በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወደ ተውሒድና ሱና የሚጣሩ ዑለማኦችን በማጠልሸት ላይ የተጠመዱ የፊትና ሰባኪዎች አሉ። ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ጀምሮ ዛሬ እስካሉት ድረስ ላይ ተሰማርተዋል። ሺ0ዎችን አይነኩም፤ እንዲያውም ያምግሳሉ። የተውሒድ ዑለማኦችን ግን ስማቸውን በማጉደፍ ላይ ተሰማርተዋል። ችግሩ የነዚህ እር- ኩሶች መኖር አይደለም። ችግሩ እነዚህን ክፉዎች የሚከታተሉ የዋሆች መኖራቸው ነው። ወገኔ ሆይ! ለራስን እዘን። የምትከታተለው ነገር ተፅእኖ ያሳድርብሃል። የሱና ዑለማኦችን ትጠላለህ። ይሄ ሲሆን ብዙ ኸይር ታጣለህ፤ መንገድም ትስታለህ። ሸይኽ ፈውዛን እንዲህ ይላሉ፦
"አላህ ከበደለኛ ሰዎች ጋር መቀማመጥን ከልክሎናል። ከበደሎችም የከፉ የሆኑት በደለኞች ወደ ፈተና የሚጣሩ ሰባኪዎች ናቸው። ከነሱ ጋር አትቀማመጥ። አታዳምጣቸው። "እኔ አውቃለሁ፣ ሊሸውዱንኝ አይችሉም" አትበል። በጭራሽ! ራስህን አታጥራራ ወንድሜ!"
[ሸርሑ ኪታቢል ፊተን ወልሐዋዲሥ፡ 78]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor