትበድል የሚሞት ሽማግሌ አታቃልል
2. የማይተማመኑ ባልንጀሮች እየወንዙ ይማማላሉ
3. ለጠቢብ አንድ ቃል ይበቃል
4. የምትሮጥበት ሜዳ የምትገባበት ቀዳዳ
5. ክረምት ከጭቃ በጋ ከግጫ

@Amharic_proverb 💬


#63 ✍️

1. ከልጅ ጋር አትጫወት አይንህን ያወጣዋል በእንጨት
2. ቀልደኛ ገበሬ ናይት ክለብ ከፈተ
3. ሲመክሩት ያልሰማ ሲያጮሉት ይሰማ
4. ነገር በሆዴ እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሆኜ ተገኘሁ
5. ያባት ሲቀር ምሰህ ቅበር

@Amharic_proverb 💬


#62✍️

1. ያልወለድኩት ልጅ አባዬ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
2. ዝሆን ቂጡን ተማምኖ ግንድ ይውጣል
3. እንደ ፈታሂነቱ ሁላችን እንኮነናለን እንደ መሃሪነቱ ሁላችን እንማራለን
4. እውር ተመሪው ሞኝ ተመካሪው
5. ቀንና ጨርቅ ያልቃል ብልህ ያውቃል

@Amharic_proverb 💬


#61 ✍️

1. ሴት ካልዋሸች ባልዋን ትወዳለች
2. ለአፍታ የለውም ፋታ
3. ልብስህን በውሀ ገንዘብህን በድሀ
4. ይሆናል ብዬ ጎሽ ጠመድኩ የማይሆን ቢሆን ፈትቼ ሰደድኩ
5. ቂጥ ቢያብጥ ልብ አይሆንም

@Amharic_proverb 💬


#60 ✍️

1. ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ያግባኝ
2. ነገር ካንሹ ስጋ ከጠባሹ
3. ያለ ጎታ ደረባ ምንድን ነው
4. እደለ ቢስ አሞራ አንበጣ ሲመጣ አይኑ ይጠፋል
5. ዶሮ ካልበሏት አሞራ ናት

@Amharic_proverb 💬


#59 ✍️

1. የልጅ ቀላቢ የአህያ ጋላቢ
2. ጆሮ ካያቱ ያረጃል
3. እኔም ፈጣጣ አንቺም ፈጣጣ ምን ያጣላናል በሰው ሰላጣ
4. እንዶድ በገርነቱ ውሀ ወሰደው
5. በቅሎ ግዙ ግዙ አሞሌ ላያግዙ

@Amharic_proverb 💬


#58 ✍️

1. ያሽላል ያሉት ኩል አይን ያጠፋል
2. ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ
3. ቁርበት ምን ያንጓጓሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ
4. ዛፍ ሲወድቅ ከግንዱ ሰው ሲቸገር ከዘመዱ
5. ያህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ የሹም ዘፋፋ አገር ያጠፋ

@Amharic_proverb 💬


#57 ✍️

1. ቸር ይመጸውታል ጠላት ያጠፋል
2. የለበሰ የማንንም ጎረሰ
3. ዳቦ በገና ቡና በጀበና
4. ጅብ ካኮተኮተ ሰው ከተከተተ
5. ቀስ እንዳይደፈረስ

@Amharic_proverb 💬


#56 ✍️

1. ለገቢህ ተንገብገብ
2. በሀምሌ ጤፍ ይዘሩ ቤት ይሰሩ
3. የቀበጡ እለት ሞት አይገኝም
4. ያገር ልጅ በምን ይማታል በኩበት ያ እንዳይሄድ ያ እንዳይሞት
5. እኔ ባልኩ ይልኩና ይላኩ

@Amharic_proverb 🔵


#55 ✍️

1. ሽበት እኖር ብዬ መጥቻለሁ አለ
2 ያው እንዳያችሁኝ ቅዳሜ የወጣሁ ይቆጡኛል ብዪ አርብ ማታ መጣሁ
3. ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ
4. ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይበረታል
5. ያንድ ቀን ስህተት የዘላለም ጸጸት ነው

@Amharic_proverb 🔵


#54 ✍️

1. ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም
2. ፍየል መንታ ትወልድና አንዱ ለወናፍ አንዱ ለመጽሀፍ
3. ጅብ ከላይ ውሀ ሲጠጣ ከታች ያለችውን አህያ አታደፍርሽብኝ አለ
4. የማያልፍለት ዘበኛ ከዋርካ ስር አይጠፋም
5. ሴት ካልወለደች ቋንጣ አትጠብስም

@Amharic_proverb 🔵


#53 ✍️

1. ቅንነት ለነፍስ መድሀኒት
2. የዋኘ ይሻገራል የሰራ ይከብራል
3. ደም ከውሀ ይቀጥናል
4. ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወዳጅ ሲሉ ይጠሉ
5. የመጣ ቢመጣ ከቤቴም አልወጣ

@Amharic_proverb 🔵


#52 ✍️

1. ከኔ ከወሰድሽው ተቀምጠሽ ልበሽው
2. ለመሆኑ ሳይሆን እንዴት ይሆናል ቢሆን
3. የወንድ አልጫ እንዶድ ሙቀጫ
4. ትሻልን ትቼ ትብስን አገባሁ
5. እንደ አይን ፈሪ እንደ እግር ደፋር የለም

@Amharic_proverb 🔵


#51 ✍️

1. ንጉስ ቢቆጣቀስ ብለህ ውጣ
2. ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይኮርታል
3. ለእውር ዝማሜ ለመላጣ ጋሜ
4. ዱላ የሚጠላው ሸክላ ብቻ ነው
5. የሴት ምክር ማሰሪያው አሽከቴ

@Amharic_proverb 🔵

20 last posts shown.