ታክስ‼️
በኢነርጂ ፍጆታ እና በልዩ ልዩ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ‼️
ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ በሚጠቀሙ ደንበኞች የፍጆታ ሂሳብ ላይ እና አዲስ ደንበኛ ማገናኘትን ጨምሮ ደንበኞች በሚፈፅሟቸው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ የ #ተጨማሪ_እሴት_ታክስ ተግባራዊ መደረጉን በላከልን መግለጫ ተናግሯል፡፡
በዚህ መሠረት ደንበኞች ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ በሚከፍሉበት ወቅት የፍጆታ መጠናቸው ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ ከሆነ እላፊ የመጣው የፍጆታ መጠን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተሰልቶ ሂሳባቸው ላይ የሚደመር ይሆናል ብሏል፡፡
ተቋሙ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ ያደረገው ከህዳር ወር የክፍያ ደረሰኝ ጀምሮ ሲሆን፤ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለባቸውን የኋላ ክፍያ በታህሳስ ወር በሚወጣው #ቢል ላይ ተጨምሮ የሚከፍሉ ይሆናል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኖችም ከመስከረም ወር ጀምሮ ባላቸው የፍጆታ መጠን መሠረት የኋላ ክፍያ በቀጣይ ይከፍላሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ደንበኞች ለተቋማችን በሚከፍሉት ልዩ ልዩ ክፍያዎች ላይም ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( #ኢቢሲ )ን የቴሌቭዥን አገልግሎት ክፍያ በወርሃዊ በደንበኞች የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ላይ በመጨመር እንዲከፍሉ ሲያደርግ መቆየቱን ተቋሙ አስታውሷል፡፡
በመሆኑም ወርሀዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ መጠናቸው ከ50 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የሆኑ ደንበኞች 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ጋር የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ እየከፈሉ ይገኛሉ ሲል በመግለጫው አካቷል፡፡
#ሸገር
======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s