ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ምድር እጅግ ሰፊ ናት፤ እኔ ወንድማችሁ በርናባስ ደግሞ ያሉኝ ሁለት ዐይኖች ብቻ! አባካችሁን ኑ...ና አጋጭተን (ዐይኖች አዋጥተን) እንይ!✍️
አሳብ አስተያየት ቢኖራችሁ፦ @barnica የግላችሁ ነው።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የጳውሎስ መልእክት ወደ በርናባስ ሰዎች!?😥
----●------
        ከበርናባስ በቀለ

ዳዊት ይባላል፣ አመለ ሸጋ የኾነ ባጃጅ ሾፌር። ትንሽዬ ዕቃ (ለማንበቢያ የሚኾን ወንበር ነው! የበዓል ሸመታ ጋር አገናኙ ደግሞ!😉) ጭኖ ወደ ቤቴ እንዲያደርስልኝ በኮንትራት ውል ተገናኝተን ከCMC አካባቢ ጉዞ ጀምረናል።

#እኔ፦ ባጃጅህን ጥሩ ይዘሃታል! እንተዋወቅ? ከደንበኝነት ያለፈ ቤተሰብ ልንኾን እንችል ይኾናል፤ ማን ያውቃል?

#ዳዊት፦ "አንተም ተመችተኸኛል! ስምህ ማን ይባላል?"

#እኔ፦ ስሜ በርናባስ ነው።

#ዳዊት፦ "ይህን ስም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው የማውቀው አይደል? Yes! እንደውም አስታወስኩት፣ 'የጳውሎስ መልእክት ወደ በርናባስ ሰዎች' የሚል ሃሳብ በቆሮንቶስ ውስጥ አንብቤአለሁ"

#እኔ፦ ወንድሜ! መጽሐፍ ቅዱስ የምታነብ በመኾንህ ደስ ብሎኛል፤ በርናባስ ከተማ አይደለም! ሰው ነው። አዎን በርግጥ ጳውሎስን ያቀና (መጋቢው) የነበረ ሰው ነው። በሐዋሪያትም ዘንድ ተወዳጅ ወንድም ነበር። የቆጵሮስ ሰው ነበርና ስሙ "በርናባስ" የተባለው በሐዋርያት ነው።

#ዳዊት፦ "ይገርማል! መጽሐፍ ቅዱስ ካነበብሁ ቆየሁ ማለት ነው አይደል? ተምሬው እኮ ነበር። ተመርቄም ጭምር! እንደውም የድቁ'ና ትምህርት አጠናቅቄ የተመረቅሁበትን ፎቶ ላሳይህ!" (ብሎኝ በአንድ እጁ እየነዳ በሌላኛው እጁ ስልኩን ከኪሱ መዥለጥ አደረገና የምርቃት ምስሉን አሳየኝ!)

#እኔ፦ ይገርማል! ታዲያ ለምንድነው በድቁ'ናው ያልገፋህበት?

#ዳዊት፦ "ከድቁ'ናው ስንመረቅ በአንድ ደብር ውስጥ ዲያቆን ኾኔ ለመቀጠር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) መክፈል እንዳለብኝ ነገሩኝ! እኔም ተስፋ ቆረጥኩኝ። ይኸው ለእነርሱ ጉቦ ከምከፍል ብዬ እጄ ላይ በነበረው ገንዘብ ባጃጅ ገዝቼ ወደ ሥራ ገባኹ እልሃለሁ!"

#እኔ፦ "አዝናለሁ በጣም!😥 አብረውህ የነበሩ ተማሪዎች እንዴት ኾኑ? አንተ እንዴት ተለየኻቸው?"

#ዳዊት፦ "አቅም ያላቸው ከፈሉ፤ እንቢ ያሉ ደግሞ እንደ'ኔው በተለያዩ የጉልበት ሥራዎች ጭምር ተሰማሩ። በውስጡ ይህ አሻጥር ያለ መኾኑን ባውቅ አልማርም ነበር እኮ! እኔ ነፍሴን ወደ መንፈሳዊ ቦታ አስጠጋለሁ ብዬ ነበር የገባኹት ይኸው ወደ ዓለም ወርውረውኝ ያነበብሁት በርናባስ የሚባል መልካም ሰው ከተማ ሆነብኝ። ቢኾንም ግን ከባጃጅ ሥራዬ እዚያ ነበር የሚሻለኝ።"

#እኔ፦ አይዞኝ ወንድሜ!😥 አንተ ጀግና ሰው ነህ። እንቢ ማለትህን በጣም አድንቄልሃለኹ። ከአመጻቸው ጋር ባለመተባበርህም ላመሰግንህ እወዳለኹ። ደግሞ ይኸው ባለ ባጃጅ ኾነሃል እኮ። ይህች ትንሽዬ የልፋትህ ጅማሮ ነገ ትልቅ እንደምትኾን አምናለኹ። 

#ዳዊት፦ ዓለም ብትቆሽሽ ወደ እግዚአብሔር ቤት ተሸሽቶ ይዳናል፣ የእግዚአብሔር ቤት በዚህ መልኩ ሲጨቀይ የት ተኼዶ እረፍት ይደረጋል? ይኸው ሁሉም አስጠላኝ!

#እኔ፦ በዚህ ጊዜ ዓለምንና የዓለማዊነትን ጥግ ለማየት የሚኬድበት ስፍራ ቤተ ክርስቲያን ኾናል፤ ይህን ዐውቃለሁ! ግን አንተና እኔም በግላችን ማድረግ ያለብን ነገር አለና በደንብ እንጨዋወታለን፤ በርታልኝ። ስላወቅሁህ ደስ ብሎኛል፣ እደውልልሃለሁ። ጥሩ ወንድም እኾንሃለሁ! ይኸው ሰፈራችን ደርሰናል፤ እዚህ ጫፍ ያዝልኝ። 😥

ይህን ልጥፍ ሙስና ጠያቂዎቹ ቢያነቡት ደስ ባለኝ፤ ለማንኛውም እናንት በድኾች ላብና ዕንባ የከበራችኹ (በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ኹኑ) እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ነው!!!!!! 💪

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ሞት ምርጡ አገልጋዬ!
----●----
      ከበርናባስ በቀለ

ስለ ክርስቶስ ሞት ስናወራ ስለ ትንሳኤውም ድል እያወራን መኾኑ ግልጽ ነው፤ ስለ አዳም ኃጥአት የሞተው እርሱ ስለ ሕያውነቱ ደግሞ ከሙታን በኩር ኾኖ ተነስቷልና። በሞቱ ኃጥአትን ገድሎ በትንሣኤው ደግሞ ሕይወትን እውን አድርጓል።

በክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል ሥራ የሚያምን ኹሉ ሞትንና ኃይሉን አሸንፏል። ከእንዲህ ሞት ለእነርሱ አገልጋይ እንጂ ገዳይ አይደለም፤ እንደውም ዓለም አቋራጭ ትራንስፖርት ነው (ከዚህኛው ወደዚያኛው ዓለም)! ማለቴ፦ አያምጣውና አሁን ካሁበት ወደ ቦሌ ልኽድ ብል ራይድ እይዝ የለ? ልክ እንደዚያው የምድር ቆይታዬን ጨርሼ ወደ ጌታዬ ስኼድ ሞት መጓጓዣዬ ነው።

ለምርጦቹ የስጋ ሞት ወደ ሌላኛው የሕይወት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት Exit door እንጂ መጥፊያቸው አይደለም። ሞት ተሸንፏላ! ኃይሉም በትንሳኤው መንፈስ ድል ተነሥቷላ! ከሰሞኑ ትንሳኤውን ስናስብ ታዲያ ሞትን በሞቱ የዘረረልን ጌታ ወደ ራሱ ሊወስደን በቅርቡ እንደሚመለስ እያሰብን ይሁን!!

"በሦስተኛው ቀን እነሳለሁ!" እንዳለ የሞትን ኃይል አጥፍቶ የተነሳው ጌታችን "እኔ ባለሁበት እንድትኖሩ መጥቼ እወስዳችኋለሁ" ብሎ አይዋሸንምና!!!!

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


እግዚአብሔርን ትወ'ደዋለህ?
----●------
ከበርናባስ በቀለ

እግዚአብሔር ሰውን በጥልቅ ፍቅር መውደዱ በርሱ በተወደዳችኹ በእናንተው የታወቀ ነው፤ ግና ይህ ፍቅሩ የተረጋገጠው ለዓለሙ ባቀረበው ውድ ስጦታ መኾኑ አይዘነጋም።

የእግዚአብሔር ፍቅር "Self giving" ነውና ልጁን ስለ'ኛ ኀጥአት ለመስቀል ስቃይ አሳልፎ ሊሰጠው ሁለት ጊዜ አላሰበም። ስለዚህም የእግዚአብሔር ፍቅር በሕያዋን ምድር የፍቅሮች ሁሉ መለኪያ ሊኾን ችሏል። "ከዚህ በላይ ፍቅር ለማንም የለውም" የተባለውን ልብ ይሏል።

ሁላችንም ርሱን የምንከተለው ስለዚህ ፍቅሩ መኾኑን አልጠራጠርም። ይህ ፍቅር ታዲያ ምላሽ የሚፈልግ መኾኑም ግልጽ ነው። የፍቅሩ ምላሽ ስለ መስጠት ብዙዎች ብዙ ብለዋል፤ "ምላሽ ከኾነልህ ምስጋናዬን ዝማሬዬን" ብለንም ዘምረናል።

ይኸው የወደደን አምላክ እግዚአብሔር ለፍቅሩ ምላሽ መስጠት የምንችልበትን መንገድ በግልጽ ነግሮናል። ምስጋና ጥሩ ነው፤ ግን ምስጋናችን የእግዜሩ ጽሕፈት ቤት ሥራ ማስኼጃ አይደለም። ርሱ ከምስጋናችን በፊት ዙፋኑ ጽኑ መንግሥቱም ከዘላለም ነውና።

"እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ውደድ" ተብለሃል፤ ርሱን መውደድህ የሚረጋገጠው ለባልንጀራህ ባለህ ፍቅር ነው። ይህን ስልህ ታዲያ ፍቅርን የምትጀምረው ከባልንጀራህ ነው እያልሁህ አይደለም፤ እግዚአብሔርን የመውደድህ ዋነኛ ማሳያ ለባልንጀራህ ያለህ ፍቅር መኾኑን ላመለክትህ አስቤ እንጂ።

ስሊዚህ "አምላኬ ሆይ ለፍቅርህ ምላሽ አጣኹ! የምሰጥህ የለኝም" ልትል አትችልም። የፍቅሩ ምላሽ መንገድ በመጽሐፉ ቁጭ ብሎልሃልና። ርሱ ራሱን ስላንተ ሰጥቶህ የለ? አንተ ደግሞ ስለ ባልንጀራህ ራስህን ትሰጣለህ። ልጁም እስከ መስቀል ሞት ወዶህ የለ? አንተ ደግሞ ርሱ የሞተላቸውን ትወድ'ለታለህ። ይኸው ነው።

ወዳጄ ይህንኑን በሚመለከት የሞተላቸውን ልንወድ'ለት በI Care Ministries የርኅራኄ አገልግሎት ክፍል የፊታችን እሁድ ሰው ከሌላቸው ሰዎች ጋር የትንሣኤውን በዓል መታሰቢያ ለማሳለፍ ታስቧልና አንተም ለፍቅሩ ምላሽህን ልትሰጥ አብረኸን መኾን ትችላለህ። ከአክብሮት ጋር!

● ልብሶች...
● የበዓል ፍጆቻ እቃዎች..
● ገንዘብ..
ለዝግጅቱ የሚፈለጉ ግብዓቶች ናቸው።

I CARE MINISTRIES
CBE: 1000426193737
የውስጥ መስመር፦ @metsafu

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ማጤን አለብህ!
-----●---
ከበርናባስ በቀለ

እንዴት እንዳገኘኸው የማታውቀውን ነገር እንዴት አንተ ጋር እንደምታቆየው አታውቅምና "ሳላውቅ እጄ ገባ" እያልህ ስትፈነጥዝ ነገሩ workout ስለሚያደርግበት መንገድ ደግሞ ማጤን አለብህ።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ጮማ ጥያቄ! 🥩
---●---
ከበርናባስ በቀለ

#ሮዚ፦ "ባርኒ በነብይ መኖር ታምናለህ?"

#እኔ፦ በነብይ ማን መኖር?

#ሮዚ፦ "አይይ፤ በዚህ ዘመን ነብይ አለ ብለህ ታምናለህ?"

#እኔ፦ እኮ ነብይ ማን?

#ሮዚ፦ "እንዴ ባርኒ! ለዘመናችን እግዚአብሔር የቀባው ነብይ!"

#እኔ፦ እንዴ... እኔስ ምን አጠፋሁ? እግዚአብሔር ለዘመናችን የቀባው ነብይ ማን?

#ሮዚ፦ "እንዴ ባርኒ ነብይነት ማንነት ነው እንዴ?"

#እኔ፦ እና ሮዚዬ ምንነት ነው?

#ሮዚ፦ "ጥያቄዬን መመለስ አልፈለግህም ማለት ነው አይደል?"😥

#እኔ፦ ይኸው ከንግግሬ አንድ ምላሽ የሚያሻው ሃሳብ አግኝተሽ የለ? ለአሁን "ነብይ አለ የለም" ብዬ ጥቁርና ነጭ ምላሼን አልነገርሁሽም። ግን "ነብይነት ማንነት ነው እንዴ?" ብለሽ ያቀረብሽልኝን ጮማ ጥያቄ ደጋግመሽ አሰላስዪው።

ከአሰላስሎትሽ ያገኘሽውን መረዳት በቀጣይ ጊዜ ታጋሪኛለሽ። ይህን ኮስታራ ጥያቄ በስልክ ከምናወራ ፊትለፊት ቢሆን እመርጣለሁ። በዘያ ላይ ከተያየን ቆየን አይደል? እስቲ ቢሮ ብቅ ነዪና እንመካከር! አሁን ስላልመለስሁ አትጨነቂ፤ ይደርሳል! ነብይነት ከገዛ አገሩ የት ይኼድና! ዋናው ነገር ጤና።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


በስፒከሮቻችን አይደለም!
---●----
ከበርናባስ በቀለ

የጥንት አማኞች "ጌታ ነው!" ማለት በማይቻልበት ዘመን የኢሱስን ጌትነት መስክረው (with their confession out of conviction) ነፍሳቸውን ሰጡ።

በዚህ ዘመን ያለን አማኞች ደግሞ ለጌትነቱ በምናሳየው መገዛት (with our submission to his Lordship) ጌታ መሆኑን እንመሰክራለን። በስፒከሮቻችን አይደለም!

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


እየሞተ ይኖራል
---●---
ከበርናባስ በቀለ

ስለ አዳም ኃጥአት የሞተው ክርስቶስ ስለ ሕያውነቱ ደግሞ ከሙታን ተነስቷል፤ በሞቱ ሞትን ገድሎ በትንሣኤው ደግሞ ሕይወትን እውን አድርጓል። በመስቀሉ ሥራ የሚያምን ሁሉ ሞትንና ኃይሉን አሸንፏል፤ ግና በየእለቱ ስለስሙ እየሞተ በሕይወት ይኖራል።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


#ከኢትዮ_ቴሌኮም_ጋር_አዲስ_ስምምነት!

#ኢትዮ_ቴሌኮም፦ "ሃሎ ሜሩት ነኝ እባክዎትን ምን ልርዳዎት?"

#እኔ፦ በርናባስ እባላለሁ፤ የሁለት አመት postpaid የኢንተርኔትና የስልክ እንዲሁም SMS አገልግሎት አስሞልቼ ነበር፤ ሙሉውን ክፍያ ፈጽሜአለሁ፤ በየወሩ የአገልግሎት ክፍያ ተብሎ ለሚከፈለው ትንሽዬ ብር SMS እየመጣ እንዳያዝገኝ እርሱንም የሁለት አመት አንድ ላይ ከፍ'ያለሁ።

ስለዚህ፦ እኔ የማውቀው በስልክና በinternet ጉዳይ ከቴሌ ጋር ከሁለት አመት በኋላ እንደምንገናኝ ነው። ግን ዛሬ ጠዋት ጀምሮ መስመሬ ቀጥ አላለም መሰለሽ? ያቺ የ'ናንተ ሴትዮ "የቴሌኮም አገልግሎት ክፍያዎ ጊዜ ስላለፈ መስመሩ ተቋርጧል" አለችኝ። (ማን ናት እሷ? ሲጀመር እኔን የት ታውቀኛለች!? ብዬ ልቀውጠው አሰብሁና ለካ ገና ጥሪውን ስጀምር ለአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱ እንዲያመች ቃለ ምልልሱ እየተቀዳ ነው ተብያለሁ፤ አሳያቸው ነበር!😥)

#ሜሩት፦ እሺ፤ እባክዎትን የመስመርዎትን ችግር ማየት እንድችል ስልኩን ሳይዘጉ ይጠብቁኝ።

#እኔ፦ ምን አማራጭ አለኝ?😥

#ሜሩት፦ አዎን! በርግጥ የርስዎ መስመር የሁለት አመት unlimited internet፣ የስልክ ጥሪና SMS Package በድህረ ክፍያ አገልግሎት አለው፤ የshort code ወርሃዊ ክፍያዎት ነው ያልተከፈለውና መስመርዎት የተቋረጠው ለዚያ ነው።

#እኔ፦ ደግሞ የshort code ወርሃዊ ክፍያ ምንድነው? ሲቀጥል ያኔ ጥቅሉን ሳስሞላ ተጨማሪ በመካከል የምክፍላቸለው ክፍያዎች እንዳሉ ለምን አልተነገረኝም? ሲቀጥል መስመር ማቋረጥ እንዲህ ቀላል ነገር ነው? "ልናቋርጥ" ነው ብሎ አንድ SMS መላክ ማንን ገደለ!?😥

#ሜሩት፦ እርስዎ subscribe ያደረጓቸው ሁለት short ኮጆች አሉ፤ 8100 እና 6491 ለሁለቱም በየቀኑ አንድ አንድ ብር (2 ብር) ይቆረጥቦታል፤ ቀድሞ መስመርዎት prepaid ስለነበር ይህን ወርሃዊ ክፍያ ከካርድዎ ነበር የምንቆርጠው፤ አሁን ግን እርስዎ ካርድ አይሞሉም ስለዚህ የ'ነዚህ አጫጭር ኮዶች ክፍያ ተደምሮ የወርሃዊ ክፍያ ቢሉ ይደርሶታልና SMS ሲመጣልዎ መክፈል አለብዎት።

#እኔ፦ እንዴ! ይህቺን ይወዳል! ደግሞ ማነው Subscribe ያደረጋቸው? እኔው? ደግሞ በየቀኑ ስከፍል ኖሬአለሁ? እስቲ በሞቴ! ካላስቸርኩሽ እዪልኝ ይህ 8100 ያልሽኝ ጉድ ከመቼ ጀምሮ ነው subscribe የተደገረው? ከካርዴ መቀነስ የጀመራችሁትስ ከመች ጊዜ ጀምሮ ነው?

#ሜሩት፦ 8100 ከ2019 ጀምሮ subscribe ተደርጓልና በየቀኑ አንድ ብር ከካርድዎ ሲቆረጥ ቆይቷል፤ የ6491ን ደግሞ አጣራሎታለሁ መስመር ላይ ይጠብቁኝ።

#እኔ፦ በቃ ተዪው እናቴ አታጣሪው! ደግሞ ሌላ ሕመም?😥 2019 ላይ አንድ ቀን እስቲ ለእነዚህ ሰዎች አንድ ብር contribute ላድርግ ብዬ ባልሁት subscription ሆኖ በእድሜ ዘመኔ የምከፍለው ሆኖ ተመዝግቧል ማለት ነው?

#ሜሩት፦ አዎን ደንበኛችን! Short ኮዶች እንደዚያ ናቸው። አንዴ Subscribe ካደረጉ በየቀኑ ይከፍላሉ፤ 8100 በየቀኑ አንድ ብር ነው፤ ሌሎቹ ከ2-3 ብር ይሄዳሉ።

#እኔ፦ ታዲያ ይህን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል? የአንድ ጊዜ ስጦታ መስሏቸው አንድ ብር በላኩበት ከካርዳቸው በየቀኑ እየተቆረጠባቸው እንደሆነስ ሁሉም ይረዳሉ? ወይስ በጉዳዩ እኔ በሌለሁበት የተደረገ አገር አቀፍ ስብሰባ ነበር? እሺ እኔ ምን አጠፋሁ? የስብሰባው ጊዜ ለምን አልነገራችሁኝም?😥 ቆይ ግን ለ5 አመታት በየቀኑ 3 ብር ሲቆረጥብኝ ኖሯል ማለት ነው?😥 እኔ ግን በቃ የአላዋቂዎች መጀመሪያ ነኝ።

#ሜሩት፦ ደንበኛችን፦ አሁን ያለብዎትን ዕዳ ይክፈሉ፤ ሲቀጥል ከአሁን በኋላ ክፍያውን ማቋረጥ የሚፈልጉ ከሆነ STOP ብለው ለshort ኮዶቹ ይላኩና ደንበኝነትዎን መሰረዝ ይችላሉ፤ ይህን ጥሪ ስናቋርጥ Short ኮዶቹ እንዳይጠፉብዎ እኔ ኮዶቹን SMS አደርግሎታለሁ።

#እኔ፦ እባክሽን በነካ እጅሽ እዚያው አንቺው አትሰርዢልኝም? 😥 ወደ ፊት ሊመጡ ያሉ short ኮዶችም ካሉ "ይህ መስመር ለshort code የማይሆን ነው!" ብለሽ ከፊት ለፊቱ ጻፊበት! ይህን ሁሉ ደክመሽልኝማ ለዚህች አትጨክኚም!😥

#ሜሩት፦ ሳቀች! ካካካካ... (እንዴ ይህ ነገር እየተቀዳ ነው አይደል? አልሁ በልቤ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ቴሌን እንደ ተቋም እያሳቅሁ እንደሆነ ተሰማኝና ትንሽዬ ኮራ አልሁ😊)፤ ከረጅም ሳቋ መልስ በእርስዎ ሲም ካርድ እኔ መሰረዝ አልችልም፤ እርስዎ ይህን ስልክ ስንዘጋ ለሁለቱም STOP ብለው ይላኩ አለችኝ።

#እኔ፦ እሺ፤ ስልክ ዘግተን እኔ ወደ ቴሌብር ገብቼ ክፍያውን እስክፈጽም አሠራር እንዳይቀየር ብዬ ነው አልዃት፤ ደግሞ እዚህ አገር አንድ የሕግ መመሪያ የሚሠራው የአንድ ስልክ ጥሪ እድሜ ያህል መሆን ጀምሮ የለ?😥

#ሜሩት፦ ደንበኛችን፦ አያሳስቦት! አሁን ያልሁትን ገብተው ያድርጉ፤ በመጨረሻም፦ ስለ አገልግሎታችን አስተያየት ካሎት?

#እኔ፦ ውይ፦ በጣም ነው የማመሰግንሽ፤ ለእኔ ከእንግዲህ ቴሌ ማለት አንቺ! አንቺም ማለት ቴሌ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ። በልቤ ግን የቴሌ አለቆች ወዳጆቼ እነ ሜርሲ፣ በለጠ፣ ኢሳይያስና ሌሎች ወዳጆቼ ይህን ለምን እስካሁን አልነገሩኝም!?😥 ላግኛቸው ብቻ እያልሁ ወደ ቴሌብሬ እያዘገምሁ ነው እላችኋለሁ! (ደግሞ የ2 አመት Unlimited አለው ብላችሁ misscall አድርጉ አሏችሁ!😊)።

አሁን ልሂድና Short ኮዶቹን STOP! አንድ ጊዜ ብቻ enjoy ያደረግኋቸው መስሎኝ ግን ሳላውቅ የሕይወት ዘመን እስረኛ ያደረጉኝ ልምምዶቼንም STOP! 🛑

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


መልኳና ውስጧ!
---●---

🪙 ሳንቲም ሊጠይቁን ፊታችን የቆሙ አባት ከሳንቲሙ በፊት ጥቂት ጥበብ ጀባ ልበላችሁ አሉን፤ ቀጥለውም፦

"ጸጉሯን አሳምራ...
...እንደ ወሎ ፈረስ🐎
አንደኛ ክፍል ብቻ ናት...
... እስከ ዛሬ ድረስ።" 🐵

እኛ "ለውስጥ ውበት ቅድሚያ ይሰጥ!" የሚል መርህ ተምረን እሳቸውም ሳንቲማቸውን ወስደው ቀናችን ቀጠለ።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ቲዎሎጂና ባሮክ
---●---
ከበርናባስ በቀለ

#ባሮክ፦ "ቲዎሎጂ ያደርቃል ይባላል አንተ ምን ትላለህ?"

#እኔ፦ "ሥጋ 🥩 ያወፍራል" ይባላል አንተ ምን ትላለህ?

#ባሮክ፦ "እርሱ እንደ ሰው blood type ነዋ ባርኒ!"💉

#እኔ፦ በቃ፣ እንደሱ! Theology ስለተማረ ደረቆ ያየኸው ሰው እርሱ ደሙ ይጠና፤ ሲጀመር እርሱ የራሰ (የረጠበ) ልማታዊ ሰው ነበር!? 😎

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ወደ ፌስ ቡክ... 🙆‍♂️

ከተወሰኑ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ለመታቀብ ከነበረኝ መርሃ ግብር የተነሳ ላለፉት ሁለት አመታት ከፌስቡክ መውረዴ ወዳጆቼ ዘንድ ይታወቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ወደ ማርቆስ ዘበርጋ (Mark Zuckerberg) ቤት (Fb)ተመልሻለሁ፤ ምልከታዎቼን በዚያ ማጋራቴንም እቀጥላለሁ።

Barnabas Bekele ብላችሁ ብትገቡ ፌስ ቡኬን ታገኛላችሁ፤ ምልክት ይሆናችሁ ዘንድ በስኩዌር ሸሚዝና በblue-cut መነጽር የዘነጠ አንድ ዓይነ-ግቡ ወጣት በፊት ገጼ profile ላይ ገጭ ብሎ ታገኛላችሁ። 😉

አካውንቴን ለማግኘት ከተቸገራችሁ በውስጥ አንዳች ብትጽፉልኝ አግዛችኋለሁ፤ አሊያም እኔ ወደ እናንተ አካውንት እመጣለሁ። ፎቶ ለጥፋችሁ 97 ሰው tag የምታደርጉ ሰዎችን አይመለከትም!😥

በሉ እንግዲህ..😊

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


የትዝታ Economics
---●--
ከበርናባስ በቀለ

"ትላንት" ትዝታ፣ "ዛሬ" ኑሮ ሲሆን "የነገ ቀን" ደግሞ ተስፋ እንደሆነ አውቃለሁና ከትዝታዬ ለዛሬዬም ሆነ ለነገዬ አንዳች ለመማር እንደ አስፈላጊነቱ የኋሊት ሄጄ ራሴን ትላንት ውስጥ አያለሁ፤ ግን ትላንት መጥቶ ከነ ሙሉ ክብሩ ዛሬዬ ውስጥ እንዲኖር አልፈቅድለትም።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


እኔው የራሴ አምላክ!
----●-----
        ከበርናባስ በቀለ

የምኖርለት ነገር እርሱ ከእኔ የማይበልጥ ከሆነ የሕይወቴ ጌታና የልቤ አምላክ እኔው ራሴ ነኝ።

ከእኔ የሚበልጥ አምላክ እንዳለኝ ስዘምር ከርሜ ሊሆን ይችላል፤ ግን ኑሮዬን በማሰብ ቀንና ማታ እየጦዝሁ ዓለምን በራሴ ዛቢያ ለማዞር ስደክም ከተገኘሁ የእኔ አምላክ የስጋዬ ምኞት ነው።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ሕጻኑ ያልተገኘበት ልደት 🎂
----●-----

        ከበርናባስ በቀለ

የልደቱን መታሰቢያ ሳከብር የተወለደበትን ቀን ሳይሆን የተወለደበትን ዓላማ እያሰብሁ ነው። የልደቱን ዓላማ ዘንግቼ ስለ ቀኑ ጠብ እርግፍ ስል ብገኝ ከልደቱ ጌታ እተላለፋለሁ። እርሱ የተወለደበት ዓላማ ግድ የማይሰጣቸው ግና ልደቱን ለማክበር እቁብ ገብተው ቀኑን ሲጠባበቁ የቆዩ እልፍ ናቸው እኮ።

አንዳንዱ ልደቱን ሲያከብር የጌታችንን ዕድሜ እያሰበ (ውይ 2ሺህ ዓመት ሞላው እኮ እያለ) ሊሆን ይችላል። ከዘላለም በፊት የነበረና የሁሉ አስገኚ የሆነው ኢ-ውስኑ አምላኬ ስለ እኔ ራሱን በጊዜ ውስጥ ወስኖ ቢገኝም እርሱ ከዚህ ይልቃልና በዚህም አልታለልም።

ለአንዳንዱ ደግሞ የልደቱ በዓል ልብስ መቀየሪያ፣ ዘመድ መጠየቂያ እና አዲስ ቢዝነስ ለመጀመር መስፈንጠሪያ ነው። የእነዚህን ሰዎች የልደት concept እንዲህ እረዳለሁ፤ "ሕጻኑ ባልተገኘበት የሚከበር ልደት"!😥🎂

የልደቱ ዕለት "ሥፍራ የለንም" የተባለለት እርሱ የፍጥረተ ዓለሙ ፈጣሪ፣ ምንም የማይችል ሕጻን ሆኖ የተገለጠው እርሱ "ሁሉን በሥልጣኑ ቃል የደገፈው" ኃያሉ ጌታ እንደሆነ ቅዱሳት መጽሐፍት ነግረውኛልና በከተማው ባየዃቸው ሕጻን አልባ የልደት ድግሶች አልዋከብም።

የመታሰቢያው ትኩረቴ የልደቱ ቀን ዓላማ ላይ እንጂ በዕለቱ ክስተቶች ላይ አይደለም፤ እነዚህ ቀናት የአምላክን ሰው መሆን (ትሰግዎ) ከመቼውም በላይ የማስብባቸው ናቸው። ልደቱን የማስበው አንድ ድንቡሽቡሽ ያለ ሕጻን እያሰብሁ አይደለም፤ እርሱ የተወለደበትን ዓላማ አሳክቶ ወደ አባቱ ሄዷልና። ዛሬ ላይ እርሱ በሰማያት በግርማው ቀኝ እንጂ በተወለደበት ግርግም ውስጥ አይደለምና!

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ድንቄም ስልጣኔ! 😉
----●-----
        ከበርናባስ በቀለ

ለባዕዱ ምድር አቆጣጠር እጅ ሰጥታችሁ ባሕር ማዶ ለምትኖሩ ኢትዮጵያን ወዳጆቼ እና እዚሁ አገር ሆናችሁ ደግሞ ፈረንጅኛ ለምታድሩ ወንድሞቼ መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ! በመላው ዓለም ያላችሁ የዚህ አጭር መልእክቴ ጭብጥ ሰለባ የሆናችሁ (😉) ሕዝቦች እንኳን ከ2023 ወደ 2024 በሰላም አሸጋገራችሁ።

እናንተ በGregorian Calendar የምትተዳደሩ ሰዎች ለመሆኑ ዘመን መለወጫዎች አሏችሁ? ወይስ እናንተ ጋር ዘመን የሚለወጠው በአመት አንዴ ብቻ ነው? እንደርሱ ከሆነ በጣም ተሸውዳችኋል። ይህን ካነበባችሁ በኋላ ቶሎ የነገድ (የብሔር) አለቆቻችሁን ሰብስባችሁ ተወያዩ።

የምር እስቲ ንገሩኝ፦ ስንት ዘመን መለወጫዎች አሏችሁ? ስለ እኛ ከጠየቃችሁኝ ደረቴን ነፍቼና አፌን ሞልቼ እነግራችኋለሁ። By the way እኛ እንደ አገር አንድ ካላንደር ግና በብሔሮቻችን ቁጥር ዘመናት ያሉን ብርቅዬ ሕዝቦች ነን። አታውቁንማ!

እናንተስ ነጭ ሕዝቦች (you ፈረንጂ people) በየብሔራችሁ ዘመን መለወጫ አታከብሩም? የብሔር ብሔረሰቦች ቀንስ የላችሁም? በብሔሮቻችሁ ዘመን መለወጫ በዓልስ የአገራችሁን ባንዲራ ወዲያ ጥላችሁ የክልሎቻችሁን ባንዲራ አታውለበልቡም?

ስሞትላችሁ! እስቲ ልጠይቃችሁ፦ አስፓልት ዳር በሚገኙ ቆርቆሮዎች ሁሉ ላይ የክልሎቻችሁን ባንዲራ ቀብታችሁ ዘመን መለወጫችሁን አታከብሩም? እሺ የበዓላቱ ቀን መንገድ አትዘጉም??? እናንተም ብሎ ስልጡን ሕዝብ!ድንቄም ስልጣኔ!

እናንተ አውሮፓውያን፦ ጊፋታ እናንተ ጋር የለም? ፍቼ ጫምባላላስ አታከብሩም? ሕዝባችንን እንዴት ብትንቁት ነው? እናንት አሜሪካዊያን እውን እናንተ ጋር ዳራሮ የለም? ያሆዴስ አይታወቅም? ሌላውስ ይቅር! ኢሬቻን በየትኛው ወር ነው የምታከብሩት? እሺ ቆይ፦ ዮዮ ማስቃላስ? ዘመን መለወጫ ሆኖ አታከብሩትም? ግን በጤናችሁ ነው?😥

እኛ ጋር እኮ ከአመቱ መባቻ እስከ መዝጊያ ዓመት በዓል ነው። በአገራችን ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች አሉ፤ ሁሉም ዘመን መለወጫ አላቸው። የአንዱን ብሔር ዘመን መለወጫ ለማክበር ቢያንስ አንድ ወር ዝግጅት ይደረጋል፤ ከዚያም የበዓሉ ወቅት ለ3 ቀናት መንገድ ይዘጋል! ከዚያ መቀወጥ ነዋ። ያለዚያ አገር ምኑን አገር ሆነ ታዲያ!?

የምር እናንተ ግን ከላይ የጠቀስኳቸውን በዓላት ሁሉ አታከብሩም? እና እንዴት ነው ዓመቱ የሚሄድላችሁ? የብሔራችሁን ልዩነትስ እንዴት ነው የምታስጠብቁት? ይህ ካልሆነ የምር አገር ወዳድ አይደላችሁም! ወይም አልሰለጠናችሁም። እኛ እንደሆንን አገር ወዳድነት ማለት ብሔር ተኮርነት መሆኑ ገብቶን ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ማማ ለመውሰድ ቀን ተሌት በመሥራት ላይ እንገኛለን። 😉

ለማንኛውም መልካም 2024!😊

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


"ፋሚሊ Planning አልጠቀምም!"😎
----●----
       ከበርናባስ በቀለ

ዛሬ ከክፍለ አገር ወደ አዲስ ጉዞ ላይ ነበርሁና ባለሁበት ባስ ሁለት እንስቶች ከአጠገቤ ተሰይመዋል፤ ጉዞ ላይ ነን!

አንዷ እህት፦ "እኔ በFamily planning አላምንም! ከባለቤቴም ጋር አውርተናል፤ ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው! በቃ እርሱ (ከሰማይ) ከሰጠኝ ዝም ብዬ ነው የምወልደው። ደግሞ ምንም ሳላጎድልባቸው ላሳድጋቸው እንደምችል እርግጠኛ ነኝ።"

እኔ፦ የኔ እህት ደህና ነሽ? ይህን እንድትዪ ያነሳሳሽ ምንድነው? (በልቤ ይኽ "የስበት ሕግ" የሚሉት ነገር እኮ ጉድ ያመጣል!) እንደው ከአንዱ የክፍለ አገር ከተማ ወደ ሌላኛው ለመሸጋገር አሥራ ዘጠኝ ጊዜ ለፍተሻ የምትወርጂበት በዚህ አገር ሆነሽ ይህን ማሰቡ አይከብድም። ጊዜውስ ይኖርሻል?

እርሷ፦ "ልጅ እኮ በረከት ነው። ደግሞ ብዙ ተባዙ ተብሎ ተጽፏል! ይህን አትቀበልም?"

እኔ፦ አዎን! በርግጥ ብዙ ተባዙ ተብሏል፤ ይኸው በዛን እኮ! በዓለማችን ላይ ካሉ ጦርነቶች መንስዔዎች አንዱ መብዛታችን እንደሆነ ይጠረጠራል። ሞት በሚሉት ገላጋይ ተፈጥሮ ራሷን balance ባታደርግ ደግሞ ሌላ ታሪክ ውስጥ እንገባ ነበር።

ሲቀጥል፦ ከጠቀስሽልኝ የቅዱሱ መጽሐፍ ክፍል አንዳንድ ነገሮችን በአስተውሎት እንድታዪ ጥያቄዎችን ልሰንዝር፦

➲ ስለ መብዛት የተጻፈው ከመግዛት ጋር እንደሆነስ አስተውለሽ ይሆን? "ብዙ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሏት...ግዟትም" የምንበዛው ልንገዛ ነው። ማለቴ፦ ልናስተዳደር!

➲ ይህ አዳም ብቻውን ሳለ የተሰጠው ትዕዛዝ ከ8 (ስምንት) ቢሊዮን ሕዝብ በላይ ባለበት ዓለም ላለሽ ላንቺ በቀጥታ ሊተረጎም የሚችለው በምን አግባብ ነው?

➲ አዳምና ሔዋን ሁላችንንም የሚወክሉ የመጀመሪያዎቹ ስጋ ለባሾች ናቸው። ለእነርሱ የተሰጠው ይህ ትዕዛዝ ተከፋፍለን (ኮታችንን አውቀን) የምንወጣው እንጂ አንቺ ብቻ የምትከውኚው ነው?

➲ እውን ፈጣሪ (እግዚአብሔር) ዓለምን በሰው ልጅ መሙላት (ማጥለቅለቅ) ልጅን ለሰዎች የመስጠት ግቡ ሊሆን ይችላል?

➲ ከመብዛታችን የተነሳ ክፋታችንም በዝቶ እኔ አሁን በምኖርበት ከተማ (A.A) በቁጥር እጅግ ብዙ የሆኑ ጨቅላ ሕጻናት በየቀኑ መንገድ ላይ ተጥለው ይገኛሉ፤ የመብዛትን ትዕዛዝ ስታስቢ ካንቺ ጉልበት የወጡ ልጆች ላይ ብቻ ተመድበሽ ነው ወይስ? ታዲያ ስለምን ሙሉ ደርዘን ካልወለድሁ አልሽ!? ተወለደው የተጣሉትን ከልጅሽ እኩል ማስተዳደሩስ ማኅበራዊ ግዴታሽ ሊሆን እንደሚችል አታስቢም?

እነዚህ እህቶቼ በስም ዝናሽ እና ሔለን ይባላሉ፤ ያለ ዛሬ አይቼአቸው አላውቅም፤ ግን በዚህ ሃሳብ ምክንያት ተዋወቅን፣ ረጅም አወራን! ይህንንም አሳይመንት ተለዋወጥን። በሃሳቦች ለመወያየት ልባቸውንና አዕምሯቸውን ክፍት ያደረጉ በመሆናቸው አድንቄአቸዋለሁ።

እናንተስ ደህና ናችሁ? ልጆቻችሁስ ጥሩ ላይ ናቸው? ከአልፋ እስከ ዖሜጋ በነጻነት መውለድ አለብኝ የሚል ሰው በእናንተ መካከልስ ይኖር ይሆን? በተነሱት የውይይት ሃሳቦች ምልከታችሁ ምንድነው? የምወዳችሁ ነኝ።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ድምዳሜ በድምዳሜ!
----●---
       ከበርናባስ በቀለ

አንዳንዴ ዓለም ሁሉ የተቃውሞ ሰልፍ የወጣብኝና ብቻዬን የቀረሁ የሚመስለኝ ነገር አለ! እንደውም የስፖርቱን ሜዳ ትንታኔ መሥራት ሁሉ ይቃጣኛል፤ "እንዴ!!! ተፈጥሮና የዓለሙ 8 ቢሊዮን ሕዝብ እንዴት አንድን ሰው ይገጥማሉ? ይህ ጨዋታ ግን ፌር አይደለም! ስፖርት ፌዴሬሽን ግን በጤናው ነው?" እያልሁ አጉተመትማለሁ።

መለስ እልና ደግሞ ታሪክንና የሕይወት ቀያሹን ልዑል ምክር አስባለሁ፤ ድምዳሜዬም ትክክል እንዳልሆነ እያሰብሁ በታሪክ ውስጥ ሩጫቸውን በጨረሱ ሰዎች እየተገረምሁ እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።

ከዚያም የቅድሙን ድምዳሜ (Conclusion) በሌላኛው ድምዳሜ እከረብተዋለሁ። የሰው ልጅ ከደረሰበት መከራ በላይ የደረሰብኝ አንዳች ነገር የለም፤ ሰሞኑን እያለፍሁ ያለሁበት ነገር ባለፉት ዘመናት ሰዎች ያለፉበት ብሎም በዙሪያዬ ያሉ ወዳጆቼም የሚልፉበት ነው።

ለነፍሴም አንዳች ምክር እለግሳለሁ፤ ነፍሴ ሆይ፦ መጀመሪያ ለድምዳሜ አትቸኩዪ! ሲቀጥል ደግሞ "ይህ ለምን መጣብኝ" ሳይሆን "ለምን ዓላማ (for what purpose) መጣብኝ!?" በዪ! "ከዚህ እንዴት እወጣለሁ?" የሚለው የሚያሳስብሽን ያህል "ምን ተምሬ እወጣለሁ?" ለሚለውም ሃሳብ ተጨነቂ! እላታለሁ። በመጨረሻም የተሳሳተ ድምዳሜዋን በድምዳሜ እሽራለሁ።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


የዞረበት ዘመን!
----●----
ከበርናባስ በቀለ

ፍርድ
.....ከፍርድ ቤት፣
ቅድስና
....ከቤተ መቅደስ፣
ትምህርት
....ከተማሪ ቤት፣
ሰናይ ምክር
......ከመማክርት፣
መድኃኒቱ
ከሐኪሙ ቤት፣

የጠፋበት ግና ሁሉ ደህና እንደሆነ የሚለፈፍበት በክህደቱም ብዛት የዞረበት ዘመን ላይ ደርሰናል።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ሴት በዛ...
----●-----
        ከበርናባስ በቀለ

ቁርሴን ልበላ ዲላይት ሆቴል ቁጭ ብያለሁ (ከተማው የት ሊሆን እንደሚችል እናንተው ድረሱበት)፤ ከአስተናጋጆቹ አንደኛዋ "ሴት በዛ ጎመን ጠነዛ" እያለች ከወደ ግምጃ ቤት ትመጣለች።

ይህን ከሰሙት ሴት አስተናጋጆች መካከል አንዷ "ምን ለማለት ፈልገሽ ነው? አንድ ሰው ስላጠፋው ጥፋት ሴትን ልጅ አንድ ላይ መደፍጠጥሽ ለጤናሽ ራሱ ጥሩ ነው?" አለቻት።

እኔስ አባባሉንም ከሰማሁት ትንሽ ቆይቻለሁና ኦውው! ይህም አባባል ነበረን ለካ! እያልኩኝ እያሰላሰልኩኝ ነው። እልፍ ነገርን በአንድ ዐ/ነገር ማስቀመጥ የሚችል ገራሚ ወግ ያለን ሕዝቦች በመሆናችን ኩራት ተሰምቶኝ ይኸው ቁርሴን ገታ አድርጌ ስለ አባባልሎቻችንና ምሳሌዎቻችን እየተገረምሁ።

አባባሉን ከባሩዶቿ ቋት የመዘዘችው ሴት ለጠያቂዋ መለሰችላት፦ "በቃ ጉዳዩ ምንም ስብሰባ አያስፈልገውም! ሴት ሲበዛ ነገር ይንዛዛል፤ ሴት ሲበዛ ሐተታ ይበዛል! ይህን አታጪውም መቼስ? ለምን እንወሻሻለን!?" እያለች እነርሱ ይጨቃጨቃሉ እኔ ቁርሴን እየበላሁ፤ ነገሩ ዛሬ መቋጫ የሚያገኝ ከሆነ ውሳኔውን ጀባ እላችኋለሁ። አሁን ወደ ቁርሱ...

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


ውሎ ማደር!
-----●-----
    ከበርናባስ በቀለ

እርሱ፦ ዘመኑ ክፉ ነው! ወደ አምላክ መጠጋት ከመቼውም ጊዜ በላይ ያሻናል።

እኔ፦ ወደ አምላክ መቅረብ ስትል ወደየትኛው አምላክ? በምን መልኩ?

እርሱ፦ እኔ ቀኔን ከአምላኬ ጋር ጀምሬ ምሽቴንም ጭምር አውርቼው ነው የምተኛው፣ የምነቃውም።

እኔ፦ እባክህን ከአምላክህ ጋር በዚህ መልኩ ልዩ ቁርኝነት የፈጠርህበትን መንገድ አሳውቀኝ! የምሬን በቅንነት ነው የጠየቅሁህ።

እርሱ፦ ቀኔን ደክሞኝ ውዬ ወደ መኝታዬ ስሄድ "በሰላም ያዋልኸኝ በሰላም አሳድረኝ" ብዬ እማጸነዋለሁ። ማለዳ ከመኝታዬ ስነቃም እንዲሁ በሰላም ያሳደርኸኝ በሰላምህ አውለኝ እለዋለሁ። ቀኔን በእርሱ ጀምሬ በእርሱ የምጨርስ ነኝ ስልህ ታዲያ ይህን ለአንድም ቀን ሳላዛንፍ እንደማደርግ እየነገርኩህ ነው።

እኔ፦ በፍጹም ትህትና ልሞግትህ! ፈቃደኛ ነህ?

እርሱ፦ እንዴታ!

እኔ፦ የምትኖረው ውሎ ለማደር ነው እንዴ? ለዚያ ለዚያማ የዱር አራዊትም ውለው ያድሩ የለ? ተራራውና ወንዙ ጋራው ሸንተረሩም ውሎ ያልድራል!

እርሱ፦ ጉድ መጣ! እና ሌላ ምን ማድረግ ነበረብኝ?

እኔ፦ ለምንድነው ውለህ የምታድረው? እንዴት ነው ውለህ የምታድረው? በምንድነው ውለህ የምታድረው? ከማን ጋር ነው ውለህ የምታድረው? የሚለው "ያዋልኸኝ አሳድረኝ" ከሚለው ጸሎትህ እኩል አስፈላጊ ነው።

እርሱ፦ ትንሽ አወሳሰብህብኝ! አሁን ለአምላኬ ምድራዊ ነገሬ (ለምን፣ ከማንና እንዴት ውዬ ማደሬ) ምን ያደርግለታል?

እኔ፦ አምላክህ ሆኖ ግን ሁለንተናህ የማይመለከተው ከሆነ አምላኩ አንተ ነህ! እርሱ አምላክ አንተ በመልክህ ያበጀኸው እንጂ ያበጀህ አይደለም።

እርሱ፦ ፈላስፋ ነህ? እስቲ ፈታ አድርገህ አውራው።

እኔ፦ ለዛሬ አንድ ጠቅለል ያለ ሃሳብ ልንገርህና ስልክ ተለዋውጠን በቀጣይ ጊዜ እናውራ? (ከታክሲው መውረጃዬ እየደረሰ ስለሆነ)

እርሱ፦ እስቲ ልስማህ።

እኔ፦ የምኖርለት ዓላማ ውሎ ከማደር ካልበለጠ እየኖርህ አይደለም! የሕይወት ግብህ ከፀሐይ በታች ከሆነ አምላክህም ከፀሐይ በታች ያለ ነው።

እርሱ፦ በቅርብ መገናኘት እንችላለን?

እኔ፦ በደስታ ወንድሜ! ይኸው ስልኬ ደውልልኝ። ስላወራሁህ ደስ ብሎኛል። አመሰግናለሁ!

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊

20 last posts shown.