ebstv worldwide📡️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Welcome to EBS TV WORLDWIDE Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates. Don’t forget to share it with your friends.
@ebstvworldwidebot
@EbswhatsnewBot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter




🇪🇹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 🇪🇷ከኤርትራ ጋር ጥቅምት 21 እና 24 ለሚያከናውናቸው የቻን በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ  ተጫዋቾች  ብቻ ሚሳተፉበት የማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጥሪው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ባማከለ መልኩ የተከናወነ በመሆኑ ሊጉ የማይቋረጥ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ዛሬ ጥቅምት 14 ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

ትላንት ፌደሬሽኑ የገበረመድህን ሀይሌን ምክትል የነበረውን መሳይ ተፈሪን በጊዚያዊ አሰልጠኝነት ማስቀጠሉ ይታወቃል

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews








🔸ከክፍለ ሀገር ወደ አዲስ አበባ ለመጡ ዜጎች የነዋሪነት ምዝገባ ከህዳር 1 ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር የከተማዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታወቀ።

🔸ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ነዋሪነት ለማግኘት ማመልከቻ አስገብተው የነበሩ አመልካቶች ከነገ ጥቅምት 14 እስከ ጥቅምት 22 ባሉት ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን ባከናወኑበት የኤጀንሲው ወረዳ ጽ/ቤቶች በድጋሚ ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ የተጠየቀ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ለአመልካቶች የዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ እንደሚካሄድ ኤጀንሲው ጨምሮ አስታውቋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew








የጥቅምት 12/2017 አበይት የአለም ዜናዎች

🇷🇺 የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ በሩሲያዋ ካዛን ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።

🇺🇸🇮🇱 የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዓመት በላይ በጦርነት ውስጥ የሚገኙትን እስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደርሱ ለማስቻል ያለመ ጉብኝታቸውን ዛሬ በእስራኤል መዲና ቴላቪቭ ጀምረዋል።

🇮🇳🇨🇳 ህንድ እና ቻይና የሚወዛገቡበትን የድንበር ግጭት በንግግር ለመፍታት ተስማሙ።

🇿🇦 የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ የብሪክስ ጥምረት አባል አገራት መዋዕለ ንዋያቸውን በአፍሪካ አገራት ኢንዱስትሪን ለማስፋፋት እንዲያውሉት ጥሪ አቀረቡ።

🇷🇺 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የብሪክስ ጥምረት የትኛውንም አካል ለመጉዳት ያለመ አለመሆኑን ተናገሩ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews




46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ከተለያዩ አገራት የመጡ ከ400 በላይ እንግዶች የተሳተፉበት ጉባዔው የካፍ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፓትሪስ ሞትሴፔ ጨምሮ የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የስብሰባው ተካፋይ ናቸው።

በመካሄድ ላይ በሚገኘው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አባል አገራቱ በአፍሪካ እግር ኳስ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ምክክር እንደሚያደርጉ ሲጠበቅ የአፍሪካን እግር ኳስ ሊያሳድጉ የሚችሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት ይሆናል።

በመዲናችን በመካሄድ ላይ ባለው 46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የኮንፌዴሬሽኑ አባል የሆኑ 54 አገራት እንደሚሳተፉ ሲገለፅ ጉባዔውም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews






የጥቅምት 11/2017 አበይት የዓለም ዜናዎች

🇺🇸🇮🇱🇮🇷 የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ማይክ ጆንሰን እስራኤል ኢራንን ለመምታት ያዘጋጀችውን ዕቅድ ያሳያል የተባለ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨ ያፈተለከ መረጃ ጉዳይ አሜሪካ መመርመር መጀመሯን ተናገሩ።

🇸🇸 በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ1 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለጉዳት መዳረጉ ተነገረ።

🇰🇷🇺🇦🇷🇺 ደቡብ ኮሪያ ሩሲያን ወግነው በዩክሬን ጦርነት ለመሳተፍ በሩሲያ ሥልጠናዎችን በመውሰድ ላይ የሚገኙ 1 ሺህ 5 መቶ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በአስቸኳይ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ለሞስኮ ጥያቄ አቀረበች።

🇺🇸 የአሜሪካ የዘንድሮ 2024 በጀት ጉድለት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ8 በመቶ ጨምሮ ከ1.8 ትሪሊዮን ዶላር በላይ መሆኑ ተሰማ።

🇰🇵 ሰሜን ኮሪያ በሀገሯ ላይ ህገወጥ ማዕቀብ የሚጥሉ ሀገራት ዋጋ ይከፍላሉ ስትል አስጠነቀቀች።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew


⚽️ ከ46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፊዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ መካሄድ በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋቾች ከካፍ አመራሮች እንዲሁም የአፍሪካ እግር ኳስ ዕውቅ ተጫዋቾች ጋር በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ እስታዲየም ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።

⚽️ በዚህ የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ የሚሳተፉ ሲሆን ከአፍሪካ የቀድሞ ኮከቦች መካከል ሳሙኤል ኤቶ፣ ጄጄ ኦኮቻ፣ አልሃጂ ዲዩፍ፣ ካሉሻ ቡዋሊያ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ታውቋል።

⚽️ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋቾች መካከል ደግሞ ሰላዲን ሰይድ፣ አዳነ ግርማ፣ ምንያህል ተሾመ እና ፍቅሩ ተፈራ በስብስቡ ተካተው ጨዋታቸውን ያከናውናሉ ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በከተማዋ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ዕለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከነገ ማክሰኞ 12/2/2017 ዓም ጀምሮ በቢሮው የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በየዕለቱ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ መሆኑን የገለፀው ቢሮው በአገልግሎት ሂደቱ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋዮችን እንግልት ለመቀነስ ያስችል ዘንድ ነዳጅ ማደያዎቹ የት ቦታ እንደሚገኙ ጨምሮ በዕለቱ የተራገፈው የነዳጅ መጠንን ጥቆማ ለሕዝቡ ማጋራት እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew





20 last posts shown.