🛩ገዳይ ድሮኖች (Slaughterbots)😱
በአለማችን ላይ ከባድ የሚባሉ የጦር መሳሪያዎች ከገደሏቸው ሰዎች ይልቅ የራሺያዎቹ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ #ኤኬ47 ክላሽንኮፍ የገደላቸው ይበልጣሉ፡፡ እጅጉኑ በደም የጨቀየ መሳሪያ ነው ይሉታል፡፡ ታዲያ ይህን መሳሪያ እንዲህ ገዳይ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል ማንኛውም ሰው በቀላል ገንዘብ ገዝቶ ሊጠቀመው መቻሉ ነው ይባላል፡፡ ከትላልቅ ጦርነቶች እስከ የሰፈር አምባጓሮ ድረስ በመውረድ ኤኬ47 በርካታ ህይወቶችን እስከወዲያኛው እንዲያሸልቡ አድርጓቸዋል፡፡
ታዲያ በርካቶች አለማችን ከእንደዚህ ያሉ የጦር መሳሪያዎች የፀዳች እንድትሆን መንግስታትም ጦርነት መደገሳቸውን አጥብቀው ቢኮንኑም ነገርየው ግን ቀንተቀን ወደሌላ ደረጃ ከፍ እያለ የበርካቶችን ህይወት ስጋት ላይ መጣሉ አልቀረም፡፡
ለምሳሌ ከዚህ በፊት #የድሮን_ቴክኖሎጂ መጠቀም ለአብዛኛው ሰው የሰማይ ያክል ሩቅ ነበር፡፡ እንኳን በግለሰብ ደረጃ በመንግስት ደረጃም እንዲህ ያለ ነገር ማሰብ ለጥቂቶች ብቻ የተተወ ጉዳይ ሆኖ ረዥም ጊዜያትን ቆይቷል፡፡
#Share_x50
#Join
@bunatech@bunatechdiscussion