#አዲስአበባ #አሶሳ
➡️ " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ (ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል
👉 " የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት ይዛ የተወለደች ቢሆንም የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላታል አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ ናት " - አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል
በአዲስ አበባ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቤቴልሄም አመኑ የተባለች እናት 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወንድ ልጅ በተደረገላት የቀዶ ህክምና በሰላም ተገላገለች።
የሆስፒታሉ የማህፀን ስፔሻሊስት እና የዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " ብለዋል።
ልጆች ከ5 ኪሎ በላይ ሆነው ሲወለዱ የሚደረግላቸው ህክምና መኖሩን የገለጹት ዶ/ር " ለልጁ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ መረጃ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጓል።
የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት (Bilateral huge cystic hygroma) ይዛ የተወለደች ስትሆን በእብጠቱ ምክንያት ጡት መጥባትም ሆነ እንደ ልቧዋ መተንፈስ አትችልም ነበር።
በ13/4/17 ዓ/ም በሆስፒታሉ የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላት አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል።
አሁን እንደልቧ መተንፈስ ጡት መጥባትም ጀምራለች ተብኳል።
በህክምናው ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎች ፦
🙏 Surgeons ፦ ዶ/ር ሮቤራ ተሾመ እና ዶ/ር መብራቴ ወ/መድህን
🙏 Anaesthesiologist ፦ ዶ/ር ሲሳይ እብስቱ
🙏 Anesthesia team: ደመቀ ወ/ኪዳን፣ ተሰፋዬ አሰፋ እና ሰለሞን አዳሙ
🙏 Scrub Nurse ፦ሲ/ር ሳይሽልዋል ወርቁ (ቹቹ)
🙏 Circulator Nrs ፦ አልሃጅ ሀሰን እንደሆኑ ሆስፒታሉ አሳውቋል።