Book Recommendation
መናፍቁ ካህሊል እና ሌሎች
The Complete works of Khalil Gibran
ብዙ ቦታ ለተበጣጠሰ እና እያንዳንዱ ብጣሽ ራሱን እንደ ምሉዕ ሕዝባዊ መንግሥት ለሚመለከት ሕዝብ እዘኑለት፡፡
ሕይወት ከሁሉም ነገር በፊት የነበረች ናት ቆነጃጅት ምድር ላይ ከመወለዳቸው በፊት ቁንጅና ነበረች ስለ እውነት ከመነገሩ ቀድሞ እውነት ነበረች፡፡
ስ
ለ መልበስና እርቃን ስለመሆን፡- መላእክቱ በብልጣብልጦች ተሰላችተዋል ትናንት አንድ መልአክ አግኝቶኝ ሲኦልን
የሰራነው ለነዚያ ለሚብልጨልጩ ሰዎች ነው እቶን እሳት ካልሆነ የሚያንፀባርቅ አካልንና የነገሮችን ውስጥ ምን ሊያቀልጠው ይችላል ? አለኝ፡፡
አበባና ፍሬ የሌለው ዛፍ ብሆን መልካም ነበር ምክንያቱም የመትረፍረፍ ሕመም ከመካንነት ይከፋል ከእጁ ምፅዋት የሚቀበለው ያጣ ሀብታም የሚመፀውተው ካጣ ድሃ የበለጠ ሀዘኑ ይከብዳልና፡፡
በዚህ በባህርዳርቻ በአሸዋና በአረፋው መካከል እጓዛለሁ ባህሩ ከፍ ሲል የእግሬን ዳና ይጠርገዋል ንፋሱም በተራው አረፋውን ይወስደዋል ባህሩና ዳርቻው ግን ይኖራሉ እስከ ዘለዓለም፡፡
ብቸኝነት የደረቁ ቅርኛጫፎቻችንን የሚገነጣጥል ዝምተኛ ወጀብ ነው ሆኖም እግሮቻችንን ሕይወት ወዳለበት የምድር ልብ በጥልቀት ያስገባቸዋል፡፡
መስኮት ዳር ተቀምጠህ ወጪ ወራጁን ስትመለከት በአንዱ በኩል መነኩሲት በሌላኛው ደግሞ ሴተኛ አዳሪ ሲመጡ ታይና በየዋህነት እንዲህ ትላለህ "እነሆ የተከበረችው እና ደግሞ የተዋረደችው መጡ" ከዚያ አይኖችህን ስትጨፍን እንዲህ የሚል ቃል ሲያንሾካሹክ ትሰማለህ"አንዱ በፀሎት ሌላው በሕመም ይጠራኛል በሁለቱም መንፈስ ውስጥ መንፈሴ ታድራለች "