ቀኜ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ(ቀኜ) /Kegne Amhara Youth Movement (Kegne) በሁሉም ከተሞች ስራ ጀምሯል‼️
የአማራ ወጣት በማንነቱ በመደራጀት ህዝባችን የገጠመውን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ችግሮች ለመቅረፍ በተለያዩ አደረጃጀቶች ሲታገል ቆይቷል ።በተለይም ለውጥ የተባለው ለአማራ ህዝብ ግን 'ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጥፍጥም ' ይሉት ብሂል ነውጥ የሆነበት ፣ጭፍጨፋ ፣መፈናቀል ፣መሳደድ ሁሉን አቀፍ ግፍና በደል ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ከፈፅሞ መጥፋት ራሳችንን ለመከላከል የአማራ ወጣት መታገል በሚችለው አደረጃጀቶች ሁሉ ታግሏል ።
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች (በተለይም በኦሮሚያ ፣በመተከል ፣በደቡብ ክልል ወዘተ ) በህዝባችን ላይ ይደርስ በነበረው የዘር ማጥፋት፥ማፅዳት እንዲሁሞ "ህግ አስከብራለሁ፣ትጥቅ አስፈታለሁ " በሚል እብሪት የዘር ፍጅቱን ለማጠናከር የአብይ ዙፋን ጠባቂ ፣ጨፍጫፊ እና ወራሪ ሰራዊት የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከገባ ጊዜ ጀምሮ የአማራ ወጣት በማንነቱ ከተደራጀ፣ከታጠቀ በኃላ አብዮቱን በማቀጣጠል ወደ ፋኖ አደረጃጀቶች በመቀላቀል በታሪክ ፊት የሚያኮራ ታላቅ ጀብዱ ፈፅሟል ።እፈፀመም ይገኛል !
አንድ አመት ከመንፈቅ ያስቆጠረው የአማራው አብዮት ለወዳጅ በሚያስደስት ፥ለጠላት በሚያስጨንቅ ሁኔታ በድል እየገሰገሰም ይገኛል ።የአማራ ፋኖ ትግል በሰው ሀይል ቁጥርም ይሁን በትጥቅና ስንቅ እጅግ ዘምኖ ፣ተደራጅቶ የአማራን ህዝብ ትንሳኤ ለማብሰር በአሁኑ ወቅት የድላችን ደጃፍ ላይ እንገኛለን ።
ትግላችን ህዝባዊ በመሆኑ ከሊቅ እሰከ ደቂቅ፦ወጣት ፣አዛውንት ፣ምሁር ፣ አርሶ አደር ፣ነጋዴ ፣ሃኪም ፣መምህር ሴት ወንድ ሳይል ሁሉም በዬ መክሊቱና ችሎታው እየታገለ ይገኛል ።በታሪክ ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ በርካታ የከተማ ወጣቶችም የትጥቅ ትግሉን ተቀላቅለው ታላቅ ጀብጁ እፈፀሙ ይገኛሉ ።
ከላይ ለመግለፅ እንደ ተሞከረው ትግላችን ህዝባዊ አብዮት ነው ።ህዝባዊ አብዮት ደግሞ ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረግ አስፈላጊ ነው ።የሁሉም ህዝብ በተለይም የወጣቱ ንቁ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ።ተገቢም ነው !
በመሆኑም በአሁን ወቅት እየተደረገ ያለውን የትጥቅ ትግል (የአማራ አብዮት) ሁሉም በዬ መክሊቱ አብዮታዊ ትግሉን ይቀላቀል ዘንድ በርካታ የከተማ ወጣቶች ምን እናግዝ ? ምን እናድርግ? ጥያቄ መሰረት ፣ትግላችን በሁሉም ረገድ ሙሉ አድርጎ ለድል ለመብቃት ይረዳን ዘንድ፣ አብዮታዊ ትግላችንን አሳምሮ ለመቋጨት ያግዘን ዘንድ ወዘተ ቀኜ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ(ቀኜ) /Kegne Amhara Youth Movement (Kegne) ተመስርቶ በሁሉም ከተሞቻችን አብዮታዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ።
የቀኜ አማራ ወጣቶች ንቅናቄ (ቀኜ) መሬት ላይ ከሚገኙ በአራቱም ማዕዘን ለሚገኙ የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የወጣት ክንፍ ሆኖ የሚሰራ ፣የፋኖ አደረጃጀቶች አካል ሆኖ ከአደረጃጀቶች ጋር ተናቦ ሁሉን አቀፍ ትግል የሚያደርግ ፣ተጠሪነቱም ለየአካባቢው የፋኖ አደረጃጀት የሆነ ነው ።ለምሳሌ፦ በባህርዳር ፣መራዊ ፣ወተት አባይ (ቢኮሎ) ፣ዳንግላ ፣ኮሶበር፣ፍኖተ ሰላም ፣ቡሬ፣ጅጋ ፣ማንኩሳ ፣ደንበጫ፣ደብረ ማርቆስ ፣ደጀን፣ቢቸና ፣ደብረ ወርቅ ፣ግንደወይን ፣መርጦ ለማርያም፣ሞጣ ፣አዴት ወዘተ የሚገኙ የቀኜ አማራ ወጣቶች ንቅናቄ (ቀኜ) አባላት ተጠሪነታቸው ለአማራ ፋኖ በጎጃም ይሆናል ።
በጎንደር፣በወሎ ፣በሸዋ የሚገኙ የቀኜ አማራ ወጣቶች ንቅናቄ አባላት ለአካባቢው የፋኖ አደረጃጀቶች ይሆናል ።ይህ የሚሆነው በአራቱም ማዕዘን የሚገኙ መሬት ረግጠው እየታገሉ የሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች አንድ ፅኑ አማራዊ ቤት ፣አማራዊ አደረጃጀት እና ድርጅት እስኪ መሰረት ይሆናል ።የአማራን ክብር ፣ልዕልና እና ጥቅም ለማስከበር በአዲሱ አማራዊ ትውልድ ፣በአዲስ አስተሳሰብ ፣በአዲስ ተስፋ ለተጀመረው አብዮት የሚመጥን አንድ የአማራ ፋኖ ድርጅት ሲመሰረት ቀኜ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ (ቀኜ) ተጠሪነቱ ለሚመሰረተው ድርጅት ይሆናል ።
[እኛ ካልሆን ማንም፣ዛሬ ካልሆነ መቼም።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!]
©Hailemichael Bayeh
ይሕ አዲሱ የአሻራ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል ነው
በጠየቃችሁን መሰረት በዩቱዩብ መረጃወችን ለማድረስ ቻናሉን ከፍተናል አሁኑኑ ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCc4BFUPttYZXRyyMZ83iGaAትኩስና አዳዲስ ሁነቶችን ለማግኘት አዲሱን የአሻራ ዩትዩብ ቻነል Subscribe ያድርጉ‼
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/UH4zZz1lxmc