ተማሪ ጎሳ ከበደ የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ምርጫ በቅርቡ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን የጆርናሊዝም እና ኮሚኒኬሽን ት/ርት ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ ጎሳ ከበደ አብላጫ ድምስ በማግኘት የ2017 ዓ/ም የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል።
የህብረቱ ም/ፕሬዝዳንት ተማሪ ራያን ራጂህ ከ ሚድዋይፈሪ ት/ርት ክፍል እንዲሁም የህብረቱ ጸሃፊ ተማሪ እውነቱ ታምራት ከ ሳይካትሪ ት/ርት ክፍል ሆነው ተመርጠዋል።
የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ማኔጅመንት አዲስ ለተመረጡት የተማሪዎች ህብረት አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የዩንቨርሲቲያችን ማህበረሰብ አዲስ ለተመረጡት አስተባባሪዎች እገዛ እና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርቧልአ።
ድሬደዋ፣ ጥር 9 ፣ 2017 (የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት)
ለበለጠ መረጃ
ድረ ገጽ:
http://www.ddu.edu.et/ ፌስቡክ:
https://www.facebook.com/DDUniv/ ቴሌግራም:
https://t.me/DDUniv/ ትዊተር፡
https://twitter.com/DDUniv/