የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራ በሚፈለገው ፍጥነት እየተሰራ መሆኑ ምልከታ ተደረገ።
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራ በሚፈለገው ፍጥነት እየተሰራ መሆኑ እና ነዋሪው ወደ ቤቱ እንዲገባ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለመሆኑ ዛሬ ምልከታ ተደረገ።
በምልከታው በ40/60 እና በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበት በአራብሳ ሳይት ሶስት አምስት እና ስድስት ፤ በበሻሌ እና በአያት 2 ጨፌ ሳይት ያሉበትን የስራ እንቅስቃሴ ለማየት ተችሏል።
አቶ አብረሃም ታደሰ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባል በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት ቀንና ምሽት 7/24 እየሰሩ ያሉ ተቋራጮች ያሉበት አፈፃፀም ጥሩ ለውጥ ያለው መሆኑን በምልከታው ማየታቸውን ገልፀው ነገር ግን ሁሉም ጋር ተመሳሳይ ፍጥነት አለመኖሩን ተናግረዋል።
የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ማለትም የቤቶች ፣ የመንገዶች የውሀ እና የመብራት ስራ በየእለቱ እየቀረበ እንዲገመገም እና ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች በየቀኑ እንዲቀርቡ ኃላፊው አሳስበው በየቀኑ ለውጥ ያለው ስራ ለማየት የስራ ባህሉም 7/24 ሆኖ ይቀጥል ብለዋል።
በምልከታው የታዩ የበር ፣ የመስኮት፣ የሳኒተሪ ፣ የፍሳሽ ፣ የመንገድ እና ሌሎችም የሚጎሉ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ኃላፊው አሳስበዋል።
በጉብኝቱ አቶ አብረሀም ታደሰን ጨምሮ የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከመንገድ ፣ ከውሀ ፣ ከመብራት የመጡ የመሰረተ ልማት ቅንጅት ተቋማት ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል ።