ኢትዮጵያ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን በየት ሀገር ታደርጋለች?በመጋቢት ወር አጋማሽ ከጅቡቲ እና ከግብፅ ጋር ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለባት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች በቅርቡ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን የሚያስመዘገቡትን ውጤት ተንተርሶ ሊታደስ በሚችል የአንድ ዓመት ውል ብሔራዊ ቡድኑን እንዲመሩ መሾማቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ በካፍ በተጣለባት ዕግድ ምክንያት ጨዋታዎቿን በገለልተኛ ሀገር ማድረግ የሰነባበተችው ሀገራችን አሁንም በቀጣይ የምታደርገውን የማጣርያ ጨዋታ በሌላ ሀገር ለማድረግ ፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ይገኛል።
በዚህም መነሻነት በሦስት ሀገሮች ኢትዮጵያ ጨዋታዋን እንድታደርግ መታሰቡን አውቀናል እነርሱም በደቡብ አፍሪካ ፣ በአይቮሪኮስት እና በሞሮኮ መሆናቸው ሲታወቅ በእነዚህ ሀገሮች ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ እየገመገመ የሚገኘው ፌዴሬሽኑ በቅርቡ በየትኛው ሜዳ ጨዋታውን ማድረግ እንዳሰበ ለካፍ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።
ከሦስቱ ሀገራት መካከል ሞሮኮ ጨዋታዎቹን የማስተናገድ የሰፋ ዕድል ያላት ሲሆን በቅርቡ ሁሉ ነገር ቁርጡ እንደሚለይለት ይጠበቃል።
- SOCCER ETHIOPIA
" SHARE " |
@DREAM_SPORT