Christian tweet


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Telegram


በዚህ ቻናል በየቀኑ ለ
➜ #Profile_picture
➜ #Instagram_story
➜ #Facebook
➜ #Telegram_story
የሚሆኑ #መንፈሳዊ_ጥቅሶች እና #መፅሐፍ_ቅዱሳዊ መልእክቶችን (በአማርኛ እና ENGLISH) ወደእናንተ እናደርሳለን ቻናሉን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ 😊
ⒸSince 5-11-2015
Buy ads: https://telega.io/c/christian_tweet

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Telegram
Statistics
Posts filter


🧿በተለያዩ የሀገራችን ቋንቋዎች የተዘመሩ መዝሙሮችን በቻናላችን ላይ ማድረስ ልንጀምር ነው

🇪🇹በየትኛው የሀገራችን ቋንቋ የተዘመሩ መዝሙሮችን ማግኘት ይፈልጋሉ⁉️

       ✴️ምረጡ✴️
የሚመጣላቹን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል በመዝሙሮቹ ይባረኩ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


'ቈላስይስ 1:6 - ይህም ወደ እናንተ ደርሶአል። ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በእናንተም ዘንድ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።'




ለአማኑኤል...ስጦታዬ!

ከሰው ባህሪ ቅር የሚለኝ ነገር መሀከል አንዱ አስደናቂ ነገሮችን ጭምር ብዙ በረከትና ተዓምራትን ቶሎ መልመዱ ነው። በተለይ ደግሞ  ከልጅነት ስንሰማው ያደግነው ጀብዱ through time we start considering them to be unremarkable. Ordinary. ነገር ግን ቃል ስጋ መሆንህ..አምላክ በመሀከላችን ማደርህ (ዩሐ 1:14)  ነብዩ "የዘለዘለዓለም አባት" ብሎ የተናገረልህ ንጉስ፣ እግዚያብሄር ወልድ ስጋን ለብሰህ (ዕብ 2:17) የትህትናህን ትርጉም ዝቅ በማለት ማሳየትህ (ፊሊ 2:6) ትልቅ ክስተት ነው።

እንደአምላክነትህ ስለማትለወጥ መለኮትነትህ ሳይነካ (ዕብ 13:8) እውነተኛ ሰው ሆነሀል። You're the defining moment in history. የአንተ መወለድ ነው መሀከለኛ ያስገኘልን።  (1 ጢሞ 2:5) አለበለዚያ ወኪል ፍለጋ "በሁለታችንም ላይ እጅ የሚጭን በመካከላችንም የሚዳኝ ቢኖር (ኢዮብ 9:33) እያልን impossible በሆነ አጣብቂኝ ውስጥ በገባን ነበር።

የእግዚአብሄር ልጅ ሆይ መለኮትነትህ የማይካድ እውነታ ነው። የውልደትህ ትርክት እስከነፋይዳው ለዘመናት የተተነበየና የተጠበቀ እውነት ነው። በጊዜ የምትገደብበት የጅማሬህ ልደት የለም። ውልደት አልፈጠረህም። በምድር ስትመላለስ የሰራኸው ጀብዱ ዛሬም መለኮትነትህን ይዘክራል። በተፈጥሮ ላይ ያለህን ጌትነት በድንቅና ተዓምራቶችህ አሳይተኸናል። ሀጥያትን በምድር ሆነህ ይቅር ብለሀል። ሙታንን አስነስተሀል። ማንም ቦታ ለማይሰጣቸው ራርተህ መፍትሄን ሰጥተሀቸዋል። ደካሞችን ልታሳርፍ የምትጠራ የሀጥያተኞች ወዳጅ ነህ። ትንሳኤህም የማይደገም ታላቅ ብርታትህ መገለጫ ነው።  I'm equally blown away by your greatness and lowliness! I love that your attributes compliment eachother so well. አይፎካከሩም።

የገና በዓል ሲመጣ ግን በአፅንዖት ማሰብ የምፈልገው ስብዕናህን ነው። ለረጅም ጊዜ ሰው'ነትህ የይስሙላ ይመስለኝ ነበር። ..እንደሰው መብላት መተኛትህን (ማቲ 4:2) ፤ ሲመቱህ መድማትህን (ዩሐ 19:34) መከፋት መቆጣትህን (ማቲ 26:37, ማር 3:5) ያለው አንድምታ እምብዛም አይታየኝም ነበር። But your incarnation is what makes Christmas joyful!  ሰው መሆንህ ያመጣልን ትሩፋት ተዘርዝሮ አያልቅም! አባቶች impassible የሚሉት የአምላክ አይነኬነት.. መከራን መቀበል አለመቻል ብቸኛ exception የአንተ መወለድ ነው። ሰው ሆነህ ባትመጣ መከራችንን መቀበል አትችልም ነበር።

የዕብራውያን መፅሀፍ እንዳለው በድካማችን የምትራራበት መንገድ ራሱ hypothetical/ anticipatory ብቻ ይሆን ነበር። አሁን ግን ለአንተ ብዙ ሳላብራራ ይገባሀል። ሰው ስለሆንክ ነው ለሰዎች የተሰጠውን ህግ የፈፀምከው።  (ገላ 4:4, ማቲ 5:17) ሰው ስለሆንክ ነው ደምህን ስለሀጥያታችን ስርየት ያፈሰስከው (ዕብ 9:22, 10:5) ደግሞ ሰውም ስትሆን የናዝሬት ሰው መሆንህ shows who you identify with. Your humility is matchless my King!

You're not just a doctrine to me. You're not a paradox for me to figure out. You're a person. You're a person to be known, to be loved, to be treasured , to be marvelled at, to be made much of, to be worshipped, to live and to die for! የሆንነውን ሁሉ የሆነው ከአንተ የተነሳ ነው። ከአንተ ወደማን እንሄዳለን? አንተ (ብቻ) የህይወት ቃል አለህ።

የሀጥያተኞች ወዳጅ ሆነህ ጠላት የነበርነውን የእግዚአብሔር ወዳጆች አደረከን። በራሳቸው የሚተማመኑ ትምክህተኞች በውጫዊ ፅድቃቸው አልሸነገሉህም። የተለሰኑ መቃብር መሆናቸውን አይተህ ቢጤዎቻችንን አህዛብ፣ ቀራጮች፣ ተቅበዝባዥ የጠፉ በጎችን ወደድግስህ ጠርተሀል። ከመለኮታዊ ክብርህ የባዘነውን ፍለጋ የወረድክ መልካም እረኛ ነህ።  (Luke 19:10, Matt 9:13..)

I (actually) owe You everything. Everything I have now was given to me because of You. Apart from you I have no claim, no plea to ask God for anything. You, Yourself are given to me as a gift. The Greatest gift there could ever be! And you have bestowed countless other gifts to me. Christ Jesus, I'm eternally grateful for all your blessings you've given me.

I am especially gratefull today for everything that is a means for me to get to know you more! Because You are the greatest Good and my greatest need. So I don't want to take all the beautiful godly people you've surrounded me with, the providence of having a functioning brain and the luxury of time to pursue you as well as having access to resources that reveal You for granted!

ያንተን መልካምነት የሚያሳየኝ ነገር ብዙ ነው። ጎደለ የምለው ሺህ ነገር ቢሟላ አንተ ከሌለህ ከንቱ መሆኑን ስለምታውቅ ነው በቅድሚያ ራስህን የሰጠኸኝ። ስጦታዬ አማኑኤል ራስህ ነህ። ከስሞች ሁሉ በላይ ስም ያለህ፣ ስልጣን ሁሉ የተሰጠህ ጌታ ኢየሱስ አንተ ሁሉ በሁሉ ነህ። የዘላለም አባት፣ ሀያል አምላክ፣ My wonderful counseler! ምክርህ በእርግጥም ሰው ያደርጋል! የወይኑ ግንድ ሆይ ያለአንተ ምንም ላደርግ እንደማልችል ገብቶኝ ይህች ቀን ከአንተ ጋር የምጣበቅበት ትሁን። My Lord and Savior Jesus Christ, draw me close so I may cleave to You alone.

የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ የሰዉ ልጅ ሆነህ ታላቅ ወንድም ከሆንከኝ ከዚህ በላይ ምን ትምክህት እሻለው? ዛሬ ራሴን define የማደርገው የአንተ ልጅ በመሆኔ ነው። ይህን የከበረ እድል በነፃ ሰጠኸኝ። ከሀጥያተኞች ዋና የሆንኩ እኔ በአንተ እንድፀድቅ ምትኬ ሆንክልኝ። በትዕቢት የወደቅኩትን እኔን ልታነሳ ራስህን አዋረድክ። ከዚህ በላይ ስጦታ ከየት ይገኛል?

አማኑኤል...እግዚአብሔር ከእኛ ጋር። No words can express how much we don't deserve this precious gift. We don't even have to wonder about it.. we are unworthy. But thats the definition and beauty of Grace. And we will do well if we use any excuse to thank God for His amazing grace he has shown us. እንደሰብዓሰገል ይዘን የምንሄደው እጅ መንሻ እንደነዚህ ብዙ ምስጋና ያዘሉ imperfect ደካማ ቃላትና ድሪቶ ሰባራ ልብ ቢሆንም ያለንን ስጦታ እንሰጠው። በበረት የተወለደው ንጉስ በደስታ ይመበለናል።


“በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ እግዚአብሔር ይመስገን።”
— መዝሙር 31፥21

“Blessed be the LORD: for he hath shewed me his marvellous kindness in a strong city.”
— Psalms 31፥21 (KJV)

@Christian_tweet
@Christian_tweet


“የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤”
— ዕብራውያን 4፥12


“For the word of God is quick, and powerful, and sharper than any twoedged sword, piercing even to the dividing asunder of soul and spirit, and of the joints and marrow, and is a discerner of the thoughts and intents of the heart.”
— Hebrews 4፥12 (KJV)

@Christian_tweet
@Christian_tweet




ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፦

          አንተ የድሀ ጌጥ ነህ፣ የምናሳየው የምንለብሰው የምድርም የሰማይም መዋቢያችን አንተ ነህ።

     አንተ የማትቆሽሽ ልብሳችን፣ የማትዝግ ዝርግፍ ጌጣችን፣ ከአልማዝና ከከበሩት ማዕናት ሁሉ ለኛ የከበርክ የልባችን ውበት ነህ።

      ሀብታም ብቻ የማያገኝህ ለድሆች ቅርብ የሆንህ፣ ለልባችንም የተጠጋጋህ፣ አትመጥኑኝም ብለህ የማትፀየፈን፣ የተቸገራችሁ ናችሁ ብለህ ጀርባ የማትሰጠን አንተ ብቻ ነህ።

     እንዳንተ ያለ የለም። እንዳንተ ያለ አይኖርም። እንዳንተ ያለ ብቸኛ ወዳጅ አናገኝም። የተረሳውን አስታዋሽ፣ የተጠሉትን አፍቃሪ፣ የሌጣዎች ሀብት፣ የጎስቋሎች አለኝታ እንዳንተ የለም።

      እንወድኃለን ስለወደድከን፣ እናከብርሃለን ስላከበርከን፣ እንቀድስሃለን ስለቀደስከን፣ እንኖርልሃለን ስለሞትክልን ስምህ ቡሩክ ይሁን።


Our Lord and Savior Jesus Christ:

          You are the ornament of the poor, the adornment of the earth and the sky that we show and wear.

     You are our garment that does not stain, our ornament that does not fade, the beauty of our hearts that is more precious to us than diamonds and all precious stones.

    Our Lord and Savior Jesus Christ:

          You are the ornament of the poor, the adornment of the earth and the sky that we show and wear.

     You are our garment that does not stain, our ornament that does not fade, the beauty of our hearts that is more precious to us than diamonds and all precious stones.
You are the only one who is not found by the rich, who is close to the poor, who is close to our hearts, who does not hate us saying that we are not worthy of you, who does not turn our backs on us saying that we are in need.

     There is no one like you. There is no one like you. We will not find a friend like you. The reminder of the forgotten, the lover of the hated, the treasure of the poor.
, The lover of the hated, the wealth of the poor, the hope of the needy, there is none like you.

      We love you because we love you, we honor you because you honor us, we sanctify you because you sanctify us, we live because you died for us. Blessed be your name.


@Christian_tweet
@Christian_tweet


1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
²³ ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።
²⁴ ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤
²⁵ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።



1 Peter 1 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² Seeing ye have purified your souls in obeying the truth through the Spirit unto unfeigned love of the brethren, see that ye love one another with a pure heart fervently:
²³ Being born again, not of corruptible seed, but of incorruptible, by the word of God, which liveth and abideth for ever.
²⁴ For all flesh is as grass, and all the glory of man as the flower of grass. The grass withereth, and the flower thereof falleth away:
²⁵ But the word of the Lord endureth for ever. And this is the word which by the gospel is preached unto you.

@Christian_tweet
@Christian_tweet


ኤፌሶን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።
⁵ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።
⁶ በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።
⁷ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።
⁸ ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።
⁹ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
¹⁰ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
¹¹ እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።
¹² ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።


Ephesians 1 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ According as he hath chosen us in him before the foundation of the world, that we should be holy and without blame before him in love:
⁵ Having predestinated us unto the adoption of children by Jesus Christ to himself, according to the good pleasure of his will,
⁶ To the praise of the glory of his grace, wherein he hath made us accepted in the beloved.
⁷ In whom we have redemption through his blood, the forgiveness of sins, according to the riches of his grace;
⁸ Wherein he hath abounded toward us in all wisdom and prudence;
⁹ Having made known unto us the mystery of his will, according to his good pleasure which he hath purposed in himself:
¹⁰ That in the dispensation of the fulness of times he might gather together in one all things in Christ, both which are in heaven, and which are on earth; even in him:
¹¹ In whom also we have obtained an inheritance, being predestinated according to the purpose of him who worketh all things after the counsel of his own will:
¹² That we should be to the praise of his glory, who first trusted in Christ.

@Christian_tweet


'ሮሜ 1:27 - እንደዚሁም ወንዶች ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወት ተቃጠሉ፤ ወንዶች ከወንዶች ጋር ነውር ፈጸሙ፤ ለክፉ አድራጐታቸውም የሚገባቸውን ቅጣት በገዛ ራሳቸው ላይ አመጡ።'


“ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
  — ዘፍጥረት 47፥9

ፀሎት፥
እግዚአብሔር ከዕድሜ ኪሳራ ይጠብቀን። በእድሜያችን አመሻሽ መለስ ብለን ስንመለከት የተኖረ ክርስትና ፤ የኢየሱስ ህይወት የተደገመበት የህይወት ሀዲድ ለማየት ያብቃን። ባለፈው ጊዜያችን ብዙ አጥፍተን ከስረን ቢሆንም በምህረቱ ተነስተን የተሰጠንን ጊዜ በአግባቡ ለመኖር ፀጋ ይብዛልን።




“And Jacob said unto Pharaoh, The years of my sojourning are an hundred and thirty years: few and evil have they been to me, and they have not attained unto the days of the sojourning of my fathers.”
  — Genesis 47:9

Prayer:
May God preserve us from the loss of life. Christianity lived in the twilight of our lives; the life of Jesus Let us see the path of life where life is repeated. Although we have lost much in our past, may His mercy be upon us and grant us the grace to live properly in the kingdom that has been given to us.

@Christian_tweet
@Christian_tweet


.           🎁ኢየሱስ ተወለደ🎁
                   ◈◈◈◉◉◈◈◈
     እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ለኢየሱስ   
           ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል
                  በሰላም አደረሳችሁ!
              🎅መልካም በዓል🎅
             
@Christian_Tweet
@Christian_Tweet


ዕብራውያን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤
⁸ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤
⁹-¹⁰ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።


Hebrews 5 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ Who in the days of his flesh, when he had offered up prayers and supplications with strong crying and tears unto him that was able to save him from death, and was heard in that he feared;
⁸ Though he were a Son, yet learned he obedience by the things which he suffered;
⁹ And being made perfect, he became the author of eternal salvation unto all them that obey him;
¹⁰ Called of God an high priest after the order of Melchisedec.

@Christian_tweet


“ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።”
— ኤፌሶን 4፥25


'ኤፌሶን 2:1 - እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤
2:4 - ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣
2:5 - በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው።'
https://t.me/christian_Tweet


የገና ዝማሬዎችን ከፈለጉ የመዝሙር ቻናላችን ይቀላቀሉ👇
👉 @zema_sink


'መሳፍንት 10:12 - ሲዶናውያን፣ አማሌቃውያንና ማዖናውያን አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን'?


Forward from: Light
“እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።” ዕብራውያን 2፥18

@worlds_light
@worlds_light


'ዕብራውያን 9:25 - ሊቀ ካህናት የራሱ ያልሆነውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንደሚገባ፣ ክርስቶስ ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት ለማድረግ ወደ ሰማይ አልገባም።'

20 last posts shown.