EBC ሀገር አና ጥበብ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Quotes


ይህ EBC ያዘጋጀው የተሰጦ PROGRAM ግዜውን የምመጥን እንዲሁም የህዝብን ወኔ የምቀሰቅሱ ፁሁፍችን እንዲሁም Video ካላቹ ልካቹልን ጥሩውን ደሞ መልሰን የምንጋብዞ ይሆናል።
Channel Join በማለት አጋርነቶን ያሳዩን።

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Quotes
Statistics
Posts filter


🧐 2+1-3(4+5)=❓


መ ቀ በ ያ ገ ነ ት

በምን ልጄምረው ይጠባል ይጨንቃል
ኬየት ልፈልግልሺ ያልተገለጸ ቃል
ሳ'ይደብቅ ሳ'ያጠብ ሳ'ይቀንስ ውበትሺን
ምስልሺን እሚያሳይ ሚነግርልኝ ሀቁን

እረ እንደው ጪንቅ ነው ቃላትን ማዳከም
ሙይው መቼም ይሁን አርሚኝ ግድየለም

አንሼ አዳይመሰልሺ ከብዶኝ ነው ጸዳልሺ
ቻይው ባልቺልሺም ፍቀጂ ልጀምር
እኔ እድፍ ልጂሺ !

ፍቅርን የቀዱብሺ ምስጥርን ያወቁ
የአለም መሰላል መሰረተ እንቁ
የጠቢቦች እናት የክብር ማክዳ
የዘመን መስፈሪያ የመዓቶች ጓዳ

ማጄትሺ የሞላ ያ'ልቀናሺ በሌቦቺ
ያ'ስቀየመሺ ጊዜ ጥበብን ቀሚዎቺ
የድህነት መገኛ ማለፊያ የጥፋት ..
የምህረት ማደሪያ
መጄመሪያ መንገድ ነሺ መሄጃ ማብቂያ

ገደሉ ተሰርቶ መሀሉ ጎርብጦ
ቢጫንሺም አሁን ቋጥኝ ተገልብጦ

ሺ' እድፍ ቢበዛ አንድሺ ቢቆሺሺ
እልፍ ነው ኢትዮጰያ የተዋበው ልጂሺ

የድል ምልክቶች የመሰረት ሀውልት
አንጋፋ መሪዎች የእሮም ጌታ አባት
በባዶ እግራቸው ክብሩን የሰው ልክ
የጻፉ በአካል ሀገር ፍቅር ታሪክ

የእኛ ምልክቶች የኢትዮጵያ ቀለም
ያ'ነሱን ትልቆች ያ'ሳዩን በአለም
የዘመን አንደኛ የብርቱዎች ፋና
ፊት ቀዳሚ አርማ የሀገሬ ጄግና

አበበ እና ማሞ ምሩጽ በለማርሹ
እናቴ ያንች ልጆች ናቼው እማ ይዋሹ

ሺ' እድፍ ቢበዛ አንድ ሸ'ቢቆሺሺ
እልፍ ነው ኢትዮጵያ የተዋበው ልጂሺ

አሰለፈች ማሬ ገ/እዛብሔር አልማዝ
ሙክታር ኀጎስ ዮሚፍ የክብራችን ደሞዝ
እጂጋየሁ እድሪስ ሰለሞን መሰረት
ጌጤ ዋሜ ብርሃኔ የኃሴት በረከት

የተጎናጸፉ አንችን ትልቅ እናት
ቀልጠው ያበሩልሺ ሰም ጣፍ ሻማ መብራት
የልጂ ሺልማቶች ያአንቺ አበርክታ
ናቼው እናት አለም የሚያውቁ ውለታ

የዘመንሺ ጥሪት የክብርሺ ከፍታ
ቁልቁለት ቢወርድም ሀቅሺ ባይፈታ

ጉሮሮሺ ቢደርቅም ስእቅታው ቢያቅሺ
ምራቅሺ ቢሰረቅ ሌቦች ቢደብቁሺ
ምንጪ አለ ፏፏቴ የሚቀዳ በህር
አንጄትሺን እሚያርስ ጊዜ ገፍቶ እማይቀር

ሺ'እድፍ ቢበዛ አንድ ሺ'ቢቆሺሺ
እልፍ ነው ኢትዮጵያ የተዋበው ልጂሺ

የኢትዮጵያ ሞተር የብዙዎች ብርታት
ጌጥ ምልክት እንቁ የእኛ አሷ ሺልማት
የከፍታ መንገድ የፍቅር ማደሻ
ደራርቱ አንድነት አድማስ መናገሻ

የክብር እንቁዎች የመስፈሪያ ልኬት
በአንች የተሰሩ የኩራት ሰገነት
እሷ'ናት እናቴ አካል መታያዬ
እሚሉሺ ወዳጆች ልጂዎች አሉ እምዬ

ጥሩዬ ገዛኀኝ ጄግናው ቀነኒሳ
ስለሺ ገንዘቤ የመጠሪያ ካሳ
ዝነዋ ግርማዋ የወርቅ መቅረዝዋ
የሀገሬ ሞገስ ናቼው ወድ አልማዝዋ

ምስክር ቃል ስራው ዋጋው የገነነ
ስም ያወጣል መልዐክ ኃይሌም ሀይልሺ ሆነ

ብዙ አሉ ገና መኳ'ያ ፍሬዎች
እናቴ አትስሚ ዘር በታኝ ዘሪዎች
መንገዱን ቢስቱት ገደል ቢናፍቁ
ቢያበቅሉ ጪካኔ እርጉም ቢመረቁ

ደሀ ስም ሰተውሺ የሀብት መጣ'ያ
ጫካ'ናት ቢሉሺም የአውሬ ማጎሪያ
አንደኛ ነሺ አንቺ የእውነት መቃ'ኛ
የእውቀት የጥበብ የአዳም ዘር መገኛ

ጥንተ ስልጣኔን ከካህኑ አባቴ
ከመልከ ጴዲቅ ልጂ ከኢትኤል ማጄቴ

አክሱም ላሊበላ ፋሲል ጄጎል ግንብ
የሶፊመር ዋሻ የሉሲ መስህብ
ከሳባ ነገድ ዘር ከሰለሞን ፍሬ
ጸንሰሺ የወለድሺ እሰከቀረው ዛሬ

የኦሪት የብሉይ የቁርዓን ቤት ማጄት
የእምነት መክበሪያ የአዲስ ኪዳን ግኝት
የዓብርኀ አጸብኀ የእነ ፍሬስ ና'ጦስ
ምስኪን ወላጂ እናት የእነ አብነ ጴጥሮስ

ጥልቅ ምጡቅ ቅኔ ቺቦ ለካሺ አብሪ
ልብ ላይ ተተክለሺ ፍቅር አስተማሪ

ነ ሺ ኢ ት ዮ ጵ ያ ሀ ገ ሬ
ነ ሺ እ ማ ሀ ገ ሬ

አባይን በጪልፋ ማን ጨልፎ ያ'ጠልቃል
ከምናውቀው ይልቅ የማናውቀ ይበልጣል

ነው እንጂ ወርጂ አንሶ ምልክቴ
ግሩም ነው ድንቅ ነው ከፍታሺ እናቴ

ለባዶዎች ባዶ ገለባ ቢመስልም
ወተት እርጎ ቅቤ ነሺ የሚታለብ ላም
ና'ጮች እሚንጧት እምታጠባ እናት
እረግታ ተገፍታ መቀቢያ ገነት

አሬራ ስልባቦት ጣ'ም የለሺ ኮምጣጣ
ፍርስራሺ እራፊ ነብስ እማያወጣ

ቢ በ ዛ ሺ ' እ ድ ፍ

ቢመጧት መጂገሮች ጊንጦች ቢጎትቷት
አልቅቶች ቢጠቧት ቢ'ጠላትም ጠ'ላት
ግፉ በርክቶባት መከራ አበሳ
መልኳ ቢወይብም እናቴ ብትከሳ

ጎጆ እያጠበብን አልጋ እየፈረሰ
ማ'ደሪያ ስናጣ እንፃ እየነገሰ
ቤት ቆሞ ግርግዳ ለተመልካች አጥር
ቢጠማን ቢርበን በያስቼግረን ቺጋር

እኔ ተንጠልጥሎ ቁስ እዬከበደ
ገንዘብ በልጦ አለም ሰው እየወረደ
ሲያቃጥለን ፀሀይ ሲመታን ውሺፍር
መንደር እዬለካን ቢመረንም መኖር

አትፈሪ እማ አይክፋሺ እናቴ
ያንቺ ሀይል ገዝፎ አለና ከፊቴ

እጂ ይዘን እጂ ይዞን ባንፈልግ ማደሪያ
እኛ ብንሼሺም ከሌለው ሰው ጉ'ያ
እረግጠን መሶብሺን እኛው ተራብን እንጂ
መቺ ከለክለሺ አንቺ አጣን ምን ከደጂ

አው እኮ ይሄው ነው አጉል ብኩን ዋጋ
ይዞ ሙሉ ሲሳይ ባዶ እርቃን ፍለጋ

ከፋታዋን አጥተን መልቶ እያጓጓ
አልታይም ቢለን ባይገባን ማዕረጓ
የፊተኞች ቀደምት የከበረች እናት
ነቺ እኮ እሷ እማ በለመዋዕል እንስት

ታዲያ የዚቺ አብራክ ስጋ ከፋይ ልጆች
ንጣት ያነጣቼው ቢሞሉም ቆሻሾች

ሺ'እድፍ ቢበዛ አንድ ሺ'ቢቆሺሺ
እልፍ ልጆች አሏት..
እናቴ የ'ጠሩ የክብርራ ተቋዳሺ

ህመም ስብራቱ እንቅፋት ግርዶሹ
አንቆ ያሊያዛቸው ጥላቻ ብጣሹ
የሚያውቁ ፍቅርሺን ቁስሉን እሚያክሙ
ዛሬም የቆሙልሺ አንቺን ያ'ስቀደሙ

ጸበል መድሃኒቶች አሉሺ እልፍ ጄግና
ለእኛ የበቀሉ የመምጫሺ ጎዳና

ልሳን ቢውተረተር አደበት ቢጠለሺ
ቃላትን ቢ'ያጎድፍ ሀቁን ቢሼሺጉሺ

መስካሪ አካሎች ልብን የተቀኙ
በአለም አደባባይ እግርዎች ተገኙ
አውነቱን ገለጹት ፍሬን አመነጩ
ክብርሺን ዘመሩ በእንባ ተራጩ

እለትዬ ሰበት ጎይቶም ጉዳፍ ስንደቅ
ታምራት ሞስነት ወርቅ ውሀ ንጹህ ስንቅ
ጌትነት ለሜቻ ዳዊት መቅደስ ህብር
የመውጫሺ መሰላል የገጽታሺ ከለር

የገላሺ መስተዋት የመልዕክሺ መለያ
የበዲራሺ ምስል የሰው እነት ማ'ያ
የንጋት ጮራዎች የጨለማ ጠላት
የአንድነት የሰላም አብሳሪ ማንነት

አ ው እ ኮ እ ና ት ዬ
አ ዎ እ ኮ እ ም ዬ

ቀስሌ ጠገገ ምንድ ነው እንዴት ነው
አባቧራሺ ተራግፎ ካባሺ ሊመለስ ነው
ዳ'ነ በአንዴ ህመሜ መራራው ጣፈጠኝ
መአዛሺ ሼተተኝ ደስታ አናወዘኝ

የመሰለኝ ቅዤት የራቀው ተስፈዬ
እውነት ሊሆን ይሆን ንገሪኝ እምዬ
የሰናፍጪ ቅንጣት የምታክል እምነት
እኔ አጣሁ እንጂ ታስነሳ የእለ ሙት

ኑሪ አንች ብቻ እማ አትድከሚ
አይንጠፍ መኀጸንሺ አፍሪ አለምልሚ

አምጠሺ ተጨቀሺ ሺ' ወለጂ ኪ'ሳራ
አጥፍ ይባረካል..
እናቴ እሚወድሺ እኛን እሚያኮራ
እምዬ እሚያከብርሺ ስምሺን እሚያስጠራ
ኢትዮጵያ እሚያነግስሺ ታሪክ እሚሰራ ❗

ተፃፋ በ ጌታነህ በላይነህ
✅ ግጥም፣የድምፅ ቅጂ እንዲሁም Video ለመላክ :- @EBCHAGERBOT


💢 ሰላም ወድ የ EBC ሀገር እና ጥበብ ተከታታዮች 💢
📌 EBC ለ አዲስ አመት ባዘጋጀው የ በአል Video ማዘጋጀት እንዲሁም EDIT አድርገው ቪዲዮውን የምትልኩበት ዘዴ በጣም ቀላል እና ግዜ ቆጣቢ ለማድረግ የ TELEGRAM BOT ሰርቶ አጠናቃል ስለዚህም ከዚን ብሀላ በ BOT ቪዲዮም ሆነ ስነ ግጥም ብትልኩልን ይደርሰናል።
⭕️ ለ Video መስፈርት ..።
✅ ከ 10 - 15 ደቂቃ ያልበለጠ
✅ በ ስልክ ብቻ መቀረፅ አለበት እንዲሁም
✅ በ HD ጥራት እና በ Landscape ይዘት በሆን አለበት...
❌ ማስጠንቀቅያ
💢 ጥላቻን የምሰብኩ ቪዲዮም ሆነ ስን ግጥም መላክ አይቻልም።
🤖 BOT :- @EBCHAGERBOT


Forward from: Negus Media
Ethiopia🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@Negus_Media


ቅኔ ሚስጥር ትርጉም
ዘመን ግብሩን ላይለቅ የሚሆነዉ ላይቀር
ከሰዉነት መጉደል ከጨቋኝ ጋር ማበር
በእንቶ ፈንቶ ፍቅር ባለየ ጥላቻ
እናንተ ሙቱልን እኛ እንብላ ብቻ
በሆነበት ዘመን ነፍስ እየቀጨጨ ስጋ እየገዘፈ
ለጥቅማቸዉ ሲሉ ካስቀመጡን ቦታ እኛ ሳንፈልግ ሽ ዓመት ከነፈ፡፡
በሽ አመቱ መሀል ከቀን ቀን ሳይጎድሉ ሁሌም የሚሰሙ
ወጀብ ማዕበሉ ያላናወጣቼዉ ለወሬ ያልቆሙ
ማይነቃቀፉ ማይረባበሹ የማይገፋፉ
ለየብቻ ቆመዉ በአንድ የተሰለፉ
ግብራቼዉ አንድነት ፍፃሜያቸዉ ፍቅር
ስጋቸው ሰው መሆን ነፍሳቸውም ሀገር
አሏህ አከብር ሲባል በስመአብ ቅዱስ ብሎ
ከሰማይ ሰማያት ለሚኖር አምላኩ ምስጋናን አድሎ
ኑረዋል ለሽ ዓመት…..
የአንደኛው ሲጎድል አንዱ እየሞላለት
በሽ ዓመቱ መሀል….
ጨለማ ላይ ቆሞ መንጋትን አላሚ
ብርሀን የናፈቀው የድል ዜና አሰሚ
ግፍ ያንሰፈሰፈው ለነፍስያው ቋሚ
የአገር ደጅን ጥላ እውነትን ተላሚ
ሲደላው ገበሬ ሲከፋው ወታደር
አማኝ ፅኑ ታጋሽ ታሪክ የሚዘክር
መሞት ሽልማቱ መድማት መቁሰል ጌጡ
ነበልባል ነው ክንዱ በሀገሩ ለመጡ
አፈር ላይ ተኝቶ አይከፋው አይጨንቀው
ድንጋይ ተንተርሶ አይበርደው አይሞቀው
ብቻ አገር አለችው ሰርክ የሚጠብቃት
መጥፋቷን በሞቱ የሚቀይርላት
በሽ ዓመቱ መሀል….
ለቅሶና ዳንኬራ ከአንድ ቤት ተከብሯል
በአባት ሬሳ ላይ ልጅ እየጨፈረ በወኔ ፎክሯል
ለአንድ ሀገር ሳይሆን ሽ ክልል መስርቷል
በኔ እነት አለም ውስጥ እኛነት ተረስቷል፡፡

በሽ ዓመቱ መሀል….
ሀገር ይሏት ነገር በእፍኝ ተጠቅልላ
የሽ ዓመትነቷን ወደኋላ ጥላ
ትላንት ገተገኘው ድንገት ተንጠልጥላ
ታሪክ ገሌ መሌ ባህል ቅብርጥሴ
ቀደምት ስልጣኔ በአክሱም ላሊበላ የታወቀው ቅርሴ
የኔነት አይገልጥም ብላለች በልጇ
ዘመን ላላወቁ ጥበብ ላልገባቸው አዋጅ አሳውጃ….
የዚህ ሁሉ ተንኮል ይሄ ሁሉ በደል
ኢትዮጲያን ለማፍረስ እኛኑ ለማጉደል
ወርቅ እየዘረፉ ቁራሽ ዳቦ ማደል
ታሪኩ ተረት ሆኖ ለፊልም መጋደል….
ሀገር አልባ ተውልድ ለመፍጠር የለፋ
ሀገራችን አለች እኛም አለን እሄው እንሱ ግን ጠፉ…

ቅኔናት ሀገሬ ደረሳ ማትፈታ
ሚስጥር ናት ሀገሬ በሞኞክ ልኬታ ቀድማ ማትረታ
ትርጉም ናት ሀገሬ ውስጧ የከረረ
ደንበሯ ነበልባል በእሳት የታጠረ
ገጣሚ ስንታየሁ ስንሻው ከባህርዳር
ሰኞ እና መስከረም ከተሠኘው መጽሐፌ የተወሰደ
@ebchager1


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
@ebchager1




ይድረስ ለከሐዲው ህወሓት(ጁንታው)

ስምሪት ቢሰጥህ የሀገሬ ዜጋ
ውድመት ጥፋት እንጂ ልም የት አል አንተ ጋ::
ሀያ ሰባት አመት ሆድክን ስታሰፋ
ምስኪን ኢትዮጲያዊን ረግጠህ ስትደፋ
ታግሼክ ነበረ ይቀየራል ብዬ
የአምለክን ምህረት በፊቴ ላይ ስዬ፡፡
አምላክም ይቀጣል ታግሶ ታግሶ
ከገደብ ካለፈ ህግጋት ተጥሶ፡፡
እዳንታገስህ ያንተም ገደብ አልፏል
ዋርካው ላይ ተሳፍረህ ቅርንጫፍ ቆርጠሀል
ጥላው ስር ያረፋ ዋኖች ታዝበዋል
ከዚህ ከበለጠ!! ጽዋው ስለሞላ የባንዲራን ቀለም ፈሶ ያደፈርሳል::
ስለዚህ ከሀዲው አበክረህ ስማ
ኢትዬጲያ ታግሳህ ውስጧ ስለደማ
ከቶ አልመለስም ያንተን መቀበሪያ እምዬ ሳትሰማ፡፡
የጀርባ ቅማል ነህ ለሀገሬ ዜጋ
ሁለት ጣት በቂ ነው ለመድረስ አንተ ጋ፡፡
ሀሳብህን ላፈርስ በእግሮቼ ተጉዤ
አፍንጫህ ስር አለሁ!! ከቅዠት ላነቃህ የአባቴን ስልት ይዤ፡፡
የወንዱ ልጅ ወንድ ያፈራው ታሪክ ያለኝ
የእናቴ ልጅ ኢትዮጲያዊ ኩሩ ልጅ ነኝ
ሀገሬን ነክተሀት!! ሕ--- ብምርህ አይማረኝ
የአጼ ምኒሊክ ታሪክ ይጠይቀኝ
ዮሐንስ, አሉላ, ቴዎድሮስ ይውቀሱኝ
ከነ ግብርአበርህ አፈር ካላስላስኩኝ፡፡


ለመከላከያ ሰራዊታችን ይነበብልኝ
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!!!
ህዳር21/03/2014
ነርስ ጌቱ በየነ
ከሐዋሳ ኮንፕሬንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
Channel
@ebchager1
#የድምፅ_ግጥም_Photo_እንዲሁም_Video_መላክ_ከፈለጉ_በዚ_Bot_ይላኩልን።
@ebchagerbot


መሳይ እንየው
ከሱሉልታ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የግጥሜ ርዕስ ወታደሩ💪
Channel
@ebchager1
#የድምፅ_ግጥም_Photo_እንዲሁም_Video_መላክ_ከፈለጉ_በዚ_Bot_ይላኩልን።
@ebchagerbot


Channel
@ebchager1
#የድምፅ_ግጥም_Photo_እንዲሁም_Video_መላክ_ከፈለጉ_በዚ_Bot_ይላኩልን።
@ebchagerbot


ተነሳ ተራመድ [Tenesa Teramed] - Ethiopian Revolutionary Song


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
Ethiopian Music I ስለ ኢትዮጵያ የተዘፈኑ ምርጥ 10 ሙዚቃዎች


Channel
@ebchager1
#የድምፅ_ግጥም_Photo_እንዲሁም_Video_መላክ_ከፈለጉ_በዚ_Bot_ይላኩልን።
@ebchagerbot


ይድርስ በጣም ለምወድሽ ሁሌም ቢሆን ሰላምሽን እድገትሽንና ብልፅግናሽን ለምመኝልሽ ለኛ ለልጂወችሽ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር እናት ኩራትና ተምሳሌት ለሆሽው ውዷ እናቴ አንችኮ ለኛ ለልጂወችሽ ያላርግሽልን ነገር የለም አንች ለኛ ለልጂወችሽ አገታችንን ቀና አርገን በመላው አለም እድንናገር አድርገው ነው የቀድሞ ልጆችሽ ያስረከቡን እማ አሁን ግን ካብራክሽ የወጡ የተበከላ አስተሳሰብ ያላቸው እኔ ከሞኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉት ብሂል የእንስሳ አስተሳሰብ ይዘው በለለሽ አቅም ታናናሽ ልጂወችሽን ፆም አሳድርሽ በዶላር እየከፈልሽ ነገ ያሳልፉልኛል ብለሽ ያስተማርሻቸው ስግብግቦች ክብርሽን ገናናው ስምሽን አይበገሬነትሽንና ተምሳሌትነትሽን ለማበላሸት ቀን ከሌት ከታሪካዊ ጠላቶችሽጋ በመዶለት የሞት ሽረታቸውን እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ ኢትዮጲያየ ነገር ግን አንች የወዳጆችሽ ሀይልና ጉልበት ከጣላቶችሽ በላይ በመሆኑ ምንግዜም ተከብረሽ ታፍረሽ ይበልጥ ታምሳሌትነትሽ ጎልቶ የሚወጣበት ቀን አንድ ጀንበር ነው የቀርው እናቴ እውነት እውነት እልሻለሁ ነገ ባድራሽ በጥላቶችሽ መቃብርላይ ሲተከል ያኔ ቀለሙ ይበልጥ ይደምቃል ጠላቶችሽ ይበልጥ ያከብሩሻል እሱን እውን ለማድርግ እኛ ልጆችሽ ለጠላቶችሽ እሾህ ሁነን ሰላማቸውን አድነታቸውን በጣጥሰን የመከራ ልብስ አልብሰን ታሪካችንን እናሳምርባቸዋለን
@ebchager
@ebchager


👮‍♀#ወቶ_አደር👮‍♂
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@leoyri
@gGetem
@gGetem
💚💛❤️
📒 #በዛን_ምሽት እንደተፃፈው
⛱high_quality
🇪🇹ማስታወሻነቱ ለመከላከያው🇪🇹🇪🇹
✍24/02/2014ዓ.ም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
...ሁሌም ሲታወሰን ይኖራል....😥
@ebchager1
@ebchager1
#የድምፅ .Photo እንዲሁም Video መላክ ከፈለጉ በዚ Bot ይላኩልን።
@ebchagerbot


ኢትዬጵያ የኛ መከታ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@ymigermegn
@tame134
@ebchager1
#የድምፅ .Photo እንዲሁም Video መላክ ከፈለጉ በዚ Bot ይላኩልን።
@ebchagerbot


እንካ ሰላምቲያ

ሀ: እንካ ሰላምቲያ፤

ለ: በምን ልምቲያ?

ሀ: በማይካድራ

ለ: ምን አለ በማይካድራ?

ሀ: ምን ቢበድሉ ነው ሽፍጣው መከላኪያ አንገት
ላይ ያኖረው ካራ።

ሐ: እንካ ሰላምቲያ፤

መ: በምን ልምቲያ?

ሐ: በሀገሬ ሕዝብ

መ: ምን አለ በሀገሬ ሕዝብ?

ሐ: የሕዎሃትን ሴራ አይረሰውም የታሪካችን
መዝገብ።

፩: እንካ ሰላምቲያ፤

፪: በምን ልምቲያ?

፩: በአሜሪካ

፪: ምን አለ በአሜሪካ?

፩: ውርደት ይከናነባል ሀገሬን የነካ።

፫: እንካ ሰላምቲያ

፬: በምን ልምቲያ?

፫: በሕልውና

፬: ምን አለ በሕልውና?

፫: በሕልውናችን የመጣ ብዙ ያያል ገና።

፣ እንካ ሰላምቲያ

፤ በምን ልምቲያ?

፣ በመከላኪያ

፤ ምን አለ በመከላኪያ?

፣ ቆራጥ ጀግኖች አሏት ለሀገሬ ኢትዮጵያ።

©ተስፋዬ ጌንሰ( ጎንደር ዩንቨርሲቲ ፍሬሽ ማን
ተማሪ)
@ebchager1


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
@ebchager1
#የድምፅ .Photo እንዲሁም Video መላክ ከፈለጉ በዚ Bot ይላኩልን።
@ebchagerbot


💚💛❤️ ሀገሬ 💚💛❤️
✍️✍️✍️
ሀገርህ ምንህ ናት? ብለህ ስትጠይቀኝ
ቤቴ ናት ያልኩህን ተወው ትቼዋለሁ

ቤት አፍርሰኽብኝ ቤት አልባ አድርገኸኝ እንከራተታለሁ

ሀገርህ ምንህ ናት? ብለህ ስትጠይቀኝ
ሀብቴ ናት ያልኩህን ተወው አታስታውሰው

ሳይጨልም ዘርፈኸኝ በህግ አምላክ እያልኩ
ፍትህ አጥቻለው

ሀገርህ ምንህ ናት? ብለህ ስትጠይቀኝ
እናቴም ሚስቴም ናት ያልኩህን መልስ ግን
ከልብህ ላይ ጻፈው

ልድፈር ያልክ ለታ ገድዬህ እሞታለው።

💚💛❤️አበቃው 💚💛❤️

ተመስገን አለሙ (ዘቂርቆስ)
@ebchager1
@ebchager1
@ebchager1


የግጥሜ ርዕስ "እናቴን ምጥ ያዛት"
ፋንትሽ አበባው
ከአዲስ አበባ 0912806472/0983132000
#Share
@ebchager1

20 last posts shown.

813

subscribers
Channel statistics