AWACH SACCOS Ltd.


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


ኅብረት ሥራ ማህበራችን የሚያከናውናቸው ተግባራት
የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት
አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
የትምህርት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
+251-11-557-97-98
+251-11-557-88-89
+251-11-557-98-99
+251-11-868-47-44
saccawach@gmail.com
https://www.facebook.com/AWACHSACCOS
@awachsaccos

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በቅርቡ የተገበረውን ሪፎርም አስመልክቶ ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በግራንድ ኤሊያና ሆቴል ውይይት አድርጓል።

ትግበራ ላይ የዋለው ሪፎርምን እና አንዳንድ በተቋሙ ውስጥ የተደረጉ የአሰራር ለውጦችን አስፈላጊነት ያስረዱት የኅብረት ስራ ማህበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ አዋጭ ከትንሽ ተነስቶ አሁን ላይ ከ380 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠር በመቻሉ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
አክለውም ሰራተኞች በተመደቡበት የስራ መስክ የአገልጋይነት መንፈሳቸውን ይበልጥ በማዳበር በቅንነት እና በታማኝነት አባላትን እንዲያገለግሉ ጠይቀዋል።

የአዋጭ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ገ/ስላሴ ኅብረት ስራ የድህነት ማስታመሚያ ሳይሆን የሃብት ማፍሪያ መሆኑን አዋጭ በአባላቶቹ አረጋግጧል ያሉ ሲሆን ሰራተኞቹንም ከዚህ በላይ ጠንክራችሁ በመስራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ትችላላችሁ በማለት አበረታተዋል።
የአዋጭ ሰራተኞች በበኩላቸው በተደረገው ሪፎርም መደሰታቸውን ገልፀዋል።






































አዋጭ 24ኛውን የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር 24ኛውን የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በጁፒተር ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።

የጉባኤውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኅብረት ስራ ማህበሩ የስራ አመራር  ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ገ/ስላሴ የዕለቱ አጀንዳ የኅብረት ስራ ማህበሩ የ2016 በጀት አመት የኦዲት ሪፖርት በውጭ ኦዲተሮች ኦዲት ተደርጎ ሪፖርት የሚቀርብበት መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም አዋጭ የአለም አቀፉ የኅብረት ስራ ህብረት (ICA) ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ መሳተፉን አስታውሰው በስብሰባው ላይ የተነሱ ሀሳቦች እና ውሳኔዎችን  ለጉባኤው ተሳታፊዎች አጋርተዋል።

በዚህም መሰረት የኅብረት ስራ ማህበሩ የ2016 በጀት ዓመት  የኦዲት ሪፖርት  ለጠቅላላ ጉባኤው ተወካዮች መደበኛ ጉባኤ እየቀረበ ይገኛል።

20 last posts shown.