ትምህርት ሚኒስቴር ከሬሜዲያል ፈተና ጋር በተያያዘ ውሳኔ አሳልፏል።
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ሳያመጡ የቀሩ ተማሪዎች በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ (ሬሜዲያል) ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው የማካካሻ ትምህርት ፈተናን ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች በሁለት የመንግሥት እና በ143 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የሪሜዲያል ፈተናውን ለመስጠት ባለመቻሉ በመስከረም 2016 ዓ.ም ፈተናውን እንዲወስዱ ተወስኖ እንደነበር ሚኒስቴሩ አስታውሷል።
በቅርቡ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቦርድ አባላት ጋር የተደረገ ውይይትን ተከትሎ ፈተናው ከነሐሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም እንዲሰጥ መወሰኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
Note፡-
• ፈተናው በበይነ መረብ ይሰጣል
• የፊዚክስ እና የታሪክ ኮርሶች በሪሜዲያል ፈተና ውስጥ አይካተቱም
(በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ለሐረር መምህራን ኮሌጅ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)
https://t.me/+-4xFxbBrBfIzNmE0