Chelo Muslim Students


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


This is official channel of Chelo Students.
Join our group @cheloMuslimStudents

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


#NationalExam

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

Via:- TIKVAH

@chelomuslimstudents
@chelomuslimstudents1


🛑 ኢድ ሙባረክ፤ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሰን!

ተቀበለላሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኸል አዕማል

🛑Iid Mubaarak! Baga ayyaana Iid al-adha bara 1443tiin nuun gahe!

Taqabbalallaahu minnaa waminkum Saalihal a'amaal

@chelomuslimstudents
@chelomuslimstudents1


ሰበር ዜና‼


በበርካታ የሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢዎች ጨረቃ ስለታዬች፤
ነገ ቅዳሜ ረመዿን 01 ይጀመራል።
የረመዳን ጨረቃ በመታየቶ
ነገ ቅዳሜ ረመዳን አንድ ብሎ
ይጀምራል ።
እንኳን አደረሰን!
@chelomuslimstudents1


ኤጀንሲው ከ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ በህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የቀረበበትን አቤቱታ እንደማይቀበለው ማምሻውን አስታወቋል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ከ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ በኢፌዲሪ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የቀረበበትን አቤቱታ እንደማይቀበለው ማምሻውን አስታውቋል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ማምሻውን ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ከ12ኛ ክፋል ፈተና ጋር ተያይዞ የፈተናው እርማት ላይ ችግር ተፈጥሯል በሚል የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። ይህንንም በተጨባጭ ያረጋገጥነው በመሆኑ አስተራረም ላይ የተፈጠረ ሥህተት የለም ብለዋል።

ስህተት የተፈጠረው ፈተናው በሁለት ዙር የተሰጠ ከመሆኑና የመረጃ ቋቱም አንድ ላይ የተቀመጠ ስለሆነ ውጤት አገላለጽ ላይ መረጃ ሲወሰድ የተወሰነ ሥህተት ተፈጥሯል። ይህንንም በቀረበ ቅሬታ መሰረት ኤጀንሲው ማስተካከሉን ነው አቶ ተፈራ የገለጹት።

ከ20 ሺህ በላይ ቅሬታ በኦንላይ እና በአካል ተቀብሎ የማጣራት ሥራ መስራቱን የጠቀሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ በኦንላይን የቀረቡ አቤቱታዎች አልታዩም የሚለውን ክስም ሥህተት ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ከመግቢያ ነጥብ ጋር በተያያዘ ያለው ቅሬታ እንደማይመለከታቸውና ጉዳዩ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑንም አቶ ተፈራ ገልጸዋል።

የኢፌዲሪ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከተማሪዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ባደረገው ማጣራት ስህተት መፈጠሩን፤ ቅሬታ አመላለስ ላይም ችግሮች መኖራቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል።

#ኢዜአ
credit: ATC


በዩኒቨርሰቲ መግቢያ ፈተና እርማት ላይ ስህተት መፈጠሩን እንዳረጋገጠ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ

-ተቋማት ኃላፊነትን በመሸሽ ተገልጋዮችን እያጉላሉ መሆኑም ተጠቁሟል

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን በተመለከተ ባደረገው ምርመራ፣ በተለይ በሁለተኛው ዙር በተሰጠው ፈተና እርማት ላይ ስህተት ስለመፈጠሩ ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡

በተቋሙ ዋና እንባ ጠባቂ እነዳለ ኃይሌ (ዶ/ር) ፊርማ መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ወጭ የተደረገው መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ ኤጀንሲው የፈተናው እርማት ላይ ስህተት መፈጠሩን ለተቋሙ ያረጋገጠው፣ የፈተናውን ውጤት ተከትሎን የመጣውን ውዝግብና ቅሬታ ለመጣራት ሲያደርግ በነበረው የምርመራ ሂደት ላይ ነው፡፡
ከኤጀንሲው ማረጋገጫ በተጨማሪ ተፈታኝ ተማሪዎች “የእርምት ስህተት አለ” በሚል ቅሬታ አቅርበው በድጋሚ እርማት ሲደረግ የተገኙ ውጤቶችም በተጨባጭ በእርማት ሂደቱ ላይ ችግር እንደተፈጠረ ማስረጃ የሚሆኑ መሆናቸውንም ያብራራል፡፡

ይሁንና የፈተናው እርምት ላይ የተፈጠሩ ስህተቶች በድጋሚ እንዲታይላቸው በፈተናዎች ኤጀንሲ ተገኝተው የጠየቁ ተማሪዎች፣ ቅሬታቸውን ተቀብሎ የሚያስተናግድ እንዳላገኙ የእንባ ጠባቂ ተቋም መርማሪዎች በቦታው ተገኝተው መመልከታቸውን ተቋሙ በመግለጫው ላይ አስረድቷል፡፡ ይልቁንም ኤጀንሲው የተነሱት ቅሬታዎች የሚመለከቱት የትምህርት ሚኒስቴርን እንደሆነ በመግለፅ ቅሬታ አቅራቢዎች ወደ ሚኒስቴሩ እንዲሄዱ ጠይቋል፡፡
Via Reporter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
@chelomuslimstudents
@chelomuslimstudents1


የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

via: @tikvahethiopia
@chelomuslimstudents1


#Kutaa 2ffaa
hiriyoota keessanaiif share godhaa.
@chelomuslimstudents
@chelomuslimstudents1


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
@chelomuslimstudents
@chelomuslimstudents1




#Kutaa 1ffaa
hiriyoota keessanaiif share godhaa.
@chelomuslimstudents
@chelomuslimstudents1


Assalaamu alaykum ijoollee keenyaa akkam jirtu hardha yeroo gara university deemnu maal qabachuu akka qabnu isinitti hima na hordofaa.

#1. Kaayyoo:

Wanti jalqaba gara university fudhannee dhufnu keessaa inni jalqabaa kaayyoo fi mooraaliidha(onnee).
Fakkeenyaaf yeroo
uv(university) galtanu qabxii ammam fiduu akka qabdanu kaayyeeffattanii dhufuudha.

=> Kaayyoon kan biraa immoo yeroo University seentanu maal barachuu akka qabdanu murteeffachuu. Wanti asii olitti kaasne hundi isaayyuu akka isin jabaattanii qabxii gaarii fiddanii fieldi barbaaddan galtanuuf isin gargaara.

#2. Uffata halkanii:

Kunis kanneen akka ansoolaa, fooxaa (birdilibsii), bijaamaa fudhattanii dhufuu. Hammamtu barbaachisa isa jedhuuf immoo amma barbaaddan fudhachuu dandeessu. Garuu ansoolaa 2 fi tiraascarqii 2 ol utuu tahe gaariidha sababni isaas yeroo miiccitanu akkan sin hin rakkisneef . Fooxaan garuu 1 gahaa natti fakkaata.

#3. Nyaata goggogaa(bassoo,kuukisii,damma.....):

Ummata keenyaa nyaanni an asii ol kaase ni barbaachisu keessattu bassoo warri kaanillee dabalata . Maaliif beektuu ? Asitti irbaanni sa'atii 11 irratti nyaatama amma. Fakkeenyaaf nu biratti sa'atiin irbaataa 10:30 -12:00 tti kanaafuu yeroo dhuma sa'atii 2 tahu beela'uu jalqabdu yeroo sana isin bassoo keessan dhugdu jechuudha

#4. Dookimeentii:

Kan akka transcript,documeti maatricii fi entranci.

#5. Photo gurdii:

Asitti hin kaanuu jettanii gaafachuu dandeessu. Inni sirriidha garuu wantichi yeroo galmee barbaachisa waan ta'eef yeroo sana maaltu asii fi achi sin fiigsa ? Ammas immoo biyya hin beekne deemtu waan ta'eef utuu fudhattanii dhuftani gaariidha.

Hadhaaf asirratti haa dhaabnu guyyaa biraa immoo isa hafe itti fufna. Nagaatti!


@cheloMuslimStudents
@cheloMuslimStudents1


Ijoollee keenyaa akka kana telegraamii irraa fagaachuun garuu bareechee gatii nu kaffalchiisa . Manatti waa tokkoyyuu hin taatanu. University yeroo seentanu garuu akka kana telegraamii irraa fagaattu taanaan shakkii tokko malee gatii kaffaltu. Kana amanaatii fudhadhaa.


#NEAEA

" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " - አቶ ተፈራ ፈይሳ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ ሰዓት ጀምሮ ከተማሪ ወላጆች እንዲሁም ከተማሪዎች በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውን ተመልክተናል።

ከጥያቄዎቹ መካከል ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብቶ ለመማር የተላለፈው 50% ማስመዝገብ ውሳኔ ከነበርንበት ሁኔታ አንፃር፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጦርነቱ ጫና ተዳምሮ ትክልል አይደልም ይህ ሊታይ ይገባል የሚል ነበር።

የተላኩትን ቅሬታዎች በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አቅርቦ ምላሽ አግኝቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ " ማንኛውም ተማሪ ብሔራዊ ፈተናውን ለማለፍ ቢያንስ 50 በመቶ ውጤት ሊያመጣ እንደሚገባ " ገልጸውልናል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች አጠቃላይ አማካይ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። " ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ " ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " ብለዋል።

ከተማሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እየተቀበሉ መሆኑን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ፤ አጠቃላይ አማካይ ውጤታቸው ከ300 በታች ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር ገና አለመታወቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ የመግቢያ ነጥብ ወደፊት በትምህርት ሚኒስቴር የሚገለጽ መሆኑም ታውቋል።

©tikvahuniversity
@chelomuslimstudents
@chelomuslimstudents1


Assalamu alaykum warahmatullahi wabarakatuh! Obboleewwan keenya warri qabxii gaarii fiddan baga gammaddan jedhaa warri qabxiin sin jalaa xiqqaate immoo kun homaa miti waa tokko gadduu hin qabdanu ,rabbitu isiniif hin jaallanne jedhaa nagaan siniif dhaama.
Guyyaa hadhaa yaada wayiin isiniif qabadhee dhiyaadhe. Yaadichis ijoolleen keenya univarsitiidhaaf maaltu isaan barbaachisa waan jedhu ibsuufi. Odeeffannoo kana hin barbaanna yoo jettani karaa koomentiidhaa fi groupi keessaan yaada keessan nuuf kennaa. Amma siniif danda'ameen ariifadhaa. Hundi keessan immoo yaada keessan irratti kennaa

groupi keenya argachuuf kana tuqaa 👇👉 @cheloMuslimStudents
@cheloMuslimStudents1


መረጃ_ስለ_ሁሉም_ዪኒቨርሲቲዎች_@QesemAcademy.pdf
1.0Mb
✳️ስለ ሁሉም ግቢዎች መረጃ የያዘ PDF
📁SIZE :1.0MB (30 ሳንቲም )
© THE CAMPUS & ቀሰም ACADEMY
💬 መረጃው ምን ያካትታል ❓

ስለ እያንዳንዱ ዮኒቨርሲቲ መገኛ አድራሻው የየአየር ሁኔታው ፤ በውስጡ የሚገኙ ካንፓሶች ብዛት ፤ የሚሰጡት ፊልድ ፤ ስለ ካፌ ምግብ ሁኔታ ፤ በሳምንት ውስጥ ካፌ የሚሰጡ ምግቦች ዝርዝር ስኬጁል ፤ ከካፌ ውጪ ስለሚገኙ ምግቦች እና ዋጋቸው ፤ ስለ ዶርም ምቹነት ፤ ስለ ግቢው ድንገተኛ ክሊኒክ ፤ ስለ ሽንት ቤት ፤ ስለ ውሃ እና መብራት ፤ በግቢው ስላለ ዕቃ ስርቆት፤ስለ ሃይማኖታዊ ተቋማት እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች የሚመልስ ዝርዝር መረጃዎች ይዟል!

credit :Qesem Academy

@cheloMuslimStudents
@cheloMuslimStudents1


Forward from: ቀሰም Academy
📚በጣም ብዙዎቻችሁ እየጠየቃችሁን ስለሆነ ዮኒቨርስቲዎቻችን ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች እስከ 4ተኛው ትውልድ ድረስ አስቀምጠንላቹሃል ።

📊ለመሆኑ የዩኒቨርስቲዎች የ ትዉልድ ደረጃ ምንድነው?

የዩኒቨርስቲዎች የ ትዉልድ ደረጃ በ አመሰራርት የጊዜ ሂደት ዩኒቨርስቲዎችን በቅደም ተከትል እንደአንጋፋነታቸው የማስቀምጥ ሂደት ነው።ከተመሰረቱ ብዙ አመታትን ያስቆጠሩ ዩንቨርስቲዎች ብዙ ነገሮችን ያሟላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ


#በ1ኛ_ትውልድ

✔️ addis ababa university
✔️Arba Minch University
✔️Bahirdar University.
✔️University of Gondar
✔️Hawassa University
✔️Haramaya University
✔️Jimma University
✔️Mekele University


የሁለተኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች ፦

✔️ Dila University
✔️ Dire dawa University
✔️Jijiga University
✔️ Mede welabo University
✔️ASTU
✔️Debra Markos University
✔️Aksum University
✔️Debra Birhan University
✔️Wollega University
✔️Wollo University
✔️Mizan Teppi University
✔️Mekdela Amba University
✔️Ambo University
✔️ Semera University
✔️ kotebe motrop. University

#የ3ኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች

✔️Adigrat University
✔️Mattu University
✔️Woldia University
✔️Wolkite University
✔️Debratebor University
✔️Wachamo University
✔️Assosa University
✔️Aastu University
✔️Arsi University
✔️ Gambela University
✔️ bulehora University
✔️ walita sodo university

#በ4ኛ_ትውልድ_

✔️Jinka University
✔️Bonga University
✔️Worabe University
✔️Injibara University
✔️Debark University
✔️Mekdela Amba University
✔️Raya University
✔️Dembidolo University
✔️Selale University
✔️Oda Bultum University
✔️ Borna university

CREDIT : ዘ Campus
✳️ከHigh school እስከ Campus አብረናችሁ ነን !
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @QesemAcademy
📚JOIN: @QesemAcademy
╚════════════╝


Forward from: ቀሰም Academy
📌 ASTU ( Adama Science and Technology University )

📚 አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ
ከአዲስአበባ በ 100km እርቀት የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ካሏት ሁለት የ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አንዱ ነው።

📚 የScience እና Technology ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ እሚሰጣቸው Departmentoch ውስን ናቸው ማለትም Engineering እና Applied Science ፊልዶች ብቻ ናቸው ።

🔎 በ Engineering ስር 3 Schooloችን
1-School of Electrical
2-School of Mechanical
3-School of Civil and Architecture

📚 በእነዚህ schoolችም ስርም ፦


1.School of Electrical computing ስር
📌-Software engineering
📌-Computer science and engineering(CSE)
📌 -Power and Control
📌 -Communication and Electronics


2.በSchool of Mechanical chemical and material ስር
📌 - Mechanical engineering
📌 -Chemical engineering
📌 -Material Science and Engineering


3.በSchool of Civil and Architecture ስር
📌 -Civil engineering
📌 -Architectural engineering
📌 -Water engineering
📌 -Geomathics engineering



📚 በApplied Science ውስጥ ፦

📌 -Applied Maths
📌 -Applied Chemistry
📌 -Applied Physics
📌 -Geology
📌 -Industrial chemistry
📌 - Pharmacy


📚 ወደ ዩኒቨርስቲው ለመቀላቀል ፈተና ያለው ሲሆን እሚቀበላቸው ተማሪወች ውስን ናቸው ተማሪ እምንቀበለው በ Laboratoryኣችን ልክ ነው ብለው ስለሚያምኑ ! በጠቅላላ ግቢው ውስጥ ከ Fresh እስከ Masters 7000 ተማሪወች 2000 ሰራተኞች ይገኛሉ ።


📚 ተማሪወች ትንሽ ከመሆናቸው አንፃር ምግብ ከየትኛውም ግቢ የተሻለ ነው ።

📚 library

1-Central Library
2-Applied Library
3-Liberal arts library
4-Post graduate library
5-Females library

📚 እንዲሁም በየdepartmentቶች የየራሳቸው library ያላቸው ሲሆን የሴቶቹ ለብቻቸው እሚጠቀሙበትም አላቸው ።ሌላው ነገር libraryወቹ በውስጣቸው በጣም ፈጣን WiFi እና Computer አላቸው ። ግቢው ለሚጠቀምበት በጣም ብዙ laboratoryወች አሉ ።

📚 DSTV በኮሮና ተዘግቶ ቆይቶ በቅርቡ የጀመረ ነው ግቢው ውስጥ Anfi እሚባል ቦታ አለ እዛ ላይ በ cinema standard led screen አለ እንዲሁም ሶስት ቦታወች ላይ አነስተኛ screenoch አሉ ። ለሴቶች ትንሽ ሻል ያለ አገልግሎት ይሰጣል በዶርመተሪ በlibraryም በብዙ ነገር ይጠቀማሉ !


📚የራሱ ውሀ ማጣሪያ ያለው ሲሆን ፤ ብዙም የውሀ ችግር የለም መብራት አይጠፋም ከጠፋም በ 5 ደቂቃ ውስጥ እሚነሳ automatic generator አለ ። Dormitory አሪፍ የሚባል ነው ። የግቢ መግቢያ ሰዓት 3:00 ከሌሎች የተሻለ ነው ። ሌላው በፍፁም ሰው እማይተናኮሉ ለማዳ ለመባል እሚቀርቡ ጅቦች አሉ ፤

🔎 በጣም ጠቃሚ ነገር 🔎

📌 ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በተለየ ነው ት/ት እሚሰጠው ለምሳሌ Comon course እሚባል ነገር የለም engineering እሚገባ ቀጥታ pre engineering ይማራል Appliedም እንደዛው ነው ።

Gpa ከ 3.5 በላይ ካለ እና ሌላ ፊልድ ደርቦ መመረቅ ለሚፈልግም dual degree ይሰጣል ሁለት degree ማለት ነው ። International degree መስጠትም እጀምራለሁ ብሎ ለ2013 ባች ቃል ገብተዋል።


🔎 ማስጠንቀቂያ 🔎

📚 ግቢው በ ት/ት ጉዳይ አይደራደርም ፈተናቸው አስመራሪ ነው ግን በደምብ ለመስራት ለሚመጣ ተማሪ እሚከብደው አይሆንም !

CREDIT:ዘ campus

✳️ከHigh school እስከ Campus አብረናችሁ ነን !
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @QesemAcademy
📚JOIN: @QesemAcademy
╚════════════╝


Forward from: ቀሰም Academy
ቅሬታን በተመለከተ አምና ቅሬታ አቅርበው ምላሽ ከተሰጣቸው ጥቂት ተማሪዎች ውስጥ በቅርብ የማውቀውን ተማሪ የሆነ ነገር በልልኝ ብዬው ነበር.....


፨የሌሎች የግቢ ተማሪዎችንም መልዕክት አስደምጣቹሃለው👍

Credit : #atc_news
✳️ከHigh school እስከ Campus አብረናችሁ ነን !
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @QesemAcademy
📚JOIN: @QesemAcademy
╚════════════╝ ⇲


Forward from: ቀሰም Academy
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et

3) በ9444 SMS)፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
✳️ከHigh school እስከ Campus አብረናችሁ ነን !
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @QesemAcademy
📚JOIN: @QesemAcademy
╚════════════╝

20 last posts shown.

28

subscribers
Channel statistics