Commercial Bank of Ethiopia


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Bookmaking


Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1700 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Bookmaking
Statistics
Posts filter




በ EthioDirect
ሀገር ቤት እጅግ ቅርብ ሆኗል!
**

በኢትዮ-ዳይሬክት መተግበሪያ
ከ5 ፟- 1000 ዶላር በብርሀን ፍጥነት
ሀገር ቤት ላሉ ወዳጅ ዘመዶችዎ
በነፃ ይላኩ!

#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ 

#CBE #ethiodirect #visa #mastercard #money #transfer #ethiopia
*****

የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ  አገልግሎቱን ይጠቀሙ።

• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect

• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491


Vacancy
=======
Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following positions:
1.  Senior Psychiatry Nurse
2.  Senior Biomedical Engineer
3.  Neurologist
4.  Radiologist
5.  Gynecologist
6.  Specialist Physician (Internist)
7.  General Practitioner
8.  Junior Pharmacy Service Officer
9.  Junior Psychiatry Nurse

Interested and qualified job seekers should apply through CBE career website
( https://vacancy.cbe.com.et ) from April 08 - 14, 2024.

For requirements and other detail information, please use the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/External_Vacancy_97b7ef4f03.pdf


በኢትዮጵያ የዲጂታል የክፍያ ስርአት እንዲያድግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ከፍተኛ እገዛ ማድረጉ የባንካችን ፐሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።
================
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዘጋጅነት ዛሬ በእስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ ኮንፍረንስ ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ ባንኮች፡ የፋይናንስ ተቋማት ፡ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት አሁን ለደረሰበት ደረጃ  የተጫወተውን ሚና አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል፡፡
አቶ አቤ እንዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታ ባንክ አገልግሎትን ለደንበኞቹ ከማስተዋወቅ እና ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ ለሌሎችም አርአያ በሚሆን መልኩ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳረገ ጠቁመዋል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ለዲጂታል የክፍያ ስርአት እድገት የላቀ ሚና እንዲወጣ አስችሎታል ብለዋል።
አቶ አቤ አክለውም ለዲጂታል የክፍያ ስርአት መጎልበት በሀገሪቱ የሚገኙ ባንኮች፡ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ፡ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና የዘርፉ ተሳታፊዎች በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዚህ መልኩ የዘርፉን ተሳታፊዎች ያሳተፈ የውይይት መድረክ ማሰናዳቱ እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።
በመጨረሻም እንደነዚህ አይነት የውይይት መድረኮች በሀገር አቀፍ ደረጃ በዲጂታል የክፍያ ስርአት ላይ ለሚወጡ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎች ከፍተኛ ግብአት የመሆን አቅም ኣላቸው ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ባንኮች ፣የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና የግሉ ዘርፍ ፋይናንስ ተቋማት ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡


ለተሻለ ነገ...
የትምህርት ቁጠባ ሂሳብ
===============
የርስዎንም ሆነ የልጆችዎን የከፍተኛ ትምህርት ወጪ ለመሸፈን
የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ይሁኑ!

#CBE #education #saving #ትምህርት #ቁጠባ #ሂሳብ #ወላጆች #ከፍተኛትምህርት #ገንዘብ


እጥፍ ወለድ....
********
ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ፤
አዲሱን የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ!

• ከመደበኛው ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል ፣
• ለውጭ ሀገር ጉዞዎ ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬ አገልግሎት እና
• የሞባይል ካርድ ስጦታም ያገኛሉ ።

ይቆጥቡ፤ የበለጠ ያግኙ!
#CBE #saving


ያለ አግባብ የራሳችሁ ያለሆነን ገንዘብ ከባንኩ ወስዳችሁ ወደ ቤቲንግ ተቋማት ላስተላለፋችሁ ግለሰቦች በሙሉ
=====================
ባንኩ መጋቢት 7 ቀን 2016 ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ይታወቃል። በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ እና በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን የገንዘብ ልክ እየመለሱ ይገኛሉ። 
ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ ቤቲንግ ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ በጠቆሙን መሰረት ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ እንዲቻል ወደ ቤቲንግ ተቋማት የራሳችሁ ያልሆነውን ገንዘብ ያዘዋወራችሁ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንድታመለክቱ እናሳስባለን።


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በድሬዳዋ እና በአዳማ ከተሞች የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረመዷንን ፆም ምክንያት በማድረግ በአዳማ (መጋቢት 17፣ 2016) እና በድሬዳዋ (መጋቢት 19፣ 2016) ከተሞች ለሚገኙ 500 ለአቅመ ደካማ  ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሂዷል፡፡

የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየዓመቱ በርካታ በጀት በመመደብ በርካታ የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎችን እንደሚያከናውን ገልፀው፣ የተለያዩ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያካሂደው የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አንዱ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

የአዳማ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይ. ኢንሴኔ መሃመድ በመርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በከተማዋ ለሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ላደረገው ማእድ ማጋራት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው "ባንኩ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማው ነዋሪዎች በማሰቡ እናመሰግናለን" ብለዋል።

የማዕድ ማጋራቱ መርሀ ግብር ተጠቃሚዎች ባንኩ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፣ ሌሎች ተቋማትም የባንኩን አርዓያነት ያለው ተግባር እንዲከተሉ ጠይቀዋል፡፡

በማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሮቹ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የየከተሞቹ መስተዳዳር የሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡


🌟 Exclusive Offer for Commercial Bank of Ethiopia Customers! 🌟

Fly hassle-free with Ethiopian Airlines! As a valued customer of Commercial Bank of Ethiopia, we're thrilled to extend a special invitation to join our exclusive Telegram channels and enjoy exciting promotions:

✈️ Join Ethiopian Airlines Ticket Telegram Channel: Stay updated on flight schedules, special offers, and travel tips. Click here: [https://t.me/ethiopianairlinesticket](https://t.me/ethiopianairlinesticket)

🎫 Looking for convenient ticket booking and assistance? Join Ethiopian Airlines Ticket Office Telegram Channel: Connect directly with our agents for personalized service and support. Click here: [https://t.me/ethiopianairlinesticketoffice](https://t.me/ethiopianairlinesticketoffice)

Don't miss out on the latest updates and exclusive deals! Fly with Ethiopian Airlines for an unforgettable travel experience. ✈️✨


በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡
******
ይህ የተገለፀው መጋቢት 16፣ 2016 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ለተገኘው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባንኩ የ2023/24 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፌሰር  መሐመድ አብዱ እንዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀገር የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ያለ ባንክ ነው፡፡

ባንኩ በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የሚጠብቀበትን እየተወጣ እንዲቀጥል እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ደግሞ የባለድርሻ አካላት የፖሊሲን ጨምሮ ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርጉለት እንደሚገባ ዋና ሰብሳቢው አሳስበው፣ ቋሚ ኮሚቴው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

የተከበሩ ፕሮፌሰር  መሐመድ ባንኩ በወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ የሠራው ሥራ የሚያስመሰግነው እንደሆነም ነው የገለፁት፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣበትንም መንገድ ዋና ሰብሳቢው አድንቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት የባንኩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ ላነሷቸው ጥያቄዎች የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ  የሚመለከታቸው የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ መስጠታቸው እና የቋሚ ኮሚቴው አባላት ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት የሚሠራውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረጃ ደህንነት ሥርዓት  ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡


Forward from: ET_Airlines_Ticket_Office
Attention! Today's flight (28th March 2024) from Addis Ababa to Bahir Dar (ADD to BJR) is fully booked. Unfortunately, no tickets are available at this time. We apologize for any inconvenience this may cause. Please consider alternative travel options or check for availability on future flights. Thank you for choosing Ethiopian Airlines.


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ ኑር አገልግሎት በአዳማ ከተማ እና አካባቢዋ ለሚገኙ ደንበኞቹ የኢፍጣር መርሃግብር አከናወነ::
==================================
በመርሃግብሩ  ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን እንደተናገሩት የሲቢኢ ኑር ደንበኞች ከባንኩ ጋር በቅርበት በመስራት በሀገራቸው የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ በንቃት ሊሳተፉ  ይገባል ብለዋል::
የሃገሪቱ የኢኮኖሚ መሰረት የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹን  በታማኝነት ለማገልገል ምንጊዜም ዝግጁ እንደሆነም ነው አቶ ኑሪ የተናገሩት::
በኢፍጣር መርሃግብሩ ላይ የተሳተፉት የባንኩ ደንበኞች ከሲቢኢ ኑር
በኢፍጣር  መርሃግብሩ ላይ የተገኙት ደንበኞችም ሐላል በሆነው የሲቢኢ ኑር ጋር እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም በይበልጥ አብረው በመስራት እና አገልግሎቱን በመጠቀም እራሳቸውንም ሃገራቸውንም ለመለወጥ  በትጋት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል::




✈️✨ Feeling the time crunch for your next flight? No sweat! Dive into the future of travel with our cutting-edge Telegram platform bot for Ethiopian Airlines ticket bookings. Glide through the process effortlessly with the assistance of our live agents or take the reins yourself for a personalized experience. Say hello to stress-free travel! Book now: [Ethiopian Airlines Ticket Bot](https://t.me/ethiopianairlinesticket_bot) #FlySmart #EthiopianAirlines #TelegramMagic ✨🌍


🌟 Don't let urgency dampen your travel plans! Introducing the Ethiopian Airlines Ticket Bot on Telegram, your ultimate solution for seamless flight bookings. Whether you prefer the expertise of our live agents or the convenience of self-service, our platform ensures swift and hassle-free ticket reservations. Experience efficiency at its finest. Book now: [Ethiopian Airlines Ticket Bot](https://t.me/ethiopianairlinesticket_bot) #FlyWithEase #EthiopianAirlines #TelegramBooking


🛫 Don't have a flight ticket for today and feeling the rush? No worries! Say goodbye to long queues and stress with our new Telegram platform bot for booking flight tickets. Experience the convenience of booking your ticket right here, with the assistance of our official live agent and even yourself. Get ready to soar hassle-free! ✈️ #FlightBooking #TelegramBot #ethiopianairlines


ቀሪ ገንዘብ እንድትመልሱ የተሰጠ የመጨረሻ ማሳሰቢያ! 
***
በባንኩ የሲ
ስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በሂሳብችሁ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ  በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዳችሁ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ሂሳባችሁ በሚገኝበት ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም ዲጂታል የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ የምታደርጉበትን ዕድል ባንካችን ማመቻቸቱ ይታወቃል።  
በዚህ መሰረት 9281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መልሰዋል፡፡ ሆኖም  ከዚህ በታች ስማችሁ፣ የሂሳብ ቁጥራችሁ እና ሂሳባችሁ የሚገኝበት ቅርንጫፍ የተዘረዘረው 5166 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም  ያላግባብ ከወሰዳችሁትን ገንዘብ በከፊል ተመላሽ ያደረጋችሁ ቢሆንም ይህ ማስታወቂያ ይፋ እስከሆነበት ዕለት ድረስ ቀሪውን ገንዘብ አልመለሳችሁም፡፡  
ባንኩ ቀደም ሲል ባስጠነቀቀው መሠረት ወደ ቀጣዩ ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ቀሪውን ገንዘብ እንድትመልሱ አንድ ተጨማሪ ዕድል የሰጣችሁ በመሆኑ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን በምትመልሱት ላይ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር ያረጋግጣል።   ነገር ግን እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን የማትመልሱ ካላችሁ ግን የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ሙሉ ስማችሁን፣ ፎቷችሁን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራችሁን ጠቅሰን ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት በማሳወቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ፤ እንዲሁም  ከሕግ አካላትና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰድባችሁ  ለመጨረሻ ጊዜ እናሳስባለን። 
መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. 
የስም ዝርዝሩን ለማየት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡
https://ow.ly/iYtO50R2WrV


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 622.9 ሚሊዮን ብር (78 በመቶ) ማስመለስ መቻሉን ገለጸ፡፡
*****

ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 6፣ 2016 ዓ.ም ሌሊት በተፈጠረ ችግር  ምክንያት 801,417,747.81 ብር ያላግባብ ተወስዶ እንደነበር ባንኩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያሳወቀ ሲሆን፣ 622.9 ሚሊዮን ብር  ማስመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ከባንኩ አላግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ለማስመለሰ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ በተዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት ችግሩ በተከሰተበት ቀን ከምሽቱ 3፡38 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ  8፡45 ድረስ   በ25,761 ሂሳቦች አማካኝነት 238‚293 ህገወጥ ግብይቶች ተከናውነዋል፡፡

አቶ አቤ ችግሩ መከሰቱ ከታወቀ በኋላ የባንኩን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ለተወሰኑ ሰዓታት በማቆም እና ችግሩ በተከሰተበት ሰዓት በገንዘብ ዝውውር የተሳተፉ ሂሳቦችን በማገድ የጉዳት መጠኑን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

አቶ አቤ እንዳሉት ባንኩ በቀጣይ በወሰዳቸው እርምጃዎች ያላግባብ የገንዘብ እንቅስቃሴ ከተደረገባቸው እና በቂ ገንዘብ ከነበራቸው ከ10,727 ሂሳቦች ቀጥታ ብር 44,668,232.41 ተመላሽ የተደረገ ሲሆን፣ ከ15,008 ሂሳቦች ደግሞ በከፊል ማለትም ብር 205,805,340.9 ብር ተመላሽ ተደርጓል፡፡

በጉዳዩ ተሳትፎ የነበራቸው 9,281 ያህል ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ብር 223,475,369.31 ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት የመለሱ መሆናቸውን የገለፁት አቶ አቤ፣ 5,160 ደንበኞች ደግሞ በከፊል ማለትም ብር 149,021,191.37 መመለሰቻውን አሳውቀዋል፡፡

አላግባብ ከወሰዱት ብር 9,838,329.12 እስካሁን ምንም ያልመለሱ 567 ግለሰቦች መኖራቸውንም ነው አቶ አቤ የገለፁት፡፡ 

አቶ አቤ ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ በፈቃደኝነት የማይመልሱ ግለሰቦችን በተመለከተ ቀደም ሲል ባንኩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት አስፈላጊውን ተግባራት በቅደም ተከተል በማከናወን ጉዳዩ ለህግ አካል እንደሚቀርብ ገልፀዋል፡፡


ለውድ የባንካችን ደንበኞች
=======
ከመንገድ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ የኔትወርክ ብልሽት የኮከበ ጽባህ ቅርንጫፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለም፡፡  ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን በሌሎች በአቅራቢያ በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች፣ እንዲሁም በዲጂታል የባንክ አገልግሎት አማራጮች እንድትጠቀሙ እናሳውቃለን።

የኔትወርክ መስመሩ ተጠግኖ  ቅርንጫፉ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ወዲያውኑ የምናሳውቅ ሲሆን ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ አንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!


የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም ያለአግባብ የተወሰደን ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ እንደሚቻል ስለማሳወቅ 
===========================
ባንካችን አንዳንድ ግለሰቦች ያለአግባብ የወሰዱትን የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ እስከ  ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ ም ድረስ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመገኘት እንዲመልሱ ጥሪ ባደረገው መሰረት በርካታ ግለሰቦች በቅርንጫፎች እየቀረቡ ገቢ እያደረጉ ቢሆንም ተጨማሪ የመመለሻ ኣማራጭ መስጠት ጠቃሚ እንደሆነ ታምኖበታል::

ስለዚህ ከቅርንጫፎች በተጨማሪ የዲጂታል የክፍያ አማራጮችንም በመጠቀም በቀጥታ ቀድሞ ገንዘቡ አለአግባብ ወጪ ወደተደረገበት በባንካችን የሚገኝ  የባንክ ሂሳባችሁ ማስተላለፍ (transfer) እና ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

20 last posts shown.