ጉብኝት በዓቢይ ቅርንጫፍ
ክፍል 2
******እጅግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አሠራር የተደራጀውን ዓቢይ ቅርንጫፍ እያስጎበኘናችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በክፍል 1 ጉብኝታችን የዓቢይ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ስለቅርንጫፉ የሰጡትን አጠቃላይ ገለፃ ተከታትለናል፡፡
ዛሬ ቅርንጫፉን ዘመናዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ካስቻሉት ዲጂታል የአገልግሎት መስጫ ሥርዓቶች መካከል አንዱን እንመለከታለን፡፡
ይህ የቅርንጫፉ ቨርቹዋል ማኔጅመንት ሲስተም (Virtual Management System) ደንበኞች ወደ ቅርንጫፉ ሲመጡ ምንም አይነት የወረቀት ንክኪ ሳያስፈልጋቸው ሲስተሙ ላይ የሚፈልጉትን አገልግሎት (ወጪ፣ ገቢ፣ ገንዘብ ማስተላልፍ፣ የቼክ አገልግሎት ሌሎችንም) በመሙላት የአገልግሎት ተራ ቁጥር ይዘው የሚሰተናገዱበት ነው፡፡
የአገልግሎቱን አጠቃቀም በተመለከተ ድጋፍ ለሚሹ ደንበኞች እገዛ የሚያደርጉ የባንካችን ሠራተኞች በቅርንጫፉ አሉ፡፡
የበለጠውን ከቪዲዮው እንመልከት፡፡
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!#cbe #commercialbankofethiopia #facts #MainBranch #banking #Ethiopia
https://youtu.be/092VsatDYiQ