E4J ስነ ፅሑፍ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


በተሰጠን ፀጋ እግዚአብሔርን እናገልግል
የተለያዩ መንፈሳዊ የስነ ፅሑፍ ስራዎችን የሚያገኙበት Channel @e4jgxm
❤️መንፈሳዊ መፅሐፍት
❤️ግጥሞች
❤️ወግ
እና
❤️ሌሎች መንፈሳዊ ፅሑፎች ይገኙበታል
ዋናውን ግሩፕ ለማግኘት
👇👇👇👇
❤️ @e4jesus❤️

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ሰላም ለእናንተ ይሁን
የኢትዮጵያን ለኢየሱስ የግጥም ቤተሰቦች
ይሄን ቻናል ስለ ማንጠቀም እዚህ ይለቀቁ የነበሩት በሙሉ የሕብረቱ ቻናል @e4jsong ላይ ስለ ሚለቀቅ እስከ አሁን ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ትቀላቀሉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያን ለኢየሱስ
የቴሌግራም ግሩፕ @e4jesus
ቻናል @e4jsong


ኢትዮጵያን ለኢየሱስ (E4J)


ርዕስ፦ ፍቅር እኛን አለ

እንኳን ለጌታችንና ና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

እንኳን በክርስቶስ መወለድ ሆነልን

🥰🥰🥰🎄🎄🎄
❤❤❤❤💥💥
መልካም በዓል

@e4jesus
@e4jgixm
@e4jsong


✍   መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ በኢትዮጵያን ለኢየሱስ ግሩፕ ( @e4jesus ) እሁድ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ  ኑ አብረን እንማማር

እንዲሁም ግጥም ይኖረናል ከE4J ገጣሚያን ጋር

   ኢትዮጵያን ለኢየሱስ

        ❤️ @e4jesus(ዋና ግሩፕ)
        ❤️ @e4jsong(መዝሙር ብቻ)
        ❤️ @e4jgxm (ግጥም)


ማን ያንከባለዋል?🤔😔

በጠንካራ ድንጋይ ታትሞ የኖረ፤
አንከባላይ ጠፍቶ ተደፍኖ የቀረ፤
ማን ያንከባለዋል?
ይህን ሸህም ድንጋይ
ጥበቆች ዝምአሉ፤
መላዕክ እስኪወርድ
እስኪመጣ ከላይ፤
እስኪ ያንከባለው
ማህተሙን ድንጋይ፤
ምስጢሩ ይገለጥ በማለዳ ይታይ፤

👆👆👆
🙏🙏🙏
❤❤❤

📖በሰብለ እዳኤ✍️


ማንንም አይንቅም የተባለለት እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ሲንቅ እናያለን በሰው ፊት እየተከበሩ በእግዚአብሔር ከሚናቁ ወይም በሰው ፊት ቢናቁም ባይናቁም በእግዚአብሔር ከሚከበሩ ሰዎች አንዱ ለመሆን ምርጫው የኛ ነው
ከትልቅነቱ የተነሳ አይተኬ ከትንሽነቱ የተነሳ አይጠቅሜ ሰው በእግዚአብሔር ቤት የለም
ሁሉ ቦታ አለው ነገር ግን ሁሌም ሰው ብቻ መሆናችንን ማስታወስ ልካችንን ማወቅ ይህንን ለሚያስገነዝቡን ሰዎች ቦታ መስጠት ( ማክበር ) ከምንም በላይ ደግሞ ቅዱሱን መንፈስ ማድመጥ ይበጀናል የእግዚአብሔርን ስራ ለስማችን ማስጠሪያ እንዳናደርገው መጠንቀቅ ይኖርብናል እራሳችንን ከፍ ከፍ እንድናደርግና ሁሉ በእኛ የተደረገ እንዲመስለን ማድረግ ከሚቃጣቸው ሰዎችም መሸሽም ደግ ነው
✍ጳውሎስ ፍቃዱ

በቸር ዋሉ🙏


#ይሰበር ብልቃጡ

እሩቅ በተባለች ቢታንያ ሀገር፤
ኢየሱስ ሲገባ በትንሿ መንደር፤
ከፈሪሳዊው ቤት ግብዣ ለመታደም
የድግሱ ተስካር፤
ምርጫውም አልነበር፤
ጣፋጭ ህይወት ሊቸር፤
የእርሱማ ቁም ነገር፤

ጎራ ሲል ወደቤት፤
ወደ ታደመበት፤

አስተናጋጅ ጠፍቶ ሀጥዕ በሞላበት
ድንገት ከተፍ አለ ህዝብ ወደሞላበት፤
ድግሱን ታዳሚ
ይመስላል ሲቀመጥ፤
ዙሪያውን ቢያማትር ወደ ግራና ቀኝ
እራሱን እሚገልጥ አጣ እኔነኝ ባይ

አንዲት ሴት ተነሳች ጌታ ማረኝ ብላ
የያዘችው ብልቃጥ በሽቶው የሞላ
በፊቱ ሰበረች፤
እግሩንም በጸጉሯ እየደባበሰች፤
የእንባዋን መንታ ከአኖቿ እየቀዳች፤
ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፤
እኔን ማረኝ አለች፤
ዝግት ባለ ልሳን ስቅ ስቅ እያለች
የድንጋይ ውርምታ
የሰዎች ጫጫታ
ዙሪያዋን ቢከባት
ነፃነቷ እንጂ እሚሰጣት ህይወት
ፃድቅ ፊት ልትቀርብ፤
ምንም እንኳ ባይኖር፤
ልቧንም ሰብራለች ውድ ስጦታዋን
የስምዖን ደስታ፤
አይጠቅመው ለጌታ፤
ለጊዜው ነው እንጂ
አያልፍም ከማታ፤

ብልቃጡ ይሰበር


ይታይ የእኛ ደስታ


📖በሰብሊ✍️


#አይቆጨኝም

መንገድእናእውነት
ህይወትንማወቄ፤
መከተል ብጀምር የመዳኔን ፅድቄ፤
ሀጥዕ ሥሬን ሳይሰድ
ጉልበቴ ሳይላላ፤

አይቆጨኝም እኔ፤

በወላፈን እሳት በእቶን ብበላ፤
መንገዱ እኔነኝ ልጄ ካለኝማ፤
ተዉኝልከተለው ምንም ሳላቅማማ፤
የህይወት ሚዛኔ የኔነቴ ካስማ፤
ሽቶዬ ቢያርሰው፤
የእግሮቹንም ወዝ
ፀጉሬ ቢያብሰው፤

በቃ አይቆጨኝም ግራ መጋባቱ፤

መስማማትን መረጥኩ፤
ልቤን ካሸፈተው ከዚህ ክንደብርቱ፤
እራሴን ብሰጠው አትርፌ ከእሳቱ፤
ከሲዖል ይሻላል
ሰማይን መምረጡ፤
የምድር ደስታ ፌሽታ
ባይገባኝም እዛ፤
ፍፁም አይቆጨኝም
ብመስል ፈዛዛ፤
ብባል እመርጣለሁ
እማይገባት ጌጃ፤
እርድና እማታውቅ
እንሰሳ ናትእንጃ፤

ቢሉኝ
ቢያሾፉብኝ፤

ምንም አልቆጭም፤

ለታወረባቸው፤
ሞኝ ለመሰልኳቸው፤
ምነው ባይነካኩኝ፤
አባሱት ንዳዴን ይልቅ ቆሰቆሱኝ፤
መንደዴን ቀጠልኩኝ፤
ማንስ ሊያዳፍነኝ፤
ጠፍቷል እሚያጠፋኝ፤

አይቆጨኝም እኔን

መዳኔን መምረጤ
ይብላኝ ለአባጆች ለእነ ምናምንቴ፤
በአዳኙ አምላክ ድናለች ህይወቴ፤

@e4jesus🇪🇹
@e4jsong🇪🇹
@e4jgxm🇪🇹

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹


📖በሰብለ እዳኦ✍️


#እኔነኝ በጊቷ

ሁሉ ከሞላበት ከአባቴ ቤት ርቄ፤
በድፍርሱ ውሀ ላልጠራ ጠልቄ፤
ውስጠቴ ቆሽሾ ተጨመላልቄ፤
በሀጢአት አሻራ ወድቄ ዘፍቄ፤

መልኬን ሲያበላሸው የራሴ እኔነት
የተመካሁበት
የእኔ ያልኩት ጉልበት፤
አውቃለሁ ባይነት፤
የእኔ ጠባብነት፤

ግድፈቴ ላይጠራ፤
ጉድለቴ ላይሞላ፤
ያተረፍኩ ሲመስለኝ
ጥብቀቴ ሲላላ፤
ለካስ ፈላጊዬ መተሀል ከኋላ፤
ጥበቃህ በዛልኝ በአውሬ ላልበላ፤
አመሰግናለሁ አባቴ ከለላ፤
አሮጠህ ታደግኸኝ አንተ ባለመላ፤
እኔ ነኝ በጊቷ የታሰብኩትማ፤
🙏😥😥🙏

መልካም.......

@e4jesus🇪🇹
@e4jsong🇪🇹
@e4jgxm🇪🇹

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹



✍️ ሰብለ እዳኦ📖


#ሰማራዊቷ ነኝ

ውሀዬን ልቀዳ ገንቦዬን ሸክፌ፤
ማዶማዶ እያዩ ሲያማትሩ አይኖቼ

ከጉድጓድ አጠገብ
አንድ ሰው ተቀምጧል፤
ደቀ መዛሙርቱ ትተውት ሔደዋል

ገና ጎንበስ ብዬ፤
ውሀ ከመቅዳቴ፤
ከጥሙ እንዲረካ፤
ሲጠይቀኝ ለአፍታ፤
ቀድቼ ሰጠሁት የውሀ ጠብታ፤

ሰማራዊነቱ ግራ ቢያጋባኝም፤

ጥያቄ ጠየኩት፤
አንተማነህ አልኩት፤
ጥያቄ ተሞልቶ የእኔነት አንደበት፤

ደግሜ ጠየቅሁት
አንተአይሁዳዊ፤
ከእኔ ሰማራዊት ምን ትፈልጋለህ፤
እንዴት ከመንደሬ ውሀ ትለምናለህ
ብዬ ከማለቴ፤
እርሱም መለሰልኝ
በጥያቄ ብዛት ውስጥሽን ስታኪ፤
ብዙ ከነበሩት በአንዱ ሳትረኪ፤

ግድ ነበር የኔ በበርሽ ማለፌ፤
ወደ ባዶነትሽ ወደ አንቺ መቅረቤ፤
ከጉድጓዱበታች
ቢመስልሽም ቀልቤ፤
ይህ የእኔ አይደለም ሀሳቤ የልቤ፤
የአንቺ እርካታ እንጂ የኔ እርካታዬ


✍️ ሰብለ እዳኦ📖


#ድርሻችን የቱ ነው?

የአደባባይ ጩኸት ሆኖ ፀሎተችን፤

ቂምና አድመኝነት ተሞልቶ ልባችን፤

አመፅን በክፋት ወርሶትውልዳችን፤

እንዴት እንመለስ ታውሮ ልባችን፤

ሰማያዊው ቀረ የእኛ መክሊታችን፤

ሻማውም ቀለጠ ጠፋ ብርሀናችን፤

በማይመጥን ምኞት ስልጣናችንበዝቶ፤

በወኔያችን ላይ ደርበን ብትቶ፤

ውስጣዊው ፀጋችን፤

በሸረሪት ብልጠትድርንም አድርቶ፤

ሻገተ እንጀራችን እሚበላው ጠፍቶ፤

አንቅረን ጥለናል ከቤታችን ሸቶ፤

እንቅቡም አረጀተጠቃሚው ጠፍቶ፤

ለአምላክ ሳናስተውል፤
ትዕዛዙን ሳንፈፅም፤

ቃላችን ታጠፈ ኪዳናችን የለም፤

እንዴት እንፈወስ፤
ማንስ እኛን ያክም፤

ውስጣችን ባዶነው፤

መፍትሔ ያጣ ህመም፤

ወላፈኑ በዝቶ በእሳት ስንፋጅ፤

ምልጃና ፀሎቱ፤
ሲርቀን ከእኛውደጅ፤

ማን ደፍሮ ይመስክር፤
ማንስ ይበል አዋጅ፤

በአደባባይ ቀርቶ የእኛ ጩኸትማ፤
እንዴት አንድ እንሁን
እንዴት እንስማማ፤

ወንጌሉን ጥለናል እግዜ/ን ሳንሰማ
ይህ ጭካኔያችን አርጎናል ጨለማ፤
እስኪ እንመለስ ልባችን አይድማ፤

ድርሻችንን አውቀን
የእውነት ክርስትና፤
መባል ይበጀናል
የወንጌል ባለአደራ፤
እንንቀ እንቸኩል ጌታ ይመጣልና፤
💔🙏🙏



✍️ ሰብለ እዳኦ📖


. #ናፍቀናል...
በስምህ  ያሾፉት
  የተዘባበቱት 
ትመጣለህ ስንል
መቼ ከወዴት ያሉት
አይነን ሁሉ እያየህ
ኢየሱስ ትመጣለህ
ናፍቀናል
የመለከቱ ድምፅ ሲነፋ ልንሰማ
ናፍቀናል
ለማየት አዲሲቱን ምድር አዲሱን ከተማ
ናፍቀናል ልዑል ሆይ 
ፊትህ ከማይደክሙት
ከማያርፉት ጋራ
ቅዱስ ቅዱስ ማለት
ናፍቀናል ልዑል ሆይ
ተስፋችንን ማየት
ከዕረፍታችን ደርሰን
ከአንተ ጋር መሰንበት
ናፍቀናል ጌታ ሆይ
ልንሆን ባለህበት


Forward from: @Seleslamenwk
ሊጠቅማችሁ ስለሚችል አንብቡት 👇

ጌታን በትጋት የሚያገለግሉ ስወች ምክርና ምክርነት መስማት በጣም እወዳለሁ ምክኒያትም ያለፉበትን ስለሚያስተምሩ ይጠቅማልና ።
በቅርቡ ወደ ጌታ የሔዱት #ወንጌላዊ #ገብሩ እንዲህ ብለው መከሩን
1/ ለታመሙ ስወች ሁሉ ጸልይ እግዚአብሔር ይፈውሳል ያልተፈወስውን ስው ስታይ እኔ እምነት የሌኝ ሆኖ ስውየው እምነት የለው ሆኖ አትበል እግዚአብሔር የሚፈውስውን ይፈውሳል ያልተፈወሱትን ለምን እንዳልፈወስ እግዚአብሔር ያውቃል

2/ ወንጌል ለመመስከር ስትወጡ 2 ሁኑ አንዱ ይመስክር አንዱ በልቡ ይፀልይ

3/ እየስራችሁ ማንንም ሳትንቁ በስራችሁ ጌታን አሳዩ
ለሚስሩት ስወች መስክሩ ከሁሉ በላይ በህይወታችሁ ጌታን ይይዩት ታማኞች ሁኑ ።

4/ ለመመስከር ስትወጡ ስወች ጋር አትከራከሩ መስክራችሁ እለፉ እናተ መስክራችሁለታል ደንዳና ልቡን አነቃንቃችሁለታልና ሌላ ስው ደግሞ ሲመስክርለት ያምናል ።

6/ ስወችን እንደ ሁኔታቸው ቅርቡ ከምስጊኑም ጋር እንደ ስውየው ሁኔታ ቅርቡት

7/ የምትፈልጉትን ጌታን በትጋት ጠይቁት

8/ ለዲያቢኖስ ምንም ክፍተት አትስጡት

9/ አገልጋዮች ከሌሎች አገልጋዮች ተማሩ ከመፅሃፍ ቅዱስ ውጭ የሚጠቅማችሁን መፅሃፍ በብዛት አንብቡ

10/ የምታገለግሉትን ህዝብ ምንም ባይረዳችሁም ውደዱት

11/ ከሁሉ በላይ ትሁትና የፍቅር ስወች ሁኑ በዚህ ህይወት ነው ጌታ የሚስራው

12/ ስራ ቦታችሁን እና ስራችሁን ለወንጌል አድርጉት ታማኞች ሁኑ ፣ እየስራችሁ ድሆችን እርዱ

13/ ለምታገለግሉት አገልግሎት የሚረዳችሁን ጸጋ ለምኑ


14/ ምንም ስወቹን ባታውቁም ባትግባቡም ለቅሶ ቤት ሒዱ ህዝቡን በእግዚአብሔር ቃል አፅናኑ እግዚአብሔር በዛ ይስራል

15/ ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሁሌ ጸልዩ
የጸጋ ስጦታ አጠቃቀሞችን በደንብ ተማሩ

16/ ስነፎች አትሁኑ ትጋት ይኑራችሁ

17/ የማካፈል ህይወት ይኑራችሁ

18/ እግዚአብሔር ሲናገር ጫፍ ይዛችሁ አትሩጡ እግዚአብሔር ተናግሮ መጨረሻ ላይ ምን አለ ? ንስሃ ግቡ አለ ? እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ አለ ? እፈውሳለሁ አለ ? ተዘጋጅ ልወስድህ ነው አለ ? የመጨረሻዋን ቃሉን በደንብ ስሙ ስምታችሁ ታዘዙ

19/ ከበሽታ እግዚአብሔር ፈውሳችኋል ይተባላችሁ ስወች ህመሙ አለባችሁ ያላችሁ ሃኪም ነውና ሔዳችሁ አርጋግጣችሁ ነው መዲሃኒት መጣልና ምስክርነት መስጠት ያለባችሁ ።

20/ ስውን በፍፁም በፍፁም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ

21/ በአስተምሮ የሳቱትን ወገኖች ምከሩ አስተምሩ እንጂ ስውየውን በፍፁም አትሳደቡ አትናቁትም


ህይወት ለየቅል

ድርሻ ተቀብሎ ከአባቱ ጉያ፤
የጠፋው ልጅ ሔደ
ተሰነባበተ ያው በራሱ ፈቃድ፤
አንዳች ሳያቅማማ፤
አንድ ሀሳብ ሳይኖረው፤
በሁለቱ እይታ ልቡ የታተመው፤
የእግዜሩ ቢሰወር፤
ታድያ ምን ዋጋ አለው?፤
ፈቃዱ ይበልጣል፤
ይሁን እርሱ ያለው፤
ይሔ ካልሆነማ፤
ህይወት ለየቅል ነው፤
ጆሮ ያለው ይስማ

ሉቃስ 15:11
@e4jesus
@e4jesong
@e4jgxm

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
🙏🇪🇹🇪🇹🇪🇹🙏


📖ሰብለ እዳኤ✍️


የታመነ ደም ነው የኢየሱስ
የረከሰን ሁሉ ሚቀድስ
ኃጢአት ቢሸት እንደ ደም ቀልቶ
ያጠራዋል ልክ እንደ ባዘቶ
ለተጨነቀች ነፍስ መሸሻ
ምሕረት አለው ፊቱን ለሚሻ...

#ቤቲ_ተዘራ
@e4jgxm


✍ የእርሱ መስቀል ይለያል!!

አሳየን የፍቅሩን ጥልቀት
                 በሰውነት እንባ
ከዙፋኑ እርቆ ስጋችንን ለብሶ
                    አፈር እስኪገባ
መስቀል ተሸክሞ በትከሻው
ጣዕር አልተለየው እስከ ነፍሱ
        ትግል እስከ መጨረሻው
አንተን የወለደች ማዕፀን
                ብለው እንዳልመረቁ
ሸላቾች ሲያሾፉ የሸላች ሳቅ ሳቁ
ለራሱ የእሾህ አክሊል ተጎነጎነ
ሰው በዘይት ሲወዛ እሱ
                       በደም ሸገነ

የሕይወት ቃል የወጣበት አንደበቱ
                           ለጣር ሲከፈቱ
ደዌያንን የፈወሱ እጆች
          ዓይንን የፈጠሩ
በደረቅ እንጨት ላይ
         ለስቃይ ሲወጠሩ
      የጅራፉ ሽራብ
    ቆዳውን ይዞ ሲነሳ
አጥንቱ አስኪገለጥ
         ቆዳው እስኪሳሳ
     ተገረፈ ተሰቃየ
    ማቀቀ ደቀቀ ላመ
እስከ ነፍሱ ስቃይ ታመመ
        ለእርድ ተጎተተ
በጦር ጫፍ ስለት
   በደረቅ አለንጋ አካሉ ተፈተፈተ
ዓይኖቹ ፍቅርን አለቀሱ
            ጀርባው ተማፀነ
ለጉዳቱ ትቶ ለበደላችን ለመነ
የወንበዴውን ንቀት ስድብና ዘለፋ
            ሁሉን ታግሶ ችሎ
ምሕረትን ለመነ እርሱ ተበድሎ
        የእርሱ መስቀል ይለያል
         በደም ተጨማልቋል

      ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
  @e4jesus    @e4jsong
        @e4jgxm


✍ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ በኢትዮጵያን ለኢየሱስ ግሩፕ ( @e4jesus ) እሁድ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ ኑ አብረን እንማማር

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ

❤️ @e4jesus(ዋና ግሩፕ)
❤️ @e4jsong(መዝሙር ብቻ)
❤️ @e4jgxm (ግጥም)




ተጀመረ
ዛሬ ምሽት ከ3.00 ሰዓት ጀምሮ
ሳምንታዊ የቃል ጊዜ
የጌታ ሰላም ይብዛላቹ ውድ የኢትዮጵያን ለኢየሱስ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ዕለተ ሀሙስ ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርታችንን እነሆ ዛሬ ለመጀመር ብናረፍድም በህብረታችን ውስጥ በቅርቡ ከተቀላቀለችን ነብይት ፈለቀች ጋር የእግዚአብሔርን ቃል በጥቂቱ እንማራለን ክብር ለጌታ ይሁን አሜን

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@e4jsong
@e4jesus
@e4jgxm
ተባረኩልን


#ወንጌል ነው እውነቱ፨

ተቅበዝባዡ ሲተርፍ፤
ባዶነቱ ሞልቶ፤
መነሳቱ ሲልቅ፤
ውድቀቱ ተረስቶ፤
የምስራቹን ቃል፤
በልብ እሚያሰርፅ፤
ወንጌል ነው እውነቱ፤
ትውልድ አሚያሳርፍ፤
በሰማይ በረከት፤
በምድር መቶ እጥፍ፤
ነፍስንና ሥጋን፤
ከሲዖል እሚያተርፍ፤
የሙታንንተስፋ፤
ህያው የሚያደርግ፤
ማይደፈርስ ሰላም፤
ህይወት የዘለዓለም፤
የዓለምን ደዌ፤
በፍቅሩ እሚያክም፤
ይህ ነው የእውነት ቃል፤
የመለኮት ዓለም፤
ፀብን እሚያስወግድ፤
እርቅን እሚዘራ፤
በጥፋት ለሚኖር፤
በምህረት ሚራራ፤
የምስራች ቃሉ፤
የፍለጋው ድምፁ፤
ዛሬም ለሚጠፋው፤
ፈላጊ ነው ልቡ፤
በባህል እስራት፤
በተተበተበው፤
ሲወርድ ሲዋረድ፤
ትናንት በነበረው፤
የልብ እምነት ከድቶት፤
ቅስም ለተሰበረው፤
የብሔርን ካባ ከትከሻ አውልቆ
የልጁን መልክ ሊገልጥ፤
ወደ ጫካው ዘልቆ፤
የእምነትን ምስጢር፤
እንዲኖር አጥብቆ፤
ተገልጧል እውነቱ ፤
ወንጌል ብስራቱ፤
ዛሬም
እየሰራ ከትናንት ከጥንቱ፤
ገና ይቀጥላል የወንጌል እሳቱ፤

@e4jgxm
@e4jsong
@e4jesus
ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
🇪🇹🇪🇹❤❤🙏

@📖ሰብለ ኤዳኦ✍️


✍️ እንጀራ እና ውሀ
****
አዳም በበደለ ፣ ቃል እንዲሞት ታዞ
ፍቅር የሕይወት ምንጭ ፣ ከአብ ልብ ፈሶ
ሰው በልቶ እንዲጠግብ ፣ ጠጥቶ እንዳይጠማው
እንጀራ ተራበ ፣ ውሀን ውሀ ጠማው

📌  የሕይወት እንጀራ 👉 #ኢየሱስ 👈 የሕይወት ውሀ!!


#ሄኖክ_አሸብር

20 last posts shown.

495

subscribers
Channel statistics