"ፍርዱ በህግ ላይ ያለን አመኔታ የሚያሳጣ ነው!" - ሚኪያስ (የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል)
እኔ የህግ ባለሙያ ነኝ። ዛሬ በወጣው መረጃ በጣም አዝኜአለው። እንዴት አባት ልጁን ደፍሮ 9 አመት ብቻ ሊቀጣ እንደቻለ ሊገባኝ አልቻለም።
ወንጀሉ እንደ ህጉ አንድ ወንጀል ብቻ አይደለም። ይልቁንም ተደራራቢ ወንጀል እንጂ ፦
1ኛ/ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል
2ኛ/ ተጠቂዋን በመደብደብ ወንጀል
3ኛ/ በዘመዳሞች የሚፈፀም ወንጀልን መጥቀስ ይቻላል።
የእነዚ ወንጀሎች ቅጣት ከወንጀሉ አፈፃፀም አንፃር ብንደምረው እና ሊነሱ የሚችሉ የወንጀል ማክበጃዋችን ብናይ፦
1ኛ/ የህዝብ አደራ የተጣለበት ዋና ሳጅን በመሆኑ
2ኛ/ እራሷን መከላከል በማትችል ልጅ ለይ ወንጀሉ መፈፀሙ ከዛም በላይ በቅርብ የስጋ ዝምድና (ልጅ) ለይ መፈፀሙ በየትኛውም ሒሳብ የትኛውም ያክል የወንጀል ማቅለያ ቢኖር 9 አመት ተገቢም ፍትሀዊም ህጋዊም አደለም።
ይህ ፍርድ እኮ ምን ያክል በህግ ላይ ያለን አመኔታ የሚያሳጣ ነው!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia