በመዲናችን በቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ ቀን፣ በተለያየ ቦታና ሰዓት በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
ከትናንት በስትያ ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሰባት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በተመሳሳይ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቡልቡላ መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም በዚያኑ ቀን 11፡00 ሠዓት ገደማ በደረሰ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ነው የተነገረው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንዳሉት
ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ኋላ ከሚመጣው መፀፀት እንደማያድን በመገንዘብ በጥንቃቄ ማሽከርከር ይገባል ብለዋል።
ፖሊስ የአደጋዎቹን መንስኤ በማጣራት ላይ መሆኑን ተናግሯል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew