Posts filter


የአማኑኤል_ሆስፒታል_ታሪኮች_@Bemnet_Library4.pdf
16.5Mb
📚ርዕስ፦ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች
✍️ደራሲ፦ ዶ/ር ዮናስ ላቀው

አማኑኤል ሆስፒታል ብዙ የሚገመቱና የማይገመቱ ነገሮች ይከሰታሉ።

✈️ @Bemnet_Library


አይ ልጅነት ለካ እግዜር ለማንም አያዳላም!አንዱን ደሀ ሌላውን ሀብታም አድርጎት አይፈጥርም!እያንዳንዱ ሰው የራሱን ዕጣ ራሱ ይወስነዋል!ህይወት ለማንም ቃል አልገባችም።ይሄን ተረዳሁ በሌላ በኩል ደግሞ እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ....ለካ  ሀብታም ማለት ብዙ ገንዘብ ማከማት ማለት አይደለም!ለካ የሰው ልጅ የራሱን የህይወት መስመር ራሱ ነው የሚወስነው!ሀብት ለካ ቁሳዊ ነገር ነው።ቁሳዊ ነገር ደግሞ ቋሚ ሊሆን እንደማይችል ተረዳሁ።

📓ርዕስ፦ኦያያ ከፓሪስ መልስ
✍️ደራሲ፦አዘርግ

📚 @Bemnet_Library


"እያንዳንዱ ሰው ስለ ራሱ መስማት ይወዳል! መጠኑ ይለያይ እንጂ እያንዳንዱ ሰው መደነቅን፤ስለራሱ ሲወራ ማዳመጥን ይወዳል።ከእያንዳንዱ ሰው ይበልጥ ደግሞ ሴቶች ስለራሳቸው መስማት ጣፋጭ ምግባቸው ነው።ስለራሳቸው ስታወራላቸው ወሲብ ሲያደርጉ ከሚሰጣቸው ሀሴት የበለጠ ይደሰታሉ።ይህን ደካማ ባህያቸውን በመያዝ ካንተ የሚጠበቀው ጉጉት  መፍጠር ብቻ ነው

📓ርዕስ፦ቋ
✍️ደራሲ፦አዘርግ

📚 @Bemnet_Library


እንደዚህ አይነት ቪዲዮችን የበለጠ እንድንሰራ ፎሎና ላይክ ማድረጋችሁን አትርሱ!

📚 Bemnet Library

https://vm.tiktok.com/ZMBdNcvSG/


ይሄን ቪዲዮ ላይክ ላደረጉና የቲክቶክ ቻናላችንን ለተቀላቀሉ ጥቂት አንባቢዎች "አልገባኝም" የተሰኘውን ተወዳጅ መጽሐፍ በሶፍትኮፒ እንሸልማለን

https://vm.tiktok.com/ZMBek9toR/


"ወንድ ክብሩን ሊገነባ ይገባል።ሴት ደግሞ ክብሯን ልጠብቅ ይገባል።ሁለቱም የሚከበሩት በዚህ መንገድ ነው"

📚 @Bemnet_Library

8.6k 0 43 12 163

እንደ እውነቱ ከሆነ ህይወት አልፎ አልፎ ካልሆነ ልክ እንደፈለግነው አይሆንም፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ልክ እንደጠበቅነው አይሆኑም፡፡በእያንዳንዱ የህይወት ቅዕበት የምንወደው ነገር እንዳለ ሁሉ የማንወደው ነገርም ይኖራል፡፡ ሁልጊዜ አንተን የሚቃረኑ ሰዎች ይኖራሉ። ሁሌም እንቅፋቶች ያጋጥምሀል። ሁሌም ነገሮችን በሌላ መንገድ የሚሰሩ ሰዎች አሉ። 

ይህንን መሰረታዊ የህይወት መርህ ካልተቀበልክ ህይወትህ በሙሉ ጦርነት ይሆናል። ሰላማዊ ህይወት ለመምራት መታገል ያለብንን ጦርነቶችና መተው ያለብንን በጥንቃቄ መምረጥ አለብን፡፡ ዋነኛ ግብህ ሁሉም ነገር እንደፈለግከው እንዲሆን ሳይሆን በንፅፅር ጫና የሌለበት ደስተኛ ህይወት መኖር ከሆነ አብዛኞቹ ጦርነቶች ከተረጋጋ ስሜት የሚያስወጡ እንደሆኑ ይገባሃል።

📙ቀላሉን ነገር አታካብድ

📚@Bemnet_Library


ብልሁ ንጉስ


በአንድ ወቅት የዊራኒ ከተማን የሚያስተዳድር አንድ የተከበረና ብልህ ንጉስ ነበር፡፡ ንጉሱ በግርማው ይፈራ፣ በጥበቡም ይወደድ ነበር፡፡ በከተማው እምብርት የሚገኘው ጉድጓድ በቀዝቃዛና የሚያብረቀርቅ ውሃ የተሞላ ነው፡፡ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ስለሌለ ንጉሱንና ባለሟሎቹን ጨምሮ ሁሉም የከተማው ነዋሪ ከዚህ ጉድጓድ ነው የሚጠጡት፡፡

አንድ ምሽት ሁሉም በእንቅልፍ ተይዘው ሳለ አንድ ጠንቋይ ወደ ከተማው ይገባና ወደ ጉድጓዱ ውስጥ ሰባት የማይታወቁ ጠብታዎች ጨምሮ «ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ያብዳል» በማለት ተናገረ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ከንጉሱና ከግል አገልጋዩ በቀር ሁሉም ነዋሪዎች ከውሃው በመጠጣታቸው ጠንቋዩ አስቀድሞ እንደተናገረው ሁሉም አበዱ፡፡

የዛን ዕለት... ቀኑን ሙሉ በጠባብ መንገዶችና በገበያ ስፍራዎች የሚመላለሱ ሰዎች ‹‹ንጉሱ አብዷል፡፡ ንጉሱና ባለሟሉ አዕምሯቸውን ስተዋል፡፡ በእብድ ንጉስ መመራት የለብንም፡፡ ከዙፋኑ ልናወርደው ይገባል» ሲሉ አንሾካሾኩ፡፡

የዛን ዕለት ምሽት ንጉሱ በአንድ የወርቅ ዋንጫ የጉድጓድ ውሃ እንዲመጣለት አዘዘ፡፡ ከዚያም ለራሱ ግጥም አድርጐ ጠጣና ለባለሟሉ እንዲጠጣ ሰጠው፡፡ ይሄን ጊዜ በዊራኒ ከተማ ሃሴት ሆነ፡፡ ንጉሱና ባለሟሉ አዕምሯቸው ተመለሰላቸው ሲሉም አሰቡ፡፡

✍️ካህሊል ጂብራን
📚@Bemnet_Library




ዛሬን ብቻ ይኑሩ፡ በመሠረቱ እያንዳንዷ ቀን ትልቅ ዋጋ ያላት ስጦታ በመሆኗ እንደዚያ አድርገው ይመልከቷት፡፡ ትናንት ያለፈ ነገ ደግሞ ገና ያልመጣ በመሆኑ በእጅዎ ያለዎትን እና ሊቀይሩት የሚችሉትን ዛሬን የትኩረት ማዕከልዎ ያድርጉ፡፡

📓የለውጥ ጥበብ
✍ዴል ካርኔጌ

📚@Bemnet_Library


ማኦ ዜዱንግ ስለ ልጅነት ትዝታው እንዲህ ሲል ፅፏል፤

“ትንሽ ልጅ ሳለሁ ከእናቴ ጐጆ አጠገብ በጣም የተዋበ የአትክልት ስፍራ ነበር፡፡ የአትክልት ስፍራው በጣም የተዋቡ አበቦች ስለነበሩት ሰዎች ከሩቅ ቦታ እየመጡ ይመለከቱት ነበር፡፡

በዚህ መሃል አሮጊቷ እናቴ ታመመችና አልጋ ላይ ዋለች፡፡ እናቴ እርጅናዋም ሆነ ህመሟ አላስጨነቃትም፤ ብቸኛው ስጋቷ የአትክልት ስፍራው እጣ ፈንታ ነበር፡፡” ትንሹ ማኦ፡-
“አታስቢ፤ የአትክልት ስፍራሽን እኔ እንከባከብልሻለሁ፡፡” በማለት ቃል ገባላት፡፡ እናም ማኦ ከጠዋት እስከ ማታ እየዋለ የእናቱን የአትክልት ስፍራ ተንከባክቦ፡፡

ከአንድ ወር በኋላ እናቱ ከህመሟ አገግማ ትንሽ መራመድ እንደቻለች በቀጥታ የሄደችው የአትክልት ስፍራውን ለመመልከት ነበር፡፡ የአትክልት ስፍራውን ሁኔታ ስትመለከትም በጣም ደንገጠች፡፡ ድራሹ ጠፍቷል፡፡ ሁሉም እፅዋት ደርቀውና አበቦቹም ጠውልገው ነበር፡፡

በጣም ተረብሻም ማኦን፡-” አንተ ደደብ! ቀኑን ሙሉ የአትክልት ስፍራ ውስጥ ስታሳልፍ ምን እያደረግክ ነበር? ሁሉም አበቦች ጠውልገዋል፤ የአትክልት ስፍራው ወድሟል፤ ሁሉም ተክሎች ሊሞቱ ተቃርበዋል፤ እንደው ምን ስታደርግ ነበር?” አለችው፡፡

ማኦ ማልቀስ ጀመረ፡፡ እሱ ራሱ ግራ ገብቶት ነበር፡፡ በየእለቱ የአክልት ስፍራውን ቀኑን ሙሉ ሲንከባከብ ይውል ነበር፡፡ ነገር ግን በማያውቀው ምክንያት እፅዋቶቹ እየደረቁ ነበር፡፡

እያለቀሰ እንዲህ ሲል ተነገረ፡-” በእጅጉ ነበር የተንከባከብኩት፡፡ እያንዳንዱን አበባ እየሳምኩ ፍቅር እየሰጠሁት ነበር፡፡ እያንዳንዱ ቅጠል ላይ የነበረውን አቧራ እየጠረግኩ ሳፀዳው ነበር፡፡ ምን እንደተከሰተ አልገባኝም፡፡ አበቦቹ እየጠወለጉ ሲሄዱ እየጠረግኩ ሳፀዳቸው ነበር፡፡ ቅጠሎቹ እየደረቁ የአትክልት ስፍራውም እየሞተ ነበር፡፡

” እናቱ መሳቅ ጀመረች፤ እናም እንዲህ አለችው፡- “ደደብ ነህ! የአበቦቹ ህይወት አበቦቹ ላይ፣ የቅጠሎቹም ህይወት ቅጠሎቹ ላይ እንዳልሆነ ገና አታውቅም!”፡፡

የአንድ ተክል ህይወት የሚገኘው ለማንም ከማይታይ ቦታ ውስጥ ነው፡፡ ህይወቱ የሚገኘው ከመሬት ስር ተደብቀው በሚገኙት ስሮቹ ውስጥ ነው፡፡ ስሮቹ እንክብካቤ ካላገኙ አበቦቹና ቅጠሎቹም እንክብካቤ ያጣሉ፡፡

የቱንም ያህል ቢሳሙ፣ ፍቅር ቢሰጣቸው፣ ከአቧራ በፀዱ ከመጠውለግ አያመልጡም፡፡ ስለ አበቦቹ ሳትጨነቁ ስሮቹን ከተንከባከባችሁ ግን አበቦቹ ራሳቸውን ይንከባከባሉ፡፡ አበቦች በስሩ አማካኝነት ያብባሉ እንጂ፣ ሁኔታው የተገላቢጦች አይደለም፡፡

📓የነፍስ መንገድ
✍ኦሾ

📚@Bemnet_Library

9.6k 0 36 2 108

እንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና በመራህያን

A1, A2, B1 and B2 and C1 Level
    •Online or Inperson

Another service:
TOEFL exam preparation and
IELTS exam preparation also given
To register:
       ☎️
0989747878
0799331774

አድራሻ፦ 22 ከ ጎላጉል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan


"አስተዋይ ሰው ከእሱ የበለጠ አስተዋይ ሰውን ቀጥሮ ያሰራል።"


📚ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍️ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ

📚 @Bemnet_Library


"የሆነን ነገር መግዛት አልችልም ወይም "አቅም የለኝም" አትበል።ያ የድሃ ሰው አመለካከትና አስተሳሰብ ነው።ይልቁኑ "እንዴት መግዛት እችላለሁ" ብለህ ራስህን ጠይቅ።

📚ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍️ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ

📚 @Bemnet_Library


📚ርዕስ፦አልገባኝም
✍️ደራሲ፦ዮናስ ዘውዴ

✈️ @Bemnet_Library

14.8k 0 26 19 169

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ለረጅም ጊዜ በዝምታ መቆየት ትችላለህ? የስነ-አእምሮ ጠበብት እንደሚሉን ከሆነ ለሶስት ሳምንታት ዝም ብለህ ከቆየህ፣ከዚያ ከራስህ ጋር ማውራት ትጀምራለህ።ያን ጊዜ ሁለት ቦታ ትከፈላለህ ማለት ነው።ተናጋሪም አድማጩም አንተ ትሆናለህ።በዝምታህ ፀንተህ ሶስት ወር ከቆየህ ደግሞ፤የእብዶች ሆስፒታል በር ወለል ብሎ ይከፈትልሀል።ምክንያቱም አሁን ሰው አጠገብህ ኖረ አልኖረ ግዴ የለህም።ታወራለህ፤ማውራት ብቻም አይደለም፤መልስም ትሰጣለህ።አሁን ምሉዕ ሆነሀል፣የሌላ ሰው ጥገኛ አይደለህም።እብድ ማለት ትርጉሙ በቀላሉ ይሄው ነው

እብድ ማለት መላውን አለም በራሱ ውስጥ ማግኘት የሚችል ማለት ነው።ተናጋሪ እሱ ነው፤አድማጭ እሱ ነው፤ተዋናዮ እሱ ነው፤ተመልካቹ እሱ ነው።በቃ ሁሉም እሱ ነው፤አለምን ሁሉ በውስጡ ያገኛታል።ራሱን ብዙ ቦታ ከፋፍሎታል።በዚህ የተነሳ ሁሉም ነገር ሽርፍራፊ ሆኗል።ሰዎች ዝምታን የሚፈሩት ለዚህ ነው፤ሳያስቡት ሊለፈልፉ እንደሚችሉ ይታወቃቸዋል።

📚ርዕስ፦ራስን ማግኘት
✍️ደራሲ፦ኦሾ

✈️ @Bemnet_Library

15.6k 0 89 12 195

አንድ የራስ ምታት የሚሰማውን ሰው ልታክሙት ትችሉ ይሆናል።ነገር ግን የሰውዬው የራስ ምታት ከምን እንደተነሳ በጥልቀት አትመለከቱም።ሰውዬው ጫና በዝቶበት፣ተጨንቆ፣ተደብቶ ሊሆን ይችላል።ምናልባትም ውስጡ ክፉኛ ተጎድቶ ይሆናል።ምናልባትም ብዙ ስለሚጨነቅ አዕምሮውን የሚያዝናናበት ጊዜ አላገኘ ይሆናል።ስለዚህም የምትሰጡት መድኃኒት ምልክቶቹን የሚያጠፋ ብቻ ነው የሚሆነው።ሆኖም በሽታው ከነስሩ ስላልተነቀለ በሌላ በኩል ብቅ ይላል።እንደኔ እምነት ግን ምልክቶች ሳይሆኑ ሰዎች ናቸው መታከም ያለባቸው።

📚ርዕስ፦ አካለ አዕምሮ
✍️ደራሲ፦ ኦሾ

📚 @Bemnet_Library


📣 በማስታወቂያ ስራችን ላይ ሁላችሁም ለምትሰጡን አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን።"

📂 Training Centers
📂 የቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ
📂 የትምህርት እቃዎች ሽያጭ
📂 ትሪትመንቶች
📂 የቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ
📂 Consultancy
📂 የሞባይል እና አክሰሰሪ
📂 እናም ሌሎችም ማስታወቂያዎችን

🖥በቀን/daily ፣ በሳምንት/weekly ፣ በ 2 ሳምንት/ bi weekly እንዲሁም በ ወር/Monthly እየሰራን እንገኛለን።ይሄ ስራ ንግዳቸውን ወይም ያላቸውን የተለያዩ ስራዎች ማስተዋወቅ ለሚፈልጉ ትልቅ ዕድል ነው

🗣 @Bemni_Alex አናግሩኝ👌


📚“በህይወቴ ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ መፀሀፍቶች ውስጥ አሉ። የኔ ምርጥ ጓደኛ ብዬ የምቀርበው ሰው ያላነበብኩትን መፀሀፍ “እንካ አንብብ” ብሎ የሚሰጠኝ ነው።” አብርሃም ሊንከን**

✅የተለያዩ መፅሐፍ በ Pdf  ድርሰቶች አጫጭር ታሪኮችን የሚያዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ!!!

ስሙ እንማር ይሰኛል !!
ቀኖትን እያሳመረ ማታዎትን እያደመቀ ምርጥ ምርጥ መፅሀፎች ይጋብዛቸዋል ።100%ትወዱታላችሁ

✈️https://t.me/Enmare1988/12032
✈️https://t.me/Enmare1988/12032


የመጀመሪያው ፍቅር ያዘኝ።የመጀመሪያው ፍቅር፤የእናትና የልጅ ፍቅር ነው።ከእናቴ ፍቅር ያዘኝ።ብን.....! አልኩ፥ እፍፍፍ...!በየደቂቃው ራሴን ፍለጋ ዐይን ዐይኗን ማየት ሆነ፨በፍቅር አበድኩላት።ፍቅር ማለት ለካስ ራስን በሌላው ውስጥ ማየት ነው።ሳድግ ለምን እንዲህ ውስብስብ መሰለኝ!? እሷም እንዲሁ ዐይኔ ዐይኔን ስለምታየኝ ፍቅር ሳይዛት አልቀረም!መተያየት በመተያየት ሆንን።

አንዳንድ ጊዜ እናቴ ዐይን ዐይኔን ስታየኝ ትቆይና በዚያው እ..ል..ም ትላለች።ብጠብቅ አትመለስም፥ብጠብቅ...፤እቁነጠነጣለሁ..ምንም መልስ የለም።አተኩሬ ዐይኗን ሳይ፤እኔም ዐይኗ ውስጥ የለሁም።የት እየሄደች ነው? እላለሁ።በብዙ ጉትጎታና መቁነጥነጥ ትመለሳለች።ስትመለስ ታዲያ የዐይኗ ነጭ፤ቀይ ደመና ያረግዛል።ትንሽ ቆይቶም ከዐይኗ ደመና፤ከፊያ ዝናብ መንጠባጠብ ይጀምራል።እኔ እረበሻለሁ።ደስ አይለኝም።ለምን እና ለማን እንደሆነ ሳላውቅ አጅባታለሁ።እናት ስታለቅስ ታሳዝናለች።ለቅሶዋ መቼም ቢሆን ስለ ራሷ አይደለም።

📓ርዕስ፦አለማወቅ
✍️ደራሲ፦ዳዊት ወንድምአገኝ

✈️ @Bemnet_Library

20 last posts shown.