Posts filter


የመጀመሪያው ባዮሜትሪክ ስማርት ሽጉጥ

በአሜሪካ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ባዮሜትሪክ “ስማርት ሽጉጥ” ገበያ ላይ ዋለ።

ይህ ሽጉጥ የጣት አሻራ እና የፊት ለይቶ ማወቂያ ቴክኖሎጂን(facial recognition) በመጠቀም የተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ብቻ ሊጠቀሙት እንዲችሉ እና ከባለ ንብረቱ ውጪ መከልከል የሚችል የጦር መሳሪያ ነው።

ይህ ስማርት ሽጉጥ የሜካኒካል የተኩስ ዘዴዎችን በኤሌክትሮኒክ ስርዓት የተካ ሲሆን የሊቲየም-አዮን ባትሪ የሚጠቀም ስማርት ሽጉጡ ነው። በአንድ ጊዜ ቻርጅ ለብዙ ወራት መስራት እንደሚችል ተናግረዋል።

የስማርት ሽጉጥ እስከ አምስት የተመዘገቡ ተጠቃሚዎችን የሚፈቅድ ሲሆን ይህም ለቤተሰብ አገልግሎት መዋል እንዲችል ያደርገዋል፣ ሽጉጡ የተፈቀደለትን ተጠቃሚ እጅ ከለቀቀ፣ እራሱን በራሱ እንደሚዘጋ አሳውቀዋል።


via @breakthecurse


የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድጋሚ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግበት ነው።

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ላይ 0.50 ኪሎ ዋት ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች የፍጆታ ታሪፍ 0.60 ሳንቲም እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን፣

የአገልግሎት ክፍያ ተመንን በተመለከተ ለድኅረ ክፍያ አሥር ብር ከ95 ሳንቲም ሲከፍሉ፣ ለቅድመ ክፍያ አራት ብር ከ18 ሳንቲም እንደሚከፍሉ ሪፖርተር ያገኘው ሰነድ ያሳያል፡፡

የመኖሪያ ቤት ታሪፍን በተመለከተ ከ51 እስከ 100 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች አንድ ብር ከ49 ሳንቲም፣ ከ101 እስከ 200 ኪሎ ዋት ሁለት ብር ከ67 ሳንቲም፣ ከ201 እስከ 300 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች ሦስት ብር ከ84 ሳንቲም እንደሚከፍሉና በየኪሎ ዋቱ መጠን ክፍያው የሚለያይ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል።

@breakthecurse


ንቅሳት የካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚጨምር አዲስ ጥናት አመላከተ።

በደቡብ ዴንማርክ እና በሄልሲንኪ ዩኒቨርሲቲዎች የተደረገው ጥናት የንቅሳት ቀለም ለቆዳ ካንሰር እና ሊምፎማ ካንሰር ያለን ተጋላጭነት እንደሚጨምር አረጋግጠዋል።

የምርምር ቡድኑ የንቅሳት ቀለሞች ከተወጉበት አካባቢ በተጨማሪ ወደ ሌሎች የሰውነት አካባቢዎች እንደሚሰራጩም የተመለከተ ሲሆን ቀለሞቹ ሰውነትን ሊጎዱ ከሚችሉ ንጥረ ነገሮች ለመጠበቅ ወደ ሚረዱት እና ሊምፍ ኖድ ወደሚባሉ የሰውነት ክፍል ማለትም በአንገት፣ ብሺሺት፣ ብብት፣ ደረትና ሆድ አካባቢ በዕብጠት መልክ እንደሚቀመጡ ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል።

በዚህም ምክንያት የተከማቸው ዕብጠት ያልተለመደ የሕዋስ እድገትን ሊያስከትል እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰር ሊያመራ እንደሚችል እና ንቅሳቶች መጠናቸው በተለቀ እና ቆታቸው በጨመረ ቁጥር በሰውነት ውስጥ ብዙ ቀለም እንዲከማች ያደርጋሉ ሲሉ አብራርተዋል።

መጠኑ ትልቅ የሆነ ንቅሳት ያላቸው ግለሰቦች ምንም ንቅሳት ከሌለባቸው ሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ የካንሰር ተጋላጭነቱ በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ እንደሆነም በጥናቱ ተመላክቷል።

via @breakthecurse


የኮንትሮባንድ ንግድ በመስፋፋቱ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጠመ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮንትሮባንድ ንግድ በመስፋፋቱና የጥሬ ገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ እጃቸው ላይ ገንዘብ ያላቸው አትርፈው መሸጥ ጀምረዋል የተባለ ሲሆን እንደማሳያም 90,000 ብር በ100,000 ብር ይሸጣል፡፡

ከባንኮች አንድ ሰው በቀን ከ500 ብር በላይ ማውጣት አይችልም ሲሉ የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት አባል እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ መብራቱ አለሙ የተናገሩ ሲሆን አያይዘውም የጥሬ ገንዘብ እጥረት በባንኮች መፈጠሩን እና የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋትን የተመለከቱት በምርጫ አካባቢያቸው በመተከል ዞን በመገኘት ባደረጉት ህዝባዊ ውይይት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

via @breakthecurse


ከነ መሀይምነቴ አስመርቆኛል በሚል ትምህርት ቤቷ የከሰሰችው ተማሪ

አሌይሻ ኦርቲዝ የተባለችው የ19 ዓመት ተማሪ ከአንድ ዓመት በፊት ነበር የሁለተኛ ደረጃ ትምህረቷን በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቀች ሲሆን በአሜሪካዋ ኮኔክቲከት ግዛት ባለ ትምህርት ቤት ትምህርቷን የተከታተለችው ይህች ተማሪ፤ ከፍተኛ ውጤት ማምጣቷን ተከትሎ የስኮላርሽፕ እድል ተመቻችቶላት በመማር ላይ ነበረች፡፡

ይሁንና የተማሪ አሌይሻ መጻፍ፣ ማንበብ እና ተያያዥ ክህሎት አብረዋት ከሚማሩት ተማሪዎች በብዙ እጥፍ ወደኋላ እንደቀረች እና ከክፍል ጓደኞቿ ጋር እኩል መጓዝ ያልቻለችው ተማሪዋ፤ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን ተዘግቧል፡፡

“እኔ መሀይም ሆኔ ሳለ ትምህርት ቤቴ ግን በከፍተኛ ማዕረግ ብሎ ማስመረቁ ትክክል አይደለም” ያለችው አሌይሻ የቀድሞ ትምህርት ቤቷ ላይ ክስ መመስረቷን ተናግራለች፡፡

via @breakthecurse


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ አደረገ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል። ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።

በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፣ የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣ የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣ የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣ የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ አሳይተዋል።

ይሁን እንጂ ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔ በ12 በመቶ እንደነበረው ይቀጥላል።

የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች በ12 በመቶ እንደነበረው እንደሚቀጥልም ታውቋል።

via @breakthecurse


የዓለም ውፍረት ቀን

ማርች 4 ቀን በአለም አቀፍ ውፍረት ቀን በዓለም ዙሪያ ስለ ውፍረት፣ መንስኤዎቹ እና የመከላከያ እርምጃዎች ግንዛቤን ለመጨመር የአለም ውፍረት ቀንን ያከብራል።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እንደገለጸው በ2016 ከ650 ሚሊዮን በላይ የሆኑ አዋቂዎችን ከመጠን ያለፈ ውፍረት ይነካል። ዛሬ ይህ ቁጥር ወደ 800 ሚሊዮን ይጠጋል።

via @breakthecurse


የትራምፕን ፊት በ250 ዶላር ቢል ላይ የሚያስቀምጥ ህግን ይፋ አደረጉ

የሪፐብሊካን ፓርቲ፣ እንዲሁም ግራንድ ኦልድ ፓርቲ (GOP) በመባል የሚታወቀው፣ የህግ አውጭዎች የትራምፕን ፊት ምስል የያዘ በ250 ዶላር ምንዛሬ ላይ ለማስቀመጥ ረቂቅ ህግ ይፋ አደረጉ።


via @breakthecurse


ክርስቲያኖ ሮናልዶ CR7 ስም የተሰየመው ጋላክሲ

የሊዝበን ዩኒቨርሲቲ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ቡድን ሲአር7ን(CR7) በማግኘቱ ረገድ የመራው ሶብራል ስሙ በክርስቲያኖ ሮናልዶ አማካኝነት እንዳገኝው ተናግራል።

በሌላ በኩል ኮስሚክ ሬድሺፍት 7(Cosmic Redshift 7) ተብሎ ይጠራል።

ሲአር7ን(CR7) የሚለውን ስም ያገኝው ጁን 2015 ላይ ነው።

via @breakthecurse


ዓለም የዱር እንስሳት ቀን

ዛሬ፣ March 3 የዓለም የዱር እንስሳት ቀን፣ ስለ ምድራችን ልዩ ልዩ እፅዋት እና እንስሳት ግንዛቤን ለማሳደግ ታስቦ የሚውል ቀን ነው።

ዋና አላማው ስለ ዕፅዋትና እንስሳት አስፈላጊነት ግንዛቤን ለማስፋፋትና ምግብ፣ ንፁህ አየር እና ጤናማ አካባቢ ስለሚሰጥ የዱር አራዊት የተፈጥሮን ሚዛን ለመጠበቅ አስፈላጊነትን ለማስገንዘብ ነው።

ይህ ቀን ግለሰቦች ዘላቂ የአኗኗር ዘይቤዎችን እንዲቀበሉ፣ የጥበቃ ተነሳሽነቶችን እንዲደግፉ እና ሰላማዊ በሆነ የተፈጥሮ ዓለም ውስጥ እንዲኖሩ ለማነሳሳት ነው።

via @breakthecurse


የእግሊዝ የእግርኳስ ህግ አውጪዎች ማህበር አዲስ ህግ ማጽደቃቸዉ ተሰማ።

የሚባክኑ ደቂቃዎችን ለመቀነስ ሲባል አንድ ግብ ጠባቂ ለ 8 ሰከንድ ኳስ ይዞ የሚቆይ ከሆነ ለተጋጣሚው ቡድን የማእዘን ምት እንዲሰጥ የሚያደርግ ህግ ጸድቋል።

አዲሱ ህግ በአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ቦርድ (IFAB) ቅዳሜ በሰሜን አየርላንድ ባደረገው አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ የጸደቀ ሲሆን በአሜሪካ ከጁን 15 እስከ ጁላይ 13 በሚካሄደው የፊፋ የአለም ክለቦች ዋንጫ ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነግራል።

ፕሪሚየር ሊግ 2ን ጨምሮ ከ400 በላይ ግጥሚያዎች ላይ የተሞከረው ህግ ተግባራዊ የተደረገው አሁን ያለው የስድስት ሰከንድ ህግ በአግባቡ ባለመተግበሩ ነው። አሁን ዳኞች ግብ ጠባቂዎችን ከመቅጣታቸው በፊት የአምስት ሰከንድ ቆጠራ ያስጠነቅቃሉ።

በተጨማሪም፣ IFAB በተጨማሪም አጥቂው አካል ከሁለተኛ እስከ የመጨረሻው ተከላካይ እኩል ከሆነ ከጨዋታ ውጪ የሚደረጉ ሙከራዎችን እንዲቀጥል ድምጽ ሰጥቷል።

via @breakthecurse


🚘 የሚፈልጉትን መኪና በባንክ 50/50 አማራጭ አቀረብንሎ👇

🆕 BYD Qin plus
🆕 BYD Yuan up
🆕 BYD Yuan plus
🆕 Toyota BZ3
🆕 Toyota BZ4X
🆕 Toyota Rav4
🆕 ID6 and ID4
🆕 BYD E2 እና ሌሎችም

💥አዲስ እና ፀዴ ፀዴ 😉 መኪናዎች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በቀላል እና ፈጣን ሂደት፣ የሚፈልጉትን መኪና ከትንንሽ እስከ ቅምጡ መኪናዎች ሁሉንም ሞዴሎች አካትተን በባንክ አመቻችተን አቅርበንሎታል።

📞 ዛሬውኑን ያግኙን! +251911593030
+251911260700

👇ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👇

👉 https://t.me/NexlineBusinesGroup
👉 https://t.me/NexlineBusinesGroup


ዜጎቻቸው ዘግይተው ጋብቻ የሚመሰርቱባቸው ሀገራት

ጋብቻ የሰው ልጆች ህይወት ምርጫዎች መካከል አንዱ ሲሆን ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ቀድመው አልይም ዘግይተው ጋብቻ ፈጽማሉ፡፡

በወጣው መረጃ መሰረት የምስራቅ አውሮፓ እና እስያ ሀገራት ዘግይተው ጋብቻ ይፈጽማሉ የተባለ ሲሆን አፍሪካዊቷ ሞዛምቢክ ደግሞ በወጣትነታቸው ጋብቻ የሚመሰረትባት ሀገር ተብላለች፡፡

በኢስቶኒያ በአማካኝ የሀገሪቱ ዜጎች በ36 ዓመታቸው ጋብቻ ይመሰርታሉ የተባለ ሲሆን በሞዛምቢክ ግን በ23 ዓመታቸው የሚያገቡ ሲሆን ጣልያን፣ ስሎቬንያ እና ናሚቢያ በአማካኝ ዘግይተው ጋብቻ ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

Via @breakthecurse


ፖፕ ፍራንሲስ የመተንፈስ ችግር እንደገጠማቸው ቤተ ክርስቲያኗ አስታወቀች

ለሁለት ሳምንታት ያህል በሳንባ ምች ህመም ህክምና ላይ ያሉት የሮማ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የመተንፈስ ችግር እንዳጋጠማቸው ቫቲካን አስታወቀች።

ያጋጠማቸው የመተንፈስ ችግር ከህመማቸው ጋር የማይያዝ እንደሆነም ቫቲካን ገልጻለች። አርብ ዕለት ሳል ካጋጠማቸው በኋላ ተከታታይ ማስታወክ እና ድንገተኛ የመተንፈስ ችግር እንደ ገጠማቸው ተናግረዉ ፤ ዶክተሮቻቸው በአሁኑ ወቅት ስለ ፖፑ ሁኔታ ከመናገር ተቆጥበዋል።

Via @breakthecurse


ቻይና የኤአይ(Ai) ባለሙያዎቿ ወደ አሜሪካ እንዳይጓዙ አገደች

የዓለም ቴክኖሎጂ የበላይ ለመሆን ብርቱ ፉክክር ላይ የሚገኙት አሜሪካ እና ቻይና አሁን ደግሞ ፉክክራቸው ወደ ኤአይ ዞሯል፡፡

እገዳው የተጣለው ምዕራባዊን ሀገራት የቻይና ባለሙያዎችን አስረው ሊደራደሩ ይችላሉ ተብሏል።

የዲፕሲክ ኤአይ ሞዴል መስራች በቅርቡ በፓሪስ በተካሄደው የኤአይ(Ai) ጉባኤ ላይ እንዲገኝ ቢጋበዝም በፍራቻ ምክንት ሳይገኝ ቀርቷል ተብሏል

Via @breakthecurse


ዜሌንስኪ በደጋሚ ወደ ዋይታ ሀውስ ለመመለስ ጥያቄ አቀረቡ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ በደጋሚ ወደ ዋይታ ሀውስ እንዲመለስ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ትራምፕ ውድቅ አድርገነዋል ብለዋል። እሱ መዋጋት ነው የፈለገው እራሱ ይወጣው ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ደግሞ "ትናንት ባደረከው ነገር ተፀፅተሃል ወይ ተብሎ ከFox news ለቀረበለት ጥያቄ "ጥሩ አልነበረም ብዬ አስባለሁ" ሲል ምላሽ ሰጥቷል አያይዘውም " እኔ እውነተኛ ሆኜ መኖር ብቻ እፈልጋለሁ፣ እንዲሁም አጋሮቻችን ሁኔታውን በትክክል እንዲገነዘቡ እፈልጋለሁ፣ እኔም ነገሩን በትክክል ለመረዳት እፈልጋለሁ። ይህ የወዳጅነታችንን እንዳንጣስ ስለሆነ ነው።" ብሎ ተናገረ።

Via @breakthecurse


ኢለን መስክ ለ14ኛ ጊዜ የልጅ አባት መሆኑ ተገለጸ

የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኢለን መስክ ሰዎች ብዙ ልጆችን እንዲወልዱ በማበረታታት ይታወቃል እናም ለ14ኛ ጊዜ የልጅ አባት መሆኑ ተገለጸ፡፡

የ352 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት ባለቤት የሆነው ኢለን መስክ ቴስላ፣ X(Twitter)፣ ኒውራሊንክ ፣ ስፔስኤክስ እና ሌሎች በርካታ ኩባንያዎችን የመሰረተው እና ባለቤት የሆነው ኢለን መስክ በቅርቡ ወንድ ልጅ አባት መሆኑ ተገልጿል ።

Via @breakthecurse


ቻይና በዓለማችን ውድ የሚባለውን አዲስ ማዕድን አገኘች፡፡

የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና ቶሪየም የተሰኘውን ተፈላጊ ማዕድን ማግኘቷን አረጋግጣለች፡፡

አሁን ላይ የዓለም የሀይል ምንጭ ወደ ታዳሽ እና የከፋ የአካባቢ ብክለት የማያደርስ አማራጭ በመፈለግ ላይ ሲሆን የጸሀይ ሀይል፣ ከውሃ የሚመነጭ የሀይል አማራጭ እና የኑክሌር ሀይል ዋነኛ አማራጮች ናቸው፡፡

ዩራኒየም እና ቶሪየም ደግሞ ለኑክሌር ሀይል አማራጭ ዋነኛ ግብዓት ሲሆኑ ዩራኒየም ማዕድን እንደ ልብ አለመገኘት፣ ማዕድኑም በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት ብቻ መገኘቱ እጥረቱን ሲያባብሰው ቆይቷል።

ቻይና አገኘሁት ያለችው ቶሪየም ማዕድን አንድ ሚሊዮን ቶን መጠን አለው የተባለ ሲሆን፤ ሀገሪቱ የሀይል ፍላጎቷን ለ60 ሺህ ዓመታት እንድትሸፍን ይጠቅማታል ተብሏል፡፡ እንደ መንግስታዊው የሳውዝ ቻይና ፖስት ዘገባ ከሆነ ቶሪየም ማዕድኑ የተገኘው በደቡባዊ የሀገሪቱ አካባቢ ሞንጎሊያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ቶሪየም ማዕድን በተለይም የኑክሌር ሀይልን ለማመንጨት፣ ቴሌስኮፕ ሌንሶችን፣ ሴራሚክ፣ ካሜራዎችን እና ሌሎች ተፈላጊ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ለማምረት ይውላል ።

Via @breakthecurse


ጄዲ ቫንስ "አመስጋኝ አይደለህም ፤ያ ጥሩ ነገር አይደለም" ሲሉም ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ተናግረዋል ።

ይህንን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ በX ገጹ ላይ "አሜሪካ አመሰግናለሁ፣ ስለ ድጋፍህ አመሰግናለሁ፣ ለዚህ ጉብኝት አመሰግናለሁ። @POTUS፣ ኮንግረስ እና የአሜሪካን ህዝብ እናመሰግናለን።
ዩክሬን ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ያስፈልጋታል፣ እናም እኛ በትክክል እየሰራን ነው። ብለዉ አመስግነዋል ።

Via @breakthecurse


1446ኛው የረመዳን ወር ነገ ቅዳሜ የካቲት 22 ይጀመራል።

የካቲት 21/2017 በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጨረቃ ክትትል ኮሚቴ የረመዳን ወር ጨረቃ ዛሬ መታየቷን አስታውቋል። በዚህም መሰረት ነገ ቅዳሜ የ1446ኛው የረመዳን ፆም የመጀመሪያው ቀን ይሆናል። ዛሬ የተራዊህ ሶላት የሚጀመር ሲሆን ነገ የረመዷን ጾም ይጀምራል።

Via @breakthecurse

20 last posts shown.