Big Habesha Tech


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Technologies


This is my user name @bighabesha
በተመሳሳይ ሰምና profile እንደትጭበርበሩ።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


Microsoft Skype የተሰኘውን ፕላትፎርም ሊዘጋ ነው።

ከAugust 29, 2003 ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የበረው Skype ከ21 አመት በኋላ ማለትም በmay 5, 2025 ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱ ሊቋረጥ ነው።

Microsoft ይህንን ፕላትፎርም በ2011 $8.5 billion አውጥቶ ቢገዛውም አሁን አሁን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተበለጠ መጥቷል።

የተጠቃሚዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱና Teams የተሰኘው የmicrosoft ፕላትፎርም ይበልጥ ውጤታማ መሆኑ ለskype መዘጋት እንደምክነያት ይጠቀሳሉ።

የskype ተጠቃሚዎችም skype ላይ ያላቸውን chat historyና መረጃዎች ወደ Microsoft Teams ማዘዋወር ይችላሉ ተብሏል።

በርካቶቻችን ለመጀመሪያ ጊዜ video call ከማውራት ጀምሮ በርካታ ትዝታዎች በዚህ ፕላትፎርም ላይ አሉን።

በዚህ መረጃ የተሰማችሁን አሳውቁን።

©bighabesha_softwares


ስልካችሁ SAMSUNG ከሆነ ያለበትን እያንዳንዱን ችግር ቼክ የምታደርጉበት app
Samsung members

Play store ላይ ስለማታገኙት በዚህ ሊንክ ማውረድ ትችላላችሁ።
https://t.me/big_habesha/287

ስለ አጠቃቀሙ ከደቂቃዎች በኋላ TikTok ላይ video post አደርጋለሁ።

9k 0 52 7 45

Adobe Photoshop በSamsung Galaxy ስልኮች ላይ መስራት ሊጀምር ነው

ዝነኛው የፎቶ ማቀናበሪያ ሶፍትዌር Adobe Photoshopን ከአንዳንድ ገደቦች ጋር በስልክ መጠቀም ሊቻል ነው።ይህም ለጊዜው የታቀደው በgalaxy ስልኮች ላይ ነው።

ይህ መተግበሪያ በርካቶች ከሚውቁት የተለየ ሲሆን ለተጠቃሚዎችም ከዴስክቶፕ version አንፃር ቀላል እና ለአጠቃቀም ምቹ ነው።

የዴስክቶፕ versionኡን ሙሉ በሙሉ ባይተካም መሰረታዊ የሆኑ edits ለማድረግ ያስችላል።

አሁን ላይ ካሉት የስልክ editing softwares በእጅጉ የተለየ ነው የተባለው ይህ መተግበሪያ ብዙ በAI የተደገፉ features እንደሚያካትትም ተገልጿል።

በዚህ ሀሳብ ዙሪያ አስተያየታችሁን አካፍሉን።
©bighabesha_softwares

11.1k 0 12 13 114

✨20% ቅናሽ✨

የስልጠና አማራጮች:

•  💻 Full Stack Web Development (HTML, CSS, JavaScript, React, Node.js,Express.js,Mongo Db...)
•  📱 Mobile App development (Flutter ለ Android እና iOS...)
•  🎨 Graphics Design (Photoshop, Illustrator, Branding,Logo design
Colour theory...)

ለምን ከእኛ ጋር ይማራሉ?

•  ✅ተግባራዊ ትምህርት!
•  ✅Real ፕሮጀክቶች ላይ መስራት!
•  ✅ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች መማር!
•  ✅100% የስራ እድል!

💫ጥቅሞቻቸን💫

•  ✨20% ቅናሽ!✨
•  📌በራስ መተማመን መጨመር!
•  📌የወደፊት ስራህን ማሳደግ!
•  📌ተመጣጣኝ ዋጋ!

አሁኑኑ ይመዝገቡ!
0975491734 / 0967482345 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @Qemer_online_training ያነጋግሩን


Meta ይቅርታ ጠይቋል።

ከትናት ጀምሮ የሚረብሹ የተለያዩ ቪዲዮዎች  reels ላይ በመምጣታቸው ምክንያት ብዙዎች X ላይ በመውጣት ሲነጋገሩበት ነበር። ይህንንም ችግር አሁን እንዳስተካከለው Meta አስታውቋል። በይፋም ይቅርታ ጠይቀዋል።

እኔ እራሴ check እንዳደረኩት Instagram reels ላይ ቪዲዮዎች ቢስተካከሉም የተለያዩ ችግሮች (bugs) ግን አሁንም አሉ።
ለምሳሌ
⚫ሁለት ወይም 3 ጊዜ scroll ካደረጋችሁ በኋላ scroll ማድረግ አትችሉም stack ያደርጋል።
⚫አንዳንድ ቪዲዮዎች ድምፃቸውን መዝጋት አትችሉም። አፕሊኬሽኑን ብትዘጉት እራሱ ድምፁ አይጠፋም። ስልካችሁን restart ወይም ዳታ እያበራችሁ ማጥፋት ይኖርባችኋል።

እናንተ ምን አስተዋላችሁ?

10k 0 14 2 61

Instagram ምን እየሆነ ነው?

ከትናንት ጀምሮ Instagram reel ላይ እጅግ ለማየት የሚሰቀጥጡ የግድያ፣ የእራ*ን ማጥፋት እነዲሁም ሌሎች አደገኛ ቪዲዮዎች በብዛት እየተለቀቁ ነው።

ይህንንም በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙዎች እየተነጋገሩበት ሲሆን ምክንያቱ ምን እንደሆነ Meta በይፋ ያለው ነገር የለም።

ይህ ነገር የሚረብሻችሁ ሰዎች ለተወሰነ ቀን Instagram ላይ ባትገቡ እመክራለሁ። ህጻናት ከሚጠቀሙበት ስልክ ላይም አፕሊኬሽኑን ብታጠፉት ይመከራል።

እንኳን ለህፃናት እኔንን እራሱ ዘገነነኝ።

አዲስ ነገር ካለ ተጨማሪ መረጃ አደርሳችኋለሁ።


አርቲስቶች ድምፅ አልባ (silent) የሙዚቃ አልበም ለቀቁ።

የእንግሊዝ መንግስት ያወጣወን ህግ በመቃወም 1ሺ የሚሆኑ አርቲስቶች ድምፅ አልባ "ሙዚቃ" ለቀቁ።

የእንግሊዝ መንግስት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ካምፓኒዎችን ለማበረታታት የቅጂ መብቶች በተመለከተ አዲስ ህግ ለማውጣት እየተንቀሳቀሰ ነው። በአዲሱ ህግ መሰረት ማንኛውም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዲቨሎፐር online ላይ ያገኛቸውን የአርቲስቶች ስራ ያለማንም ፈቃድ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንሱ ግብአት ማድረግ እንዲችሉ ይፈቅዳል።

ይህን ህግ በመቃወም ሰኞ ዕለት የተለያዩ አርቲስቶች በመሰባሰብ "Is This What We Want?” የተሰኘ ድምፅ አልባ አልበም ለቀዋል። 12 ትራኮችን የያዘውና ባዶ እስቲዲዮ ውስጥ የተቀረፀው ይህ "ሙዚቃ" Spotify ላይ ተለቆ ብዙዎቹ ተመልክተውታል።

አርቲስቶቹ "መንግስት የሙዚቃን ዘረፋ ህጋዊ ሊያደርግ አይገባም" በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

Spotify link click_here


የቀደሞ  ተማሪዎቻችን ስኬታማ ሆነዋል! አሁን የእርስዎ ተራ ነው! 🏆
✨የቀሩትን 4 ወንበሮች ለመያዝ ፈጥነው ይመዝገቡ✨
በ GRAPHICS DESIGN🎨 ስልጠና
      ✅ Photoshop
      ✅ Illustrator
      ✅ Branding
      ✅ Banner Design
      ✅ Business Card Design
      ✅ Logo Design እና ሌሎችም!

🔥100% የስራ እድል 🔥
   ፈጥነው  ይመዝገቡ!"


0975491734 / 0912970734 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @Qemer_online_training ያነጋግሩን

Follow us:
http://tiktok.com/@qemer_softwaretechnology
https://t.me/Qemertech


🔸📈🔸📈

Bybit በ1 ቀን ውስጥ 42.89 Million dollar የሚያወጣ ክሪፕቶ ከተለያዩ ኤክስቸንጆች ጋር በመተባበር እንዳይንቀሳቀስ freeze ማድረጉን አስታውቋል።

በጣም የሚያስቀው
ከተዘረዘሩት CEX ዉስጥ Bitget freeze ያደረገው 84 usdt ብቻ ነው።😂


አራቱንም አነፃፅሬ የትኛው የተሻለ እንደሆነ የሰራሁትን Video YouTube ላይ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።

https://youtu.be/KiFtI2CSdXU?feature=shared

16k 0 6 14 71

በአማርኛ search ለማድረግ የተሻለው generative AI የትኛው ይመስላችኋል?
Poll
  •   chatGPT
  •   Google Gemini
  •   DeepSeek
  •   Microsoft copilot
1075 votes


በኢትዮጵያ የተመረተ ኢ-ፓስፖርት ይፋ ሆነ

በTOPPAN Security Ethiopia እና በEthiopia investment holding የተመረተው ይህ ፖስፖርት የግለሰቡን የbiometric መረጃዎች የያዙ electronic chips ያካተተ ነው።

ይህ ፓስፖርት ደህንነትን ከማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያን ከማስተዋወቅ እና ለዜጎች ፈጥኖ ከመድረስ ረገድ አውንታዊ ተፅዕኖ እንዲሚኖረው ተመላክቷል።

በፊት አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ፓስፖርት የቆየ እና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይወጣበት እንደነበርም ተመላክቷል።

ከዚህ በኋላ ፓስፖርት ለሚያወጡ ሰዎች አዲሱ ዲጅታል ፓስፖርት የሚሰጣቸው ሲሆን ለዚህም ሲባል 1.5 ከሚልዮን በላይ ኢ-ፓስፖርት ተዘጋጅቷል።

ይህ ኢ-ፓስፖርት ከ25 አመት በላይ ለሆናቸው የአገልግሎት ዘመኑ 10 አመት ነው። ዋጋውም ነባሩ ፓስፖርት ሲሰጥበት ከነበረው ዋጋ ጋር እኩል ነው።

በተጨማሪም ይህ ፓስፖርት አለም የደረሰበትን የፓስፖርት ቴክኖሎጂ መጠቀሙ እና በከፍተኛ ሁኔታ የደህንነት ችግሮችን መቀነሱ ከነባሩ ፓስፖርት የሚለይባቸው ምክንያቶች ናነው።

በዚህ ፓስፖርት ዙሪያ ሀሳባችሁን አካፍሉን።
©bighabesha_softwares

18k 0 26 40 86

አለም አቀፍ የcrypto exchange የሆነው Bybit ላይ በደረሰ security breach 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ Ethereum ኮይን ተዘረፈ።

በEthereum cold wallet የደረሰው ይህ የሳይበር ጥቃት እስከዛሬ ድረስ ካጋጠሙ የክሪፕቶ ጥቃቶች ትልቁ ነው ተብሏል።

የBybit CEO, Ben Zhou እንዳስታወቀው 514,000 ETH የተዘረፈ ቢሆንም የተጠቃሚዎች ኮይን ምንም ጉዳት አልደረሰበትም ብሏል።

በዚህ የሳይበር ጥቃት ምክንያት የክሪፕቶከረንሲ ገበያው ቅናሽ ያሳየ ሲሆን ቢትኮይን ወደ $97,000 usdt ሲያሽቆለቁል Ether ደግሞ 2,700 ዝቅ ብሏል።

ዋና ሃላፊው እንደገለፀው ባይቢት ከብሊኦክቼይን ሴኪውሪቲ ኤክስፐርቶች ጋር በመተባበር የተወደበትን ክሪፕቶ ለማስመለስ እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል።
የተዘረፈው ክሪፕቶ በብዙ የክሪፕቶ አድራሻዎች ተበታትኖ ስለተላከ ተከታትሎ ለማስመለስ ከባድ አድርጎታል።


⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️
በFragment username እንገዛለን የሚሉ አጭበርባሪዎች መጥተዋል ተጠንቀቁ።

በfragment አማካኝነት username መሸጥ የምትችሉት እናንተ bid ወይም ጫረታ ካወጣችሁ ብቻ ነው።

ሌላው እናንተ ቅድሚያ የምትከፍሉበት ምንም አይነት አሰራር የለም። commission ምናምን sax ነው።

ተጨማሪ
Fragment ላይ በጣም ብዙ የሚሸጥ username እያለ የእናንተን ድንገት ልግዛችሁ የሚልበት ምንም ምክንያት የለም።

So ጥንቃቄ‼️‼️

18k 0 9 10 104

Meta 50,000 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የኢንተርኔት ኬብል በውቅያኖሶች ስር ሊዘረጋ ነው። 

የFacebook, Instagram እና WhatsApp እናት ኩባንያ የሆነው Meta የሚዘረጋው መስመር እንደ አሜሪካ፣ ብራዚል፣ ህንድና ደቡብ አፍሪካ ያሉ ሀገራትን ያገናኛል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም የአለማችን ረጅሙ የኢንተርኔት ገመድ ይሆናል። ይህም ከምድራችን ዙሪያ/circumference ይበልጣል።

አምስት አህጉሮችን የሚያካትተው ይህ ፕሮጀክት በAI መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ተገልጿል።

በተጨማሪም በዓለም በኢኮኖሚ እና ቴክኖሎጂ ላይ አውንታዊ ተፅእኖ ሊያሳድር  ይችላል።

95% የሚሆነውን የአለም ክፍል የሚያገናኘው የኢንተርኔት-ትራፊክ የሚተላለፈው ከውቅያኖስ ስር በተዘረጉ የኢንተርኔት መስመሮች አማካኝነት ነው።

©bighabesha_softwares




ለተለያዩ ድረገፆች ወይ የማህበራዊ ሚድያ አካውንቶች የይለፍ ቃላትን ስንሰጥ የምንጠቀመው
⚫26 Uppercase letters
⚫26 Lowercase letters
⚫10 ቁጥሮችን
⚫32 የተለመዱ (special characters)ን ነው።
ይህም በአጠቃላይ በእንግሊዝኛ ኪቦርድ 94 ካራክተሮችን ለይለፍ ቃልነት እንጠቀማለን።

እንበልና አንድ ድረገፅ ላይ መጠቀም የምንችለው የይለፍ ቃል የካራክተሮች ርዝመት 8 ቢሆን በአጠቃላይ 94^8 = 6,095,689,385,410,816 ወይም 6.1 ኳንቲሊየን ወይም 6 ቢሊየን ቢሊየን የተለያዩ የይለፍ ቃሎችን መፍጠር እንችላለን።

በሳይበር ሴኪዩሪቲ ዘርፍ የይለፍ ቃል ለመስበር ከምንጠቀምባቸው መንገዶች መካከል ዋናው Brute-force attack ይባላል።

Brute-force attack ማለት 1 user ሊጠቀመው የሚችለውን የይለፍ ቃል ለማወቅ የተለያዩ የይለፍ ቃላትን በተደጋጋሚ እያስገቡ በመሞከር መስራቱን ማረጋገጥ ማለት ነው።ይህም በጣም አድካሚና ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም ብዚ ጊዜ የተለመዱና ተገማች የይለፍ ቃላትን የሚጠቀሙ ሰዎችን በቀላሉ ሃክ ለማድረግ ይጠቅማል። Brute-force attack ተጠቅሞ የይለፍ ቃልን ለማወቅ የሚወስደው ጊዜ እንደምንጠቀመው የሃኪንግ ኮምፒውተር ፍጥነት፣ የተጠቀምነው የይለፍ ቃል ርዝመት እንዲሁም ተለዋዋጭነት (የተለያዩ ካራክተሮችን ቀላቅሎ መጠቀም) ላይ ይወሰናል።
safetydetectives.com ባወጣው ጥናት መሰረት በ2023 ብዙ ሰው የሚከተሉትን ቃላት በብዛት ለይለፍቃልነት ተጠቅመዋል።

123456, password, 123456789, 12345, 12345678, qwerty, 1234567, 111111, 1234567890, 123123, abc123, 1234, password1, iloveyou, 1q2w3e4r, 000000, qwerty123, zaq12wsx, dragon, sunshine, princess, letmein, 654321, monkey, 27653, 1qaz2wsx, 123321


አንድ ሃከር እነዚህን የይለፍ ቃላት በቀላሉ crack ማድረግ የሚችል ሲሆን ምናልባት 1ዱን ፊደል Uppercase ብናደርገው ወይም special character ብናስገባ ግን ለመስበር እጅግ ከባድ ይሆናል።


🔖የFULL-STACK MOBILE APP. DEVELOPMENT ስልጠና በቅርቡ ይጀመራል 🔥
✅ Flutter (ለ Android እና iOS)
✅ Setting up Flutter environment
✅ Dart basics
✅ Flutter basics
✅ layout in Flutter
✅ State management
✅ Navigation & routing
✅ Handling user input
✅ Networking
✅ Asynchronous Programming and more topic...
ድርጅታችን ላይ ኢንተርንሺፕ ይወጣሉ
"እርስዎስ ምን ይጠብቃሉ? 🚀 ይፍጠኑ አንዳያመልጣችሁ!
ውስን ቦታዎች ብቻ ቀርተዋል አሁኑኑ ይመዝገቡ!"
0975491734 / 0912970734 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @Qemer_online_training ያነጋግሩን

አዳዲስ መረጃ ለማግኘት የቲክቶክ ገጻችንን ይከታተሉ
http://tiktok.com/@qemer_softwaretechnology

https://t.me/Qemertech


Market cap ምንድን ነው?
(Crypto case)

Market capitalization ወይም market cap ብዙ ሰፋ ያለ ትርጉም ቢኖረውም ቀለል ባለ አገላለፅ "አንድ የክሪፕቶ ቶክን ገብያ ላይ ያለው ጠቅላላ የfiat መጠን ማለት ነው።"

ለምሳሌ አንድ ክሪፕቶ ገበያው ላይ የሚዘዋወረው መጠን 1 Billion token ቢሆንና የአንዱ ቶክን ዋጋ 0.5 usdt ቢሆን የዚህ token market cap 500M dollar ይሆናል።

Market Cap = Current Price per Coin x Total Circulating Supply


የቶክኑ ዋጋ ከጨመረ ያለው market cap ይጨምራል። ከቀነሰ ይቀንሳል።

Join our crypto channel @bighabesha_crypto


የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች ከአየር ላይ Carbon dioxide (CO2) በመምጠጥ ወደ ነዳጅ መቀየር የሚችል ቅጠል ሰሩ።

ይህ ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ ግኝት በጣም ጥቃቅን የመዳብ አበባዎችን በመጠቀም ወደ multi-carbon products ይቀይራል። ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ ጠቀሜታ ወዳላቸው ግላይስሬት፣ ላክቴት እና ፎርሜት ወደ መሳሰሉ ተረፈ ምርቶች ይቀይራል።

ይህ ምርምር ከትልልቅ ኢንዱስትሪዎች የሚመጣውን የካርቦን ልቀት በመቀነስ የአለማችንን አየር ንብረት እንደሚያስተካክል ታምኖበታል።

ዝርዝር መረጃ ከፈለጋችሁ Click me

20 last posts shown.