Dr Lombamo Medium Clinic


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Medicine



Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Medicine
Statistics
Posts filter


** የወባ በሽታ ስርጭት**

የወባ በሽታ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ በሆኑ የአየር ፀባይና አካባቢዎች በቀላሉ ሊስፋፋ ይችላል፡፡  በተለይ ቆላማ በሆኑ ቦታዎች ለወባ መስፋፋት ምቹ የሆነ ሙቀትና የአየር ርጥበት ያለባቸው ሲሆን

    👉 በዝናብ ምክንያትና አንዳንዴም በድርቅ ወቅት ወንዞች በመቆራረጣቸው የተነሳ
    👉 በየአካባቢው ውሀ ያቋቱ ስፍራዎች መበራከትና
    👉 በአግባቡ ያልተያዙ ረግረግ  መሬቶች መፈጠር እንዲሁም ከደጋማው ለወባ ተጋላጭ ካልሆኑ አካባቢ ወደነዚህ ቆላማ ስፍራዎች የህብረተሰብ እንቅስቃሴ መጨመር ለወባ መስፋፋት ምቹ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 

👉 የወባ በሽታ መከላከያ መንገዶች

    👉 ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ስራዎችን መስራት

    👉 የጸረ ትንኝም ሆነ የጸረ ዕጭ ኬሚካል መጠቀም
    👉 በኬሚካል የተነከረ አጎበር  ሁል ጊዜ መጠቀም

👉 የወባ በሽታ ምልክቶች

በትንኝ ንክሻ ወቅት ተሀዋሲው  ወደ ደም ዘልቆ በመግባት የደም ሴሎችን በማጥቃትና በሌሎች የውስጥ አካላት ላይ ጉዳት በማድረስ በሽተኛውን ለከፋ ጉዳት ብሎም ለሞት ይዳርጋል፡፡
አንድ ሰው የወባ በሽታ አምጭ ተህዋሲውን በያዘች ትንኝ ከተነከሰና የበሽታ ተሃዋሲ በደሙ ውሰጥ ከገባ በኋላ በሽታው በደም ዝውውር አማካይነት በጉበቱ ውስጥ ይገባል፡፡ ጉበት ውስጥ ገበቶ ተራብቶ አስፈላጊውን ሁኔታዎችን ባሟላ ከ7- 14 ባሉት ቀናት ውስጥ አንድ ሰው የበሽታውን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡ ከእነዚህም ምልክቶች ውስጥ
   👉  ከፍተኛ ትኩሳት፣
   👉 ብርድ ብርድ ማለት፣
   👉  ማንቀጥቀጥ፣
   👉 የመገጣጠሚያ አካላት ህመም፣
   👉 ቁርጥማት፣
   👉 የራስ ምታት፣
   👉 የምግብ ፍላጎት መቀነስና 
   👉 ማስታወክ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ 
ምልክቶቹ በየ2 ቀኑ እየተመላለሱ የሚያሰቃዩ ሲሆን በተለይም ህመሙ ኘላዝሞዲየም ፋልሲፓረም በተባለው የበሽታ አምጭ ተህዋሲ የመጣ ከሆነና በቂ ህክምና ካልተገኘ ከዚህ በከፋ ሁኔታ ማለትም እንደ ራስን መሳት፣ እንደሚጥል በሽታ አይነት መንፈራገጥ፣ እንዲሁም በከፋ ደም ማነስና የጉበት፣ የኩላሊትና የሳንባ ጉዳት ሊያደርስና ለሞት ሊዳርግም ይችላል፡፡

እነዚህን ምልክቶች ካዩ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ!

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦ https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


የወባ በሽታ ወረርሽኝ

👉 የወባ በሽታ ምንነት

የወባ በሽታ ኘላዝሞዲየም በሚባል የደም ውስጥ ጥገኛ ተህዋሲ አማካይነት የሚመጣ አደገኛ በሽታ ነው፡፡ሌሎች እንስሳትን የሚያጠቁ  ዝርዎችም እንዳሉ ቢታወቅም የሰውን ዘር የሚያጠቃው ኘላዝሞዲየም ፉልሲፓረም፣ኘላዝሞዲየም ቫይቫክስ፣ ኘላዝሞዲየም ኦቫሌ እና ኘላዝሞዲየም ማለሪዬ በተባሉ አራት አይነት ዝርያዎቹ ነው፡፡

👉 የወባ በሽታ መተላላፊያ መንገዶቹ

የወባ በሽታ አኖፌለስ በተባሉ የትንኝ ዝርያዎች እንደሚተላለፍ የሚታወቅ ሲሆን በሴቷ ትንኝ ንክሻ አማካይነትም ከህመምተኛ ወደ ጤነኛ ሰው ይተላለፍል፡፡ የወባ በሽታን የሚያስላልፉት አራት አይነት ብቻ ናቸው፡፡

የወባ በሽታ አስተላላፊ ትንኝ የምትራባው በአብዛኛው በጊዜያዊነት ባቆሩ ውሃዎች ላይ  ሲሆን አልፎ አልፎ ዕጮቿ በወንዞችና በሀይቆች ዳርቻ ሊገኙ ይችላሉ፡፡  በተጨማሪ በመኖሪያ አከባቢ በሚገኙ ዉሃ መያዝ በሚችሉ ቁሳቁሶች ላይ በቀላሉ ትራባለች፡፡

ትንኟ ዕቁላሏን ለማኩረት የሚጠቅማትን ደም ለማግኘት ስትል  በሰዎች ጠረን፣ ሙቀትና ትንፋሽ በመሳብና ወደ ሰዎች አካል በመቅረብ ትናከሳለች፡፡ ንክሻው በአብዛኛው በምሽትና (ከምሽት እስከ ንጋት ባለው ጊዜ ውስጥ) በቤት ውስጥ ሲሆን ከቤት ውጭም ይከናወናል፡፤ አኖፊለስ  አረቢየንሲስ የተሰኘችው ዋናዋ የወባ አስተላላፊ ትንኝ ቤትም ተመገበች ውጭ በአብዛኛው የምታርፈው በቤት ውስጥ ነው፡፡

**ይቀጥላል**




Vacancy Announcement

Dr Lombamo Medium Clinic, located at Hossana, wants to hire a General practitioner who has Graduated from recognized medical institution

Number: 1
Work experience: 0 years
Gender:  Male/ Female
Salary : negotiable
Employment form : full time
Hadiyisa language proficiency is preferable

How to apply : All interested applicants can apply in person at Dr Lombamo Medium Clinic, Hosanna, Gombora, 50meters on the way from taxi marozia to Gofermeda or using our telegram

Tel: 0911512338 or via our email Address- babeshoy@gmail.com

Application deadline : October 9 to 14,  2024


እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሰዎ!! እያልን በዓሉ የሠላምና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

ክሊኒካችን በሞያቸው አንቱታን ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀኪሞች ከተሟላ የላቦራቶሪ ምርመራ ጋር አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦ https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።


እንኳን ለ2017ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሰዎ እያልን አዲሱ ዓመት የሠላምና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

ክሊኒካችን በሞያቸው አንቱታን ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀኪሞች ከተሟላ የላቦራቶሪ ምርመራ ጋር አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦ https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዻጉሜ 1-5 የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ።

እርሶም በስራ ሰዓት በክሊኒካችን በመገኘት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ጋብዘኖታል።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com telegram ፦https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው !!!!


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዻጉሜ 1-5 የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ።

እርሶም በስራ ሰዓት በክሊኒካችን በመገኘት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ጋብዘኖታል።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com telegram ፦https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው !!!!


አስደሳች ዜና ለሆሳዕና እና አከባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዻጉሜ 1-5 የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

እርሶም በስራ ሰዓት በክሊኒካችን በመገኘት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ጋብዘኖታል።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው !!!!


ካለፈው የቀጠለ ፨፨፨፨፨፨

ከዚህ በተጨማሪ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም፣ አልኮል መጠጥ መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት የዘር ፍሬን መጠን ሊቀንስ ይችላል።


ወንዶችን ለመካንነት የሚያጋልጡ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?


ሲጋራ ማጨስ
አልኮል መጠጥ መጠጣት
አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም
ከመጠን ያለፈ ውፍረት
ጭንቀት
የአባለዘር በሽታ
በዘር ፍሬ ላይ የሚደርስ የኬሚካል፣ የጨረር እና የከፍተኛ ሙቀት አደጋ፤
በወንድ የመራቢያ አካል ላይ የሚሠራ የቀዶ ጥገና፤
በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ችግር ከአለ ወይም ከነበረ፤


የወንዶች መካንነት እንዴት ይታከማል?

በወንዶች ላይ መካንነትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች እንደሚለያዩ ሁሉ ሕክምናውም ይለያያል።
ጥንዶች ቢያንስ ለ 12 ወራት ያለ ወሊድ መቆጣጠሪያ በቂ ግብረ ሥጋ ግንኙነት እየፈፀሙ ልጅ ካላገኙ ወደ ሐኪም ቤት በመምጣት የሕክምና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ሐኪም ቤት ከመጡ በኋላ ሁለቱም የተለያዩ ምርመራዎች ይደረግላቸዋል።

ለወንዱ ከሚደረግለት ምርመራዎች ውስጥ ዋንኛው የዘር ፍሬውን መለካት እና በቂነቱን ማረጋገጥ ሲሆን ይህም ምርመራ ሴመን አናሊሲስ (semen analysis) ይባላል።

የተለያዩ ምርመራዎች ከተደረጉ እና ችግሩ ከተለየ በኋላ እንደ ችግሩ የተለያዩ የሕክምና አማራጭች ይቀርባሉ።

ለምሳሌ
የዘር ፍሬ ፈሳሽ እንዳይወጣ የሚያግድ ጠባሳ ካለ በቀዶ ጥገና ማስተካከል ይቻላል።

በተመሳሳይ ቫሪኮሴሌ የሚባለው መካንነትን የሚያመጣው የጤና እክልም በቀዶ ጥገና መስተካከል የሚችል ነው።

በተጨምሪም የወንዱን የዘር ፍሬ ሕዋስ በማውጣት ላብራቶሪ ውስጥ የሴቷ ዕንቁላል ጋር ይደባልቁታል።

የተለያዩ መንገዶች ተሞክረው ልጅ መረገዝ ካልተቻል እንደ ጉዲፈቻ ያሉ አማራጮችን መጠቀም ይቻላል።

ምንጭ - wecare


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


ካለፈው የቀጠለ ፨፨፨፨፨፨

ከእነዚህ በሽታዎች ውስጥ ጥቂቶቹ
አንድ አንድ ጊዜ የዘር ፍሬ ከረጢትን የሚመግበው የደም መልስ ቧንቧ ሊያብጥ ይችላል።

ይህም ቫሪኮሴሌ (varicocele) ይባላል። ይኽንን በሽታ አክሞ ማዳን የሚቻል ቢሆንም የወንዶች መካንነትን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች መካከል ዋንኛው ነው።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ጨብጥ ያሉ በልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች የዘር ፍሬ የሚታልፍበትን መንገድ በጠባሳ ሊዘጉ ይችላሉ። አንዳንድ ኢንፌክሽኖች ደግሞ የዘር ፍሬ ሕዋሳት እንዳይመረቱ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ስንፈተ ወሲብን ጨምሮ የተለያዩ ከግብረ ሥጋ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ለመካንነት ምክንያት ሆነው ይጠቀሳሉ።

ሌላው ምክንያት የዘር ፍሬ ፈሳሽ ወደ ውጭ መውጣቱን ትቶ በተቃራኒው ወደ ሽንት ፊኛ ሲገባ ነው። ይህም ሬትሮግሬድ ኢጃኩሌሽን (retrograde ejaculation) ይባላል።

ይህም ሁኔታ በስኳር በሽታ፣ በተለያዩ መድኃኒቶች አማካኝነት፣ ኅብለ ሰረሰር ላይ በሚደርስ አደጋ እንዲሁም በፊኛ ቀዶ ጥገና አማካኝነት ሊፈጠር ይችላል።

አንዲሴንድድ ቴስቲስ (Undescended testicles) በፅንስ ዕድገት ጊዜ የወንድ የዘር ፍሬ ከረጢት ከፅንሱ ሆድ ውስጥ ወጥቶ ወደ ታች ይወርዳል።

አንድ አንድ ሕፃናት ላይ ግን ይህ አይፈጠርም።
በዚህ ጊዜ የዘር ፍሬን የሚያመነጨው አካል በሆድ ውስጥ ስለሚቀር እና ለከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ስለሚጋለጥ የዘር ፍሬ ማምረቱን ይቀንሳል ወይም ያቆማል።

ይህም ለመካንነትን የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል።

አነስተኛ የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን፤
መካንነትን የሚያመጡ በዘር የሚወረሱ የተለያዩ የጤና ችግሮች አሉ።
ለምሳሌ ክሌንፌልተርስ ሲንድረም (Klinefelter's syndrome) የሚባል በሽታ የወንድ መራቢያ አካል በትክክለኛ መልኩ እንዳይሠራ የሚያደርግ በሽታ ነው።

በወንዱ መራቢያ አካል ላይ የሚሠሩ የተለያዩ የቀዶ ጥገና ዓይነቶች ጠባሳን በመፍጠር የዘር ፍሬ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ሊያግዱ ይችላሉ።

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ለተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች፣ ጨረር እና ለከፍተኛ ሙቀት መጋለጥ የዘር ፍሬ ምርትን ሊቀንስ ይችላል።

አንዲሴንድድ ቴስቲስ (Undescended testicles) በፅንስ ዕድገት ጊዜ የወንድ የዘር ፍሬ ከረጢት ከፅንሱ ሆድ ውስጥ ወጥቶ ወደ ታች ይወርዳል።
አንድ አንድ ሕፃናት ላይ ግን ይህ አይፈጠርም።

በዚህ ጊዜ የዘር ፍሬን የሚያመነጨው አካል በሆድ ውስጥ ስለሚቀር እና ለከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ስለሚጋለጥ የዘር ፍሬ ማምረቱን ይቀንሳል ወይም ያቆማል።

ይህም ለመካንነትን የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል።
አነስተኛ የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን፤

ይቀጥላል
ምንጭ - wecare


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


መካንነት በወንዶች ላይ ሊከሰት ይችላል ?????

መካንነት በወንዶች ላይ ( Male Infertility )

መካንነት የሚባለው ጥንዶች ቢያንስ ለ አንድ ዓመት ያህል ሞክረው (ቢያንስ በሳምንት 3 ጊዜ ያለወሊድ መቆጣጠሪያ) ልጅ መውለድ (ማርገዝ) ካልቻሉ ነው። ነገር ግን ሴቷ ከ 35 ዓመት በላይ ከሆነች በ6 ወር ብቻ ምርመራ ሊጀመርላት ይችላል።
በተደረገው ጥናት መሠረት 85% የሚሆኑ ጥንዶች በመጀመሪያው 12 ወር ውስጥ ሴቷ ትፀንሳለች። የተቀሩት 10% የሚሆኑት ጥንዶች ደግሞ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ይሳካላቸዋል።
መካንነት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ። ከእነዚህ ውስጥ፤
አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ የሴቷ ችግር፤
አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ ደግሞ የወንዱ ችግር ሲሆን፤የተቀሩት አንድ ሦስተኞቹ ላይ በሴቷም በወንዱም ላይ ችግር ተገኝቷል።

መካንነትን በወንዶች ላይ የሚያመጡ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?
የተለያዩ የጤና ችግሮች በወንዶች ላይ መካንነትን ያመጣሉ። እነዚህ የጤና እክሎች እንዴት መካንነት እንደሚያመጡ ለመረዳት በመጀመሪያ ትክክለኛው የዘር ፍሬ እንዴት እንደሚሠራ እና መጠኑን መረዳት ያስፈልጋል።
የወንድ የዘር ፍሬ የሚመረተው የዘር ከረጢት ውስጥ ነው፡፡ ወንዱ ለዐቅመ አዳም ከደረሰ ጊዜ አንሥቶ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዘር ፍሬዎች ይመረታሉ። እነዚህ የዘር ፍሬ ሕዋሳት እንዲመረቱ ቴስቴስትሮን (Testosterone) የሚባል ሆርሞን ዋነኛውን ሚና ይጫወታል። እነዚህ የዘር ፍሬ ሕዋሳት ከተመረቱ በኃላ በአምስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያድጋሉ። ቀጥሎም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሴሚናል ፈሳሽ ከሚባል ጋር በመደባለቅ በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ወደ ሴቷ መራቢያ ክፍል ይገባሉ።
በአማካኝ
በአንድ ግዜ የሚፈስው የዘር ፈሳሽ 1.5 - 5 ሚሊ ሊትር ሲሆን
በአንድ ሚሊ ሊትር ውስጥ የሚኖረው የዘር ፍሬ ብዛት ከ15 ሚሊዮን ይበልጣል፡፡ በጠቅላላው ከ39 ሚሊዮን የሚበልጥ የዘር ፍሬ ሕዋሳትን በውስጡ ይይዛል።
በመጨረሻም ከቁጥሩ በተጨማሪ የዘር ፍሬ ሕዋሶቹ መጠናቸው እና ቅርፃቸው እንዲሁም የሚንቀሳቀሱበት ፍጥነት አስተዋጽዖ አለው።
ከላይ ከተጠቀሰው ሂደት ውስጥ አንዱ ላይ ችግር ከአለ መካንነት ሊከሠት ይችላል። በዚህ ምክንያት የወንዶች መካንነት በተለያዩ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል ማለት ነው። ከ 30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው የመካንነት ችግር የሚፈጠረው ቆለጥ ላይ በሚደርስ ችግር ነው፡፡ ከ 10 እስከ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከ ዘር ፍሬ ከረጢት ተነሥቶ የሴቷ የመራቢያ አካል እስኪደርስ ባለው መተላለፊያ ቱቦ ላይ በሚደርስ ችግር ምክንያት የሚከሠት ነው።
ይቀጥላል
ምንጭ - wecare


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


መካንነት በወንዶች ላይ


Habayyi 2016HD Yesuus kiristoos leh kich ugudina xumine afisukko

እንኳን ለ2016ዓ.ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም  አደረሰን የሚለን ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እንዲሆን ይመኛል ።

       መልካም የትንሣኤ በዓል
ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


ወንዶች ልጆቻችንን መቼ ነው ማስገረዝ ያለብን?

ብዙ ቤተሰቦች ልጃቸውን ለማስገረዝ ተመራጩን  ዕድሜ ይጠይቃሉ፡፡ ልጅ ለማስገረዝ በጣም ተመራጩ ዕድሜ ከተወለደ ከ 8 ኛው ቀን ጀምሮ እስከ ሦስተኛው ወር መጨረሻ ድረስ ነው፡፡ ምክንያቱም ፤

1. ህጻናት በዚህ እድሜ ትንሽ ህመም ይሰማቸዋል

2. በግርዛት ወቅት ብዙ ስለማይንቀሳቀሱ  አያስቸግሩም

3. ወደፊት የዚህን ግርዛት (የቀዶ ጥገናውን) ምንም ትውስታ አይኖራቸውም

ከአዋቂዎች ግርዛት ጋር ሲነጻጸር፤ የሕፃናት ግርዛት ቀላል በሆኑ ዘዴዎች ይከናወናል እንድሁም ለመዳን አጭር ጊዜ ይወስዳል፡፡በልጅነት ጊዜ የተገረዙ ወንዶች የቁስሉ ቦታ በጊዜ ሂደት በትክክል ስለሚድን የተሻለ (የማይታይ) ጠባሳ ይኖራቸዋል።

ካለን ልምድ የቀለበት የግርዛት ዘዴ አንድ ልጅ ከአራት ወር በታች ሲገረዝ የተሻለ ይሰራል። ይህ እድሜ ለእናቲቱም ሆነ ለህፃኑ በጣም ተስማሚ ነው፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ አብዲሳ
የቀዶ ህክምና ስፔሻልስት

በዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ ዘወትር በስራ ሰዓት በቀዶ ጥገና እስፔሻሊስት ሀኪም

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።
አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338/0913762936


የኩፍኝ በሽታ


የኩፍኝ በሽታ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሰዎ!
በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!
ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ
አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው
መልካም የገና በዓል!


*የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን*

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሽንት ስርዓት አካላትን ማለትም (ኩላሊትን፣ የሽንት ፊኛን እና የላይኛውን (Ureter) እና የታችኛውን (urethra) የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦዎች የሚያጠቃ የኢንፌክሽን አይነት ነው። ብዙዎቹ ኢንፌክሽኖች የታችኛውን የሽንት ቧንቧዎች (Urethra) እና የሽንት ፊኛንና (Urinary Bladder) ያጠቃሉ። ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ኢንፌክሽኖች ከሽንት ፊኛ አልፈው ወደ ኩላሊት ከተሻገሩ አሳሳቢ የጤና እክል ሊያስከትሉ ይችላሉ።

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው?

አንዳንዴ ምልክት ላያሳይ ይችላል ፤ ካሳዩ ግን ምልክቶቹ እነዚህን ይመስላሉ፣
• በመጠን አነስተኛ ግን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት
• ደመናማ የመሰለ የሽንት ከለር
• የሽንት ከለር መቀየር – ቀይ፣ ሮዝ ወይም ጠቆር ያለ ሽንት —ከሽንት ጋር የደም ምልክት
• ያልተለመደ ጠንከር ያለ የሽንት ሽታ
• ማህፀን አካባቢ የሚሰማ የመጫን ህመም (ለሴቶች) ወይም ወንዶች ብልታቸው አካባቢ እና የሽንት ፊኛ አካባቢ የሚሰማ ህመም፡፡

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መንሰኤዎች

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ባክቴሪያ ወደ ሽንት ቧንቧ ገብቶ በሚራባበት ጊዜ ነው። የሽንት ስርዓታችን በተፈጥሮ ባክቴሪያዎችን እንዲያስወግድ የተሰራ ቢሆንም አንዳንዴ ተፈጥሮአዊው መከላከያ መንገድ አሰራሩን በማሽነፍ ባክቴሪያዎች ወደ ሰውነታችን ገብተው በሽታ ሊያመጡ ይችላሉ። በተፈጥሮ የብልቶቻችን አቀማመጥ የተነሳ ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተጋለጡ ናቸው ። የግብረ ስጋ ግንኙነት ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሴቶችን በተለይ የበለጠ ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል።
ሴቶች በተለይ ባላቸው የሰውነት አቀማመጥ (Female anatomy) ምክንያት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት፣ በማህፀን ውስጥ በሚቀመጡ አንዳንድ የወሊድ መከላከያዎች እንዲሁም የሴቶች ማረጥ (Menopause) ጊዜ የበለጠ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከፍተኛ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
ከነዚህም በተጨማሪ የሚከተሉት ሁኔታዎች የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ይጨምራሉ::

• ጤናማ ያልሆነ የሽንት ቧንቧ ኖሯቸው የሚወለዱ ህጻናት
• የሽንት ቧንቧ መደፈን፦ በኩላሊት ጠጠር ምክንያት
• የበሽታ መከላከያ ስርዓት መጎዳት፦ ለምሳሌ በስኳር በሽታ ምክንያት – ተፈጥሮአዊው በሽታ መከላከያ ብቃት እንዲቀንስ በማድረግ ለኢንፌክሽኑ ተጋላጭ እንድንሆን ያደርጋል።
• አርቴፊሻል የሽንት ቱቦ (ካቴተር )የሚጠቀሙ ህመምተኞች
• የሽንት ፊኛ፣ ፕሮስቴት ወይም የኩላሊት ቀዶ ጥገና ያደረጉ ሰዎች ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የበለጠ ተጋላጭ ናቸው::

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከበረታ ምን አይነት ችግር ሊያመጣ ይችላል ?

የታችኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በአግባቡና በጊዜ ከታከመ ለክፉ አይሰጥም። ካልታከመ ግን ከባድ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። እነዚህም
• ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች
• ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ኢንፌክሽን እና መዳከም
• ነፍሰጡሮች ላይ ከተከሰተ ደግሞ የሚወለደው ህጻን መጠኑ ከሚገባው ያነሰ ወይም ያለጊዜው ሊወለድ ይችላል።
• Sepsis, ለህይወት አስጊ የሆነ እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ኢንፌክሽን ነው፤ በተለይ ወደ ኩላሊት የሚዛመት ከሆነ።

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መከላከያ መንገዶች ምንድን ናቸው?

1. በቂ ውሃ መጠጣት:- ውሃ መጠጣት ሽንትን ይበርዛል፤ እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንድንሸና በማድረግ ባክቴሪያው ኢንፌክሽን ሳያመጣ ከሽንት ቧንቧ እንዲወርድ ያደርጋል።
2. ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሽንት ቧንቧ አካባቢን ማጽዳት፤ እንዲሁም ውሃ በመጠጣት ባክቴሪያው እንዲወገድ ማድረግ፣
3. የሴቶች የተለያዩ የብልት ማጽጃዎች እንደ ዴወደራንት እና ፓውደር አለመጠቀም። እነዚህ አይነት ማፅጃዎች ባክቴሪያ ወደ ሽንት ቧንቧ እንዲገባ እድል ይፈጥራሉ፣
4. የወሊድ መከላከያ መንገዶችን መቀየር ካለብዎት ከሐኪምዎ ጋር ይማከሩ ፣ በተለይ ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያጠቃዎት ከሆነ። እንደ ዲያፍራም (Diaphragm) ወይም spermicide-treated ኮንደሞች ለባክቴሪያ እድገት አስተዋጽኦ አላቸው።
5. በጊዜ ሐኪምዎን ያማክሩ ፣ መድሃኒት ከታዘዘሎት በአግባቡ ይውሰዱ።



20 last posts shown.