Awtar Express አውታር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


በቻናሉ
#ፈጣን ፥#ትኩስ #ወቅታዊ እና #አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
Get updated information on our Channel
Share For Your Friends
ለማንኛውም ሀሳብ፣አስተያየት፣ጥቆማ እና ማስታወቂያ ለ ማሰራት ከ ስር ባለው ሊንክ ላይ ይፃፉልን ።
@awtarex

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


Never give up!

ህይወት ተገማች አይደለችምና ትናንት ሌላ ሰው ነበርክ፣ ዛሬም እንዲሁ ሌላ ሰው ሆነሃል፣ ለውጥህ ነገም እንዲሁ ይቀጥላል። የሚጓዝ ስው ይደናቀፋል፤ ግፋ ሲልም ይወድቃል፤ ይጋጋጣል፤ ይጎዳል፤ ይታመማል። ነገር ግን በእንቅፋቱ ምክንያት ከመንገዱ አይገታም፤ በውድቀቱ ምክንያት ወደኋላ አይመለስም፤ በጉዳቱ ምክንያት ሊሔድ ካሰበበት ቦታ አይቀርም። ምንም ያጋጥምህ በማቆም የሚመጣው ሽንፈት፣ በማቋረጥ የሚያገኝህ ተስፋ መቁረጥ እንዳይቆጣጠርህ እራስህን አበርታ። አንድ ሁለቴ ልትሸነፍ ትችላለህ፣ ወደኋላም ልትመለከት ትችላለህ ተስፋ ቆርጠህ ያቆምክበት ወቅት ግን የመጨረሻው አንገት አስደፊ የስቃይ ሽንፈትህ ይሆንብሃል። ለሽንፈት እጅ እንዳትሰጥ፤ በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ፤ ድሉ ያንተ እንጂ የሽንፈትህ፣ የተስፋ መቁረጥህ፣ የውድቀትህና የበታችነትህ አይደለም። ያቆምክ እለት ሽንፈትህ ይጀምራልና ምንም እንኳን ቢከብድህ መቼም ጥረትህን እንዳታቆም፤ እንዳታቋርጥ።

Via fb(meta) page


ትናንት የግብፅ ጦር ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሞቃዲሾ ጭነት ማጓጓዛቸውን ተከትሎ የኢ/ያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማምሻውን ያወጣው ጠንከር ያለ መግለጫ።


"የበረራ ደህንነትን የሚጥሱ ደንበኞች በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ህግ ይጠየቃሉ"
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

አቶ መስፍን እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኛ ንጉስ ነው ብሎ የሚያምንና ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ህግን አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ ባጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥ የበረራ መርሐ-ግብር ወደ መቀሌ ተጉዘው የነበሩ ሁለት አውሮፕላኖች ማረፍ ሳይችሉ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አስታውሰዋል፡፡

ሌላ ወደ መቀሌ ለመብረር በዝግጅት ላይ የነበረው አውሮፕላን የአየር ሁኔታው ለደኅንነት አስጊ በመሆኑ መብረር አልቻልም። በመሆኑም ተጓዦች ወደ ተርሚናል ውረዱና የሚሆነውን ነገር እንነግራችኋለን ሲባሉ "አንወርድም፤ መሄድ አለብን፤ አውሮፕላኑ ይከስከስ" ሲሉ የነበሩ ያሉ አንዳንድ ደንበኞች በህግ እንደሚጠየቁ አስታውቀዋል።

አየር መንገዱ የአገልግሎት ጥራት ደረጃን በማውጣት ደንበኞችን በአገልግሎት አሰጣጥ የማርካት፣ እያንዳንዱ አውሮፕላን በተመደበለት ስዓት እንዲወጣ የማድረግ፣ የደንበኞች ሻንጣ ጉዳት ሳይደርስበት ከደንበኞች ጋር እኩል እንድሄድ የማድረግና ሌሎች በርካታ ስራዎችን መስራቱን አስታውቀዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በየጊዜው በመገምገም ደንበኞችን ለማርካት እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።


ሙሉ አውቶቢስ ተሳፋሪ ታገቱ !

ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ እና ቱሉ ሚልኪ መሀከል አንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪ ከሾፌር ረዳት ጋር በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል።


ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ምርጡ የኢኮኖሚ ክላስ አየር መንገድ ዘርፍ ለሽልማት ዕጩ ሆነ

ዜጎች በዚህ ሊንክ https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow በመግባት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንዲመርጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘንድሮው የ “World Travelers Award” ሽልማት በስድስት ዘርፎች መታጨቱ ይታወቃል፡፡

#የኢትዮጵያአየርመንገድ


"የበረራ ደህንነትን የሚጥሱ ደንበኞች በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ህግ ይጠየቃሉ"
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

አቶ መስፍን እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኛ ንጉስ ነው ብሎ የሚያምንና ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ህግን አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ ባጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥ የበረራ መርሐ-ግብር ወደ መቀሌ ተጉዘው የነበሩ ሁለት አውሮፕላኖች ማረፍ ሳይችሉ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አስታውሰዋል፡፡

ሌላ ወደ መቀሌ ለመብረር በዝግጅት ላይ የነበረው አውሮፕላን የአየር ሁኔታው ለደኅንነት አስጊ በመሆኑ መብረር አልቻልም። በመሆኑም ተጓዦች ወደ ተርሚናል ውረዱና የሚሆነውን ነገር እንነግራችኋለን ሲባሉ "አንወርድም፤ መሄድ አለብን፤ አውሮፕላኑ ይከስከስ" ሲሉ የነበሩ ያሉ አንዳንድ ደንበኞች በህግ እንደሚጠየቁ አስታውቀዋል።

አየር መንገዱ የአገልግሎት ጥራት ደረጃን በማውጣት ደንበኞችን በአገልግሎት አሰጣጥ የማርካት፣ እያንዳንዱ አውሮፕላን በተመደበለት ስዓት እንዲወጣ የማድረግ፣ የደንበኞች ሻንጣ ጉዳት ሳይደርስበት ከደንበኞች ጋር እኩል እንድሄድ የማድረግና ሌሎች በርካታ ስራዎችን መስራቱን አስታውቀዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በየጊዜው በመገምገም ደንበኞችን ለማርካት እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።


የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ለ3 ሺህ 611 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ በክልሉ ህጉን መሰረት በማድረግ ይቅርታ መደረጉን ገልጸዋል።

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ጉዮ ዋሪዮ በመግለጫቸው የክልሉ የይቅርታ ቦርድ በየደረጃው ማጣራት አድርጎ ለፕሬዚዳንቱ በማቅረብ ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች መካከል 3 ሺህ 334 ወንዶች ሲሆኑ ፤ 247 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ባህሪ ማሰየታቸውና ከቅጣቱ መማራቸው በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ መሆኑን አንስተዋል።

ታዳጊ ታራሚዎች ሆነው አንድ አራተኛ የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እና ልጅ ይዘው በማረሚያ ቤት የሚገኙና እረጉዝ ሴቶች ይቅርታ ከተደረገላቸው መካከል መሆኑን ዐቃቤ ህጉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶችና የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ከ10 ዓመት በላይ በማረሚያ ቤት ያሳለፉ ይቅርታ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።

በይቅርታው ካልተካተቱት መካከል የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው፣ በተደጋጋሚ ወንጀል የተሳተፉ፣ ዘረፋ፣ በሙስና እና በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የተሳተፉትን እንደማይመለከት አስረድተዋል።


አየር መንገዱ ከ28 ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ልዩ ስልጠና በመስጠት አስመረ

ስልጠናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ እና ቲንክ ያንግ ኩባንያ ጋር በመተባበር ነው የተሰጠው፡፡

ሰልጣኞቹ ከ28 የተለያዩ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ÷መርሐ ግብሩ በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቪርሲቲ በኩል መሰጠቱ ተጠቁሟል፡፡

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶች (ኤስ ቲ ኢ ኤም) የተሰኘው ፕሮግራም አሁን ላይ ለሁለተኛ ጊዜ እንደተሰጠም የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስልጠናው የትምህርት ተደራሽነት በበቂ ሁኔታ ባልተሟላባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡


በአሜሪካ የቦይንግ አውሮፕላን ጎማ ፈንድቶ 2 የጥገና ሰራተኞች ህይወት አለፈ

ቦይንግ 757-232 የሚል የምርት መለያ ያለው አውሮፕላኑ የአሜሪካው ዴልታ አየር መንገድ ንብረት ሲሆን በአትላንታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሶስት ቀናት የቴክኒክ ጥገና ሲደረገለት እንደነበር ተመላክቷል፡፡

አውሮፕላኑ በጥገና ላይ በነበረበት ወቅት ጎማው በመፈንዳቱ ሁለት የጥገና ሰራተኞች ሲሞቱ በተጨማሪ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉም ተገልጿል።

የአውሮፕላኑ የጎማ ፍንዳታ መንስዔ አለመታወቁን የገለጸው የአር ቲ ዘገባ፤ የቦይንግ አውሮፕላን በየጊዜው የሚያጋጥሙት የቴክኒክ ችግሮች በርካታ አደጋዎችን ከማስከተሉ ባለፈ ለደንበኞች ደህንነት ስጋት እየሆኑ እንደሆነ ጠቅሷል።


በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዘረፋ፣ በቅሚያ፣ በሌብነት፣ በቤት ሰብሮ ስርቆት እና በደንብ መተላለፍ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ ተችሏል።

ተጠርጣሪው ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ ፣ ጀማል ኑሩ እና ዳዊት ድሪባ በዳኔ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም 11 ጦር መሣሪያ መዝረፍ ወንጀል፣ 6 ቅምያ ወንጀል፣ 3 ሌብነት ወንጀሎች፣ 3 ሰው መግደል ወንጀል፣ 2 ስርቆትና ቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች፣ አንድ ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል፣ ከእስር ማምለጥ ወንጀል እና አንድ ደንብ መተላለፍ የወንጀል ሪከርድ በአጠቃላይ 28 የወንጀል ሪካርዶች ያሉበት እንደሆነና ከዚህ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 24 ቀን በዋለው ችሎት ስድስት መዝገቦችን ሦስት ጊዜ አጣምሮ ሦስት ጊዜ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር መገንዘብ ተችሏል።

እንደገና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት በጦር መሣሪያ የታገዘ የዘረፋ፣ ከአስር ቤት የማምለጥና በሌብነት ወንጀል የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጠት ያስተላለፈት መሆኑን የፖሊስ የምርመራ ማህደር አመላክቷል።


በቅናት በመነሳሳት ባለቤቷን በመጥረቢያ በመምታት የገደለችዉ ተከሳሽ ‼️

በደሴ ከተማ ቧንቧ ዉሀ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 10 ዉስጥ ልዩ ስፍራዉ ደመና ጨፌ ከተባለ ቦታ ነዋሪ የሆነችዉ ተከሳሽ ፋጡማ ይመር ከሟች ባለቤቷ አብዱሮህማን ጋር በትዳር አስራ ሶስት አመታትን አብረዉ ቆይተዋል ከአብራካቸዉም ሁለት የዘጠኝና የሁለት አመት ህፃናት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

ባልና ሚስት ቤት ዉስጥ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት መግባባት ባለመቻላቸዉ ጉዳያቸዉን በቤተሠብ ሽምግልና እንዲታይ ካደረጉ በሗላ መታረቅ ባለመቻላቸዉ ተከሳሹዋ ሚስት ራሷ ለመለያየት ፈልጋ ለፍች በቀነ ቀጠሮ ይለያያሉ፡፡

እንደገና ሀሳቧን በመቀየር ተከሳሽ ፋጡማ ይመር እኔን ፈትቶ አሰሪዉን ሊያገባነዉ በማለት በቅናት በመነሳሳት ባለቤቷ ሟች አብዱሮህማን መሀመድ ለሊት በተኛበት በመጥረቢያ በተኛበት ሶስት ግዜ ደጋግማ በመምታት መግደል መቻሉሏን በደሴ ከተማ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ ፖሊስ የሆኑት ዋና ሳጅን እሸቱ ተፈራ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ግለሠቧ ግድያዉን ከፈፀመች በሗላ በረኪና በመጠጣት እና ዉሀ የቋጠረ ጉድጎድ ዉስጥ በመግባት ራሷን ለማጥፋት ብትሞክርም እንዳልተሳካላት ዋና ሳጅን እሸቱ ተፈራ አስረድተዋል፡፡በህብረተሰብ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏን መርማሪ ፖሊሱ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ በተከሳሹዋ ላይ አስፈላጊዉን ምርመራ በማካሄድ መዝገቡን በሰዉና ሀኪም ማስረጃ በማስገደፍ ለሚመለከተዉ የፍትህ አካል ልኳል፡፡ከፖሊስ የደረሰዉን መዝገብ የተመለከተዉ የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት የተከሳሹዋን ጥፋተኝነት በማስረጃዎች በማረጋገጡ በቅርቡ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ፋጡማ ይመር በ17 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል፡፡


Dogs Token ኖሯችሁ Wallet Verify አድርጎ P2p ላይ መሸጥ ላልቻላችሁ እኛ እየገዛን ነው ።

Inbox

ቀጥታ መሸጥ የፈለጋችሁት Token Screenshot አድርጋችሁ ትልካላችሁ ዋጋ ነግረናችሁ ከተስማማን እንገበያያለን  ።

ከDogs Bot Claim ያላደረጋችሁ አትምጡ እሱ አይሸጥም ።

መሸጥ የምትፈልጉ  👉🏻

@awtar45


#Mpox #Ethiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተገኝቷል ?

“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” - ጤና ሚኒስቴር

ኦክስፋም ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የተጠረጠረ ኬዝ መገኘቱን የሚያሳይ አጭር ሪፖርት ትላንት ይፋ አድርጎ ነበር፡፡

ሌላ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ድርጅትም እዛ ካሉ ሰዎቹ የበሽታው ኬዝ በሶማሌ ክልል መገኘቱን እንደሰማ ገልጿል።

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሶማሌ ክልል ባለስልጣን ግን " ምንም የተገኘ ነገር የለም ውሸት ነው ያወጡት ሪፖርት " ብለውናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ እውነት ተከስቷል ? የሚለውን ጉዳይ ለማጣራት ሞክሯል፡፡

ጤና ሚኒስቴርንም በሽታው ወደ ሀገራችን ገብቷል እንዴ ? ሲል ጠይቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ደረጀ ጉዱማ (ዶ/ር) በሰጡን ምላሽ፣ “ አላጋጠመም፡፡ ያው ለነገሩ ትላንትም አረጋግጠን ነበር፤ ሰዎቹ (ኦክስፋም ኢትዮጵያን ማለታቸው ነው) የለጠፉትን እንዲያነሱ እያደረኩ ነበር፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” ሲሉ ገልጸውልናል፡፡

“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው፡፡ በእርግጥ ይመሳሰላል ሲምፕተማቸው፡፡ እንደ ቤተሰብ ሀፕን ያደረገ ነው፡፡ ኦረዲ ሌሎቹም ሪከቨር ስላደረጉ ሳምፕልም ወስደን ቼክ አድርገናል ሞንኪይፖክስ አይደለም ” ነው ያሉት፡፡

“ ቺክንፖክስ የሚባል አለ ፤ ሌላ በሽታ አለ ቀለል ያለ፡፡ ይህ ብዙ ቦታዎች አለ፤ ሰሞኑን ይሄኛው ስለተነገረ፣ ሰው ሲጠራጠር ቁስል፣ ቀላል የቆዳ ኢንፌክሽን እየመጣ ስለሆነ ከጥርጣሬ የተነሳ ነው ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“ በእርግጥ ጥሩ ነው እንደዛ መሆኑ ግን ውዢምብርም ሊፈጠር ስለሚችል ጥንቃቄ አድርጉ፣ ፖስት እንዳታደርጉ ሚኒስቴሩ ነው ፖስት ማድረግ ያለበት ቼክ አድርጎ ከተፈጠረም፡፡ ሰስፔክትም አይባልም፡፡ ሰስፔክት በራሱ የራሱ ደፊኔሽን አለው ” ብለዋል፡፡

ቺክንፖክስ ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ ነው እንዴ ? ስንል የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከ100 በላይ ተመሳሳይ ምልክቶች ያሏቸው የቆዳ ኢንፌክሽኖች፣ ሌሎችም ኢንፌክሽኖች አሉ ” ብለዋል፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በኢትዮጵያ ደረጃ ተከስቷል ? አልተከሰተም ? ለህዝቡስ ምን የጥንቃቄ መልዕክት ታስተላልፋለችሁ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ምንም ነገር የለም በርካታ ሳምፕሎችን ወስደን ቴስት አድርገናል፡፡ የእኛ ልጆች በየክልልም እየወረዱ በሁሉ ቦታ ላይ ሩመር ሲነሳ ያያሉ፡፡ ኢንቨስቲጌት ያደርጋሉ፡፡ ሳምፕል ይወስዳሉ፡፡ ሳምፕሉ ወደ እኛ ወደ ላብራቶሪ ይላክል፡፡ በርካታ ቴስቶች አድረገናል፡፡ ግን ምንም የለም ኔጌቲቭ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“ ኤርፖርት ላይ ሥራችንን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡ መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የተያዩ ምልክቶችን እናያለን በተለይ ትኩሳት ያላቸውን ሰዎች እንለያለን፡፡ የትኛውም ቆዳቸው እብጠት ካለ እያረጋገጥን  እንገኛለን ” ብለዋል፡፡

“ ማህበረሰቡ ግን ይህን አይነት ምልክት ካለ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ግን በተለይ ለጤና ተቋማት ሪፖርት እንዲያደርግ ነው የሚጠበቀው፡፡ እንደዛ አይነት ሰው ካለ ደግሞ ንክኪ እንዳይኖር ጥንቃቄ  ማድረግ፡፡ ንክኪም ካለ ቶሎ በአግባቡ እጅን መታጠብ፣ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ከጤና ሚኒስቴር ጠይቆ ባዘጋጀበት ሰዓት ኦክስፋም ኢትዮጵያ " በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠረ ኬዝ ተገኝቷል  " የሚለውን መረጃ ከገጹ ላይ አጥፍቷል።




ዜና እረፍት🕯🕯

በበርካታ ፊልሞች ላይ የምናውቀው ተዋናይ ጌታቸው እጅጉ (ባቡጂ) ትላንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ባቡጂ ከ60 በላይ ፊልም ሰርቷል። በብዕር ስም ቢሆንም የጻፋቸው መጽሐፍ አሉት። ድንቅ የኮሜዲ ትወና ብቃት እንዳለውም ይመሰክሩለታል። Rip🕯


ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን!


የቴሌግራም መስራችና ባለቤት በፈረንሳይ ታሰረ‼️
የቴሌግራም ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ባለቤት ፓቭል ዱሮቭ በፈረንሳይ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የሩሲያ ተወላጁ ፓቭል ዱሮቭ የግል ጀቱ በፈረንሳይ ቦርጌት የአየር ማረፊያ ካረፈ በኋላ ነው በፈረንሳይ ፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡

ዱሮቭ  በቁጥጥር ስር የዋለው  ከሚያስተዳድረው  የመልዕክት መለዋወጫ መተግበርያ ቴሌግራም ጋር በተያያዘ ሲሆን ይህም የቴሌግራም ይዘቶችን በመሀል የሚቆጣጠር አካል (ሞደሬተር) ስለሌለው ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ወንጀለኞች መልዕክት ምንም ሳይታወቅባቸው መላላክ በመቻላቸውና ለወንጀለኞች ምቹ እድል በመፍጠሩ ነው በሚል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በፈረንሰይ የሩሲያ ኤምባሲም ጉዳዩን ለማጣራት ፈጣን እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑም ተመላክቷል።

ቴሌግራም በሩሲያ በዩክሬን እና በቀድሞ የሶቪዬት ህብረት አገራት ዘንድ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በ2018 በሩሲያ መተግበርያው ታግዶ ነበር፡፡ ምክንያቱም ባለቤቱ የተጠቃሚ መረጃ አልሰጥም በማለቱ ነው። ይሁን እንጂ በ2021 እንደገና አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡

1 ቢሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎች ያሉት ቴሌግራም በተለይም የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ዋነኛ የኢ-መደበኛ የመረጃ ምንጭ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስለጦርነቱ የተሳሳቱም ያልተሳሳቱም መረጃዎች እንደሚሰራጩበት እንዲሁም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪና የሩሲያ መንግስትም እንደሚጠቀሙት ተጠቁሟል፡፡ በዚህም “ምናባዊ የጦር ሜዳ” እስከመባል መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡


የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል በተባሉ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ

ተጠርጣሪዎቹ፦
• ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
• አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
• ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
• ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
• ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
• እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል።


#ደመወዝ

" ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም የደመወዝ ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ለመንግስት ጥያቄ ቀርቧል " - ኢሠማኮ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት ይፋ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ይደረጋል በተባለው ልክ፣ ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርቧል።

የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤  " በመንግሥት በጀት ለሚተዳደሩት የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ የግል ድርጅቶችና ተቋማት በራሳቸው በጀትና ትርፍ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑናቸው፣ በትርፋቸው ላይ ተመሥርተው ለሠራተኛ የደመወዝ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ከመንግሥት አቅጣጫ እየተጠበቀ ነው " ብለዋል።

" የሠራተኞችና የደመወዝ ዝቅተኛው ወለል እንዲወጣ እየወተወትን ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

የመንግሥት እና የግል ሠራተኞች አንዱ የተሻለ አንዱ የወደቀ የሚባል ክፍያ ሊኖር አይገባም ሲሉ አክለዋል።

" መንግሥት ይህን ጉዳይ ሊዘነጋው አይችልም የሚል እምነት ቢኖረንም፣ መሰል አገራዊ አጋጣሚዎችና ቀውሶች በሚኖሩበት ጊዜ ባለሀብቶችንና ተቋማትን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች በማድረግና ውይይቶች በማካሄድ አቅጣጫዎች ሊሰጡበት ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ለአገርም አይጠቅምም፣ የኢንዱስትሪ ሰላም አይኖርም፣ ሠራተኛውም ተረጋግቶ ሥራውን ማከናወን አይችልም " ብለዋል።

አቶ አያሌው፣ " ጉዳዩ እጅግ በጣም አሳሳቢ ስለሆነ መንግሥት አቅጣጫ የማይሰጥበት ከሆነ ኢሠማኮ ጥያቄውን በጽሑፍ ለመንግሥት ያቀርባል " በማለት አስረድተዋል፡፡

" ሠራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት በልቶ ማደር አልቻለም፣ የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻለም፣ ይህን ማንም ያውቀዋል ሚስጥር አይደለም፣ አሠሪዎቹ ለሚያሠሯቸው ዜጎች ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ መክፈል አለባቸው " ብለዋል፡፡

የሠራተኛ መብት መከበር እንዳለበት " የሚያረጋግጥ ወጥ የሆነ ሕግ ያስፈልጋል " ያሉት አቶ አያሌው፣ " የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ሌሎች የሠራተኞች መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን መንግሥት ለምን እንዳዘገያቸው አልገባኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጉዳይ ላይ አሁንም መንግሥት የዘነጋው ይመስላል " ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ኢሠማኮ ተጨማሪ ጥያቄ ሊያቀርብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

አክለው ፥ ከመንግሥት ተቋማት በተሻለ የሚያተርፉት የግል ተቋማት፣ ከመንግሥት የደመወዝ ጭማሪ ጋር እኩል ላለመጨመር ትልቁ ችግር የአስተሳሰብ ጉዳይ እንጂ፣ የገንዘብ እጥረት አይደለም በማለት ለዜጎች ማዘን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ለራስ ብቻ ከማግበስበስ ዕሳቤ በመውጣት ምርታማ ሠራተኛን ለማፍራት፣ አሁን  ተመጣጣኝ የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ ብዙ ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን ገልጸዋል።



20 last posts shown.