ከራሳችን በላይ ሌላውን ስንወድድ ራሳችንን እንበድላለን። በሕይወታችን ውስጥ ላሉ ሌሎች ሰዎች በትንሿ ልባችን ላይ ቆራርሰን የሰጠነው ስፍራ ብዙ ነው። ስለዚህም በእኛ ዓለም ውስጥ ለእኛ የሚሆን ቦታ አጥተናል። በልባችን የወደድነው ሌላውን ሰው ብቻ እንጂ የገዛ ራሳችንን አይደለም። የገዛ ራሳችንን እንዴት መውደድ እንዳለብን አናውቅም። አልተማርንምም።
•••
ከሌሎች በላይ ራሳችንን አስበልጠን ስንወድድ ሌላውን እንበድላለን። ራሳችንን ስንወድ ለሌላ ሰው የሚሆን ቦታ በልባችን አንተውም። ስለዚህ በእኛ ዓለም ውስጥ ሌሎች ሰዎች ስፍራ ያጣሉ። በልባችን አብዝተን የወደድነው ራሳችንን ብቻ እንጂ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ጭምር አይደለም። ሌሎችን ሰዎች እንዴት መውደድ እንዳለብን አናውቅም። አልተማርንምም።
"ትዝታሽን ለእኔ፣ ትዝታዬ ለአንቺ " በእሱባለው አበራ ንጉሴ