አትሮኖስ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።

Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....


❤ የሚያማምሩ ፕርፋይሎች ይፈልጋሉ?


‹‹ጥሩ ..እኔም ቢጃማ ነገር ብለብስ ደስ ይለኛል…››አሉና ሁለቱም ወደ የሻንጣቸው ሄዱ…ከ10 ደቂቃ በኃላ ሁለቱም በለሊት ልብሳቸው ለበሱና እጃቸውን ታጥበው የምግብ ጠረጴዛው ፊት ለፊት ተቀመጡ…ከአመታት በኃለ አንደኛው በሌለኛው እጅ በፍቅርና በሳቅ ታጅበው ራታቸውን በሉና ሻምፓኛቸውን ከፈቱ..ሁሉ ነገር ውብ ነበር…ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተያዩ ነው የሆነው…የሁለቱም ልብ ምት እንደወጣት ልብ ነው ከቁጥጥር ውጭ የሆነው…ከአመታት በኃላ ነው የአንዳቸው ገላ ለሌለኛቸው ምላሽ በመስጠት እንደ እሳት ጎመራ መንቀልቀል የጀመረው….ከአስራ ምናምን አመት በኃላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የአንደኛቸው ከንፈር ሌላኛቸው ላይ ያረፈው….የአንዳቸው እጅ የሌለኛቸውን ፓንት ወደታች አንሸራቶ ያወለቀው፡፡
///
በፀሎት እና ለሊሴ ዛሬ የመጨረሻ ቀን የወንጪ ቆይታቸው ነው፡፡በዚህም የተነሳ ቀኑን ሙሉ ላለፉት 15 ቀን ሲያስተናግዶቸው የነበሩትን ዘመዶቻቸውን በጠቅላላ እየዞሩ ተሰናብተው ጨለምለም ሲል ቀጥታ ሻንጣቸውን አንጠልጥለው የመጨረሻ አዳራቸውን በፓርክ ውስጥ ለማድረግ  እነአቶ ኃይለልኡል እንዳያዮቸው እየተጠነቀቁ ቀጥታ ሰለሞን ወደ ያዘላቸው ሎጅ ነው ያመሩት፡፡ክፍላቸው ከሰለሞን ክፍል ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን በለሁለት አልጋ ክፍልነው፡፡
ሰለሞን አቶ ኃይለልኡልና ባለቤታውን ራት ካበላና ወደ መኝታ ቤታቸው ካስገባቸው በኃላ ሌሊሴንና በፀሎትን እራት ለመጋበዝና ውቡን የመጨረሻውን ምሽት አብሮቸው ለማሳለፍ ይዞቸው ወጣ፡፡
ከሎጃቸው ፊትላፊት ባለው ጉብታ ላይ ቁጭ ብለው ሀይቁን ቁልቁል እያዩ እያወሩ ነው፡፡
‹‹በእውነት በሕይወቴ እንደዘንድሮ አስደማሚና አስደናቂ ነገር ገጥሞኝ አያውቅም›› በማለት የጫወታውን ርዕስ የመረጠው ሰለሞን ነበር፡፡
‹‹እንዴት ማለት?››አለችው ለሊሴ፡፡
‹‹እንዴ ..ይታይሽ አንድ ሴት ዝም ብላ በስልኬ በመደውል ስራ ልቀጥርህ እፈልጋለው
…አሁን  መቶ ሺብር  ልላክልህ  ፣  ስራውን  ስትጨርስ  5  ሚሊዬን  ብር  እንድታገኝ

አደርጋለው››ስትለኝ መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሰለኝ…ይገርምሻል የባንክ ቁጥሬን አንኳን ስልክላት ቆይ እስኪ ጉዷን አያለው ብዬ ነበር…እሷ ግን ብሩን ልካ አስደመመችኝ፡፡ወዲያው ከወላጆቾ ስር ጠፍታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የምትፈለግ ልጅ ሆና አገኘኋት..በእውነት ያንን ሳውቅ በጣም ፈርቼ ነበር፣በዛ ተገርሜ ሳልጨርስ እንቺ ለማሪያም ድግስ በጠራሽኝ ጊዜ እናንተ ቤት ቁጭ ብላ አገኘኋት….ከዛ የሁሉ ነገር መነሻ አንቺ እንደሆንሽ ተረዳሁ…ምክንያቱም ስለእኔ ከአንቺ ባትሰማና ስልኬንም ካንቺ ዘንድ ባታገኝ ይሄን ሁሉ ታሪክ አምልጦኝ ነበር…ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ደግሞ አሁን የምሰማው ነገር ነው…የአንቺ እህት ለእሷ ልቧን መለገሷ……ይገርምችኋላ ለቀናት እንዴት ያንን ቤት መረጠች …?ብዬ ስብሰለሰል ነበር..ለካ ከዛ ቤተሰብ ጋር ያላታ ትስስር ጥልቅና በደም የተገመደ ነበር›››
‹‹ታድዬ ደግሜ ደጋግሜ ነው ያስደመምኩህ ማለት ነው››አለችው በፀሎት
‹‹በጣም..እንጂ››
‹‹ምን እሱን ብቻ እኔንም ነው ስታስደምሚኝ የከረምሽው…በተለይ በቀደም ማንነትሽን ስትነግሪኝ….አብጄ እየቃዠው ነበር የመሰለኝ››አለች ለሊሴ፡፡
ለተወሰነ ጊዜ ዝም ተባባሉና በለሊሴ ጥያቄ ሌላ ርዕስ ተከፈተ
‹‹ሶል አሁን ቤተሰቦቾን የምታገኘው ከዚህ እንደተመለስን ነው እንዴ?››ስትል ያሳሰባትን ጥያቄ የጠየቀችው፡፡
‹‹ምነው ጠየቅሽኝ?››
‹‹እኔ እንጃ የእኛ ቤተሰብ በፀሎትን እንዲህ በቀላሉ ለማጣት ዝግጁ የሚሆኑ አይመስለኝም…በተለይ ስለማንናቷ እነ አባዬ ሲያውቁ በጣም ነው የሚከብዳቸው..››
‹‹በፀሎት ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደለሊሴ ተጠጋችና አቅፋ እየወዘወዘቻት‹‹‹እህቴ ስለምን ማጣት ነው የምታወሪው…?ከአሁን ወዲህ እኔ ሁለት ቤተሰብ ነው ያለኝ…አንድ ቀን እዚህ ቤት ካደርኩ በሚቀጥለው ቀን እዛ አድርለሁ….ከተቻለ እና ሁሉም ከተሳማማ ደግሞ ሁላችንም ተሰብስበን አንድ ቤት ውስጥ እንድንኖር ነው የምፈልገው…እርግጥ ይሄ በአንዴ አይሆንም አውቃለው…ግን ሁለቱም ቤተሰቦቼ ቀስ በቀስ በደንብ እንዲተዋወቁና እንዲግባቡ ካደረግኩ በኃላ አንድ ላይ ሰበስባቸዋለው…የቦሌው ቤታችን እኮ አርባ ምናምን

ክፍል ነው ያለው…ከዛ ውስጥ አስሩን አንኳን አንጠቀምበትም…..እና እህቴ ስለመለያየትና ስለማጣት ምንም አታስቢ››
ለሊሴም‹‹እህቴ  በጣም  ነው  የምወድሽ….ከእህቴ  ሀዘን  እንድፅናና  ስላደረግሺኝ አመሰግናለው፡፡››ብላ እሷም በተራዋ አቅፋ ጉንጮን ሳመቻት፡፡
‹‹በቃ በቃ…መላቀሱ ይብቃችሁ…ለማንኛውም በፀሎት ቤተሰቦችሽን የምታገኝው እንዴት እና መቼ እንደሆነ ነገ ጥዋት ቁርስ እየበላን እናወራለን፡፡››
‹‹ለምን አሁን አናወራም… ?››መለሰችለት
‹‹አይ አሁን መሽቷል…ተነሱ እናንተም ወደክፍላችሁ ግቡ››ብሎ ቀድሞ ተነሳ..ለሊሴና በፀሎትም ተከትለውት ተነሱ
ሰለሞን እነሱን ወደክፍላቸው አስገብቶ ወደገዛ ክፍሉ ገባና ቢጃማውን ቀይሮ ቀድሞ ያዘጋጀውን ቢራ ከፈፍቶ መጠጣት ጀመረ…ሁለት ጠርሙስ ካገባደደ በኃላ አስቴር ትዝ አለችው፡፡ ሞባይሉን አነሳና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አልፏል…ደወለ….ከበርካታ ጥሪዎች በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ኪያ ተኝታሻል እንዴ ?ቀሰቀስኩሽ?››
አስቴር መለሰችለት‹‹አይ ወንድሜ ገና ለመተኛት እየተዘገጃጀው ነበር፡፡››
‹‹ደህና ነሽ?››
‹‹ደህና ነኝ…ምነው ቆየህ እኮ !አልጨረስክም አትመጣም እንዴ?››
‹‹ነገ ከሰዓት የምመጣ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ጥሩ ነው…ልደውልልህ ነበር…››
‹‹ምነው በሰለም…፡፡››
‹‹አይ የፊታችን እሁድ የመስፍኔ ልደት ስለሆነ ሰርፕራይዝ ላደርገው አስቤላው…አንተም እንድትገኝ እፈልጋለሁ››
‹‹እንዴ እስከአሁን ወደመጣበት አልሄደም እንዴ?››

‹‹አይ ቀረ እኮ ….በፊትም ጥዬሽ የሄድኩት እየቆጨኝ ነው….ትዳሬን አክብሬ እዚሁ እየሰራሁ ከአንቺ ጋር ልጄን አሳድጋለው አለኝ››
‹‹እና መፋታቱን ሙሉ በሙሉ ተዋችሁት ማለት ነው?››
‹‹አንተ ደግሞ ስለምን መፋታት ነው የምታወራው….?በቃ ደህና እደር በሰላም ተመለስልኝ…መስፍኔ ከመኝታ ቤት እየጠራኝ ነው…››ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
ጨጓራው ሲለበልበው ይታወቀዋል…በቃ ውስጡ እየነደደ ነው…አሁን ምንም የማያውቀውን አዲስ ነገር አልነገረችውም…ምን እንዳበሳጨው ለራሱም አልገባውም….ሌላ ቢራ ከፈተና አንደቀደቀው…ስልኩን ደግመኛ አነሳና ደወለ…

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

የባልና ሚስቶቹ የምክር አገልግሎት እንደቀጠለ ነው…ዛሬ ወንጪ ከከተሙ አስራአራተኛው ቀን ላይ ሲሆኑ በዚህ የ14 ቀን ጉዞቸው ከፍተኛ ለውጥ ላይ ደርሰዋል…
አሁን በዚህ ሰአት ከሁለቱም ፊት ለፊት ተቀምጦ ተራ በተራ እያያቸው እያተናገረ ነው..
‹‹ሰው ምን ጊዜም ከስህተት ጋር ሚኖር ፍጡር ነው፡፡ከሰው ጋር ስንኖር ስህተት ፈላጊ ከሆን በማንኛውም ሰው ላይ ከመጠን ያለፈ ስህተቶችን በቀላሉ ማግኘት እንችላለን…..ያ ደግሞ ከሰው ጋር አያኖረንም…አንዳችን የሌላችንን ክፍተት ለመድፈን መፈጠራችንን እስካላሰብን

ድረስ ምንም ነገር ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡ደግሞ አስቡት የጋብቻ ዋናው አስፈላጊነትም ይህ ነው ፡፡ወንድ ልጅ በራሱ ፍፅም ወንድ ብቻ አይደለም..75 ፐርሰንት የወንድነት ሆርሞን ሲኖረው 25 ፐርሰንት ግን የሴት ሆርሞን በውስጡ ይዞል..ሴቷም በተመሳሳይ 75 ፐርሰንት የሴት ሆርሞን ሲኖራት 25 ፐርሰንት የወንድ ሆርሞን ይዛለች…አያችሁ የተፈጥሮን ረቅቂነት ..ሁለቱ ሲጣመሩ ...አንድ ሙሉ ወንድና አንድ ሙሉ ሴት ይገኛል ማለት ነው፡፡ለመዋሀድ ደግሞ ፍቅር ዋናው አገኛኝ መሰላል ነው፡፡››
‹‹ግልፅ ነኝ አይደል?››
‹‹አዎ .. ቀጥል››ሲሉ የተናገሩት አቶ ኃይለ ልኡል ናቸው
ሰለሞን ንግሩን ቀጠለ‹‹በአንድ መንደር ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት ሶስት ሽማግሌዎች ከቤቷ አካባቢ ከውጭ በፀጥታ ተቀምጠው ተመለከተች። ሴትዬዎም ከቤቷ ወጣችና ወደሽማግሌዎቹ ቀርባ" እናንተን ከዚህ በፊት አይቼያችሁ አላውቅም።ግን እዚህ በደጃፌ ለረጅም ጊዜ ተቀምጣችኋል። እርግጠኛ ነኝ እርቦችኋል። እባካችሁ ወደቤቴ ዘልቃችሁ ግብና ቤት ያፈራውን ቅመሱ››አለቻቸው።
ከመካከላቸው አንደኛው ሽማግሌ‹‹የቤቱ አባወራ በቤት አለ?››ሲሉ ጠየቋት። እሷም መለሰች‹‹አይ የለም››ስትል መለሰች።
ሽማግሌውም"ስለዚህ ወደቤት መግባት አንችልም።"ሲሉ መለሱላት።
ሴትዬዋም ወደውስጥ ተመልሳ ገባች ።መሸቶ ባሏ እንደመጣ ስለሰዎቹ ነገረችው። ባሏም
‹‹በይ አሁን ሂጂና ወደውስጥ እንዲገብ ጋብዢያቸው››አላት።
እሷም ወጣችና ወደውስጥ እንዲገብ በድጋሚ ጠየቀቻቸው‹‹ባለቤቴ ቤት ነው ያለው..ወደውስጥ እንድትገብም ጋብዛችኋል...እባካችሁ ወደ ውስጥ ዝለቁና የሆነ ነገር ቅመሱ››
‹‹እኛ በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም››አሏት
‹‹ለምን ?››ግራ ገብቷት ጠየቀች።

ከሽማግሌዎቹ አንድ መመለስ ጀመረ "ይሄውልሽ ..."ወደአንደኛው ጓደኛው በጣቱ እየጠቆመ "..እሱ አቶ ሀብት ነው ወደቤትሽ ከገባ ቤትሽ በሀብት ለዘላለም እንደተሞላ ይዘልቃል።...ይሄኛው ደግሞ አቶ ስኬት ነው ከአንቺ ጋር ተከትሎ ወደውስጥ የሚገባው እሱ ከሆነ ቤትሽ በስኬት ይሞላል።እኔ ደግሞ አያ ፍቅር እባላለሁ። እኔ ከገባሁ ደግሞ በዘመንሽ ሁሉ በቤትሽ ፍቅር ሞልቶ ይፈሳል።ክፍቱ ግን አስቀድመን እንደነገርንሽ ሶስታችንም በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም። ስለዚህ ወደቤትሽ ተመለሺና ከባልሽ ጋር በመማከር ከሶስታችን ማንኛችንን ወደውስጥ እንደምታስገብ ወስኑ "በማለት አብራሩላት።
እሷም እንደተባለችው ወደውስጥ ተመልሳ የሰማችውን ሁሉ ለባሏ አስረዳችው። ባሏ በሰማው ነገር ፈነጠዘ‹‹አቶ ሀብትን እንጋብዘው ፤ይግባና ቤታችን በሀብት ይሙላው፤ከእሱ የሚበልጥ ምን አለ?።››አላት።
ሚስትዬው ግን ውሳኔውን ተቃወመች"ለምን ስኬትን አንጋብዘውም፤ከሀብት ይልቅ ስኬት ነው የሚጠቅመን"አለች። እቤት ውስጥ የነበረች የልጃቸው ሚስት ወሬቸውን ስታዳምጥ ስለነበረ ወደእነሱ ቀረበችና‹‹ለምን ፍቅርን አንጋብዘውም..ከሁሉም በላይ በቤታችን ፍቅር ቢሞላ ይሻላል››የሚል ሀሳብ አቀረበች።
ጥቂት ካሠላሠሉ እና ከተከራከሩ በኃላ ባልና ሚስቶቹም በሀሳቧ ተስማሙ ፤ሚስትም ተመልሳ ወጣችና ወደእንግዶቹ ሄደች። ‹‹ከመካከላችው ፍቅርን ለመጋበዝ ወስነናል፤አያ ፍቅር እባክህ ተነስና ወደቤታችን ዘልቀህ ግባ...የተዘጋጀውን መአድም አብረኸን ተቋደስ..ሌሎቻችሁ ስላልመረጥናችሁ ይቅርታ "ስትል ተናገረች።
ፍቅር ተነሳና ወደቤት ለመግባት መንቀሳቀስ ሲጀምር ስኬትና ሀብትም ከተቀመጡበት ተነስተው ከኃላው ተከተሉት። ሴትዬዋ ግራ ገባት ‹‹አብረን መግባት አንችልም.. ከመሀላችን አንዳችንን ምረጪ አላላችሁኝም ነበር እንዴ?"ስትል ጠየቀች።
ከመሀከላቸው አንደኛው ማስረዳት ጀመረ‹‹ልጄ ስትመርጪ ስኬትን ወይም ሀብትን መርጠሽ ቢሆን ኖሮ አንዳችን ብቻ ነበር ወደቤትሽ የምንገባው።አሁን ግን የመረጥሽው ፍቅርን ነው። እኛ ደግሞ ፍቅር በገባበት ሁሉ ተከትለን መግባት ግዴታችን ነው።እኛም እራሳችን የፍቅር ምርኮኞች ነን።በዚህ ምክንያት ሶስታችንም የግድ ወደቤትሽ እንገባለን። ካዘጋጀሽውም መአድ እንቋደሳለን።ቤትሽንም ዘላለም በሚትረፈረፍ ሀብት ፤ስኬትና ፍቅር እንሞላዋለን።"አሏት። እሷም በደስታ እየፈነጠዘች ወደቤቷ ይዛቸው ገባች።

አያችሁ እናነት ሀብታም ናችሁ ስኬታማም ናችሁ…አሁን እየጣርን ያለነው ከመሀከሏችሁ ሾልኮ ተሰዶ ነበረውን ዋናውን ፍቅር ለመመለስ ነው..ፍቅር ከተመለሰ ሁሉ ነገር ሙሉ ይሆናል››
ዛሬ በዚህ በሰጠኋችሁ ምሳሌ በመሀከላችሁ፤በቤታችሁና በአካባቢያችሁ ፍቅር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እያሰላሰላችሁ እንድታድሩ እፈልጋለው…ነገ እዚህ የምናሳልፍበት የመጨረሻ ቀናችን ነው…ተነገ ወዲያ ወደአዲስ አበባ እንመለሳለን….አሁን ዋናውን ነገር አጠናቀናል…በቀጣይ ቤታችሁ ሆናችሁ ልጃችሁም ተመልሳ ስራችሁን እየሰራች የምናደርገው ይሆናል…››በማለት የእለቱን ፕሮግራም አገባደደ
ባልና ሚስቶቹ ክፍላቸው ተያይዘው ሲገቡ የጠበቃቸው የተለየ ነገር ነበር፡፡የመኝታ ክፍላቸውን ግራና ቀኝ ግድግዳ ታኮ የነበረው ሁለት አልጋ ሁለቱም ወደመሀል ተስቦና አንድ ላይ እንዲገጥም ተደርጎ አንድ አልጋ ሆኗል….ግዙፉ የተዋሀደው አልጋ በነጭ ውብ አልጋ ልብስ ተሸፍኗል.. አልጋ ልብሱ መሀል ላይ በልዩ ዲዛይን የተሰራ ባለቀይ ቀለም የልብ ቅርፅ ይታያል..ሙሉ ወለሉ በቀይ ፅጌረዳ አበባ ከመሞላቱም በተጫማሪ ባለቆርቆሮ ልዩ ሻማ በመሀከል መሀከል ጣልቃ በማስገባት የተለያ ቀለም ያው ብርሀን እየረጩ ነው፡፡አደኛውን ግድግዳ ተጠግቶ በሚታይ ጠረጴዛ ላይ ሻማፓኝ መጠጥ ከውብ ብርጭቆዎች ጋር ይታያል…በሚገፋ ተሸከርካሪ ጠረጴዛ ላይ አስጎምዢ ምግቦች ተደርድረዋል…
ሁለቱም ባልና ሚስት በመጀመሪያ የተሳሳተ ክፍል የገቡ ነበር የመሰላቸው….የገዛ ሻንጣቸውንና ሌሎች የግል እቃዎችን ሲያዩ ተረጋጉና ወደውስጥ ዘልቀው በራፉን ዘጉት፡፡
‹‹ስንድ ይሄ ጉደኛ ልጅ የ20 አመት ጎረምሳ አደረገን እኮ..››
ወ.ሮ ስንዱ እንባቸው እየረገፈ ተናገሩ‹‹ያበቃልኝ መስሎኝ ነበር….እድሜ ለልጄ ይሄው ዳግመኛ ልጃገረድ ሆንኩ››
‹‹እንዴ ስንድ ዛሬ ሳቅና ፈንጠዝያ ነው እንጂ የምን ለቅሶ?››አሉን እጃቸውን ወደባለቤታቸው ጉንጮች በመላክ እንባቸውን ጠረጉላቸውና አቅፈው ሳሞቸው….‹‹በይ ዛሬ ምሽቱ የእኛ መሰለኝ..እንቀመጥ››
‹‹መጀመሪያ ልብሴን ልቀይርና ቀለል ያለ ልብስ ልልበስ…እስከዛ እንተ ቁጭ በል››


#አልፎ_አልፎ_መሞት

ሰው
አንድም - በእግዜር፡
አንድም - በመውዜር፡
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል።

ሰው ቢያጣ መንገድ  ሰው ቢያጣ ምርጫ፡
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ።

ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ፡
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ።

እኔ ግን፡
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን፡
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን።

ሰው
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት፡
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#አዎ !
ለጊዜውም ቢሆን፤ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ ፤ ወደፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፤ ሚስቱን ያስረግዛል

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#እንደምትወዳት_ንገራት

ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::

ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


‹‹እሱማ ምን ጥርጥር አለው….ግን እንደው ትረዳዋለች ወይ የሚለው ጥርጣሬ አድሮብኝ ነው..እሷን ለማታለል ለማስመሰል ያደረግነው መስሎ እንዳይሰማት››ወ.ሮ ስንዱ ጥርጣሬያቸውን አሰሙ፡፡
‹‹እሷ የምታውቀንን ያህል እኛ እኮ ልጃችንን አናውቃትም …..››ሃይለልኡል የሚስታቸው ሀዘንና ጥርጣሬ ውደውስጣቸው እንዳይገባ እየታገሉ መለሱ፡፡
‹‹እሱስ እውነትህን ነው….የልጃችን ትልቅ ውለታ አለብን››
‹‹አዎ .አሁን ልጃችን በጣም በስላለች…ምን አስቤለው መሰለሽ….ካምፓኒው ውስጥ የሆነ ቦታ ይዛ ስራ መጀመር አለባት…እኔ በቅርቡ ጡረታ ወጥቼ ከአንቺ ጋር አለምን እየዞርኩ ዘና

ማለት ነው የምፈልገው…ከአሁን በኃላ በተጨናነቀው የቢዝነስ አለም ውስጥ ቀሪ ህይወቴን ማባከን አልፍልግም››
‹‹እና ስራውን ሙሉ በሙሉ እንድትረከብህ ነው የምትፈልገው?፡፡››
‹‹አዎ ከእኔ ጋር ሆና አንድ ሁለት አመት ከሰራች በቃ ከእኔ በተሻለ ውጤታማ እንደምትሆን እርግጠኛ ነኝ..እይ እስኪ እኔና አንቺን ወደስምምነት ለማምጣት የተጠቀመችበት የረቀቀ ውጤታማ ዘዴ….እንዴት እንዳቀናጀችው…ያን የመሰለ ባለሞያ እንዴት እንደመለመለች
…በእውነት ይህቺ የእኛ ልጅ ነች ብዬ እስክደነቅ ድረስ ነው ያስደመመችኝ፡፡››በንግግራቸው ኩራታቸውን ሲግልፁ ፊታቸውም በደስታ እያበራ ነበር፡፡

…በሶስተኛው ቀን
ሰለሞንና በፀሎት ቢያንስ በቀን አንድና ሁለት ጊዜ እየተደዋወሉ ለረጅም ሰዓት ማውራትና የተለያዩ ርዕሶች እያነሱ መወያየት ልምድ አድርገውታል..ይሄ ደግሞ እርስ በርስ የበለጠ እንዲተዋወቁና በደንበኝነት መልክ ሳይሆን ልክ እንደአንድ የልብ ጓደኛ ወጣ ባለ ርዕሶች ላይም ረጅም ሰዓት ማውራት ጀምረዋል፡፡፡ይሄ ጉዳይ ለሁለቱም በጣም ተመችቷቸዋል፡፡አሁንም ተደዋውለው እያወሩ ነው፡፡
በፀሎት‹‹አንድ ሰው እንዳፈቀረን እንዴት ማወቅ እንችላለን…?ለምሳሌ እኔ አንድ አብሮኝ ያለ ወንድ የእውነት እንደሚያፈቅረኝና በምን ማረጋገጥ እችላለው፡፡››ስትል ያስደነቀውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ሴት ልጅ ካለገመች በስተቀር አንድ ወንድ እንደሚያፈቅራትና እንደማያፈቅራት በቀላሉ መለየት ትችላለች…አንዳንድ ጊዜ ግን ምን ይሆናል ?እሷ በጣም ካፈቀረችው እሱ እንደማያፈቅራት ብታውቅ እንኳን ሽንፈትን ላለመቀበል ብላ እንደሚያፈቅራት እራሷን ለማሳመን ትጣጣራለች..የዛን ጊዜ የምታያቸውን ምልክቶች ሁሉ በተቃራኒው ተርጉማ ለመረዳት ትሞክራለች››
‹‹እና ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?››

‹‹ለምሳሌ ድምፅሽን ለመስማት ብቻ ይጠራሻል።ስትስቂ ስቆ ስታለቅሺም ያለቅሳል። ከመተኛቱ በፊት በመጨረሻዋ ደቂቃና ከእንቅልፍ በነቃ በመጀመሪያው ደቂቃ ስለአንቺ ነው የሚያስበው።ያለምክንያት ሊያቅፍሽ እና ከሰውነቱ ሊለጥፍሽ ይፈልጋል።አንቺን ከነማንነትሽ ለመቀበል ፍቃደኛ ሆኖ ይገኛል።አንቺን በሌላ ለመቀየር ፍፅም ፍቃደኛ አይደለም።ስህተት ሲሰራ አንቺ እንዲያስተካክል ከመጠየቅሽ በፊት ቀድሞ ለማስተካከል ጥረት ሲያደርግ ታገኚዋለሽ፤ሁል ጊዜ ሊረዳሽ ጥረት ያደርጋል።እንቅልፍ አሸልቦሽ ሊመለከትሽ ነቅቶ ይጠብቃል።ግንባርሽን በስስት ይስማል።መክሳትሽም ሆነ ክብደት መጨመርሽ ከውበትሽ አንፃር ብዙም አያስጨንቀውም፡፡በጓደኞቹ መካከል እጆችሽን ይይዛል።ወይም አቅፎ ጉያው ይሸጉጥሻል።ወዘተ…እንግዲህ እኚንና መሰል ምልክቶችን በማየትና በማመዛዘን አንድ ሰው አፍቅሮሽ ይሁን ወይስ አይሁን መለየት ትችያለሽ››
‹‹እሺ ወሲብስ ምንድነው..?በፍቅር ውስጥ ያለው ድርሻስ?››
‹‹ወሲብን የፍቅር ተጣማሪሽ ጋር ያለሽን ግንኙነት ለማጠንከር እና ለማዋሀድ እንደ ሲሚንቶ የሚያገለግል ተፈጥሯዊ ቅመም ነው፡፡ወሲብ በአግባቡ ከተጠቀምሽበት ፍቅርን በማሳደግና በማጎልበት ትልቅ የሆነ ድርሻ አለው፡፡አይደለም ወሲብ መተሻሸትና መሳሳም እራሱ የፍቅር ግለትን ጠብቆ ለማስቀጠል ትልቅ ጥቅም አለው፡፡››
‹‹እና ከፍቅረኛሽ ጋር ተሳሳሚ እያልከኝ ነው››
‹‹ፍቅረኛው ካለ አዎ በደንብ..ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሚስቶች በጋብቻ ውስጥ ከከራረሙ በኃላ ለመሳሳም ያላቸው ፍላጎትና ትኩረት በጣም ይቀንሳል ወይም እስከወዲያኛው ይጠፋል።ላጤዎች ደግሞ ብዙውን ጊዜ በዚህ ረገድ ትኩስና ያልተገደበ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ይሄ ግን አግባብ አይደለም ።ባልዬው ድንገት ውጭ ሌላ ላጤ ሴት ቢያጋጥመው ከኤክስፐርት ጋር ነው የሚላተመው...ልዩነቱ ሰፊ ስለሚሆንበት ይከብደዋል።ቶሎ ስህተቱን ለማረም እንዳይችል ይፈተናል።››
‹‹እኔ ግን ሳገባ እንደዛ አላደርግም…ለባሌ በጣም የምመቸው ይመስለኛል›››
‹‹እያስጎመዠሺኝ ነው››
‹‹ምን ያስጎመዠሀል ..አንተን አላገባ?››

‹‹ምን ይታወቃል….ካፈቀርሺኝ ለምን አታገቢኝም?››
‹‹ሳላውቅህ እንዴት ላፈቅርህ እችላለው?››
‹‹ከዚህ በላይ እንዴት ታውቂኛለሽ..ለወራት ድምፄን በስልክ ስትሰሚ ነበር…በቀደም ደግሞ በአካል አይተሸኛል…ምነው አላምርም እንዴ?››
‹‹አረ ቆንጆ ነህ…ግን ቁንጅና ብቻ በቂ አይደለም››
‹‹እስኪ እናያለን››
‹‹ለማንኛውም ለባልሽ መዋብ የምትጀምሪው ከእርቃን ገላሽ ጀምሮ መሆን አለበት...ፓንትሽንና ጡት ማሲያዛሽን የሚያየው ባልሽ ነው።...ለእነሱ ትኩረት መስጠት መቻል በባልሽ እና በአንቺ የፍቅር ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይፈጥራል።ከላይ ያሉ ልብሶችሽን፣ ፀጉርሽን ፣ጌጣ ጌጦችሽን ለሁሉም ሰው በጋራ የምታደርጊያቸው መዋቢያዎች ናቸው።የውስጥ ልብሶችሽ ጥራት ግን የባልሽ ስሜት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚኖራቸው ግንዛቤ ሊኖርሽ ይገባል፡፡››
‹‹ገባኝ››

‹‹አይ ስለአንቺ እኮ አይደለም ያወራውት አጠቃላይ ስለፍቅር እና ፍቅረኛሞች ለማውራት ፈልጌ ነው…ባልሽ በአጋጣሚ የሚያገኛቸው እንግዳ ሴቶች ድንገት ፊቱ ልብሳቸውን የማውለቅ እድል ካገኙ እመኚኝ የውስጥ ልብሶቻቸው ብቻ አይደሉም ውብና አማላይ የሚሆነው.. ለሊቱንም ውብና አማላይ እና ያልተለመደ አይነት ያደርጉለታል።አንቺ ሚስቱ ነሽና ብዙ ኃላፊነትና የህይወት ውጣ ውረዶች ስላለብሽ የአመቱን ቀናቶች ሁሉ ውብና አማላይ ልታደርጊለት አትቺይም ግን በሳምንት አንድ ቀን ካልሆነም በወር አንድ ቀን መቼም ሊረሳው የማይችል እንደዛ አይነት ውብ ለሊቶችን በገፀ-በረከትነት ልታቀርቢለት ይገባል።የዛኔ ከውጭ፣በአጋጣሚ የሚፈቱኑትን በልበ ሙሉነት ሊያልፋቸው አቅም ይኖረዋል።››
‹‹ይገርማል …ምንም ሳልከፍልህ በነፃ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና እየሰጠኸኝ ነው፡፡››
‹‹ያው ማወቅሽ ዞሮ ዞሮ ጥቅሙ ለእኔው ነው ብዬ ነው››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ነገርኩሽ እኮ…ምን አልባት እድለኛው ባልተቤትሽ እኔው ልሆን እችላለሁ››

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ከላይ የተለቀቀው ክፍል 24 ሳይለቀቅ 25  ተለቆ ነበር ክፍል 24 አሁን ተለቋል ለነበረው መዛባት ይቅርታ  እጠይቃለው🙏 ቤተሰቦች


ለሊሴና በፀሎት በእቅዳቸው መሰረት በአንቦ በኩል አድርገው ወንጪ በመድረስ የለሊሴ አጎት ቤት ከደረሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በአካባቢው ያሉ የአቶ ለሜቻ ዘመደች ጋር እየዞሩ ሰላም ማለት እና መጋበዙ እራሱ ማደረስ አልቻሉም…እሷ ብዙ የሀብታም ድግሶችና ፓሪዎችን እንጂ እንዲህ አይነት በየሳር ጎጆውና በየደሳሳ የቆርቆሮ ቤቶች እየዞሩ በግዳጅ መጋበዝ በህይወቷ አይታው የማታውቅ ትዕይንት ስለሆነ በጣም አስገራሚና ትንግርታዊ ነው የሆነባት..በየሄደችበት የሚቀርብላት እርጎ፤ ለወተት…የማር ወለላ…አንጮቴ……ጨጨብሳና  ገንፎ..ሁሉም  ውብ  ነበር፡፡በዚህም  የተነሳ  ወደፓርኩ

ለመሄድና ለመጎብኘት ጊዜ አላገኘችም..ቢሆንም በአካባቢው ቢያንስ የሚመጡትን 15 ቀን ስላምታሳለፍ ሁሉንም ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ እንዳላት ስላወቀች ብዙም አልተጨናነቀችም፡፡
ሰለሞንም የበፀሎትን ወላጆች ይዞ ወደወንጪ እያመራ ነው፡፡በመጀመሪያ እቅዱ ወደላንጋኖ ወይም ሰደሬ ይዞቸው ሊሄድ እንጂ ወንጪ የሚባል ስፍራ ፈፅሞ በአእምሮው አልነበረም..ግን በፀሎት ወደወንጪ እንደሄደች ስትነግረው ግን ወደያው ሀሰቡን ቀየረና ለእነአቶ ኃይለልኡል ሀሳብን ነገራቸው፡፡እነሱ የትም ሆነ የትም ለቦታም ብዙም ግድ ሳልልነበራቸው ወዲያው ነበር ሀሳቡን የተቀበሉት፡፡ከዛ ወዲያው ቻርተር አውሮፕላን ተከራይተው ወንጬ ኢኮቱሪዝም ፓርክ እንግዳ ሆነው ተከሰቱ፡፡ጉዞ ተገባዶ ከቻርተር አውሮፕላኑ እንደወረዱ እነሱን ባሉበት ትቶ ቀጥታ ወደኢንትራንስ ጌት ነው የሄደው
…ስለጠቅላላ የጉብኝቱ ፓኬጅ ማብራሪያ ጠየቀና ሁለት መኝታ ክፍል ተከራየ፡፡ የኤሌክትሪክ መኪና ተከራይቶ እቃቸውን በመጫን ቀጥታ ወደተከራየበት ሎጅ ይዞቸው ሄደ…
ሰለሞን ወላጆቾን ወደወንጪ ይዞ መምጣቱን ለበፀሎት አልነገራትም፡፡እሷ የምታውቀው ወደላናጋኖ እንደሚሄዱና ሲደርስና ሲመቸው እንደሚደውልላት ነው፡፡
ወንጪ ከአዲስ አበባ በ135 ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ክልል በአንቦ እና በወሊሶ ከተሞች መካከል የሚገኝ ድንቅ ስፍራ ነው ፡፡ወንጪ ሀይቅ ከባህር ወለል በላይ 3000ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ 75 ሜትር ገደማ ጥልቀት ያለው ንፁህ እና ጥርት ያለ ሀይቅ ነው፡፡ሀይቁ ከ3000 ዓመት በፊት በተከሰተ እሳተ ጎመራ የተፈጠረ እንደሆነ ይነገራል፡፡በአካባቢው የሚነገሩ አፈታሪኮች እንደሚያስረዱት በወቅቱ እንደሶደም አይነት ተንቀልቃይ እሳተ ጎመራ ተነስቶ የአካባቢውን ፍጥረት ለረጅም ጊዜ እየበላ ከቆየ በኃላ ድንገት በቦታው አርባ አራት ምንጮች ተፈጥረው የሚንቀለቀለውን ውሀ ካጠፋት በኃላ በእሳተ ጎመራው አማካይነት የተፈጠረውን ረባዳ አካባቢ መሙላት ይጀምራል….ውሀው ግን ሞልቶ በመሀከል ትንሽ ደሴት በውሀ ሳትዋጥ ደረቅ መሬት ሆና ትቀራለች…ከዛ ያንን የታዘብ የአካባቢው ኑዋሪዎች ያቺ መሬት በውሀው ሳትሸፈን የቀረችው የተቀደሰች ስፋራ ስለሆነች ከአሁን በኃላ ቦታዋና እንደማመስገኛና ከፈጣሪ ጋር መገናኛ የተለየች ስፍራ አድርገን እንገለገልባታለን ብለው ይስማማሉ…በአሁኑ ወቅት በቦታው ላይ ቤተክርስቲያን ታንፆበታል፡፡

የውንጪ ኢኮቱሪዝም መዝናኛ..መንገዶቹ ጠባብ ስለሆኑና የመኪና መተረማመስ የአካባቢውን ተፈጥሮ እንዲያበላሽው ስለማይፈለግ .ማንኛውም ጎብኚ በራሱ መኪና ወደውስጥ ዘልቆ መግባት አይችልም…ግን ወደሎጆችም ሆነ ወደመዝናኛ ፓርኮች ወይንም ደግሞ ወደገበሬዎች መኖሪያ ቤት ለመሄድ የፈለገ ሰው የተለያዩ አይነት ቀላል የትራንስፖርት አማራጭ ተዘጋጅቶ ይጠብቀዋል..ለምሳሌ…የፈረስ ትራንስፖርት ..ሳይክል
…ኤሌክትሪክ መኪና ካልሆነም ደግሞ በጠባበቹ የአስፓልት መንገድ ግራ ቀኝ ያለውን ውብ ተፈጥሮና የፓርክ ክፍሎችን በመጎብኘት በእግሩ ወክ እያረገ ስጋውን ማዝናናት ነፍሱንም ማስፈንጠዝ ይችላል፡፡
አጠቃላይ የወንጪ የመንገድ ልማት 70 ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲሆን ተራራውን የሚዞር 10 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ … ወደ ዲንዲ ሚሄድ ሀይ ወይ …ማራቶን ራጮች እንዲለማመዱበት ታስቦ የተሰራ የሩጫ ትራክ ሁሉም ውብ ነው፡፡በተለይ ተራራውን በሚዞረው መንገድ ላይ ሁለት ሶስት ሆነው ሳይክል እየነዱ ወይም ፈረስ እየጋለቡ ዙሪያ ገባውን መጎብኘት ገነት ደርሶ እንደመመለስ አይነት አስካሪ ስሜት ውስጥ ይከታል፡፡
አንድ ጎብኚ ሎጆቹን የመከራየት አቅም ማይኖረው ከሆነ እዛው ከሪስፕሽን በፓርኩ ግንባታ ምክንያት ከቦታቸው የተነሱ ገበሬዎች በመንግስት በካሳ መልክ የተሰራላቸው ዘመናዊ ቤቶች ውስጥ ከክፍሎቹ የተወሰኑትን ለቱሪስት እያከራዩ ገቢ እንዲያገኙ ታስቦ የተሰራላቸው ስለሆነ ቀጥታ እዛው ሬስፕሽን ቡክ ያደረገ ሰው የየትኛው የገበሬ ቤት እንደሚያድር ይነገረውና ቀጥታ እዛ ሄዶ በተመጣጣኝ ዋጋ ማደሪያ ያገኛል፡፡
ወንጪ ውበትን ለመግለፅ እግዜያብሄር እንደምሳሌነት ለማሳያ የፈጠራት ስፍራ ትምስላለች…ውበቷ ሀይቆ ብቻ አይደለም…ዙሪያዋን የከበቡት አረንጋዴ ልብስ የለበሱት ሰንሰለታማ ወጣ ገባ ተራሮች ፣አየሩ ሁሉ ነገር ጠቅላላ ውብ ነው፡፡አሁን ደግሞ ቦታውን የቱሪስት መነኸሪያ ለማድረግ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች ይበልጥ ወደፍፁምነት ያስጠጋው ነው፡፡ደረጃቸውን የጠበቁ ሙሉ ተራራውን የሚሽከረከሩ የአስፓልት መንገዶች በእያንዳንዱ ኮርነር ላይ የታነፁ የተላያዩ ታሪክ እንዲሸከሙ ተደርገው በጥንቃቄና በጥበብ እንዲታነፁ የተደረጉ ህንፃዎች፤ ሎጆች፤ ካፌዎች ፤ፈንጠርጠር ብላው ከሩቅ የሚታዩ የገበሬ ቤቶች እርሻዎች …ሁሉ ነገር አይን ሞልቶ የሚፈስ የመንፈስ ትፍስህት ነው፡፡በወንጪ ኢኮቱሪዝም ፤የባንክ አገልግሎት፤ የአካባቢው ልጆች ተደራጅተው የሚሰጡት የሬስቶራንት አገልግሎት ፤የተለያዩ የባህል እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች..ካፍቴሪያ …አነስተኛና ትላልቅ

አዳራሾች…አንፊትያትሮች ሁሉም በአቅሙ ልክ አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጎ የተዘጋጀ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ይገኛሉ ፡፡
ወንጪ ኢኮቱሪዝም ባህልና ተፈጥሮን ማእከል አድርጎ የተገነባ ነው፡፡የወንጪ አካባቢ ስድስት ወር አካባቢ ዝናብ የሚዘንብባት ለምለምና እርጥብ ቦታ ነው፡፡እነሰለሞን የተከራዩት ክፍል የእሱ ባለአንድ አልጋ ሲሆን የባልና ሚስቶቹ ግን ሁለት አልጋ በአንድ ክፍል ያለበት ለቀቅ ያለ ዘመናዊና ባህላዊ እቃዎች በስምምነት ተሰባጥረው ያሳመሩት… ለሀይቁም ሆነ የአካባቢውን ተፈጥሮታ ለማየትና ለማድነቅ ውብ እይታ ያለው በአንቦ ድንጋይ ተጠርቦ የተሰራ…በአሻራ ወይም በካርድ የሚከፈት ውብ ክፍል ነው፡፡ መኝታ ክፍሉ ዘመናዊ ማሞቂያ የተገጠመለት ስለሆነ ምቹ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ ተቀምጠው ወይም ተኝተው በተከፈተው መስኮት ቁልቁል ሀይቁን ሲመለከቱ ልብን ጥፍት ያደርጋል፡፡
ምሽት ነው…አራት ሰዓት አካባቢ..አቶ ኃይለ ልኡልና ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ክፍላቸው በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ቁልቁል የጨረቃዋ ብርሀን ወንጪ ሀይቅ ላይ ስታርፍ እና ከሀይቁ ጀርባው ያለውን ውብ ሰንሰለታማ ተራራ እያዩ ያወራሉ
‹‹ሃይሌ..ልጃችን ግን አሁን ወደአዲስአባ እንደተመለስን የምትመጣ ይመስልሀል?››
‹‹አታስቢ….ትመጣለች….››
‹‹እንደማስበው አሁን እሷ እንድንሆንላት የምትፈልገውን አይነት ወላጆች የሆን ይመስለኛል…፡፡››


‹‹በጣም የተቀደሰ ሀስብ ነው››ቀድሞ የተነሳ ሰለሞን ነው..ሴቶቹም ተከተሉት፡፡እያተሳሳቁና እየተጫወቱ በእግሩ ጉዞ እስካይ ብሪጁ ጋር ደረሱ…..
ለሊሴና ሰለሞን ቀድመው የብረት ተንጠልጣ ድልድዩ ላይ ቢወጡም በፀሎት ግን ልትደፍር አልቻለችም..‹‹ምነው ፈረራሽ እንዴ?››
‹‹ለምን አልፈራም…እየው እስኪ ቁልቁል በሆነ ተአምር ቢበጠስስ?››
‹‹አንቺ ደግሞ በለሊት ሞተር የምታበሪ ጀግና እዚህ ድልድይ ላይ መውጣት ትፈሪያለሽ?››ለሊሴ በትዝብት ጠየቀቻት፡፡
ወደተሸፈነ ፊቷ እያመለከተች‹‹በለሊት ሞተር መንዳቴ ያመጣብኝን ጣጣ አትመለከቺም?››አለቻት፡፡
ወደኃላ ተመለሰና እጇን ይዞ እየጎተተ አስወጣት ….ተጠመጠመችበትና እጆቾን በወገቡ ዙሪያ አዙራ ተለጠፈችበት፡፡ልክ የመጀመሪያ ልጁን ዳዴ እንደሚያስተምር አባት ቀስ ብሎ እየጎተተ ይዞት ይጓዝ ጀመረ…እንደምንም ድልድዩን ተሻግራ እግሮቹ መሬት ሲረግጡ እፎይ አለችና በረጅሙ ተነፈሰች….ሁለቱም ተሳሳቁባት፡፡
‹‹ተፈጥሮ እኮ ምትገርም ነች ..ከጎንና ጎን ሁለት መለስተኛ ኩሬዎች አሉ…ሁለቱም በተለያየ አይነት ቀለም ባላቸው ውሀዎች ተሞልተዋል ..አንደኛው ፈዛዛ አረንጓዴ አይነት ቀለም አለው…ውሀው በጭቃ የተሞላ እና ሙቅ ነው…በህመም የሚሰቃዩና ፈውስ ሚፈልጉ ሰዎች ውስጡ ይገቡና ሰውነታቸውን በጭቃ በመለቅለቅ ይዘፈዘፋሉ…ከዛ ቀላ ያለ ድፍርስ መሳይ ኩሬ ውስጥ ገብተው ይዘፈዘፋሉ..ደግሞ ከተራራው ላይ እየተንፏፏ የሚፈልቅና ውብና ንፅህ ሙቅ ፏፏቴ አለ…በአካባቢው ባለው ወንዝ አጎንብሰው ከወንዙ ሚጠጡ ፈረሶችና ከብቶች ዙሪያውን ያለው ጫካ ከዛፍ ዛፍ ሚዘሉ ዝንጀሮዎች ጦጣዎችና ጉሬዛዎች አካባቢውን በውብ ዜማ የሚያደምቁ የወፍ ዝርያዎች ሁሉም ድንቅ ነው፡፡
ጉብኝታቸውን አገባደው ሰለሞንም ወደሎጁ በፀሎትና ለሊሴም ወደአረፉበት የዘመድ ቤት ጉዞ ጀመሩ…ግን ማረፊያቸው ከመደረሳቸው በፊት ከተለያዩ 20 ደቂቃ በኃላ ነበር ሰለሞን

ለበፀሎት የደወለላት..ስልኩን አነሳችና ከለሊሴ ወደኃላ ቀረት ብላ አዋራችው…ጨርሳ እንደተመለሰች ወዲያው ነበር ለሊሴ በነገር የተቀበለቻት፡፡
‹‹እኔ ይሄ ሰውዬ ምኑም አላማረኝም?››
‹‹የትኛው ሰውዬ?››በፀሎት ያልገባ መስላ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ሀለቃዬ ነዋ››
‹‹ደግሞ ምን አደረገ?››
‹‹አንዴ …እዚህ ያለንበተ ድረስ መጣ …አብረን ረጅም ሰዓት አሳለፍን ..አሁን ከተለያየን ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሞላም …ግን ይሄው ደወለልሽ››
‹‹እና?››
‹‹እናማ …አፍቅሮሻል እያልኩሽ ነው…››
‹‹ጥሩ ነዋ››
ለሊሴ ያልጠበቀችውን መልስ ስላገኘች ይበልጥ ተገረመችባት‹‹ጥሩማ ጥሩ ነው…ግን አንቺስ ታፈቅሪዋለሽ ወይ…?››
‹‹አፈቅረዋለው እንዴ ?››እራሷን ጠየቀች..ቁርጥ ያለ መልስ ለማግኘት አልቻለችም››
ለሊሴ መልስ ስታጣ ንግግሯን ቀጠለች..‹‹ቅድም እንደነገርኩሽ ሁለታችሁም አብራችሁ ብትሆኑ እንደእኔ ደስተኛ የሚሆን ሰው የለም…ሀለቃዬ በጣም የማከብረው ሰው ነው፡፡ አንቺም የምወድሽ እህቴ ነሽ፡፡ የሁለታችሁ አንድ ላይ መሆን ልዩ ነው..ግን አንቺ ፍላጎት ማይኖርሽ ከሆነ ከአሁኑ ነው ግንኙነታችሁን ማቆም ያለብሽ…ምከንያም ከዚህ በላይ ስር እየሰደደ ሄዶ እሱ ሙሉ በሙሉ ፍቅር ውስጥ ከተዘፈቀ በኃላ አይሆንም ዞር በል ብትይው…በእኔ ስራ ላይም ከፍተኛ ተፅእኖ ይፈጥርብኛል..ታውቂያለሽ ስራውን በስንት መከራ ነው ያገኘሁት..በእናንተ ጉዳይ እንዲበላሽብኝ አልፈልግም፡፡››
በፀሎት በፀጥታ አሰበች..ሆነም ቀረ በቅርብ ቀን ሁሉ ነገር ፍርጥርጥ ማለቱ አይቀርም
..ታዲያ ለምን ልጅቷን አጨናንቃታለሁ? ስትለ አሰበችና ወሰነች..ወደማረፊያችው ሊደርሱ

የ10ደ ደቂቃ መንገድ ነበር ሚቀራቸው…‹‹ነይ እስኪ እህቴ ወደቤት ከመግባታችን በፊት እዚህ ዛፍ ስር ትንሽ እንቀመጥ…››
‹‹ምነው ቤት ብንገባ አይሻልም ..?ደርሰናል እኮ››
‹‹ገብቶኛል…የምነግርሽ ነገር ስላለነው፡፡››
‹‹እሺ›› አለችና ከመንገድ ዳር ወዳለች ዛፍ ሄዱና ጎን ለጎን ሳር ላይ ተቀመጡ….
‹‹ለሊሴ እኔ ሰለሞንን የማውቀው በቀደም ለማሪያም ቀን ሲመጣ አይደለም.››
‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹ማለቴ እርግጥ በአካል ፊት ለፊት የተገናኘነው የዛን ቀን ነው…..ግን ከዛን በፊትም  እንደዋወል ነበር››
‹‹የምታወሪው ምንም እየገባኝ አይደለም፡፡››
‹‹ትዝ ይልሽ ከሆነ ስራ የጀመርሽ ሰሞን ስለ እሱ ጥሩነት ደጋግመሽ ታወሪኝ ነበር..ለሆነ ስራ ስለምፈልገው ስልኩን ከአንቺ ሞባይል ወሰድኩና ደወልኩለት …ተነጋግረን ትስማማንና ቀጠርኩት፡፡››
‹‹ቀጠርኩት››
‹‹አዎ ቢሾፍቱ ለ15 ቀን የቆየበት ስራና አሁንም እዚህ የመጣበት ስራ የእኔ ስራ ነው….እርግጥ እዚህ እንደሚመጣ እኔም ከአንቺ እኩል ነው ያወቅኩት ቢሆንም የእኔን ወላጆች ይዞ ነው የመጣው››
ለሊሴ ከመገረምና ከመደንጧ የተነሳ ከተቀመጠችበት ተነሳች፣ጭንቅላቷን ያዘች፡፡‹‹እህቴ ቁጭ በይ ዋናውን ነገር አልነገርኩሽም››
‹‹ከዚህም በላይም ዋና ነገር አለ?››
‹‹አዎ ቁጭ በይ›› ቁጭ አለች…

‹‹እኔ ማለት….››
‹‹አንቺ ማለት?››
እጇን ያዘችና ጎትታ ደረቷ ላይ አስቀመጠች….‹‹ይሰማሻል?››
‹‹ምኑ?››
‹‹የልብ ምቴ››
‹‹አዎ ይሰማኛል….አመመሽ እንዴ? በፍጥነት ነው የሚመታው››
‹‹አይ ደህና ነኝ…እንዴት እደምነግርሽ ስለጨነቀኝ ነው ..ምን መሰለሽ…ይሄ አሁን ውስጤ የሚመታው ልብ የእህትሽ ልብ ነው፡፡››
‹‹አዎ፣ እሱማ አውቃለው የእህቴ ልብ ነው››
‹‹ማለቴ የበሬዱ ልብ ነው….እኔ ይሄንን ልብ ከእህትሽ ነው የተለገሰኝ››
‹‹ወይኔ  በፈጣሪ..ምን  እያልሽኝ  ነው….?አንቺ  ማለት….ወይኔ  በፈጣሪ…ለምን  ዋሸሺን
…..አሁን አባዬ ሲሰማ ምን ይላል….?››
በፀሎት ለሊሴን ለማረጋጋትና ሙሉን ታሪኳንና እቅዷን ለማስረዳት ከአንድ ሰዓት በላይ ነው የፈጀባት…ሁሉ ነገር ተስተካክሎና በመሀከላቸው የነበረው የተካረረ ስሜት ረግቦና ሰላም ወርዶ ወደቤት ተቃቅፈው ሲመለሱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት አልፎ ነበር…

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞንና የበፀሎት ቤተሰቦችን አብዛኛውን ጊዜያቸውን አካባቢውን ያለውን እያንዳንዱን መስህብ በመጎብኘት ነው የሚያሳልፉት….እያንዳንዱ ውይይትና ምክረ-ሀሳብም በመዝናናት ውስጥ ሆነው የሆነ ቦታ አረፍ ሲሉ ወይም ቡና ለመጠጣት የሆነ ካፌ ሲቀመጡ በውይይትና በጫወታ መልክ የሚሰጥ ስለሆነ እንደ ቢሾፍቱ አስጨናቂና ጭንቅላት የሚይዝ አይነት አልነበረም፡፡

በወንጪ ኢኮ ቱሪዝማ ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት እና ለጉብኝት ዝግጁ ከሆኑት ዋና ዋና አይን ሳቢና ቀልብ አስደንጋጭ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ ጥቂቶቹ
ጎሮ በሚባለው ስፍራ የተገነባው ጎሮ ካልቸራል ሴንተር የወንጪ ኢኮቱሪዘም ፓርክ አንዱ መገለጫና ውበት ነው፡፡ በህንፃው ላይ ባህላዊ ምግቦች የሚገኙበት ውብ የሆነ ሬስቶራንት..ባህላዊ የሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶች የሚሸጥባቸው ሱቆች…የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት የሚያገለግል እስከ 3መቶ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ውብ የሆነ አምፊ ትያትር ከአካባቢው ከሚገኙ አገልግሎቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እና አካባቢው ላይ ሆኖ ቁልቁል ወደታች ሀይቁንና ከማዶው ያለውን ተራራ ሲያዩት ልብን ስውር የሚያደርግ የተለየ አይነት አስደማሚ እይታ አለው፡፡

ከጎሮ 2.3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ነዲ ካልቸራል ሴንተር ደግሞ ሌላው ልብ ሰዋሪ ቦታ ነው፡፡ነዲ ከስሙም መረዳት እንደሚቻለው በአካባቢው የሚመረት የወንጪ ማር እና የማር ውጤቶች እንደብርዝና ጠጅን ጨምሮ መሸጫ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ህንጻ ነው…የህንፃው ጠቅላላ ዲዛይን አገልግሎቱን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ውብ ነው፡፡በማር እንጀራ ቅርፅ የተሰራ ሁለት ሶስት ጓደኛሞች ተቀምጠው ቁልቁል ሚታየውን ውብ እይታ ዘና እያሉ ወሬያቸውን የሚጠረቁበት ውብ ስፍራ አለ፡፡

ሙለታ ወንጪ ሬስቶራንት ሌላው በስፍራው የሚገኝ ውብ ቦታ ነው …በዚህ ስፍራ ሬስቶራንቶችና ሱቆች የፈረስ ማስዋቢያና ባህላዊ እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች ሲኖሩ ኩኪስ ብስኩት የመሳሰሉትም ቀላል ምግቦችን ማግኘት ይቻላል ፡፡
ነዲ ሰስፔንድድ የመስታወት ቴራስ ሌላው በአካባቢው ያለ ውብ ህንፃ ነው፡፡ይህ የመስታወት ወለል ግማሽ ክብ አይነት ቅርፅ ሲኖረው በሶስት ድርብርብ ተደርጎ የተሰራና እላዩ ላይ ወጥታው በመስታወቱ አሻግረው ወደታች ሲመለከቱ ከስር የሚታየው አስፈሪ ገደል መሳይ ግን በአረንጓዴ ሳርና ተክሎች የተሸፈና ውብ ስፍራ በማዶ የሚገኘው የጠራ ሀይቅ …በቃ አስፈሪ ግን ደግሞ አስደሳች እይታ ነው፡፡ይህ የመስታወት ቴራስ በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 400 ኪ.ግራማ የመሸከም አቅም እንዳለው ቢታወቅም በርከት ያለ ሰው ከወጣበት ግን ከአሁን አሁን መስታወቱ ተፈርክሶ ሾልከን ወደገደሉ ብንንከባለልስ? የሚል የፍራቻ ስሜት ሰቅዞ የሚያሲዝ አይነት ነው፡፡ከዚህ አስደማሚ የመስታወት ቴራስ ጎን አምፊትያትር ያለ ሲሆን በተያያዥነትም…ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሰጥ ካፍቴሪያ አለ፡፡ከዚህ ስፍራ ቀጥታ ወደሎጅ የሚወስድ የመኪና መንገድ ከላይ የመስታወት ቴራሱ ላይ ሆነው ከስር ማየት ይቻላል፡፡
ከዛ ደግሞ የተፈጥሮ ፍል ውሀ ያለበት በደን የተሸፈነ ሲሆን በአካባቢው ጉሬዛ ፤ጦጣ አእዋፍት ፤አምቦ ውሀ የተፈጥሮ ፏፏቴ ይገኛል …ጎን ለጎን ያሉ ሙቅና ቀዝቃዛ ኩሬ የኬብል ድልድይ ፤ወንዝ ..ብዙ ብዙ አስደማሚ ተፈጥሯዊ ነገር ይገኛል፡፡የነዲ መዝነኛ ስፍራን እና የተፈጥሮ ፍል ውሀን የሚያገናኝ በብረት የተሰራ እስካይ ብሪጅ አለ፡፡ብሪጁ 72 ሜትር ርዝመትና ኖሮት ሀምሳ ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ አስፈሪ ግን ደግሞ የራሱ የሆነ ውበትና የተለየ ስሜት የሚያጭር ልዩ ድልድይ ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ ባለፈው አንድ ሰምንት ውስጥ የጎበኞቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 9ሰዓት አካባቢ ለበፀሎት ደወለላት
‹‹ሄሎ..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ…ገነት ገብቼለሁ››
‹‹ወደድሽው ማለት ነው››

‹‹እንዴ ትቀልዳለህ እንዴ …?አካባቢው እኮ እንኳን እንደእኔ አፍጥጠው የሚያዩ ሁለት አይኖች ላሉት ሰው ይቅርና አይነ-ስውር ቢመጣበት እንኳን ውበቱ በሽታ ሳይቀር ይታወቀዋል፡፡››
‹‹ዋው ድንቅ አገላለፅ ነው….በጣም ማርኮሻል ማለት ነው…እኔንም አንድ ቀን ወስደሽ እንደምታስጎበኚኝ ትስፋ አለኝ፡፡››
‹‹በደንብ እንጂ…ለዛውም በቅርብ ነዋ››
‹‹አሁን የት ነሽ…?ላለፉት አንድ ሰዓት ለሊሴ ጋር በሳይክል አካባቢውን ስናካልል ነበር.. አሁን ድክም ብለን ነዲ ካልቸራል ሴንተር የሚባለው ስፍራ ላይ ነን ፡፡
‹‹ምነው…ጠጅ እየጠጣችሁ ነው እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ትኩስ ወለላ ማር እየበላን››
‹‹በቃ ..ሰዓታችሁን አልውሰድባችሁ…..ዘና በሉ››
‹‹እሺ ቸው…ለሊሴ ሀይ እያለችህ ነው፡፡››
‹‹ሀይ በይልኝ‹‹ስልኩ ተዘጋ፡፡
‹‹አንቺ ሀለቃዬን ምን ልታደርጊው ነው?››ለሊሴ በመገረም ውስጥ ሆና ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አደረኩብሽ…?››
‹‹እንዴ እያየሁ…ከተዋወቃችሁ ገና ሳምንት ነው..ግን ይሄውና በየቀኑ ይደውልልሻል፣ ገባሽለት እንዴ?››
‹‹አረ አንቺ ደግሞ…››በፀሎት እንደማፈር ብላ ተሸኮረመመች፡፡
‹‹ምነው..ቢሆን ደስ ይለኛል..ምርጥ ሸበላና የተማረ ሰው ነው..በዛ ላይ ትህትና አለው…እና አንቺን እህቴን ብድርለት በጣም ደስ ይለኛል››
‹‹በይ አንቺ ካዳመጡሽ …ብዙ ታወሪያለሽ››

ለደቂቃዎች ሁለቱም ዝም ተባባሉና በየግላቸው ሀሳብ መብሰልሰል ጀመሩ፣…በፀሎት ድንገት‹‹አካባቢው ግን አያስደንቅም?››ብላ አዲስ የመወያያ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹ በጣም እንጂ…እያንዳንዱ ስፍራ የራሱ የሆነ እይታ አለው…አሁን ጎሮ ጋር ሆነሽ ቁልቁል ስታይ የተለየ አይነት እይታ..ከሊበን ሆነሽ ስታይው ደግሞ የተለየ አይነት እንደምታይው እዚህ ሆነሽ ስትመለከቾ ደግሞ ሌለ አይነት…በእውነት ይሄ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ቦታ በቀየርሽ ቁጥር የምታይውም ነገር ይቀየራል…››
‹‹አዎ እንግዲህ …አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም….››
‹‹እውነት ነው አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም››የሚል ጣልቃ ገብ ዓ.ነገር  ሁለቱንም ከተቀመጡበት በርግገው እንዲነሱ አደረጋቸው፡፡ሌላ ሰው ነበር ከጀርባቸው የተናገረው፡፡
‹‹አንተ….እንዴት?››
‹‹ያው እንደዚህ››አለና ሁለቱንም በየተራ ሰላም አላቸው፡፡ተያይዘው ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ሆነህ ነበር እንዴ የምትደውልልኝ…?››በፀሎት በገረሜታና ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ…››
‹‹እኔ ደግሞ ምን አይነት ሞኝ ነኝ ..የት ነሽ ስትለኝ ያለሁበትን በየዋህነት መዘርዘሬ››
‹‹ምነው ስለመጣው ከፋሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም››
የሰለሞንንና የበፀሎትን የማያቆርጥ ጥያቄና መልስ በዝምታ እየታዘበች በውስጦ እነዚህ ሰዎች ምንድነው እንዲህ ያቀራረባቸው..?ሰውዬውስ እሷን ፍለጋነው እንዴ እዚህ የመጣው
?እያለች በውስጦ ተብሰለሰለች ፡፡ልክ ልቧን እንዳነበበ ለጥያቄዎቾ መልስ ይሰጣት ጀመር…‹‹ያው ባለፀጋዎቹ ደንበኞቼ እዚህ ካልመጣን ሲሉ ተከትያቸው መጠሁ..ያው አስገድደው ሲያስደስቱኝ ምን ላድርግ..እየመጣሁ ሳለሁ ደግሞ እናንተ እዚህ እንዳላችሁ ትዝ ሲለኝ..የበለጠ ዘና አልኩ››
‹‹እና ታዲያ ሰዎችህ የታሉ?››በፀሎት ከወላጆቾ ጋር ድንገት ፊት ለፊት የመፋጠጥ ስጋት አስጨንቋት ጠየቀች

‹‹አሁን ክፍላቸው አረፍ ብለዋል….ለሚቀጥሉት ሁለት ሶስት ሰዓት እረፍት ነኝ….›› በፀሎት‹‹እና ታዲያ ወደፍል ውሀ ለምን አንሄድም?››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡


ለሊሴ ግቢው ውስጥ ይዛው ገባችና መጀመሪያ ከአባቷ ጋር ከዛ ከወንድሞ ጋር አስተዋወቀችውና ይዛው ወደ ሌላ ክፍል ውስጥ ይዛው ገባች…ክፍሉ አዲስ የተሰራ መሆኑን ያስታውቃል….ጥግ ላይ በስርአት የተነጠፈ አንድ አልጋ ..ከዛ ሁለት ወንበር እና አነስተኛ ጠረጴዛ ይታያል..ጠረጴዛ ላይ ሁለት ነጭ ሻማ ተለኩሶ እየበራ ነው…የቤቱ ወለል ሙሉ በሙሉ ቄጤማ ተጎዝጉዞ አውዳአመት መስሏል…አልጋው ጠርዝ ላይ አንድ ወጣት ተቀምጣለች …ከዛ ውጭ ቤቱ ባዶ ነው፡፡
በፀሎት‹‹ግባ ዝለቅ…. ››የሚል ድምጽ ስትሰማ ካቀረቀረችበት ቀና አለችና ግባ እየተባለ ያለው ሰው ላይ አፈጠጠች…ጠይም ነው…ባለደማቅ ጥቁር ፀጉር…ቆንጆ ወንዳወንድ
ነው…ልክ እንደባንክ ቤት ስራአስኪያጅ ሽክ ብሎ ሰማያዊ ሱፍ ለብሶል..ሰማያዊ ሱፍ በነጭ ሸሚዝ…ከረባት አላሰረም….በቅፅበት ውስጥ ነው ሙሉ ቁመናው ውስጧ ስምጥ ብሎ የገባው፡፡ስሯ ደርሶ ሲቆም ከተቀመጠችበት ተነሳች…..‹‹ተዋወቂው ሀለቃዬ ነው….እሷ ደግሞ እህቴ ነች››
‹‹ሰለሞን እባላለሁ››ብሎ እጁን በትህትና ዘረጋላት፡፡
በደመነፍስ እጇን ዘረጋችለት..ጨበጣትና እየወዘወዛት ስሟን እስክትነግረው ይጠብቅ ጀመር…..ምን ብላ ትንገረው….ለእሷ በዛሬው ቀን ይሄ ሰው ያለችበት ቦታ ድረስ መጥቶ እጇን መጨበጥ የማታሰብ ነገር ነው….፡፡
‹‹ስምሽን ንገሪው እንጂ …?.›››
‹‹ስሜን የማን የእኔ..ማለቴ..››ተርበተበተች፡፡
‹‹ተዋትና ተቀመጥ ልጄ…..››እጇን ለቀቀና ወደመቀመጫው ሄዶ ተቀመጠ… ፡፡ ለሊሴ‹‹ተጫወቱ መጣው..››ብላ ወደ ዋናው ቤት ሄደች፡፡
‹‹ምነው ስምሽ ያስጠላል እንዴ?››ሲሌ ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ እንጃ….ሰናይት እባላለሁ››
‹‹እና ሰናይት የሚለውን ስም ለመናገር ነው የተናነቀሽ?››
‹‹አይ …ሱፍ ለባሽ ክፍላችን ሰተት ብሎ ይገባል ብዬ ስላልጠበቅኩ ነው፡፡››
‹‹ቱታ ለብሼ መምጣት ነበረብኝ…?››
‹‹ለካ እንዲህ ነገረኛ ና አሽሟጣጭ ሰው ነው እንዴ? ››ስትል በውስጧ አሰበች…ዝም አለችው….. ወዲያው ለሊሴ እና እናቷ እንጀራና ወጡን ይዘው መጡ…እዛው የእጅ ውሀ አስታጠቡትና የሚበላ ቀረበለት…እንጀራውን ሲነሳ ደቦና ቆሎ ቀረበለት..ለእሱ ተብሎ የተገዛ ቢራ ተከፈተለት…..
‹‹እንዴ ቢራ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ ምጠጣው…?››

‹‹ለጊዜው አዎ…አባዬ ትንሽ ቆይቶ መጥቶ ይቀላቀልሀል….እንግዶች ስለመጡ እማዬን ባግዛት ቅር ይልሀል..አልቆይም፡፡ ››
‹‹ሂጂ ችግር የለውም ..እህትሽ ታጫውተኛለች›› ለሊሴ‹‹ጥሩ ..በቃ መጣሁ››ብላ ወጣች
ሰለሞን ወደ በፀሎት ዞረና ‹‹አሁን ብቻችንን ቀርተናል….››አላት፡፡ ደንግጣ‹‹ ማለት?››
‹‹አትደንግጪ ሰኒ…ምን አስደነገጠሸ?››
‹‹አይ እሱማ ምን ያስደነግጠኛል…?አልደነገጥኩም…››እውነቱን ለመናገር ከመደንገጥም አልፋ ሰውነቷ በላብ እየተዘፈቀ ነው፡፡
‹‹አህቴ ስለአንተ ብዙ ነገር ነግራኛለች….››
‹‹እህትሽ ብቻ… እኔስ ብዙ ነገር ነግሬሽ የለ እንዴ?››
‹‹መቼ ..?የት ተገናኝተን….?››
መልስ ይመልስልኛል ብላ ስትጠብቅ ስልኩን አወጣና እያየችው ደወለ…ኪሷ ያለው ስልክ ተንጣረረ…አወጣችና አየችው…ምን እንደምትል እንዴት እደምታደርግ ግራ ገብቶት
አፍጥጣ እስክሪኑን እያየች ባለችበት ሰዓት ለሊሴ ከውጭ ገባች….ሰለሞን ስልኩን ዘጋው..የሚያንጣርረው የበፀሎት ስልክም ተቋረጠ…፡፡
‹‹በፀሎት ሀለቃዬን እንዳታስደብሪው››
‹‹አረ …የምን መደበር አመጣሽብኝ….እህትሽ ካንቺ በላይ ተጫዋች አይደለች እንዴ?››
‹‹እንግዲያው ጥሩ ..ቢራውን ጨምሪለት››ብለ ተመልሳ ወጥታ ሄደች፡፡
‹‹እሺ ጨምርለታለው››
መሄዷን ከረጋገጠች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀና ብላ በትኩረት አየችው‹‹ምነው ቆንጆ ነኝ?››

‹‹በጣጣጣ…..ም››
‹‹አንቺም ልክ እንደጠበኩሽ ነሽ…ግን እንዳትታወቂ ነው የተሸፋፈንሽው….››
ቀስ ብላ ሻርፕን ከፊቷ አነሳችና አሳየችው…..ደነገጠ….ወዲያው በፍጥነት መልሳ አሰረችው፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››
‹‹የጠፋው ቀን በሞተር ነበር ከቤት የወጣሁት..እና ይዚህን ጊቢ አጥር ጥሼ ከበሩ ጋር ተላትሜ ነው የቆምኩት….እግሬ ሁሉ ተሰብሮ ነበር…አሁን ግን ድኛለሁ››
‹‹ይሄንን እንዴት እስከዛሬ ሳትነግሪኝ?››
‹‹ለምን ነግርሀለው..?ምን እንድታደርግልኝ?››
‹‹ምን ባላደርግልሽስ….እኔ ላንቺ አንደዚህ ነኝ?››
‹‹እንዴት ነህ?››
‹‹ትናት ማታ እንደዛ ዳባሪ ስሜት ላይ ሆኜ ለማን ደወልኩ ?ላንቺ አይደል?››
‹‹በነገራችን ላይ በጣም ስታሳስበኝ ነበር…ለሊቱን ሙሉ ስላአንተ እየተጨነኩነው ያሳለፍኩት…..እንደማይህ ግን እንደማንኛውም ወንድ ወዲያው ማገገምና ወደተመደ እንቅስቃሴ መግባት ችልሀል፡፡››
‹‹ምን ጠብቀሽ ነበር…?ዛሬም አልጋዬ ላይ ተኮራምቼ እንዳለቅስ?››
‹‹አዎ.. እኛ ሴቶች ብንሆን እንደዛ ነው የምናደርገው››
‹‹ይሁን…አሁን እንደተመለስኩ እንዳልሺኝ አደርጋለው….በነገራችን ላይ ይሄንን የመቁሰልሽን ዜና ወላጆችሽ ቢሰሙ በቃ ቁም ስቅሌና ነበር የሚያሳዩኝ…››
‹‹ቆይ እንዴት እኔ መሆኔን አወቅክ…..ማለት እንዳየሁህ እኮ ስሜን ቀይሬ የነገርኩህ ማንነቴን የምትለይበት ምንም መንገድ እንደሌለ እርግጣኛ ሆኜ ነበር፡፡››
‹‹እንግዲህ ይሄን ያህል ነው የማውቅሽ….››
‹‹በጣም ነው ያስገረምከኝ››

‹‹ያው ሰውን ማስገረሙን ካንቺው ነው የኮረጅኩት››
‹‹እሺ..በመሀከላችን ስላለው ነገር ለሊሴ ምንም ማወቅ የለባትም››
‹‹እንዴ በመሀከላችን የሆነ ነገር አለ እንዴ?››
‹‹አትቀልድ››
‹‹እሺ እንዳልሽ››
‹‹በነገራችን ላይ ከለሊሴ ጋር ከነገ ወዲያ ወደወንጪ ልንሄድ ነው…የጋሼ ዘመዶች እዛ አሉ….እንዝናናለን፡፡››
‹‹ደስ ይላል..ያው እኔም ከተውሻቸው ወላጆችሽ ጋር የሆነ ቦታ ሄጄ ዘና እላለው…ሳስበው አንቺ እዚህ ስለተመቸሽ አነሱን ለእኔ ብትሰጪኝ ደስ ይለኛል፡፡;;
‹‹ውሰዳቸው››
‹‹ተይ በኃላ..እንደድሮ እንዳይመስሉሽ…ፍቅር ሲያገረሽ አደገኛ መሆኑን ያየሁት በእነሱ ነው…ጎረምሳ በያቸው››
ለሊሴ አባቷን አስከትላ መምጣቷን ጫወታቸውን እንዲያቆርጡ አደረጋቸው፡፡

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..

የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ  መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ

እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡


‹‹አይ..ያ እውነት አይደለም…ቤተሰቦቼን ምን ያህል እንዳገዝካቸው እኔ ነኝ ማውቀው..አረ የእነሱን ተወውና እኔን እራሱ በስልክ ብቻ በምታወራኝ ምን ያህል ጥንካሬና ብርታት እንደምትሰጠኝ አታውቅም..ፈፅሞ በምንም ምክንያት ተስፋ መቁረጥ የለብህም..ደግሞ አንድ ግንኙነት አልተሳካምና ጠቅላላ ያንተ ህይወት አበቃለት ማለት አይደለም…አንዳንዱ ግንኙነቶች ምንም ቢለፋባቸውና ፍሬ አያፈሩም…ያንተም እንደዛ ሆኖ ይሆናል››
‹‹ይገርማል››
‹‹ምኑ ነው የሚገርመው?››
‹‹እኔ ሳልሆን አንቺ ነሽ የፍቅር አማካሪ መሆን የነበረብሽ››
‹‹እንግዲህ በችሎታዬ ከተማመንክ ስልጠና ሰጥተህ ወደፊት በረዳትነት ልትቀጥረኝ ትችላለህ››
‹‹ደስ ይለኝ ነበር…ደሞዝሽ ይከብደኛል እንጂ››
‹‹አይዞህ..አትፍራኝ …አንደራደራለን››
‹‹አመሰግናለሁ…አንቺ ጋር መደወሌ ምክንያታዊ ባይሆንም ..ግን ሰርቷል አግዘሺኛል፣አሁን ትንሽ ቀለል አለኝ፡፡››
‹‹አሁን መጠጣቱ ይብቃህ…ሻወር ወሰድና ተኛ…ጥዋት ስትነሳ ሁሉ ነገር ቀለል ብሎህ ታድራለህ››
‹‹እሺ….እንዳልሺኝ አደርጋለው….ደህና እደሪ››

‹‹ደህና እደር››ብላ ስልኩን ዘጋችው ፡፡

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


‹‹‹አይ ይሄ ለነገሮች ያለን ትርጉም ልዩነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡እኔ ወላጅ አልባ ብቻ ሳልሆን ዘመድ አልባ በሆንኩበት በዛ ጨለማ ጊዜ እናትና አባትህ ያለምንም ማቅማማት ወደቤታቸው ወስደው ከዛሬ ጀመሮ አንቺም ሌለኛዋ ልጃችን ነሽ አሉኝ፡፡እውነትም እንዳሉት ለእህትህ ስህን የሚደረገው ሁሉ ለእኔም ይደረግልኝ ነበር..ለእሷ ቀሚስ ሲገዛ ለእኔም ዘለውኝ አያውቁም.. ከፓንት አቅም ለእሷ የተገዛው አይነት ለእኔም ይገዛልኝ ነበር… የእውነት ልጃቸው ነበርኩ..ዩኒቨርሲቲ ገብቼ አንድም ወር የኪስ ገንዘብ ለእኔ ከመላክ እረስተውና ዘለውኝ አያውቁም…እና ሁለቱም ሲሞቱ ከእናንተ እኩል ነው ያጣዋቸው…..አንተ የምትወዳቸውን ያህል እኔም ወዳቸዋለው…አሁን የሚናፍቁህን ያህል

እኔንም ይናፍቁኛል..እና እኔ የእውነትም አንተም ወንድሜ እነሱም ወላጆቼ እንደሆኑ ነው የማምነው..ይሄንን እምነቴን ማንም በየትኛውም ሎጂክ ተከራክሮ ሊያስቀይረኝ አይችልም…እምነት ያው ከቃሉም እንደምትረዳው ዝምብለህ ነገሩን በቀና ልብ መቀበል አይደል..እኔም እንደዛው ተቀብዬዋለው…፡፡አሁን እንተ የደም ትስስር የለንም ምናምን ብትለኝ.በአንዱ ጆሮዬ ገብቶ በአንድ ይፈሳል እንጂ በእኔ ስሜት ላይ ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም…አንተ እንደፈለከው ማመን ትችላለህ…እህቴ አይደለሽም ልትለኝም ትችላለህ…በግድ ላሳምንህ አልችልም..፡፡››
‹‹ይገርማል… ልጅ እያለንም ጭምር እንዲህ ነገሮችን ውስብስብ ማድረግ ትወጂ ነበር…እሺ አሁን ለምን ተመልሼ እንደመጣሁ ታውቂያለሽ?››
‹‹ያው የሰው ሀገር አይደል ..ደብሮህ ነዋ››
‹‹አይ አይደለም….ከመስፍን ጋር እንደተፋታችሁ ስሰማና ፣አገር ለቆ እንደሄደ ሳረጋግጥ…ዳግመኛ እድሌን ለመመከር ነው..ምን አልባት አሁን እነአባዬና እማዬ በህይወት ስለሌሉ እሺ ብለሽ ፍቅሬን ትቀበይዋለሽ..እኔንም ከቁም ሞት ቀስቅሰሽ ታድኚኛለሽ..ባል አድርገሽ ታገቢኛለሽ ብዬ ነው››
ዝም ብላ በፍዘት ታየው ጀመር…ቡዝዝ ባሉት አይኖቾ እንባ ሞላባቸው…
‹‹ወንድሜ እኔ በጣም ነው የምወድህ..ያንተ ከጎኔ መሆን የሚፈጥርልኝ ጥንካሬና የመንፈስ ከፍታ ልትገምተው አትችልም…አንተ የራስህን ሰው አግኝተህ አፍቅረህና አግብተህ እዚሁ
አጠገቤ አዲስአበባ እንድትኖር ነው የምፈልገው…እባክህ ወንድሜ መልሰህ ጥለሀኝ አትሂድ
..ዳግመኛ እሰደዳለሁ ካልከኝ..በጣም ነው የማዝነው..እራሴንም መቼም ይቅር አልለውም››
‹‹የምታወራው ምንም ሊገባው አልቻለም..እሱ የሚያወራው እሷን ስለማግባት እና አብሮ አንድ ቤት ስለመኖር…እሷ የምታወራው ስለእሱ ዳግመኛ መሰደድ…‹‹ድንገት ሳላውቅ ተመልሼ ሄዳለው ብያት ይሆን እንዴ ?››ሲል እራሱን ተጠራጠረ፡፡
‹‹ኪያ ምን ነካሽ…?ተመልሼ ሔዳለው ብዬሻለው…እንዴ..?››
‹‹አላልከኝም…ግን ወንድሜ በወላጆቻችን አጥንት ይዤሀለው፣ምንም ቢፈጠር ምንም ጥለኸኝ እንደማትሄድ ቃል ግባልኝ››

‹‹እሺ..እንዳልሽ ቃል ገባልሻለው…ምንም ቢፈጠር ምንም ተመልሼ በድጋሚ አልሰደድም፡፡››
‹‹ጥሩ….ማታ የምቀበለው እንግዳ መስፍን ነው››
የቤተሰቦቹን ሞት የሰማ ቀን እንኳን እንዲህ አልደነገጠም‹‹ምን ..?መስፍን….?ከየት…ወጭ አይደል እንዴ?››
‹‹አዎ..ለአለፉት ሁለት ሶስት ወራት ስንደዋወል ነበር..ችግሮቻችን ተነጋገርን ለመፍታት እና የተበላሸውን ግንኙነታንን ለማስተካከል ወስነን አሁን እየመጣ ነው…ዛሬ ሁለት ሰዓት ነው የሚገባው..ቀጥታ ከቦሌ እኔ ነኝ የምቀበለው..እየመጣ መሆኑን ቤተሰቦቹም አያውቁ..ማለቴ ከቦሌ ቀጥታ ወደቤት ነው ይዤው የምመጣው..ልጅንም በጣም ናፍቆል..እና ተነጋግረን ችግሮቻችንን መቅረፍ ከቻልን ነገሮች ወደድሮ ቦታቸው ይመለሳሉ ማለት ነው..ያው ታውቃለህ የፍቺው ጉዳይ ገና ፕሮሰስ ላይ ነው…ያ ማለት አሁንም በህግ ፊት ባልና ሚስቶች ነን››
ድንዝዝ ባለ ስሜት ንግግሯን እስክትጨርስ ዝም ብሎ አዳመጣት…በፍጽም ፀጥታ ነው የተቀመጠው…ሰውነቱ አይንቀሳቀስም…የአይኖቹ ቅንድቦች እንኳን መንቀሳቀስ አቁመው ነበር፣ትንፋሹ መተንፈስም እንዳቆመ አይነት የመታፈን ስሜት እየተሰማው ነው…ንግግሯን ካጠናቀቀች በኃላም እሱ በዝምታው እንደቀጠለ ነው፡፡
ግራ ገባት…የሆነ ነገር እንዲል እየጠበቀችው ነው…እንዲወቅሳት..እንዲረግማት….በእሷ እንዲያማርር እየጠበቀች ነው..እሱ ግን እንደዛ እያደረገ አይደለም…አስፈሪ ዝምታ ላይ ነው፡፡
‹‹ወንድ….ሜ››
‹‹ሂሳብ ክፈይና እንሂድ››ብሎ መኪናውን ቁልፍ ከጠረጴዛ ላይ አነሳና ቀመ ..ወደመኪናው መራመድ ጀመረ…ከቦርሳዋ ብር አውጥታ ጠረጴዛ ላይ ወረወረችና ፈጠን ብላ ከኃላው ተከተለችው፡፡በህይወቱ እደዛሬው ባዶነትና ተስፋ ቢስነት ተሰምቶት አያውቅም..ፍፅም ተስፋ መቁረጥ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የገባውም ዛሬ ነው..በቃ መቼም ይህቺን ሴት ማግባት እንደማይችል አምኖ ተቀበለ…ባያገባትም ግን መቼም ደግሞ ማፍቀሩን እንደማያቆም ያውቃል፡፡

እቤት አድርሷት ብዙም ሳይቆይ ነው ወደቤቱ ያመራው፡፡የሚኖረው ወላጀቹ ቤት ነው ሁሉም ወንድሞቹ የራሳቸውን ህይወት መስርተውና የገዛ ቤታቸውን ሰርተው ቤቱን የለቀቁት ገና ወላጆቹ በህይወት እያሉ ነው፡፡እህቱም ሀገር ውስጥ አትኖርም አሁን በብቸኝነት እየኖረበት ያለው እሱ ነው፡፡ወደቤት ሲገባ ሙሉ ጠርሙስ ጎርደን ጅን ይዞ ነበር የገባው….ገና በቀኑ ነው መኝታ ቤቱን ዘግቶ መጠጣት የጀመረው…
ማታ አንድ ሰዓት ሲሆን ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ነበር‹‹ይሄን ያንን ጉረኛ ልትቀበለው ቦሌ አየር ማረፊያ ቆማ ብርድ እያንቀጠቀጣት ነው››አለ..አሳዘነችው…‹‹ለእሷ የምገባት እኔ ነበርኩ….››ማልቀስ አማረው..እዬዬ ብሎ ማልቀስ አማርው..ግን ማድረግ አልቻለም፡፡ስልኩን ከኪሱ አወጣና ‹‹ማውራት ከቻልሽ ደውይልኝ ››ብሎ ፃፈና ለከ..
ከ5 ደቂቃ በኃላ ተደወለለት‹‹ወይ እግዜር ይስጥሽ…አትደውይልኝም ብዬ ፈርቼ ነበር››
‹‹ምነው? ችግር አለ እንዴ…?ወላጆቼ ምን ሆኑ?››
‹‹‹እነሱ ሰላም ናቸው..በጣም ሰላም ናቸው…ዛሬ አዲስ አበባ ተመልሰናል..እነሱም እቤታቸው ናቸው….እኔ ግን…››ሲያወራ አፉ ይኮለታተፋል..
‹‹ምነው ?አንተ ምን ሆንክ?››
‹‹ተሰብሬለሁ…ሌላ ማወራው ሰው ስለሌለን ነው አንቺ ጋር የደወልኩት…አይገርምም ደህና ጓደኛ እንኳን የለኝም….ቢኖረኝም እንዲህ አይነት ነገር የምነግራቸው አይደሉም››
‹‹ወይኔ በፈጣሪ..እስኪ የሆንከውን ንገረኝ…?.››
‹‹በፀሎት…››
‹‹ወዬ››
‹‹አሁን ካለሽበት መጥተሸ አጠገቤ ብትሆኚና ብታጣጪኝ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹እኔም ደስ ይለኝ ነበር…እይዞህ አንተ ብዙ ነገር የምታውቅ ሰው አይደለህ..?››
‹‹ማወቅ ምን ይሰራል…በፍቅር ስትንኮታኮቺ እኮ ያንቺ ማወቅ እርባነ ቢስ ነው፡፡እኔ እንደውም ይሄንን የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ የሚባለውን ጫወታ መተው አለብኝ..አዎ ፍቃዴን መልሼ ቢሮዬን ዘጋለሁ…››

‹‹ለምን ..ያ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹አይታይሽም እንዴ…ከልጅነቴ ጀምሮ ሳፈቅራት የኖርኳትን ሴት የሆነ ዘዴ ተጠቅሜ እንድታፈቅረኝና እሺ ብላኝ እንድታገባኝ ማድረግ ካልቻልኩ እንዴት ነው ሌላ ሰውን ማገዝ የምችለው…ይሄው ለሁለተኛ ጊዜ አጣኋት …ያሁን ማጣት ደግሞ ይግባኝ የሌለው ነው…እራሴንም ሰዎችንም እያጭበረበርኩ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡››


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ባልና ሚስቶቹን ቤታቸው ወስዶ እንደጣላቸው ቀጥታ የመኪናውን መሪ ወደአስቴር ቢሮ ነው የጠመዘዘው…ገብቶ ምሳ እንዲበላ ቢለምኑት እንኳን እሺ አላለቸውም፡፡እንደሚመጣ አልነገራትም ቀጥታ ከቢሮዋ ፊት ለፊት አቆመና ደወለ
‹‹ሄሎ ወንድሜ….እንዴት ነው ቢሾፍቱ በጣም ተመችታሀለች መሰለኝ?፡፡››
‹‹መጥቻለው….ምሳ አትጋብዢኝም?፡፡››
‹‹የእውነት መጣህ?››
‹‹አዎ ቢሮሽ ፊት ፊት መኪናዬን አቁሜያለው፡፡››
‹‹በቃ መጣሁ››ብላ ስልኩን ዘጋች….5 ደቂቃ ነው ያስጠበቀችው፡፡ገና የቢሮዋን የህንፃ ደረጃ ስትወርድ ጀምሮ ነው አይኑ ውስጥ የገባችው…ሙሉ ሮዝ ቀለም ያለው ጉረድ ቀሚስና ኮት ለብሳለች…ፀጉሯ ወደኃላዋ ትከሻዋ ላይ እንዲተኛ ተደርጎል…ውብ ሆናለች….መኪናዋን ስለምታውቃት ብዙም ሳትደነጋገር ቀጥታ ወደእሱ ነው ያመራችው…ይህቺ ሴት እህቱ እንድትሆን አይደለም የሚፈልገው…ጓደኛም እንድትሆነው አይደለም…የፍቅር አጋሩ ሚስቱ ሊያደርጋት ነው ምኞቱ..ይሄ ምኞቱ ደግሞ አሁን በቅርብ በውስጡ የበቀለ ስላልሆነ ህመሙ ቀላል አይደለም…ገና አፍ ፈቶ በኮልታፋ አንደበት መንተባተብ በጀመረበት በጮርቃነት እድሜው ጀመሮ እሷ ሚስቱ እንደሆነች ያስብ ነበር፣እርግጥ በዛን እድሜ ሚስት ማለት እራሱ ትርጉሙ ምን ማለት አንደሆነ አያውቅም ነበር፣ቢሆንም ጭላንጭል የሆነ ግንዛቤ ነበረው…ሚስት ማለት አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ ሁሌ አብራ

የምትተኛ ሴት እንደሆነች ከአባትና ከእናቱ ግንኙነት መረዳት በቻለበት ጊዜ ነው፣ከእሱ ጋር ለዘላለም መተኛት ያለባት ሴት አስቴር እንደሆነች ወስኖ የነበረው፣በዛን የልጅነት ጊዜ እናቷ የቤታቸውን እንጀራ ልትጋግር ስትመጣ አስከትላት ስትመጣ ጀምሮ እዛው እሷን ማስቀረት ምኞቱ ነበር…እና ያ ምኞት ግለቱን ጠብቆ እየፋመ ነበር የቀጠለው…
ጊዜው ሲደርስ ግን ነገሮች ቀደም ብሎ እንዳሰባቸው ቀላል አልነበሩም…ገቢናውን ከፈተላት ገባች.. ጉንጩን አገላብጣ ሳመችው…ሁል ጊዜ የእሷ መሳም ከሌላው መሳም በጣም ይለይበታል…ወፈር ብሎ ወደፊት ግልብጥ ያለው ፍም ከንፈሯ ሰውነቱ ላይ ሲርፍ የተለየ ሙቀት ነው ሰውነቱ የሚያመነጨው…ልክ የጋለ ቢላዋ አካል ላይ ሲያርፍ የሚሰማው አይነት ትሽሽሽ..የሚል የማቃጠል የመለብለብና የመላጠ ስሜት……
‹‹አንተ ወፍረህ ነው የመጣሀው….ስራ ላይ ነበርክ ወይስ ጫጉላ ሽርሽር ላይ?››
‹‹በይው…አንቺም ተመችቶሻል…ምሳ የት አንብላ?››
‹‹ወደ እኔ ቤት ንዳው››
‹‹ምነው ከሰዓት ስራ የለሽም እንዴ?››
‹‹ዛሬ ቅዳሜ እኮ ነው…ግማሽ ቀን ነው የምንሰራው››
‹‹እና አራበሽም ..በልተን ብንሄድ አይሻልም?››
‹‹አይ ሰራተኛዬ አዘጋጅታ እየጠበቀችን ነው…ዘና ብለን ቤታችን ብንበላ ይሻላል….ወንድሜ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል››
‹‹እኔም ከሰዓት ስራ ስለሌለሽ ደስ ብሎኛል››ብሎ መኪናዋን ወደ አስፓልት መሀል አስገባና ነዳት….የእውነትም ከሰዓት ስራ የለኝም ብላ ወደቤቷ ይዛው እየሄደች በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተስምቶታል…ከአመታት በኃላ መልሶ ዛሬ እድሉን ይሞክራል፡፡አዎ በስደት ከሄደበት ባእድ ሀገር ተመልሶ የመጣውም ለዚሁ ነው፡፡ከባሎ እንደተለያየችና እሱም በዛ ንዴት ከሀገር ውጭ መሰደዱን ሲሰማ ነው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ የመጣው…አንሆ ተመልሶ በመጣበት ባለፉት ስድስት ወሮች እሷን ከገባችበት ድባቴ እንድትወጣና ያልተሳካ ትዳሯ ከፈጠረባትን የስነልቦና መሰበር እንድታገግም እንደወንድም እንደ ጓደኛም ከዛም አልፎ እንደባለሞያም  ከጎኗ  ሆኖ  ሲያግዛትና  ሲደግፋት  ነበር…አሁን  ግን  ልቧ  ሌላ  ፍቅር

ለማስተናገድ ዝግጁ ነው ብሎ ያስባል..በዛ ላይ የእሱ እና የእሷ ፍቅር አዲስ ዛሬ የበቀላ ሳይሆን ድሮ በየሁለቱም ልብ ተዳፍኖ ያለ ነው…አሁን ያንን መቆስቆስና መልሶ እንዲቀጣጠል ትንሽ የፍቅር ቤንዚል ማርከፍከፍ ነው…ለዚህ ድርጊት ያበረታታው ሰሞኑን ያየው በአቶ ሃይለልኡል እና በወ.ሮ ስንዱ መካከል የተከሰተው የፍቅር ግርሻ ነው፡፡
‹‹አዎ…አስቴርን አገባታለሁ…ከበፊት ባሏ የወለደችውን አንድ ልጅም እንደልጄ አድርጌ አሳድገዋለው››በውስጡ አልጎመጎመ…‹‹እና በቅርብ ቀን እሷም ወንድሜ የምትለውን ጥሪ ትተውና ባሌ ብላ ትጠራኛለች…ልጇም አጎቴ ብሎ የሚጠራውን አቁሞ አባቴ እንዲለኝ
አደርጋለው››ይሄንን ስላሰበ ብቻ ውስጡ በደስታ ተፍነከነከ..ቤት ሲደርሱ እውነትም እንዳለችው ቆንጆ ምሳ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው፡፡እየተጎራረሱ በሉ፡፡ከምግብ በኃላ ብና ተፈላላቸው..እሷ ሁለት ሲኒ እሱ አንድ ሲና ጠጡና ተጠናቀቀ፡፡
‹‹እዚሁ ልንገራት ወይስ ይዣት ወጣ ልበልና ዘና ያለ ቦታ ወስጄ ዘና ባለ ስሜት ላይ ከሆነች በኃላ ልንገራት ››እያለ ሲወዛገብ ቆየና‹‹እ…ፕሮግራማችን እንዴት ነው….?ወጣ እንበል ወይስ እዚሁ ነው የምንቆየው?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አይ…ወጣ እንላለን..ሱፐርማርኬት ወጥቼ መሸማመት አለብኝ..መጠነኛ ድግስ ደግሳለው፣ማታ እንግዳ አለብኝ››
ንግግሯ ግራ አጋባውም.. ደነገጠም፡፡
‹‹የማታ እንግዳ ምን አይነት ነው?›› our
‹‹አንተም አለህበት…ዛሬ እዚህ ነው አይደል የምታድረው?››
እሷ ጋር እንዲያድር ስለጠየቀችው ደስ ብሏታል ..ግን እንግዳውስ…?ለመሆኑ ማን ነው
…?ሴት ነው ወንድ?፡፡‹‹እሺ ..እዚህ ነው የማድረው…ግን እንግዳውስ?››
‹‹እንግዲህ እሱን ከመጣ በኃላ ነው የምናውቀው…ልደር ካለ ግን እምቢ ማደር አትችልም የምለው አይነት ሰው አይደለም››በማለት ግራ አጋቢ መልስ ሰጠችው፡፡መልሷ ይብልጥ ቁርጠት ለቀቀበት…ይሄኔ ከመስሪያ ቤቷ ባለደረቦች አንዱ ነው….ሀለቃዋ ይሆን እንዴ…?ቢሆንስ ልደር ስላለ እንዴት እሺ ልትለው ትችላለች..?››ወይ ሴቶች ምን አይነት ቅኔ የሆኑ ፍጡሮች እንደሆኑ ሁሌ እንደደነቀው ነው፡፡ወንድም ሴትም በአንድ ላይ ሰው ተብሎ

መፈረጁ  አግባብ  አይደለም….አስተሳሰባችን  እምነትና  ፍላጎታችን  ምኑም  እኮ አይገናኝም››ሲል በውስጡ አብሰለሰለና..ነገሮች እስኪደርሱ ጠብቆ ለማየት ወሰነ…
‹‹ከዛ በፊ የተመቻቸ ጊዜ ካገኘው ነግራታለሁ…እንደውም ከማታው ፕሮግራሞ በፊት የእኔን ሀሳብ መስማት አለባት››የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ‹‹በቃ እንሂዳ››አላት፡፡
‹‹እሺ፣ተነስ ብላ ቦርሳዋን አንጠለጠለችና ተነሳች..ተያይዘው ወጡ ..ያለችው ሱፐር ማርኬት ይዛው ከገባች በኃላ ምትፈልገውን ነገሮች ሁሉ ተገዝተው በመኪናው ከተጫኑ በኃላ.. ማኪያቶ እንጠጣ ብሎ አንድ ፀጥተኛ ካፌ ይዞት ገባና..ፊት ለፊት እንደተቀመጡ እንደምንም እራሱን አጠንክሮ ወደነጥብ መንደርደር ጀመረ
‹‹ለምን ወደውጭ እንደሄድኩ ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹ሁለተኛ ዲግሪህን ለመማር ነዋ››
‹‹አይ ያማ ሽፋን ነው….እውነተኛ ምክንያቴን አንቺም በደንብ ታውቂዋለሽ..ወደውጭ የሄድኩት ባንቺ ተበሳጭቼ ነው፡፡››
‹‹አንተን ለማበሳጨት ብዬ ግን ምንም ያደረኩት ነገር የለም››
‹‹እሱን ማግባት አልነበረብሽም››
‹‹ለምን …ታዲያ አንተን ወንድሜን ማግባት ነበረብኝ?››
‹‹ምን ችግር አለው?እርግጥ እንደወንድምና እህት አንድቤት አድገናል..ግን የስጋ ትስስር አልነበረንም››


በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ‹‹በእውነት እምቢ ብትለን ምንድነው የምናደርገው?›ወ.ሮ ስንዱ በተሰበረ ድምፅ ባላቸውን ጠየቁ፡፡
አቶ ኃይለልኡልም እጅ በሰጠ ድምፅ‹‹አንተ ምን ብናደርግ ትመክረናለህ?››ሲሉ እሱኑ መልሰው ጠየቁት፡፡
‹‹ይሄውላችሁ እንደእኔ እንደእኔ በፀሎት ወደቤት መመለስ ያለባት በእናንተ ላይ የነበራት ቅሬታ ሙሉ በሙሉ ተቀርፎ…ሁሉን ነገር በራሷ መንገድ አረጋግጣና ፈቅዳ…ደስ ብሎት ነው
…ይሄውላችሁ አሁን አብዛኛውን አስቸጋሪ የነበረውን መንገድ ተጉዛችኃላ …እስኪ አስቡት ከአስራአምስተ ቀን በፊት ወደቢሾፍቱ ስንሄድ አንድ መኪና ውስጥ መቀመጥ እራሱ የሚቀፋችሁ ሰዎች ነበራችሁ፣ትዝ ይላችኃላ ጋሼ ገቢና ነበር የተቀመጥከው…አሁንስ ይሄው በደስታ ጎን ለጎን በራሳችሁ ፍቃድ ተቀምጣችሁ እርስ በርስ ተጣብቃችሁ የደስታ ወሬ እያወራችሁ ትሳሳቃላችሁ..ከባዱ ነገር እናንተን እዚህ ስሜት ላይ ማድረስ ነበር…ከአሁን ወዲህ ያለው ይሄንን ግንኙነት መሰረት እንዲይዝና ስር እንዲሰድ ማድረግ ብቻ ነው… ያ ደግሞ ቀላል ነው…ቢያንስ 15 ቀን መታገስ ያቅታችኃላ….?፡፡››
‹‹እና ባለችበት ትቀመጥ እያልክ ነው…?ያለችበት ሁኔታ… እቤቱ የሰዎቹ ኑሮ ምኑም አይመቻትም እኮ…››
ከቀናት በፊት ስላለችበት ቤት ሲጠይቃት ያለችው ነገር ትዝ አለውና ፈገግ አለ፡፡

‹‹እውነቴን ነው..እርግጥ ሽማግሌው በጣም ጥሩና ደግ ሰው ናቸው….ቢሆንም ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው..ልጄ ከቤት ስትወጣም ደህና ብር እንኳን ይዛ አልወጣችም››
‹‹አይዞችሁ እስከዛሬ ድምጻን አጥፍታ ኖረች ማለት በጣም ቢመቻት ነው….ደግሞ እንዳላችሁ ባይመቻትም ለ15 ቀን ምንም አትሆንም፡፡አለመመቸትን ማጣጣም በቀጣይ ለሚመጣ መመቸት መደላደል መፍጠር ነው፡፡››
‹‹እሺ ቢያንስ እንሄድና ከሩቅም ቢሆንም እንያት››
‹‹እንደእሱ ይቻላል››አላና ያጠፋውን የመኪና ሞተር አስነሳው፡፡
ሰለሞን መኪናውን ነዳና  ከተካ መኪናው ፊት ለፊት አቆመ….ተካ መኪናውን ከፊቷ ወጣን ወደእነሱ መጣ ..ሰለሞን የገቢናው በራፍ ከፈተለት ……ገባና ቁጭ አለ››
ወደኃላ ዞረና…..‹‹አሁንም ውስጥ ነች…እንዴት ነው ምናደረገው? ››
‹‹ቆይ እስኪ ተረጋጋ ስትወጣ እንያት….››ሁሉም አይናቸውን የግቢው መውጫ መግቢያ ላይ ተከሉ….በርከት ያሉ ሴቶች ሲወጡ ሲገቡ ይታያል፣››
‹‹ምንድነው ብዙ ሰዎች ይታያሉ… ችግር አለ እንዴ?››አቶ ኃይለ ልኡል ጠየቁ፡፡
‹‹አይ ጌታዬ ችግር የለም… እኔም በመጀመሪያ ግራ ገብቶኝ ነበር…ስጠይቅ ግን ፣ሰዎቹ ነገ የማሪያም ፅዋ ማህበር አለባቸው ..የድግሱ ስራ ለማገዝ የመጡ ጎራቤቶች ናቸው››
‹‹እ …እንደዛ ነው….››በፀሎት ወጥታ ከሩቅ ለማየት ከአንድ ሰዓት በላይ በትዕግስት መጠበቅ ነበረባቸው….ግቢ ውስጥ ካለ የማንጎ ዛፍ ስር ቆማ ከአቶ ለሜቻ ጋር እየተሳሳቀች ስታወራ ነበር የተመለከቱት…ሁለቱም ወላጆች ሄደው ልጃቸው ላይ ለመጠምጠም የሚተናነቃቸውን ስሜት በመከራ ነበር የተቆጠጠሩት፡፡ሁለቱም ስሜታዊ ሆነው እንባ አውጥተው እስከማልቀስ ደርሰው ነበር፡፡
‹‹አሁን በቃ ይበቃናል…ከዚህ በላይ እዚህ ከቆየን  ራሳችንን ማጋለጥ ይሆናል…ድንገት እዚህ እንዳለች እንደደረስንባት ካወቀች….ቦታ ለመቀየር ታስብና ዳግመኛ አድራሻዋን ትሰውርብን ይሆናል፡፡››ሰለሞን ነው የተናገረው፡፡
‹‹አዎ ትክክለ ነህ….እንዴት ነው ምናደርገው ታዲያ? እሱ እዚሁ ይጠብቃት አይደል…?››.

‹‹አይ ምንም ጠባቂ አያስፈልግም…ባይሆን በየቀኑ እየመጣ ለተወሰነ ደቂቃ ሰላም መሆኗን ብቻ ካረጋገጠ ይበቃል፣አሁን ሁላችንም ነን አካባቢውን መልቀቅ ያለብን፡፡››ሰለሞን ቁርጥ ያለ ውሳኔውን አስተላለፈ…የተቃወመው ወይም የተከራከረው አልነበረም፡፡
‹‹እሺ ይሁን …..በቃ ተካ አንተም ወደቤትህ ሄደህ እረፍ …ነገ ደውልልሀለው››ብለው አሰናበቱት…‹‹እሺ ጌታዬ እንዳሉ››ብሎ ገቢናውን ለቆ ወረደና ወደአቆማት መኪና ተንቀሳቀሰ…..ሰለሞንም ባልና ሚስቱን ይዞ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተፈተለከ…..

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
:
:
#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ተካ አቶ ኃይለልኡል ባዘዙት መሰረት ሽጉጡን ሙሉ ጥይት ሞልቶ ወገቡ ላይ ከሸጎጠ በኃላ አጉሊ መሳሪያ ያዘና  ማንን ሳያስከትል ቀጥታ መኪና ውስጥ ገብቶ ወደ ቃሊቲ ነዳው….የሰውዬውን ጥርጣሬ ምንም አልተዋጠለትም…‹‹ልጅቷ ስንት አማራጭ እያላት እንዴት እዛ ጭንቁርቁስ ቤት ከጭርቁስቁስ ሰዎች ጋር ለመቆየት ታስባለች? ››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ሊዋጥለት አልቻም…፡፡

በፀሎት ከጠፋችበት ቀን አንስቶ በመላ ሀገሪቱ ፍላጋ የተሰማሩትን በመቶ የሚቆጠሩ ግለሰቦችን የሚመራው ..መረጃ የሚቀበለው አዲስ ቦታ ስምሪት የሚሰጠው እሱ ነው፡፡እና የእሱ እቅድ የሆነ ቦታ መኖሯን በሆነ መንገድ ቀድሞ ቢደርስበት እንደምንም ብሎ የራሱ ሰው በሚስጥር እንዲያገኛት አድርጎ በእጅ አዙር 5 ሚሊዬኑን የሽልማት ገንዘብ ለመቀባበል አቅዶ ከልቡ እየሰራ ነበር...እርግጥ እንደዚህ እያደረገ መሆኑን ቀድመው ቢደርሱበት ያለምንም ማቅማማት ግንባሩን በጥይት እንደሚነድሉት እርግጠኛ ነው…ግን በህይወት የተሻለ ነገር ማግኘት ሪስክ መውሰድ የግድ እንደሆነ የሚያምን ስለሆነ ነገሩን ልክ እንደቁማር ነው ያየው..‹‹ወይ በላለሁ..ወይ ደግሞ እበላለው››ብሎ ነበር ውሳኔ ላይ ደርሶ በተግባር ሲንቀሳቀስ የከረመው፡፡…አሁን ሰውዬው እንደሚሉት ልጅቷ የገመቱት ቦታ የምትገኝ ከሆነ ያ ሁ እቅዱ ውሀ በላው ማለት ነው፡፡ቦታውን ራሳቸው ቀድመው አውቀው ስለነገሩት ሽልማት የሚሰጡበት ምንም ምክንያት የለም….መኪናውን ወደእዛ ሲያሽከረክር በውስጡ በፀሎት የተባለው ቤት በፍፅም እንዳትገኝ እየፀለየ ነበር፡፡እንደደረሰ ከመንገድ ማዶ አስፓልት ጠርዝ ላይ መኪናውን ፓርክ አደረገና የመኪናው መስኮት በከፊል ከፍቶ ማጊሊያ መነፅሩን ወደእነ አቶ ለሜቻ ግቢ አነጣጠረና ገቢ ወጪውን መመልከትና በመሀከልም የተለየ ነገር ያገኘ ሲመስለው በሞባይሉ ፎቶ ማንሳት ጀመረ…
ስራ የጀመረው ከጥዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ቢሆንም እሰከ 10 ሰዓት ሁለት ሶስት ጊዜ አሮጊት ሴት ስትወጣ ስትገባ ከማየት ውጭ በግቢው ውስጥ አይን የሚስብ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም…ሰዓቱ እየረዘመ ሲሄድ ተስፋ እየቆረጠና እየተሰላቸ መጣ…ለዛሬ ይበቃኛል ብሎ 11 ሰዓት ላይ አካባቢውን ለቆ ወደቤቱ ሄደ ..
በማግስቱ በጥዋት ማለዳ አንድ ሰዓት ላይ ነበር የመጣው፣እና ሁለት ሰዓት ላይ የሚፈልገውን አገኘ ..ደጋግሞ ፎቶ አነሳው…በቤቱ አንድ ሴት ልጅ ብቻ እንዳላቸው አጣርቷል ..አሁን እየገቡ እየወጡ ያሉት ግን በተቀራራቢ እድሜ ላይ የሚገኙ ሁለት ወጣቶች ናቸው፡፡አንደኛዋ የቤቱ ልጅ እንደሆነች እርግጠኛ ነው…ሁለተኛዋ ግን የሚፈልጋት የባለፀጋው ቅምጥል ልጅ ትሁን አትሁን መለየት አልቻለም…የለበሰችው ልብስ የተለመደ አይነት ነው..በዛ ላይ ፊቷን ጭንቅላቷን ጭምር በሻርፕ ሸፍናለች…ዝም ብሎ ከመኪናው በመውረድና በእግሩ ወደ አጥሩ በመጠጋት ከቅርብ ርቀት በርከት ያለ ፎቶ አነሳና ለአቶ ኃይለ ልኡል ላከላቸው፡፡

አቶ ኃይለልኡል በዚህ ጊዜ ከባለቤታቸው ጋር በሰለሞን በሚሾፈር መኪና ከቢሾፍቱ ወደአዲስ አበባ እየተመለሱ ነበር፡፡ስልካቸው ድምፅ ሲያሰማ ከኪሳቸው አወጡና ተመለከቱት..መልዕክት መሆኑን ሲያዩ ከፈቱት…አይናቸው ተጉረጠረጠ….
‹‹እራሷ ነች ..ልጄ እራሷ ነች….ከጎናቸው ያለችው ሚሳታቸው ላይ ተጠመጠሙና ጉንጮቾን አገላብጠው ይስሙ ጀመር››
‹‹እንዴ ኃይሌ ምን ተፈጠረ..?ምን ተገኘ..አረ ንገረኝ?››
‹‹ይሄውልሽ..እንቺ እይው..ፊቷን ብትሸፋፈንም እራሷ ነች፡፡››ወይዘሮ ስንዱ ስልኩን ከባላቸው እጅ ተቀበሉና አፍጥጠው ተመለከቱ…..ከባላቸው በበለጠ በመደነቅ ኡኡ.አሉ…መኪናዋን በእልልታ አደባላለቁት…ሰለሞን የነገሩ ውል ስላልገባው መሪውን ጠመዘዘና የመንገዱን ዳር አስይዞ መኪናዋን አቆማት…በራፉን ከፍተው ወረዱ….እሱም ተከትሏቸው ወረደ‹‹አረ ለእኔም ንገሩኝ ምንድነው? እንዲህ የሚያስፈነጥዝ ደስታ፡፡››
‹‹ልጃችን የት እንዳለች አወቅን..እያት ተመልከት››ስልኩን ከሚስታቸው ተቀበሉና ለሰለሞን አቀበሉት..አንድ ፊቷ በቅጡ የማይታይ ወጣት ፎቶ ነው…ግን በፀሎት እንደሆነች ወዲያው ነው ያወቃት..ሙሉ ፊቷን ሳያይ እሷ እንደሆነች አንዴት እንዳወቀ አልገባውም…››
‹‹አየህ …ልጃችን እራሷ ነች…ሰው እንዳይለያት ነው ፊቷን የሸፋፈነችው……››
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለችው?››ጠየቀ ሰሎሞን፡፡
‹‹የት እዳለች ቆይ ነግራችኃላው››ብለው ስልኩን ተቀበሉና ደወሉ
‹‹ሄሎ….ፎቶው ደርሶኛል፡፡››
‹‹አዎ ሳስበው እሷ ትመስለኛለች››
‹‹አዎ እሷ እራሷነች…ከቦታው እንዳትንቀሳቀስ..እዛው ጠብቀን…ከቢሾፍቱ እየተመለስን ስለሆነ ከ15 ደቂቃ በኃላ ያለህበት እንደርሳለን››
‹‹ወጥታ ከሄደችስ…?ላስቁማት››
‹‹አይ..ልጄን ቀጥታ እኔው ነኝ የማገኛት..እንዳታስቆማት ትደነግጥብኛለች…ከቤት ከወጣች ዝም ብለህ በርቀት እየተከታተልክ ያለችበትን ታሳውቀኛለህ፡››

‹‹እሺ..ጌታዬ እንዳሉት አደርጋለው››
‹‹ጎበዝ ..እንዳስደሰትከኝ አስደስትሀለው…ቆንጆ ጉርሻ ይጠብቅሀል ››
‹‹እሺ ጌታዬ››ስልኩን ዘጉና‹‹በሉ ጊዜ አናባክን ..ግቡና እንሂድ››
‹‹እንዴ የት አንዳለች ንገረን እንጂ……?››ወ.ሮ ስንዱ ጠየቁ
‹‹ስንድ ልጃችን ሰዎቹ ጋር ነው ያለችው….››
‹‹የትኞቹ ሰዎች››
‹‹እነአቶ ለሜቻ ጋር..ማለቴ የልብ ለጋሾ ቤተሰብ ጋር ነው ያለችው››
‹‹ወይ ጉዴ….አሁን ምንድነው የምናደርገው?››እያሉ ወደመኪናው ገቡ፡፡ አቶ ኃይለልኡልም ተከትለዋቸው ገቡ….ሰለሞን በሰማው ያልተጠበቀ ነገር ግራ እንደተጋባና ምን ማድረግ እንዳለበት እያሰላሰለ ገቢና ገባ፡፡ መኪናውን አንቀሳቀሳት…ባልና ሚስቶቹ በደስታ ሰክረው እሱን ከቁብ ሳይቆጥሩት እርስ በርስ በፈንጠዝያ ሲጎሻሸምና ሲሳሳሙ እሱ ምን ማድረግ እንዳለበትና ይሄንን ያለጊዜው ያጋጠመውን ነገር እንዴት እንደሚፈታ እያሰላሰለ ነበር የሚነዳው….
አቃቂ አቶ ለሜቻ ቤት ለመድረስ 500 ሜትር ያህል ሲቀራቸው የመኪናውን መሪ ወደግራ ጠመዘዘና ፊት ለፊት ከሚታየው ሆቴል ይዞቸው ገባ..ባልና ሚስቶቹ በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሰለሞን…ምን እያደረክ ነው?››አቶ ኃይለልኡል ጠየቁ፡፡
‹መነጋገር አለብን››
‹‹ስለምን?››
‹‹አሁን ልጃቹህ ጋር ከመሄዳችሁ በፊት አረፍ ብለን መነጋገር አለብን››
‹‹ምን መነጋገር ያስፈልጋል…?በቃ እኔና እናቷ ሄደን ልጃችንን ወደቤት ይዘን እንሄዳለን….እንደምታየው  አሁን  ሁሉ  ነገር  ውብ  እና  የተስተካለከለ  ነው..አይዞህ

አታስብ…ከንተጋር  ያለንን  ነገር  እንቀጥላለን..ከሶስት  ቀን  በኃላም  ወደአልከው  ቦታ ትወስደናለህ››
መኪናውን  አቆመና  ሞተሩን  አጥፍቶ  ወደኃላ  ዞረ..ፊት  ለፊት  እያያቸው‹‹ይሄ  ነገር እንደምታስብት ቀላል ይመስላችኃላ?››
‹‹ማለት?››
‹‹አሁን ያለችበት ቤት ሄደችሁ በማንኳኳት..ነይ ልጄ በቃ አግኝተንሻል አሁን ወደቤትሽ ተመለሺ ብትሏት ..እሺ ብላ በደስታ ዘላ የምትጠመጠምባችሁ ይመስላችኃላ…እምቢ መሄድ አልፈልግም ብትል ምን ታደርጋላችሁ ?በግድ በጎረምሳ አሳዝላችሁ መኪና ውስጥ በመክተት ወደቤት ትወስዷታላችሁ….?ከዛስ..?አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፋችሁባት በራፍ ላይ ሁለት ጠብደል ጠባቂ ታቆማላችሁ?እስኪ ንገሩኝ ምንድነው የምደርጉት?››


ጥቅም አልባ ነው። ለፍቅረኛ ወይም ለትዳር አጋር የሚኖር አክብሮት ጥልቅና ሩቅ መሆን አለበት። ከልብ የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነፍስም የተጨለፈ መሆን አለበት።ሚስት ለባሏ ሚስት ብቻ አይደለችም..የሴት ጓደኛ…የእናት ምትክ ዘመድ ጭምር መሆን አለባት..ባልም ለሚስቱ ወንድ ጓደኛ..ከዛም አልፎ የአባት ምትክ ዘመድ መሆን አለበት፡፡የማወራው ግልፅ ነው አይደል?››
‹‹አዎ ..በጣም ግልፅ ነው..ቀጥል››

ትንፋሽ ወስዶ ከንፈሩን በምራቁ አረጠበና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ‹‹…ከቤት ወጥታችሁ ስትለያዩ የሚኖር ሽኝት እና ከውጭ ውላችሁ ስትመለሱ እርስ በርስ የሚኖር የሞቀ አቀበል በጣም ወሳኝ ኩነት ነው።ተሳሳሞ ደህና ዋል..ደህና ዋይ ተባብሎ መለያየት እና ሲገናኙ እንዴት ዋልሽ…?እንዴት ዋልክ? ተባብሎ በናፍቆት መሳሳም በመሀከል ያለን ግንኙነት ያደረጃል ፍቅርም ግለቱን ጠብቆ እንዲጓዝ ያግዛል።በመጨረሻው ሚቻላችሁ ከሆነ እቤት ከገባችሁ  በኃላ  ለተወሰነ  ሰዓት  ስልክ  የሚጠፋበት  እና  ቲቨ  የሚዘጋበት  ልዩ የሆነ የቤተሠብ የጋራ የመጫወቻና የመወያያ ሰአት ቢኖር እንደቤተሠብ ለሚኖር መስተጋብር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
‹እና ሌላው ልጃችሁ ላይ ያላችሁ አቋም ትልቅ ማስተካከያ ሊደረግበት ይገባል፡፡››
‹‹ማለት?››
‹‹በፀሎት ነገሮች ተስተካክለው ወደቤት ስትመለስ..ለምሳሌ ስትወጣ ስትገባ በጋርድ እንድትጠበቅና እንድታጀብ ማድረግ አይገባችሁም..እንደማንኛውም ሰው በነፃነት ከፈለገችው ሰው ጋር ወጥታ ከፈለገችው ጋር የመመለስ መብት ሊኖራት ይገባል፡፡››
‹‹ሰለሞን እዚህ ላይ አንድ ያልገባህ ነገር አለ…እኔ እኮ ልጄን በጋርድ ማስጠብቀው ወድጄ አይደለም…..ልጄ ልብ በሽተኛ ነኝ..የልብ ንቅለ ተከላ ተደርጎላታል …በጣም ጥንቃቄ የምትፈልግ ልጅ ነች..ድንገት መንገድ ላይ ወድቃ አጉል እንዳትሆንብኝ ስለምሰጋ ነው ዘወትር ሰዎች በዙሪያዋ እንዲሆኑ የማደርገው፡፡››ሲሉ ተቃውሞቸውን ያሰሙት አቶ ኃይለልኡል ናቸው

‹‹ቢሆንም ለዛ መፍትሄው ያ አይደለም….ይሄ የልጅቷን ነፃነት ከመንፈጉም በላይ በራስ የመተማመን ችሎታዋን በጣም ይጎዳዋል…በየሄደችበት በሰው መጠበቅ የመታፈን ስሜት እንዲሰማት ነው የሚያደርጋት፣እና የእዛ ውጤት ደግሞ እንዲህ አሁን እንዳደረገችው ራሷን ነፃ ለማውጣት አላስፈላጊ ጣጣ ውስጥ እንድትገባ ትገደዳለች››
‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ …ግን ያው ነፃ ትሁን… ብቻዋን ትንቀሳቀስ ብዬ ከፈቀድኩላት አንዳንድ አላስፈላጊ ቦታዎች ትሄድና የማይሆን ነገር ትሰራለች፡፡››
‹‹ለምሳሌ የት?››
‹‹ይሄውልህ የልብ ንቅለ ተከላ ሲደረግላት ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦች እዚሁ አዲስ አበባ አቃቂ አካባቢ ነው የሚኖሩት ..ልጄ አሁን አሁን ተወች እንጂ በፊት ሰሞን ቀንና ሌት እዛ ካልወሰድከኝ እያለች ታስቸግረኝ ነበር፣..እኛ ደግሞ ከልጅቷ አባት ጋር ስንስማማ በምንም አይነት ከእኛ በአካል መገናኘት እንደማይፈልጉ ነው ያነገሩን..እሷ ቤታቸው ሄዳ ቢያገኟት ልጃቸውን ስልምታስታውሳቸው ሀዘናቸውን ክፉኛ ትቀሰቅሳባቸዋለች.. እንደዛ አይነት ውለታ የዋሉልኝን ሰውዬ ደግሞ የማይፈልጉትን ነገር ማድረግ ላሳዝናቸው አልፈልግም..አንድ ለዛ ነው የማስጠብቃት››ንግግራቸውን እየተናገሩ ሳለ የሆነ እስከዛሬ ያላሰብት ገራሚ ሀሳብ በአእምሯቸው ብልጭ አለ….እንዴት እሰከዛሬ ትዝ ሊላቸው እንዳልቻለ ግራ ገባቸው‹‹ልጄ እነሱ ጋር ሄዳ ቢሆንስ?››ሀሳቡን በውስጣቸው አፍነው ያዙት፡፡
‹‹የልጃችሁን ደስተኝነትና ሳቅ የምትፈልጉ ከሆነ ለችግሮች ሁሉ ሌላ መፍትሄ አበጁላቸው..ደግሞ ለበፀሎት በግልፅ ነገሮችን ቢያስረዶት ይገባታል…ብስልና አስተዋይ የ22 ዓመት ወጣት ነች….ይልቅ እናንተ  በመሀከላችሁ ያለውን ችግር ፈታችሁ ሰላም ከሆናችሁና ስትወጣ ስትገባ የሚከታተላት ሰው መመደብ ካቆማችሁ የልጃችሁን ደስታና ሳቅ መመለስ ብቻ ሳይሆን መቼም መልሳችሁ አታጦትም››
ወ.ሮ ስንዱ መለሱ ‹‹እሺ እንዳልክ እናደርጋለን….ኃይሌ እንዲህ ማድረግ ያቅተናል እንዴ?››
‹‹አረ አያቅተንም..ችግር የለውም ሁሉን ነገር እኔ አስተካክለዋልው..አሁን ከፈቀድክልኝ ወደካማፓኒው አንድ አጭር ስልክ መደወል አለብኝ..ከባድ የስራ ጉዳይ ነበረ ..ምን እንዳደረሱት ልጠይቃቸው፡፡››

‹‹ችግር  የለም..በቃ  ጨርሰናል..አሁን  ለጥዋት  ጉዙ  እቃችንን  መሸካከፍ  መጀመር እንችላለን፡፡››
‹‹ጥሩ…››ብለው ቀድመው ከመቀመጫቸው ተነሱና  ወደክፍላቸው በመሄድ ስልካቸውን ካስቀመጡበት አንስትው በጀርባ በኩል ባለው በር ከቤት ወጡ….  ስልክ ደወሉ…
‹‹ስማ አቃቂ ለልጄ ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦችን ታውቃቸወላህ አይደል..?››
‹‹አዎ አውቀዋለው››
‹‹አሁኑኑ እዛ ሂድና ቀስ ብለህ ማንም ሳያይህ ወደቤታቸው የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው ተከታተል…ከተቻለህ ሁሉንም ፎቶ አንሳ››
‹‹እሺ….ግን በቀጥታ ምን ለማጣራት ነው የምንፈልገው…?ነገሩን ማወቄ ስራዬን ያቀልልኛል››
‹‹አዎ….ምን መሰለህ..ለማንም እንዳትናገር..ልጄ ምን አልባት እዛ ቤት ተደብቃ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል…እና ከአሁኑ ጀምረህ በቃ እስክልህ ደረስ እንዳልኩህ ተከታተለልኝ…እሷን በተመለከተ የሆነ ትንሽም ቢሆን ፍንጭ ካገኘህ ወዲያው አሳውቀኝ፡፡››
‹‹ስልኩን ዘጉና ኪሳቸው ውስጥ ከተው ወደውስጥ ተመለሱ …ወ.ሮ ስንዱ አልጋቸው ላይ አረፍ ብለው አገኞቸው ፡፡በራፉን ዘጉን የራሳቸውን አልጋ ትተው ወደባለቤታቸው ሄዱና ከጎናቸው ተቀመጡ፡

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

‹‹አግብተሀል እንዴ?››
ድንገት ከርዕሳቸው ውጭ የሆነ ጥያቄ ስለጠየቁት ድንግርግር አለው፡፡
‹‹ለምን መሰለህ የጠየቅኩህ..?እንዲሁ ሳስበው አንተን ያገባች ሴት በጣም እድለኛ ትመስለኛለች….፡፡››
‹‹ምን አልባት ልትሆን ትችላለች ..እስከአሁን ግን አለገባሁምም አረ እንደውም ፍቅረኛም የለኝም››
ፈገግ አሉ….‹‹ሸክላ ሰሪ በገል ይበላልል›› አሉ…ብዙ ማወቅም እኮ መጥፎ ነው››
‹‹እንዴት?››
‹‹የምትፈልገውን ሁሉ የምታሟላ ሴት ለማግኘት በጣም ይከብድሀላ…ሁሉን ነገር አሟልታ ጥንቅቅ ያለች ሴት አታገኝም..በዛ እርግጠኛ ሆኜ ልነግርህ እችላለው…ግን ምትወድህና ምትወዳት ልጅ ሆና እራሷን ለመለወጥና ለማሻሻል የምትጥር ከሆነ በቂ ነው…አንተ ጎበዝ አንደበተ ርትኡ ባለሞያ ስለሆንክ መስመር ታስይዛታለህ››
እንዴት ብሎ መምከሩን ትቶ ተመካሪ እንደሆነ አልገባውም፡፡‹‹እሺ…የእናንተን ጉዳይ ከዳር ካደረስኩ በኃላ አስብበታለው….ምን አልባት እናንተ ትሆናላችሁ የምትድሩኝ…››
‹‹ለዛውም ድል ባለ ድግስ ነዋ››

‹‹እሺ..አሁን ይበቃናል…የምሳ ሰዓት ስለደረሰ ወደሳሎን እንሂድ››
‹‹አዎ ..ይበቃናል..ይሄኔ ኃይሌ ብቻውን ደብሮታል››
ፈገግ እለ ….. ከመቀመጫው ተነሳና ወደውጭ መራመድ ጀመረ…ወ.ሮ ስንዱም ተከተሉት፡፡


ከሳምንት በኃላ……..
በቢሾፍቱ ቆይታቸው በባልና ሚስቶቹ መካከል አስገራሚ የሚባል ለውጥ ነው የታየው፡፡ቢያንስ እረስ በርስ በመሀከላቸው ያለ ንግግር የጥሩ ጓደኛሞች መምሰል ከጀመረ ሰነባብቷል…ይሄ ለውጥ ሰለሞንን ይበልጥ እንዲበረታታ እና ሙሉ ኃይሉን ስራው ላይ እንዲያውል አግዞታል፡፡
‹‹እንግዲህ ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው ነገ ወደአዲስአባ እንመለሳለን…ሶስት ቀን እረፍት እንወስድና ምን አልባትም ለመጨረሻ ጊዜ ለሌላ 15 ቀን ወደሌላ መዝናኛ ቦታ እንሄዳለን፡፡በቀጣይ የምንሄድበት ከዚህ የተለየ ነው…ሌሎች ሰዎች ማለቴ ጎብኚዎች የሚኖሩበት ቦታ ነው…እዛ ምንሄደው ነፃ ሆናችሁ እንድትዝናኑ ነው..እኔም አብሬያችሁ ኖራለው ግን ነፃ ናችሁ…እዚህ እንዳለው ብዙ ማዕቀብና እገዳ የለም…ስልካችሁን እንደፈለጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ.ሰሻል ሚዲያ ቴሌቪዝን ማየት ትችላላችሁ …ከሰው መተዋወቅና መገባበዝ ትችላላችሁ..አንድ ማትችሉት ነገር መለያየት ብቻ ነው….ለ15 ቀን የምታደርጉትን ሁሉ አብራችሁ ታደርጋላችሁ..››
‹‹ገባን ..ያልከው 15 ቀን የመጨረሻችን ይመስለኛል››
አዎ እኔም እንደዛ ነው የማስበው..በእውነት እዚህ ባሳለፍነው 15 ቀን ሁለታችሁም ካሰብኩት በላይ ከፍተኛ ጥረት አድርጋችኃል …እናም ትልቅ ለውጥ እንዳመጣችሁም ይሰማኛል…እናንሰትስ ምን ይሰማችኃል…?አቶ ኃይለልኡል እስኪ ከእርሶ ልጀምር፡፡

‹‹እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ…እስከዛሬ ሚሲቴን ብቻ የምበድል መስሎ ነበር የሚሰማኝ ለካ ልጄንም ራሴንም ጭምር ነበር እያሰቃየው የነበረው….እውነት አንተና ልጄ የእድሜ ልክ ባለውለታዎቼ ናችሁ››
ፊቱን ወደወ.ሮ ስንዱ ዞረና ተመሳሳዩን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
‹‹አዎ…ኃይሌ እንዳለው ደስተኛ ነን…በፊት ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ገዳም ገብቼ መመልኮስ ነበር ምኞቴ ..ምክንያቱም ህይወት አስጠልታኝ ነበር…ቤቴም ኑሮዬም ይቀፈኝ ነበር…ጨለማ የሆነ ሀዘን ውስጥ ገብቼ ነበር..አንድ ያለችኝ አስደሳች ነገር ልጄ ብቼ ነበረች
..እሷም ከጠፋች በኃላ ደግሞ ነገሮች ለእኔ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው…አሁን ግን እንደዛ አይደለም የሚሰማኝ….ደግመኛ እንደመወለድ አይነት የመታደስ ስሜት እየተሰማኝ ነው…የመከራና የሀዘን ቆዳዬን ከላዬ ገፍፌ ጥዬ በአዲስ ተስፋና ፍቅር ተወልጄለሁ..አሁን ቤቴም ባሌም ይናፍቁኛል….ሃይሌን ከዚህ በፊት ለሆነው ሁሉ ይቅር ባዬዋለሁ.. እሱም ይቅር እንደለኝ ገምታለው፡፡››
ኃይለልኡል ተፈናጥረው ከመቀመጫቸው ተነሱና ሚስታቸው ላይ ተጠመጠሙ…ሁለቱም ተቃቅፈው መላቀስ ሲጀምሩ….ሰለሞንንም ስሜታዊ አደረጉት፡፡ተላቀው ወደቦታቸው ለመመለስ..ከ10 ደቂቃ በላይ ፈጅቶባቸዋል፡፡
ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ‹‹ጥሩ እንግዲህ… እዚህ ደረጃ ላይ ከደረስን አንዳንድ አጠቃላይ ስለሆኑ ነገሮች እናውራ፡፡ያው እናንተ በጋብቻ ውስጥ ረጅም እድሜ ስለአሰለፋችሁ ከእኔ የበለጠ ልምድ እንዳላችሁ አውቃለሁ....አሁን የማወራው የምታውቁትን ነገር ነው…ላሳውቃችሁ ሳይሆን ላስታውሳችሁ ፈልጌ ነው››
‹‹ጥሩ እየሰማንህ ነው ….ቀጥል››
‹‹እንግዲህ እቤት የባል ብቻ አይደለም፣የሚስትም ብቻ አይደለም፣ እቤት የልጆችም ጭምር ነው።በዚህ ምክንያት ለሁሉም ኑዎሪዎች እኩል ምቹ መሆን አለበት።እናንተ ከአሁን ወዲያ በቤታችሁ የሚዘረጋው ስርአት ህግና የአኗኗር ዘየ..ሶስታችሁን በእኩል ከግምት ያስገባ መሆን አለበት፡፡ሌላው ንብረታችሁን በተመለከተ የእኔ የሚለውን ቃል ከመጠቀም የእኛ የሚለውን የጋራ ቃል መጠቀም የተሻለ ነው።የእኛ ቲቪ..የእኛ ቤት...የእኛ ጊቢ የእኛ ፋብሪካ፣ብሎ የመናገር ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል።እያንዳንድ የቤተሰብ አባል የእዛ ቤተሠብ

የአክሰዬን ባለድርሻ ናቸው።ያንን ደግሞ በተግባርም በስነ-ልቦናም መረጋገጥ አለበት።በቤተሰብ ቢዝነስ ውስጥ ስለሚፈጠር ዋና ዋና ክስተት ስለትርፍም ሆነ ኪሳራ ሁሉም ሰው በተገቢው መጠን መረጃ ሊኖረው ይገባል….ሁሉንም ኃላፊነት አንዱ አካል ብቻ ጠቅልሎ መውሰድ የለበትም…እዚህ ላይ በተለይ አቶ ኃይለልኡል ብዙ ነገር ማስተካከል የሚጠበቅቦት ይመስለኛል››
‹‹ገብቶኛል..እሺ…አስተካክላለው፡፡››

‹‹ሌላውና ወሳኙ … የተለየ ችግር ከሌለ በስተቀር ባልና ሚስት መኝታ ክፍላቸውንም ሆነ አልጋቸውን መለየት የለበቸውም…በተጨማሪም ባልና ሚስት በምንም አይነት ሁኔታ ወደመኝታቸው ሲሄድ አኩርፈውና በውስጣቸው ተበሳጭተው ወይ ቂም ይዘው መሆን የለበትም።መኝታ ክፍል ለባለትዳሮች እንደቤተመቅደስ ነው መሆን ያለበት ። የሚሳሳሙበት... የሚተቃቀፉበት.... የሚዋደድበትና የሚፋቀሩበት ….ስለጋብቻቸው እና ስለልጆቻቸው ደህንነትና ሰላም የሚማከሩበትና የሚፀልዩበት የገመና መክተቻ ቦታቸው ነው መሆን ያለበት ። ስለዚህ ... ቅያሜያቸውን ሆነ ቅሬታቸውን ሳሎን ጨርሰው ለጭቅጭቃቸው መፍትሄ አበጅተውለት እና ይቅር ተባብለው ነው በሳቅና በፈገግታ ወደመኝታቸው መሄድ ያለባቸው። አዎ ወደመኝታ ክፍላቸው ሲያመሩ በፍፁም ሰላምና ፍቅርና መሆን አለበት...የበለጠ ለመፍቀር...የበለጠ ለማረፍና ..የበለጠ ለመታደስ ።ይሄ ሁለታችሁንም በእኩል ደረጃ የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡››
ሁቱም አንገታቸውን እላይ እታች በማነቃነቅ መስማማታቸውን ገለፁ

‹‹ሌላው በቤት ውስጥ አንደኛው ሌለኛውን ማገልገል አለበት...ማገልገል ማለት በፍፅም ፍቃደኝነትና ፍላጎት አንደኛው ሌላኛውን መርዳት ማለት ነው።ባል የቤቱ ንጉስ ከሆነ ሚስት ደግሞ ንግስት ነች ማለት ነው ልጆች ደግሞ ልኡላን ናቸው።ማንም ከማንም የበለጠ አስፈላጊ አይደለም...ማንም ከሌላኛው ያነሰ አይደለም።ለቤቱ ሙሉነትና ፍፁምነት ሁሉም የየራሱ ኃላፊነትና ድርሻ አለው።በፍቅርና በጋብቻ ህይወት ውስጥ እርስ በርስ ያለ መከባበር በጣም ወሳኝ ነው።አንድ ለሌላዎ ጥያቄዎችን አስተያየቶችን ሲኖሩት በትህትና እና ክብር በተሞላ ሁኔታ ጥያቄውን ማቅረብ አለብት።እርስ በርስ ያለ ግንኙነት የማስመስል መሆን የለበትም...እንግዳ ሲኖር የሚደረግ አርቴፊሻል የማስመሰል እንክብክቤ እና አክብሮት

20 last posts shown.