"እለሰ የአምኑ ርቱዐ ይሜህሩ ከመ ቃል ተቀብዐ በሥጋሁ" ቅዱስ ቄርሎስ።
።
ክፍል ፫
ቅባቶች ይህንን ቃል ይይዙና ቃል በሥጋ ተቀባ (ከበረ) ይላሉ። ይህ እጅግ አደገኛ ክህደት ነው። ቃል በሥጋ የሚቀባው (የሚከብረው) ቅድመ ዓለም ራሱ ክቡር አይደለምን? የመምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስን ቃል አጣሞ መተርጎም ትልቅ ነውር ነው። ሊቁ የትስብእትና የቃልን ተዋሕዶ በጋለ ብረት መስሎ አስተምሯል። ብረት በእሳት ሞቀ ይባላል እንጂ እሳት በብረት ሞቀ ይባላልን?! ሐሰ። አይባልም። እሳት በብረት ተያዘ ይባላል እንጂ ብረት በእሳት ተያዘ ይባላልን!? ሐሰ። አይባልም። ቃል በሥጋ ታመመ ይባላል እንጂ ሥጋ በቃል ታመመ ይባላልን?! በጭራሽ አይባልም። ቃል በሥጋ ከበረ ማለት ትልቅ ክህደት ነው። ቃል ቅድመ ተዋሕዶም፣ ጊዜ ተዋሕዶም፣ ድኅረ ተዋሕዶም ክቡር ነውና። ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስም ቃል በሥጋው ከበረ አላለም። ሊቁ ያለው "እለሰ የአምኑ ርቱዐ ይሜህሩ ከመ ቃል ተቀብዐ በሥጋሁ" ነው። የዚህም ትርጉሙ እንደሚከተለው ነው። "በትክክል የሚያምኑ ቃል ሥጋን እንደተዋሐደ ያስተምራሉ" ማለት ነው። "በሥጋሁ" ሲል "በ" የሚለው አገባብ በግእዝ ቦታ የገባ ነው። ይኽውም በቅዱሳት መጻሕፍት በስፋት ይገኛል። ቀስተ ዮናታን ኢተቀብዐት በቅብዕ ዘእንበለ ደመ ኃያላን ሲል "በቅብዕ" ያለው ቅብዐ ሲል ነው። ኦሪት ወነቢያት ሰበኩ በክርስቶስ ሲል "በክርስቶስ" ያለው ክርስቶስሀ ማለት ነው። "በ" በአገባብ "ን" ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ በሥጋሁ ሲል "ሥጋን" ተብሎ ይተረጎማል። "ተቀብዐ" ተዋሐደ ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ "ቃል ተቀብዐ በሥጋሁ" ማለት ቃል ሥጋን ተዋሐደ የሚል ትርጉም አለው። ሊቁ መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ የተናገረው ይህንን ነው። ቃልን በሥጋው ክብር አገኘ ማለት ቀድሞ ክቡር አልነበረም የሚል ትልቅ ክህደት ነው።
።
ተቀብዐ-ተዋሐደ ተብሎ እንደሚተረጎም ተጨማሪ ምሳሌ በመጽሐፈ አርጋኖን "ዘተቀባዕከ ሥጋሃ ለማርያም" ይላል። በዚህ ጊዜ "የማርያምን ሥጋ የተዋሐድክ" ተብሎ ይተረጎማል። ቅባቶች ተዋሐደ ተብሎ አይተረጎምም ካሉ ግን የዚህ ትርጉም "የማርያምን ሥጋ የተቀባህ" የሚል ትርጉም ያመጣባቸዋል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሥጋ ማርያም ቅብእ ሊሆን ነው። ይህ ደግሞ ተሰምቶ የማይታወቅ ታላቅ ክህደት ነው። ዘተቀባዕከ ሥጋሃ ለማርያም- የማርያምን ሥጋ የተዋሐድክ ተብሎ ይተረጎማል። ይህም ቃል ከድንግል ማርያም የነሣውን ሥጋ መዋሐዱን ይገልጽልናል። በዚህ አገባብ ነው ቃል ተቀብዐ በሥጋሁ- ቃል ሥጋን ተዋሐደ ተብሎ የተተረጎመው። ዶክተር ሥርግው ገላው መራኁተ ቅብዐት ወተዋሕዶ በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 174 "ጌታ መንግሥቱን ክህነቱን ከባሕርይ አባቱ ተቀብሎታል" ይላሉ። ለዶክተሩ የምጠይቀው ጥያቄ ጌታ መንግሥቱን ከባሕርይ አባቱ የሚቀበለው በመንግሥትነትማ አብ ወልድ መንፈስቅዱስ አንድ አይደሉምን?! እንዲያ ከሆነ ደግሞ አንዱ ሰጪ አንዱ ተሰጪ አይሆንም። ይህ የተነገረ ቃልን በመዋሐዱ መንግሥትነትን ገንዘቡ ስላደረገው ሥጋ ነው። ሃይ. አበ. ፻፫ "ዕሩያን ሥላሴ በህላዌ ወበመንግሥት ወስባሔ ወበፈጢረ ኵሉ ፍጥረት ወበኵሉ ግብር ዘይደሉ ለእግዚአብሔር" እንዲል። ሥላሴ በመንግሥት፣ በምስጋና፣ በመፍጠር አንድ ናቸውና። ሥጋ በቃል ገንዘብ ንጉሥ ሲሆን መንግሥትነትን ማን ሰጠው ቢሉ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስቅዱስ ናቸው። ሀብትን በመስጠት ሦስቱ አካላት አንድ ናቸውና። ሥጋ ይህንን ሁሉ ክብር ያገኘው ደግሞ ቃልን በመዋሐዱ ነው።
።
የፌስቡክ ገጼ
Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።
።
ክፍል ፬ ይቀጥላል
መ/ር በትረ ማርያም አበባው
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን