Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Telegram


New and current information specifically about SMEs training, eligibility for the lease financing, documents required by DBE for this service, and other relevant issues are addressed through this channel.

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Telegram
Statistics
Posts filter





38k 0 239 106

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባወጣው ክፍት የስራ ቦታ ለመወዳደር የትምህርትና የስራ ልምድ አሟልተው ነገር ግን የተቀመጠውን የእድሜ ገደብ፣ የመቼ ዓ.ም ምሩቅ፣ ስንት የመመረቂያ ነጥብ የያዙ እና ሌሎች መሰል ጉዳዮችን አስመልክቶ ስለጉዳዩ ካለማወቅ አንዳንድ አመልካቾች የተቀመጡትን መስፈርቶች ባያሟሉም እንደሚያመለክቱ አመላካቾች ታይተዋል፡፡
በመሆኑም፣ ባንኩ ላወጣው ክፍት የስራ ቦታ ለማመልከት የሚሹ ሰዎች ከማመልከታችው በፊት ከስር Notes to the DBE job application የሚለውን ምስል ከፍተው መረጃውን መመልከት ይችላሉ፣ በተለይም፡-

• በጀማሪ መኮንን የሚያመለክቱ
1. እድሜያቸው ከ30 መብለጥ የለበትም
2. በ2020 ወይም ከዛ ወዲህ የተመረቁ መሆን አለባቸው
3. የመመረቂያ ነጥባቸው 3.00 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል

• አንድ አመልካች ማመልከት የሚችለው በ2 የስራ መደቦች ላይ ብቻ ነው
• ሙሉውን ከምስሎቹ ይመልከቱ

የማመልከቻው አድራሻ https://jobs.dbe.com.et/


🆕 አዲስ ዜና🆕

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ኛ ዙር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠናን ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች የቢዝነስ የአዋጭነት ምክረ ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ፡፡

ባንኩ ከወራት በፊት በ4ኛ ዙር የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና 112 ሺህ ለሚሆኑ ስራ ፈጣሪዎች ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ከሰልጣኞች መካከል አምስቱንም ቀናት ስልጠናውን የተከታተሉና ሰልጠነው ያጠናቀቁ ለምስክር ወረቀት ዝግጁ የሆኑ ሰልጣኖች ብቻ ወደ ባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉና የቢዝነስ አዋጭነት ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ነው ባንኩ ያሳሰበው፡፡

ሙሉ በሙሉ ስልጠናውን ተከታትለው ለአጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የማዘጋጀቱ ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ የሰልጣኞችን የስራ ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም ሲባል ቀሪ የሌለባቸው ሰልጣኞች የቅድመ ዝግጅት ስራቸውን እንዲጀምሩ ነው ባንኩ ሁኔታዎችን ያመቻችው፡፡

ሰልጣኞች ወደ አምራች ኢንዱትሪ ዘርፍ ለመግባት ያላቸውን የስራ ተነሳሽነት ባንኩ መደገፍና ማበረታታት ስላለበት የስልጠና የምስክር ወረቀቱ እስኪሰራጭ ድረስ በልዩ ሁኔታ ማስታናገድ እንደሚገባ ስለታመነበት ነው፡፡

በዚህም መሰረት ሙሉ በሙሉ ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ የሰለጠኑ ሰልጣኞች እድሉን በመጠቀም ወደ ተመዘገቡባቸው የባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ በተመቻቸው እድል እንዲጠቀሙ ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡


ማስታወሻ

1️⃣ የ 4ኘው ዙር ስልጠና ተመዝጋቢዎች ሆነው በአንደኛው ምእራፍ/ዙር ያልተጠሩ ሰልጣኞች መኖራቸውን፣ ስለዚህ በቀጣይ በሌሎች 2 ምእራፎች የተቀሩት ተመዝጋቢዎች ጥሪ እንደሚደረግ መነገሩ ይታወቃል።

ሆኖም ግን አንዳንድ ተመዝጋቢዎች ስልኬ ስለማይሰራ ስለነበር፣ ከሀገር ውጪ ስለነበርኩ፣ እና በመሰል ምክንያቶች ለ1ኛው ዙር/ምእራፍ ተጠርተው ከነበር ለማረጋገጥ አሁንም ድረስ በቅርንጫፍ ቢሮዎች እየቀረቡ እየጠየቁ መሆኑንና እነርሱ የሚያውቋቸው ለመጀመሪያው ምእራፍ ስልጠና ጥሪ ከተደረገላቸው ሰዎች ስልክ በመውሰድ እየደወሉ ለማረጋገጥ እየሞከሩ እንደሆነ ተስተውሏል። ስለዚህ ለመጀመሪያው ምእራፍ/ዙር ስልጠና የተጠሩ ሰልጣኞች ስም እስካሁን ያልደረሳችሁና መሰል ጥያቄ ያላችሁ ከ https://www.dbe.com.et/ ድረ ገፅ ላይ እንድትመለከቱት እንጋብዛለን።

2️⃣ የ4ኛው ዙር ተመዝጋቢዎች ቀጣይ ምእራፍ ስልጠና መቼ ነው የሚለው የአብዛኛዎቹ ጥያቄ መሆኑ በተግባር ከሚቀርቡ ተመዝጋቢዎች ጥያቄ ማውቅ ተችሏል።

ይህ ጥሪ መቼ ተደርጎ ስልጠናው ይሰጣል የሚለውን ባንኩ ባሉት የሚዲያ አማራጮች የሚያስታውቅ የሚያስታውቅ ስለሆነ በትእግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።

3️⃣ እንዲሁም ይህንን ስልጠና የወሰዳችሁ የምስክር ወረቀት ስለመዘጋጀቱ ለማወቅና ለመውሰድ እየጠየቃችሁ መሆኑ ታይቷል። ስለዚህ የምስክር ወረቀታችሁ ተዘጋጅቶ እንዳለቀ ባንኩ የሚያሳውቅ ስለሆነ አሁንም በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።

4️⃣ አንዳንዶች ባለማወቅ በአካል እየመጡ በአክስዮን ሰልጣኞችን እንድናደራጅ ባንኩ ፍቃድ/እውቅና ይስጠን የሚል ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ታይቷል።

በአክስዮን መደራጀትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፍላጎቱ ያላቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ዕጩዎችን እንዲደራጁ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ እንጂ ለማንም አካል በአክስዮን የማደራጀት ስራ እንዲሰራ ወይም እንዲሰራለት እውቅና እሰጣለሁ ወይም እፈቅዳለው ብሎ ያስተላለፈው መልዕክት የለም።

ስለዚህ፣ ሰልጣኞችን በአክስዪን እናደራጅ የሚል ጥየቄ እያቀረቡ ያሉ ሰዎች ባንኩ ከሚመራበት ፓሊሲና እና ፕሬዚደንቱ በስልጠና ማእከላት ከተናገሩትና እና በሚዲያ ከሰጡት ማብራሪያዎች መረዳት ያለባቸው ማመልከት የሚሹ ሰልጣኞች/አመልካቾች በሚፈልጉት ፕሮጀክት ዙሪያ ተሰባስበው፣ የአክስዮን ህግን እና አሰራርን ጠብቀውና አሟልተው ሲገኙ ባንኩ ያደራጃቸውና ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል የሚለውን ነው። ባንኩ ለማንም አካል የማደራጀት እውቅና እሰጣለው አለማለቱን መገንዘብ ያስፈልጋል።


ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአክሲዮን ለማደራጀት ፈቃድ የሰጠው አካል የለም!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሰቃሾች ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ በማስገባት ላይ ላይ መሆኑን ተከትሎ በአንዳንድ አካላት ተቋሙን የማይወክሉ የተሳሳቱ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችም ሆነ የአክሲዮን ማደራጀት ስራውን ባንካችን በራሱ አሰራር መሰረት የሚፈጽም እንጂ ሌላ ተቋም እንዲሰራለት ውክልና አልሰጠም።

በመሆኑም የአክስዮን አደረጃጀትን ጨምሮ ሌሎች ባንኩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከባንካችን ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን እና ዌብሳይታችን ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተያያዘውን መረጃ እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ ዜናዎች ከባንካችን ፈቃድ አግኝተው እየሰሩ አለመሆናቸውን እንድትረዱ እናሳስባለን።

ከሰሞኑ አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እየሰጠ ያለውን ስልጠና እንደ መልካም አጋጣሚያቸው ተጠቅመው በአክሲዮን የመደራጀት መልካም እድል እንደተፈጠረላቸው በማስመሰል መኪናን ጨምሮ በወር እስከ 60,000 ብር የሚደርስ ገቢ የሚያስገኝ ስራ እንዳላቸው፣የትርፋማ አክስዮን ድርሻ ባለቤት፣የኤሌክትሪክ መኪና እንደሚያገኙ፣የልማት ባንክ ብድር እንደሚያመቻቹ በመግለፅ ቴሌግራምን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም የባንካችንን ስም በመጠቀም እናደራጃለን፣ ብድር እናሰጣለን በሚል የትኛውም አካል የሚያሰራጨው መረጃ ህገወጥ የወንጀል ድርጊት መሆኑን እንድታውቁና እንዳትጭበረበሩ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአክሲዮን ተደራጅቶ ለመምጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ሂደቶችን በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፆቻችን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

ተመሳሳይ ጥቆማዎችን ለባንካችን በማድረስ ሃሰተኞችን እንድታጋልጡ እየጠየቅን መሰል የማጭበርበር ድርጊቶችን በሚከተሉት ቁጥሮች እንድታሳውቁን በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡

1. 0904374444 ወይም
2.  0904357735 ወይም
3.  0904364436






Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የአባ መላ ሙሉ ቪዲዮ ክፍል አንድ


ረ፡ የማምረቻ ማሽኖችን ከውጪ ሀገር ብቻ ነው መግዛት የሚቻለው?
ለደንበኛው የሚገዙ የካፒታል ዕቃዎች በደንበኛው በራሱ ምርጫ ከሚያቀርበው ድርጅት ነው፡፡ የማሽኖቹ አቅራቢ ድርጅት ከሀገር ውስጥም ከውጪ ሀገርም መሆን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር የሚገዙት ዕቃዎችን የሚያቀርበው ድርጅት በዓለም አቀፍ መስፈርት በባንኩ ተለክቶ ተመራጭ መሆን መቻሉ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መስፈርት መሰረት ተወዳድሮ እሰካሸነፈ ድረስ የማሽኖች ግዢ ከሀገር ውስጥ አምራችም የፈፀማል፡፡

ሰ፡ ለሚገዛው የካፒታል ዕቃ የኢንሹራንስ ወይም መድን ሽፋን የሚገዛው/ኢንሹራንስ የሚገባው ባንኩ ነው ወይስ ደንበኛው?

የካፒታል ዕቃው ከጉዳትና ከብልሽት እንዲጠበቅ ለማድረግ ደንበኛው ከታወቀ የኢንሹራንስ ኩባንያ በልማት ባንክ ስም በካፒታል ዕቃው ጠቅላላ ዋጋ መጠን አስፈላጊውን ዓይነት የኢንሹራንስ/የመድን ሽፋን የሚገዛ እንዲሁም የተገባው የመድን ሽፋን ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ደንበኛው የሚያሳድስ ይሆናል፡፡

ሸ፡ የካፒታል ዕቃውን ሰርቪስ የማስደረግ/የማስጠገን ሀላፊነት የባንኩ ነው ወይስ የደንበኛው?

የካፒታል ዕቃውን በአግባቡ የመያዝና በአምራቹ ድርጅት በተቀመጠው መደበኛ የሰርቪስ ጊዜ ወቅቱን እየጠበቀ ሰርቪስ የማስደረግ/የማስጠገን ግዴታ የደንበኛው ነው፡፡

ቀ፡ ካሁን ቀደም በባንኩ ፋይናንስ ለተደረጉ ድርጅቶች ተጨማሪ ማስፋፊያ ይሰጣል?

አዎ። እንደአዲስ ባንኩን ለሚቀርቡ የተመሰረቱ ድርጅቶች የማስፋፊያ የማሽን ኪራይ /ብድር/ ለሚጠይቁ  አመልካቾች ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር ባንኩ ቀድሞ ፉይናንስ ላደረጋቸው ድርጅቶችም ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት ስኬታማ የስራ እና የፋይናንስ አፈፃፀም ማስመዝገባቸው ሲረጋገጥ ለማስፋፊያ የሚሆኑ የካፒታል እቃዎችን ያቀርባል::


ማብራሪያ ከሚሹ በተለይ በአንዳንድ ሰልጣኞች ተደጋግመው ከሚነሱ ግርታ ካጠላባቸው ሀሳቦች በከፊል

ማውጫ
ሀ፡
ከ500 ሺ እስከ 15 ሚ ካፒታል ብቻውን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ ያደርጋል?
ለ፡ የአገልግሎት ክፍያ መሰላት የሚጀምረው ከመቼ ጀምሮ ነው?
ሐ ፡ የካፒታል ዕቃ ዋጋ በመጀመሪያው ውል ተገብቶ ከነበረው ስምምነት በልጦ ከመጣ ጠቅላላ የብድሩ መጠን እንዴት ይያዛል?
መ: ከላይኛው ጥያቄ ጋር በተያያዘ የስራ ማስኬጃ 20% መዋጮ ከለውጡ ጋር አብሮ ይሻሻላል?
ሠ:ወለድ አልባ የሊዝ ፋይናንሲንግ ማለት ከካፒታል ዕቃው ዋጋ ሌላ ምንም ክፍያ የለውም ማለት ነው?
ረ፡ የማምረቻ ማሽኖችን ከውጪ ሀገር ብቻ ነው መግዛት የሚቻለው?
ሰ፡ ለሚገዛው የካፒታል ዕቃ ኢንሹራንስ የሚገዛው ባንኩ ነው ወይስ ደንበኛው?
ሸ፡ የካፒታል ዕቃውን ሰርቪስ የማስደረግ/የማስጠገን ሀላፊነት የባንኩ ነው ወይስ የደንበኛው?
ቀ፡ ካሁን ቀደም በባንኩ ፋይናንስ ለተደረጉ ድርጅቶች ተጨማሪ ማስፋፊያ ይሰጣል?

ሀ፡ ከ500 ሺ እስከ 15 ሚ ካፒታል ብቻውን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ ያደርጋል?

በተለይ በስራ ላይ ያሉ ድርጅቶች ጥያቄ ከ500 ሺ ያላነሰ ከ15 ሚ ያልበለጠ ካፒታል መኖሩ ብቻውን በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማእቀፍ ለሊዝ ፋይናንሲንግ ብቁ እንደሚያደርግ ይሰማቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ግን በዚህ ማእቀፍ ውስጥ የሚስተናገዱ ድርጅቶች ሊዝ ፋይናንሲንግ የሚጠይቁበት ድርጅት ሊኖረው የሚገባው አጠቃላይ የሀብት ጣሪያ ገደብ አለው፣ ይህም 75 ሚሊዮን ብር ነው፣ ድርጅቱ ያለውን የስራ ማስኬጃ ጨምሮ (የዚህ 20 % 15 ሚሊዮን ብር/አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ጣሪያ፣ 80 % ደግሞ 60 ሚሊዮን ብር/ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የሚያገኙት የብድር ጣሪያ መስጠታቸውን ልብ ይሏል)። ድርጅቱ የሚያስተዳድረው የሀብት መጠን ከዚህ በላይ ነው ማለት 20 በመቶ እና 80 በመቶ ጣሪያዎች ይጣሳሉ እንደማለት ስለሆነ ድርጅቱ የሚስተናገድበት የፋይናንሲንግ አይነት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሳይሆን በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ ይሆናል ማለት ነው።

ለ: የአገልግሎት ክፍያ መሰላት የሚጀምረው ከመቼ ጀምሮ ነው?
የአገልግሎት ክፍያ መታሰብ የሚጀምረው ደንበኛው የካፒታል ዕቃውን መረከቡን የሚያረጋግጠውን የርክክብ ሰነድ ከባንኩ ጋር ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡

ሐ፡ የካፒታል ዕቃ ዋጋ በደንበኛውና በባንኩ ስምምነት ከተደረገና ውል ከተገባ በኋላ በስምምነቱ መሰረት ከውጪ ሀገር የሚገዛው የካፒታል ዕቃ ግዢ ሲፈፀም በገንዘብ ምንዛሬ ለውጥ ምክንያት እንዲሁም ዕቃውን የደንበኛው የማምረቻ ቦታ ለማድረስ የሚከፈለው የማጓጓዣ፣ የተከላ ሥራ እና ተያያዥ ወጭዎች በመጀመሪያው ውል ተገብቶ ከነበረው ስምምነት በልጦ ከመጣ ጠቅላላ የብድሩ መጠን እንዴት ይያዛል?

ይህ አይነት ሁኔታ በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የሚከሰት ነው፣ ደንበኛውና ባንኩ ስምምነት በሚያደርጉበት ጊዜና ዕቃው ተገዝቶ እስኪመጣ ባለው ጊዜ ውስጥ የምንዛሬ ለውጥ የሚኖርበትና ተያያዥ ወጪዎችም የሚንሩበት እድል ሰፊ በመሆኑ። ስለዚህ የመጀመሪያ ውል ላይ የተጠቀሰው ገንዘብ ከግዢ በኋላ በተረጋገጠውና ልቆ በመጣው ወጪ/ገንዘብ ተተክቶ የብድሩ ውል ተሻሽሎ የሚዘጋጅና የሚፈረም ይሆናል፡፡

መ: ከላይኛው ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሚነሳው ሌላ ጥያቄ የስራ ማስኬጃ 20% መዋጮ ከዋጋው ለውጥ በኃላ የደንበኛው መዋጮም አብሮ ይሻሻላል ወይስ መጀመሪያ በባንኩ በሚከፈተው ዝግ አካውንት ውስጥ ተቀማጭ በተደረገው መዋጮ ሂደቱ ይቀጥላል? የሚል ነው፡፡

መረዳት የሚኖርብን ጉዳይ 20፡80 የሚለውን የፋይናንሲንግ ስርአት ነው፡፡ የመዋጮው እሳቤ ባንኩ ለደንበኛው ህልሙን እውን ከሚያደርግለት ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ ላይ 20% መዋጮ ከደንበኛው ያስፈልጋል ነው፡፡ ስለዚህ ደንበኛው በትክክል የፕሮጀክት ባለቤት የሆነበት የገንዘብ መጠን መጀመሪያ የተዋዋለው ሳይሆን በተግባር ከግዢ በኋላ ያለው ወጪ ነው፡፡ ስለሆነም የደንበኛው መዋጮ በሚሻሻለው አዲሱ ጠቅላላ ወጪ ልክ የሚሻሻልና በመጀመሪያውና በአዲሱ መዋጮ የሚኖረው ልዩነት ቀድሞ በማይንቀሳቀስ አካውንት ውስጥ ገቢ የተደረገው ብር ላይ ተጨምሮ ገቢ መደረግ አለበት።

እንደምሳሌ፣ በመጀመሪያ በተገባው ስምምነት መሰረት መዋጮው በዕቅድ ከተያዘው 10 ሚሊዮን ላይ የመዋጮው መጠን 2 ሚሊዮን የነበረ ቢሆን እና ከግዢ በኃላ የፕሮጀክቱ የተረጋገጠ ጠቅላላ ወጪ 11 ሚሊዮን ቢሆን የደንበኛው መዋጮ በሚሻሻለው ስምምነት መሠረት 2.2 ሚሊዮን ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ የብድሩ መጠን ከ10 ወደ 11 ሚ ሲያድግ የመዋጮው መጠንም በዚሁ አግባብ ከ2 ሚ ወደ 2.2 ሚ እንዲያድግ እና የደንበኛው መዋጮ ልዩነቱ ብር 200,000 ቀድሞ በተከፈተው ዝግ አካውንት ደንበኛው ገቢ የሚያደርግ ይሆናል ማለት ነው።

ሰ: ወለድ አልባ የሊዝ ፋይናንሲንግ ማለት ከካፒታል ዕቃው ዋጋ ሌላ ምንም አይነት ወለድም ሆነ ሌላ ክፍያ የለውም ማለት ነው?

በተለይ በአንዳንድ ሰልጣኖች በግልፅ ሲቀርብ የሚሰማው ጥያቄ ይህንን የሚጠቁም ነው፡፡ ወለድ አልባ የሊዝ ፋይናንሲንግ ማለት የሸሪዓ ህግን ተከትሎ አገልግሎት የሚሰጥበት የኪራይ አገልግሎት ማለት ነው፡፡ ይህ የፋይናንስ ስርአት ከብዙ መገለጫዎቹ በዋናነት ወለድን መክፈልም ሆነ መቀበል የሌለበት እና ትርፍና ኪሳራን መጋራትን መሠረት ያደረገ የፋይናንሲንግ አይነት ነው፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ወለድ የሚታሰብበት የብድር አይነት ባይሆንም ምንም ክፍያ የለውም ማለትም አይደለም ከተከራዩ ጋር በሚደረግ ስምምነት ጥቅምን መጋራት በሚል መርህ ስለሚመራ፡፡

የዚህ ወለድ አልባ ፋይናንሲንግ አሰራር ባንኩ የካፒታሉን ዕቃ ገዝቶ ለተበዳሪው አስረክቦ የገዛበትን ገንዘብ ብቻ መልሶ የሚሰበስብበት አይደለም፡፡ ባንኩ የሸሪዓው ህግ በሚፈቅደው አግባብ በኢጃራ ሊዝ ፋይናንሲንግ መርህ መሠረት ለደንበኞቹ አገልግሎት የሚሰጥበት የፋይናንሲንግ አይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ሀገራትና ባንኮች በስራ ላይ ከሚያውሉት ሁለቱ የኢጃራ አፈፃፀሞች ውስጥ ደንበኛው በኪራይ የሚጠቀምበትን የካፒታል ዕቃ ዋጋና የኪራይ ዋጋ በባንኩና በደንበኛው መካከል በሚደረግ ስምምነት መሠረት ለክፍያ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የተተመነውን የክፍያ ድርሻ እየከፈለ ዕቃዎቹን በኪራይ መልክ የሚጠቀምበት እና ባንኩም የኪራይ ውሉ ሲያበቃ ባለቤትነቱን የሚያስተላልፍበት አሰራር ነው የሚሆነው።


የአባ መላ ንግግር በድምፅ አማራጭ




የአነስተኛና_መካከለኛ_ድርጅት_የአስተዳደር_መጽሐፈ_መመሪያ.pdf
1.8Mb
ቢያስፈልግዎ

በአራተኛው ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና እንዲሁም ካሁን ቀደም በነበሩ ስልጠናዎች ላይ በቂ የሆኑ የተለያዩ የስልጠና ሰነዶች ደርሰዋችኋል፡፡

ይህ የአለም ባንክ ቡድን በሆነው የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን በተለይ ለአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ጠቃሚ ምክሮችን የያዘ መጽሀፍ ነው፡፡ ተጨማሪ እውቀት ይሆናል፡፡


የሰልጣኞች ድንቅ ስራ ውጤት

በ4 ኛው ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሰልጠና ሲሰጥባቸው ከነበሩ አጠቃላይ የስልጠና ማዕከሎች ውስጥ ከአስራ አንድ ማዕከላት ብቻ ቃል ከተገባው ውጪ 458,246.50 ብር ተሰብስቧል!!!

እስካሁን በተለያየ አካውንት/ሂሳብ ከሰልጣኞች የተሰበሰበው ገንዘብ በአንድ የጋራ ሂሳብ ውስጥ እንዲጠራቀምና ለተጎጂዎች እንዲደርሰ ሲባል ባንኩ በከፈተውና በሰልጣኞች በሚንቀሳቀሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000530552137 ገቢ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

በቀጣይም ከሰልጣኞች ተወካዮች ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ገቢ አሰባሳቢ አስተባባሪዎች በተገኙበት ገንዘቡን የሚያስተላልፍ ይሆናል፡

እንዲሁም በጎ ምግባር ተሳትፏችሁን ለማስቀጠል የጠየቃችሁ ሰልጣኞች በዚሁ የባንክ ሂሳብ (1000530552137) በ DBE 4TH ROUND SME TR. CONT FOR BORENA አማካኝነት ድጋፋችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።


አክስዮናዊ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
1• በአክስዮን የሚመሰረተው ድርጅት አጠቃላይ መዋቅራዊ ገፅታ ምን ይመስላል?
2• በአክስዮን ለመስራት የሚደራጅ አጋር ከየት ይገኛል/እንዴት እንሰባሰብ?
3• ለመደራጀት ምን ያስፈልጋል?
4• ስንት ሼር መግዛት አዋጪ ነው?

በአክስዮን የሚመሰረተው ድርጅት አጠቃላይ መዋቅራዊ ገፅታ ምን ይመስላል?

በአክስዮን የሚመሰረት ድርጅት ከአሁን ቀደም ከልማት ባንክ ፕሬዚደንት ጋር በተረገው ቃለ ምልልስ እንደተብራራው በቦርድ እና በማኔጅመንት መዋቅር ተከፍሎ ይደራጃል፡፡ የቦርዱ አካል የፖሊሲ ሁኔታዎችን የሚይዝ ሲሆን ማኔጅመንቱ ደግሞ ኦፕሬሽን አካልን የሚይዝ ነው፡፡

የቦርድ መዋቅር፡ ከፍተኛ ሼር ያላቸው በቦርድ እንዲሳተፉ ሲደረግ ትንንሽ ሼር የያዙ ደግሞ እነሱን በሚወክሉ በቦርድ ውስጥ ቦታ ተሰጥቷቸው ይሰራሉ፡፡

የማኔጅመንት መዋቅር፡ ፕሮፌሽናል የሆኑ እንደፕሮፌሽናቸው ድርጅቱ የሚፈልገውን የሰው ሀይል ለሟሟላት በተለያዩ የስራ ክፍሎች ውስጥ (እንደ ፋይናንስ፣ ማርኬቲንግ እና ቴክኒክ የመሳሰሉት) ተቀጥረው ሊሰሩም ይችላሉ፡፡ ይህ ሁለት ዕድልን ይፈጥራላቸዋል አንደኛው እንደፕሮፌሽናቸው ተወዳድረው ተቀጥረው ሰራተኛ ሆነው ደምወዝ እንዲያገኙ ሲያስቻላቸው ሌላኛው ደግሞ ባላቸው ሼር አማካኝነት ባለአክስዮን /ሼርሆለደር/ ያደርጋቸዋል፡፡

በአክስዮን ለመስራት የሚደራጅ አጋር ከየት ይገኛል/እንዴት እንሰባሰብ?

 በአክስዮን ለመደራጀት የሚፈልጉ አካላት በራሳቸው ተሰባስበው/ግሩፕ ሆነው/ መጥተው ሊመሰርቱ ስለወጠኑት አክስዮን ድርጅት ምዝገባ ማከናወን ይችላሉ፡፡
 መሰባሰብ ያልቻሉና /ግሩፕ መፍጠር ያልቻሉ/ በግለሰብ ደረጃ መጥተው በባንኩ አማካኝነት ለመደራጀት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የአክስዮን መስራች አጋርን ለማግኘት ቀላል መንገድ ተፈጥሮላቸዋል፡፡ ይህም በአክስዮን ለመደራጀት የፈለገና የወሰነ ሰው በአካል በልማት ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ቀርቦ ሲመዘገብ ከሚሞላቸው ነጥቦች ሁለቱ ሊሰማራ ያቀደውን ዘርፍ እና የሚገዛውን የአክስዮን ብዛት ያካትታል። አንደኛው ተመዝጋቢ ለመደራጀት በመረጠው ዘርፍ ሌሎችም የሚመርጡ እጩ አክስዮን መስራቾች ይኖራሉ። ስለዚህ በተመሳሳይ ዘርፍ መሰማራት የሚሹ አካላት ሊሰባሰቡ የሚችሉበት አንዱ አማራጭ ይህ ስለሆነ መደራጀት ከሚፈልግ ሰው የሚጠበቀው ለመሰማራት ያቀደበትን የኢንቨስትመንት ዘርፍ አስቀድሞ መርጦ በባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ፎርም ምዝገባ ማከናወን ነው።

ለመደራጀት ምን ያስፈልጋል?

 በአክስዮን የመደራጀት ውሳኔ ‘እስኪ ልሞክረው’ በሚል መንፈስ የተቃኘ መሆን አይኖርበትም፡፡ ይልቁንም በባለቤትነት ስሜትና አመለካከት ከሌሎች ባለራዕዮች ጋር በጋራ ድርጅታዊ ሁለንተና ፈጥሮ የገንዘብ አቅም ያለው ድርጅት ለማቋቋም እና ከልማት ባንክ ለሚቀርበው ሊዝ ፋይናንሲንግ የሚጠበቀውን መዋጮ አቅርበው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በመሆን በጋራ ለመስራትና ለማደግ ፅኑ ፍላጎትና አቋም ያስፈልጋል።
 በመቀጠል የሚሰማሩበትን ዘርፍ እና መግዛት የሚችሉትን ሼር መጠን መወሰንና በዚሁ አግባብ ሼር ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡ ዝቅተኛው የአክስዮን ድርሻ መጠን 5 ሲሆን የእያንዳንዱ ዋጋ 1000 ብር ነው:: ስለዚህ በጠቅላላው ቢያንስ ለትንሹ የሼር መጠን 5,000 ብር ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግዎ ልብ ይሏል፡፡

ስንት ሼር መግዛት አዋጪ ነው? (እይታ፡ አጠቃላይ የአክስዮን ህግ)

(ይህ ፅሁፍ እዚህ መስፈሩ ለጠቅላላ ዕውቀት ታልሞ እንጂ የልማት ባንክን አሰራር በቀጥታ ስለሚውክል አይደለም)

ስንት ሼር መግዛት ጥሩ/አዋጪ እንደሚሆን በቁጥር ማስቀመጥ ምክንያታዊ ስላይደለ ጥያቄውን በምሳሌ መመልከቱ የተሻለ ገላጭ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያ የሚመሰረተው ድርጅት ምን ያህል መነሻ ካፒታል እንዲኖረው ያስፈልጋል የሚለው ተቋማዊ ውሳኔ የሚፈልግና ዋናው ገንዘቡ/ካፒታሉ/ አስቀድሞ ተወስኖ በአክሲዮን የተከፋፈለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለቀለለ ገለፃ ሲባል ብቻ ይህንን የመነሻ ካፒታል መጠን በባንኩ የሊዝ ፋይናንሲንግ ፖሊሲ መሠረት በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች መደብ ውስጥ ለመካተት ሊዝ ፋይናንሲንግ ጠያቂው ድርጅት ሊኖረው የሚገባው የተመዘገበ ካፒታል ከ500,000 እስከ 15 ሚሊዮን መሆን አለበት ከሚለው መስፈርት ውስጥ ዝቅተኛውን 500ሺ እንደሆነ እናስብ፡፡

እንዲሁም አንድ በአክስዮን የሚደራጅ ድርጅት የሊዝ ፋይናንሲንግ ጥያቄ የሚያቀርብበት የፕሮጀክት አይነት አጠቃላይ ወጪ (የማሽኑን፣ ተያያዥ ወጪዎችን፣ እና ስራ ማስኬጃውን ጨምሮ) ብር 10 ሚሊዮን ቢሆን፣ የዚህን 10 ሚሊዮን ብር ሀያ በመቶ (20%)  የሚሆነውን ብር 2 ሚሊዮን የስራ ማስኬጃ መዋጮ መጠን እንደሆነ እንያዝ፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ የሚያስፈልገው የመነሻ ካፒታል እና ከልማት ባንክ ለሚጠይቀው ሊዝ ፋይናንሲንግ የስራ ማስኬጃ መዋጮ በድምሩ 2.5 ሚሊዮን ብር በሚመሰረተው አክስዮን ድርጅት መሰብሰብ ያስፈልጋል ማለት ነው (በምን አግባብ የተከፈለ የድርጅቱ የመነሻ ካፒታል ይመዘገባል እንዴትስ ሀያ በመቶ መዋጮ ለታለመለት አላማ እንዲውል ይደረጋል የሚለው ህጉ በሚፈቅደው አግባብ እንደሚስተናገድ ታሳቢ ተደርጎ)፡፡ በዚህ መነሻ የሚከተሉትን ምሳሌዎች እንመልከት፡-

ም1፡- ይህ ድርጅት ዝቅተኛና ከፍተኛ አክሲዮን ገዢ ሊኖረው እንደሚችል ይታመናል፡፡ ለምሳሌያችን መጀመሪያ እንዲሆን ግን ዝቅተኛ የአክሲዮን ድርሻ ገዢ ብቻ እንዳለ እናስብ፡፡ ስለዚህ በዝቅተኛው 5 የአክስዮን ድርሻ መጠን እያንዳንዱ አክስዮን 1ሺ ብር ሲሰላ በአጠቃላይ 5,000 ብር በአንድ ባለአክስዮን ተዋጣ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የሚፈለገውን ገንዘብ ለማመንጨት በጠቅላላው 500 ባለ አክስዮኖች በጋራ መደራጀት ይኖርባቸዋል እንደማለት ነው (500 ሰው መደራጀት ይችላል ለማለት ግን አይደለም ስንት ሰው መደራጀት ይችላል የሚለው ገና በባንኩ የሚወሰን ስለሆነ)፡፡

ም2፡- በሌላኛው መንገድ ስሌቱን ብንከውነውና ከፍተኛው የተገዛ የሼር መጠን 100ፍሬ እንደሆነ ይህም ማለት በአንድ ባለአክስዮን የ100ሺ ብር አክስዮን እንደተገዛ ብናስብ ድርጅቱን ለመመስረት በጠቅላላው 25 ባለአክስዮኖች መደራጀት ይኖርባቸዋል እንደማለት ነው፡፡

ም3፡- ምሳሌያችንን ተደራሽ ለማድረግ ከላይ የተቀመጠውን ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻ መጠን/ገንዘብ አማካኝ 50 የአክስዮን ድርሻ ወይም 50,000 ብር ብለን ብናሰላው የሚፈለገውን መነሻ ካፒታልና ሀያ በመቶ መዋጮ መጠን ድምር ለማመንጨት 50 ባለአክስዮኖች መደራጀት ይኖርባቸዋል እንደማለት ነው፡፡

ስለዚህ ስንት አክስዮን አንድ ባለአክስዮን ቢገዛ ጥሩ/አዋጪ ነው የሚለው ጥያቄ ከሌላ እይታ ምላሾችን ማግኘት የሚችል ሆኖ ከጥያቄያችን እና ከምሳሌያችን አንፃር ስንመለከተው ግን በአክስዮን ለመደራጀት ከብዙ ምክንያች መሀል በነዚህ በሶስቱ ሃሳቦች ዙሪያም ያጠነጥናል:-

1. በአክስዮን ለመደራጀት የወሰኑ ባለአክስዮን እጩዎች በምን ያህል መቶኛ የድርጅቱን ባለቤትነት መያዝ ይፈልጋሉ (ምክንያቱም በአክስዮን ድርሻቸው ልክ በድርጅቱ ላይ ባለቤትነት ሊኖራቸው መቻሉ)
2.  የተጣራ ዓመታዊ ትርፍ የሚከፋፈለው ባለአክሲዮኖቹ ባሉአቸው አክሲዮኖች መጠን ልክ ሊሆን መቻሉ  (የተጣራ ትርፍ በምን ሁኔታ ይከፋፈል የሚለው ውሳኔ በማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የሚተላለፍ ሆኖ)
3. ባለአክስዮኖች አክስዮን ለመግዛት ባላቸው የገንዘብ አቅም ላይ የተወሰነ መሆኑ፡፡






ጠቃሚ መረጃ አይሲቲን መሰረት ላደረጉ ጀማሪዎች እና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ጋር በመተባበር ለፈጠራ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (Innovative SMEs) እና ለጀማሪዎች (Start-ups) ቀጥተኛ ፋይናንስ አቅርቦትን ለማሳደግ ከፊል የብድር ስጋት ዋስትና ፈንድ (Partial Credit Risk Guarantee Fund) ለማቅረብ ፍላጎቱ ላላቸው የቢዝነስ ፕሮፖዛላቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ እነዚህ የፈጠራ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና ጀማሪዎች ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ (Home Grown Economic Reform Agenda) ጋር የሚሄዱ ዘርፎች/ተግባራት ውስጥ ሊተገበር የሚችል የንግድ ሥራ ሀሳብ ያላቸው እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡

ማን ማመልከት ይችላል
• የኢትዮጵያ ዜግነት መታወቂያ ካርድ ያላቸው
• በአይሲቲ ላይ የተመሰረተ ፈጠራ ያለው የንግድ መፍትሄ ያላቸው ጀማሪዎች እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች
• የንግድ ፕሮፖዛላቸውን በድረ-ገጹ ላይ በተሰቀለው ቅርፀት /Format/ መሠረት ለማቅረብ ያዘጋጁ
• ያዘጋጁት የንግድ መፍትሔ በኩባንያ ደረጃ ወይም አስቀድሞ በገበያ ላይ መሆን አለበት።

ስለምልከታው ሂደት፣ የምርጫ ሂደት እና በምርጫው ሂደት ስላሉ መስፈርቶች ለማወቅ ከዚህ ጋር የተያያዘውን ሰነድ/ምስል ይመልከቱ፡፡

ለዚህ ፕሮግራም ለመመዝገብና ፕሮፖዛላችሁን ለማቅረብ የሚቀጥለውን ሊንክ ተጭነው ይድረሱ
http://registration.mint.gov.et

የማመልከቻ ጊዜ
>ፌብሩዋሪ 30, 2023 ይጀምራል
>ማርች 30 ቀን 2023 ያልቃል

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0967-94-45-00 ወይም 0993-53-01-03 ይደውሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ዩኤንዲፒ፣ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA)


ካስያዙት የስራ ማስኬጃ ተጨማሪ የስራ ማስኬጃ ብድር ማግኘት ይችላሉ?

ያስያዝነው 20% መዋጮ ለስራ ማስኬጃ ከተለቀቀ እና ካለቀ በኃላ በቀጣይ በሚኖረው የምርት ሂደት የስራ ማስኬጃ እጥረት ቢገጥመን ባንኩ የስራ ማስኬጃ ብድር ይሰጠናል ወይ? የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ እየተነሳ ይሰማል።

በመሠረቱ የስራ ማስኬጃ ተብሎ ደንበኛው ካስያዘው መዋጮ የሚለቀቀው ብር ድርጅቱ ወደስራ ለመግባት የሚያስችለውን መነሻ አቅም የሚፈጥርለት ነው። አቅም የፈጠረ እና ማምረት የጀመረ ድርጅት ደግሞ ለስራ ማስኬጃ የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን በአብዛኛው ከድርጅቱ ምርታማነት እና ገቢ እንደሚያመነጭ ሳይንሳዊው የስራ ካፒታል አስተዳደር አስተምህሮ ያስቀምጣል። ይህም ማለት ያለ ሃብት (current assets) (ለምሳሌ በባንክ የተቀመጠ ብር ፣ ማስያዣዎች (securities)፣ በመጋዘን ያሉ ንብረቶች እና በ12 ወራት ውስጥ ወደጥሬ ገንዘብ የሚቀየሩ ተከፋዮች (receivables)) ድርጅቱ ካሉበት ዕዳዎች ማለትም ከሚከፈሉ ወጪዎች (ለምሳሌ ለጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች ፣ ለአከራዮች፣ ለውሃ፣ ለመብራት፣ ስልክ እና ወለድ የሚከፈል) እና በ12 ወራት ውስጥ መከፈል ካለባቸው ወጪዎች አንፃር በልጦ የሚገኝበት ሁኔታ እሙን ነው፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ በቀላሉ አሁናዊ የፋይናንስ ግዴታዎቹን በራሱ ሊያሟላ እንደሚችል ይታመናል፡፡

ሆኖም ደንበኛው በዝግ አካውንት ገቢ ያደረገውን የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ተጠቅሞ ሲጨርስ ልላ የስራ ማስኬጃ ብድር ማግኘት ቢፈልግ በተሻሻለው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንሲንግ ፖሊሲ LFP/002/2022 መሠረት ተከራዩ ተጨማሪ የስራ ካፒታል ብድር ከንግድ ባንኮች ወይም ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዋስትና ሊበደር ይችላል። ባንኩ ይህንን መሰል የአጭር ጊዜ የስራ ካፒታል ብድር ሊሰጥ የሚችለው ደግሞ ከሁለት አመት የስራ ጊዜ በኋላ የድርጅቱ የስራ አፈጻጸም ደረጃ ታይቶ ነው።

⁂ ካስያዙት የስራ ማስኬጃ ተጨማሪ የስራ ማስኬጃ ብድር ማግኘት ይችላሉ?
»»»»» አዎ፣ የባንኩ የሊዝ ፋይናንሲንግ ፖሊሲ ያስቀመጠው መስፈርት እስከተሟላ ድረስ፡፡

በስልጠና ወቅት በአግባቡ እንደተገለፀው (ከስልጠናው ፓወር ፖይንት ቀጥታ ግልባጭ)፡-
1. ተከራዩ ተጨማሪ የስራ ማስኬጃ ካፒታል ብድር ከንግድ ባንኮች ወይም ከባንኩ በመያዣነት መበደር ይችላል።
2. ባንኩ ከሁለት አመት የስራ ጊዜ በኋላ የስራ አፈጻጸም ደረጃ ላላቸው ደንበኞች የአጭር ጊዜ የስራ ካፒታል ብድር ሊሰጥ ይችላል።

20 last posts shown.

29 604

subscribers
Channel statistics