Ethiopian Electric Utility


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Career


EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Career
Statistics
Posts filter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በኦ.ቢ.ኤን ይጠብቁን

ውድ ደንበኞቻችን ከ ነገ ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 3፡20-3፡40 በየሁለት ሳምንቱ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ /ኦ.ቢ.ኤን/ ቴሌቪዥን በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሚተላለፈውን ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

Kabajamtoota maamiltoota keenya guyyaa boruu kamisa Gurraandhala 25/2017 A.L.I. galgala 3፡20 hanga 3፡40-tti Oromiyaa Biroodkaastiing Neetwork(OBN) irratti walitti aansuun turban lama gidduutti altokko Sagantaan Afaan Oromoo kan tamsa’u ta’uu isiniif ibsaa saganticha akka hordoftan kabajaan isin affeerra.

TAJAAJILA ELEKTIRIKII ITIYOOPHIYAA


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከፍተኛ አመራሮች የመስክ ምልከታ አካሄዱ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከፍተኛ አመራሮች ኮተቤ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የልህቀት ማዕከል፣ የስካዳ ሲስተም፣ የብሄራዊ ሃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

በግንባታ ላይ የሚገኘውን የዲስትረቡሽን መቆጣጠሪያ ማዕከል (ስካዳ ሲስተም) ወቅቱን የጠበቀ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ እና አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ በመስክ ምልከታው ተጠቁሟል፡፡

የልህቀት ማዕከሉ ሁለገብ የሰው ኃይል ማሰልጠኛ፣ የምርምርና የልህቀት ማበልፀጊያ፣ ብሄራዊ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ስካዳ መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ አዳራሽ፣ የሰልጣኞችና እንግዶች ማረፊያ ቤቶች እና ክሊኒክን የያዘ ነው፡፡

በተጨማሪም የልህቀት ማዕከሉ የዲስትሪቡዩሽን ዕቃዎች ጥራት ፍተሻ እና ላብራቶሪ ፋሲሊቲዎችን የሚያሟላ ሲሆን አጠቃላይ ሲቪል ግንባታ ስራዎች ዘጠኝ የተለያዩ ስፋትና ከፍታ ያላቸው ህንፃዎች እንዲሁም ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ያካተተ ነው፡፡

በመስክ ምልከታው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እና የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ሪጅኑ 6 የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አደረገ

የሶማሌ ሪጅን በበጀት ዓመቱ 8 ወራት 6 የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን የሪጅኑ አገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረሚካኤል ገብሬ ገለፁ፡፡

ሃላፊው አክለውም ሪጅኑ ባለፉት በ8 ወራት በክልሉ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙት ወልጀኖ፣ ገላዲድ፣ አቡኩደን፣ ኦባታሌ፣ ኦማር እና በቆልማዮ የተሰኙ 6 የገጠር ቀበሌዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ቀበሌዎቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግም 110 ኪ.ሜ መካከለኛና 86 ኪ.ሜ ዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ፤1190 መካከለኛ እና 1903 ዝቅተኛ መስመር ኮንክሪት ምሰሶ ተከላ እንዲሁም 20 ትራንስፎርመር ተከላ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

ሪጀርኑ በቀጣይ አራት የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊ ግብዓት እንዲቀርብ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ተጠቃሚ ከሚሆኑት መካከል የነጎብ ዞን ከተማ የሆነው የኤለወይን እና የያሁፕ ወረዳ ይገኙበታል ብለዋል።

አያይዘውም ሪጅኑ የፀኃይ ኃይል ማመንጫዎችን በስፋት እየገነባ መሆኑን ጠቅሰው የበቆሎማዩ የገጠር ቀበሌን የፀኃይ ኃይል ማመንጫ በመገንባት ተጠቃሚ ተደርጓል፡፡

ለበቆልማዮ 23 ኪ.ሜ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 5 ትራንስፎርመሮች ተከላ መከናወኑን የገለፁት የ10 ቀበሌዎች የፀሀይ ኃይል ማመንጫዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ኃላፊው የሶማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በእቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦ http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1323?lang=am


ቋሚ ኮሚቴው የደሴን ሪጅን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኘ

በተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የደሴን ሪጅን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት የሪጅኑ አመራርና ሠራተኞች ህዝቡን ለማገልገል ከአሰተዳደር አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርቦላቸዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ከጉብኝቱ ባሻገር ከሪጅኑ አመራርና ሠራተኞች ጋር መምከራቸውን የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ኃብቱ አበበ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የሪጅኑ ሠራተኞች ለሕዝብ ውጤታማ አገልግሎት እንዳይሠጡ ለደሴ ከተማ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ባለ66 ኪቮአ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ መሙላት እየፈተናቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሠራተኞቹ ቃል ተገብቶ የነበረው በምዕራብ ወሎ አቃስታ ላይ ሊገነቡ የነበሩት ሦስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች አለመጀመራቸው በሠራተኞች እንደጥያቄ ለቋሚ ኮሚቴው ቀርቧል ሲሉ አቶ ኃብቱ አስታውቀዋል፡፡

በውይይቱ የቂጣ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ በወቅቱ አለመጠናቀቁ ያልተቆራረጠና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት አዳጋች እንዳደረገባቸው ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ መግለጻቸውን ዳይሬክትሩ ገልፀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ለመግንባትና ለማጠናቀቅ እንደሚሠሩ ቃል መግባታቸውን ከዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ሪጅኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያድርገው የተሳለጠ ግንኙነት እና የደንበኞን ቅሬታ ፈጥኖ ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታና የሚመሰገን በመሆኑ በዚሁ መቀጠል እንዳለበት የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


የአዲስ አበባ ትራንስሚሽንና ዲስትሪቢዩሽን ስካዳ ሲስተም ፕሮጀክት አፈፃፀም 71.35 አፈፃፀም ደረሰ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በከተሞች ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ ለማድረግ ስካዳ ሲስተም በመጠቀም የተቋሙን ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በማዘመን ላይ ይገኛል፡፡

የስካዳ ሲስተሙ መካለኛ መስመር ላይ ያለን የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስና ከተቋረጠም በፍጥነት ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን ከአንድ ቦታ ሆኖ ለመቆጣጠር የሚረዱ መሳሪያዎችን ለመጠቀም ያለመ ፕሮጀክት ሲሆን ኦፕሬተሮች በብቃት እና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲያስተዳድሩ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

ሲስተሙ በአዲስ አበባ እና አካበቢው እየተተገበረ ሲሆን በቀጣይ በመላ ሀገሪቱ ለመተግበር እየተሰራ ይገኛል፡፡

ሲስተሙን ለመተግባር ከተለየዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ከ60 በላይ በለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ስራ መግባታቸው ተጠቁሟል፡፡

የስካዳ ሲስተም ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጀት በመከናወን ላይ ሲሆን የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 14.5 ዶላር ነው::

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውንቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1320?lang=am


ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል

የነጌሌ ቦረና ከፍተኛ የኃይል አስተላለፊያ መስመር 66kv  በብልሽት ምክንያት በቀን 21/07/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ በመቋረጡ ምክንያት ነገሌ ቦረና ከተማ፣ፋልቱ፣ቢድሬ፣ዋድራ እና ሀረቀሎ  አካባቢዎቻቸው ተቋርጦ የነበረው  የኃይል አቅርቦት ዛሬ በቀን 22/07/2017 ከረፋዱ 5:05 ላይ ተገናኝቷል።

የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት ለጠበቃችሁን ክቡራን ደንበኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ለሐረር ከተማ የመጠጥ ውሃ የመስመር ዝርጋታ እየተከናወነ ነው

ለሐረር ከተማ የመጠጥ ውኃ አገልግሎት የሚሰጥ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ እየተከናወነ ነው፡፡

ከተማው የመጠጥ ውኃ አገልግሎት ሲያገኝ የነበረው ከደንገጎ ሰብስቴሽን እና ረጅም ርቀት ይሄድ ከነበረ መስመር ያገኝ ስለነበር ለኃይል መቆራረጥ መንስዔ ሲሆን ቆይቷል፡፡

ከሐረር ክልል ፕሬዝዳንት በተደረገ ውይይት ለፕሮጄክቱ አስፈላጊ የሆነውን ምሰሶ ማቅረብ እንዲቻል በመግባባት በአሁኑ ወቅት የምሰሶ ተከላ ስራው የተጀመረ ሲሆን 225 ኮንክሪት ምሰሶ ተከላ እና 13 ኪ.ሜ ዝርጋታ በማከናወን በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

አሰሊሶ ከሚገኘው ጉድጓድ የሚመረተው መጠጥ ውኃ ደንገጎና አሰሊሶ ባሉ ሁለት ፓምፒንግ ስቴሽኖች አማካኝነት ወደ ከተማዋ የሚሰራጭ ይሆናል፡፡

ሪጅኑ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን በልዩ ጥንቃቄ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታው ሲጠናቀቅ የከተማዋን ውኃ ለማዳረስ ከማስቻሉም ባሻገር አስተማማኝ የሆነ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል ተብሏል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በሐረር ከተማ የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎችለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1318?lang=am


አዲስ ሃይል ፈላጊ ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

ውድ ደንበኛችን አዲስ ቆጣሪ ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ ከዚህ በታች የተገለፁትን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያሟሉ እንጠይቃለን፡፡

የነጠላ ፌዝ ቆጣሪ /Single Phase Meter/ ለማግኘት፡-

• የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፣
• አንድ ጉርድ ፎቶ /3 በ 4 የሆነ/፣
• የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ፣
• ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
• ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ፤

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ያንብቡ: -
http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/contents/getting-electricity?lang=am


በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል  አቅርቦት  

የነጌሌ ቦረና ከፍተኛ የኃይል አስተላለፊያ መስመር 66kv በብልሽት ምክንያት በቀን 21/07/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ ተቋርጧል ፡፡ በዚሁ ምክንያት ነገሌ ቦረና ከተማ፣ፋልቱ፣ቢድሬ፣ዋድራ እና ሀረቀሎ አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦቱ ተቋረጧል።

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን መስመሩ ተጠግኖ ወደ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን እናሳስባለን።


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን እንኳ ለ1446ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!

ኢንጅነር ጌቱ ገረመው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ

7.1k 0 17 56 55

ለቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኢድ-አልፈጥር በዓልን አስምልቶ ለቅድመ-ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በበዓሉ ዕለት በተመረጡ ማዕከላት ካርድ መሙላት እንዲችሉ ሁኔታዎችን ያመቻቸ መሆኑን እየገለፅን የቅድመ-ክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን ዝርዝር ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ: http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/contents/prepaid?lang=am


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን እንኳ ለ1446ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!


በአዲስ አበባ ከተማ የመልሶግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1316?lang=am


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ለመጪው የኢድ አል-ፈጥር በዓል የተደረገ የቅድመ-ዝግጅት ስራ በሐረረ እና በሶማሌ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት !!


በፓወር ትራንስፎርምር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የሃይል አቅርቦቱ በፈረቃ እየተሰጠ ነው

በአዲስ ዌስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፓወር ትራንስፎርምር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት፣ ደጉ ሆቴል፣ ታይዋን ገበያ ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ፣ ፈፊሊጶስ ቤ/ክ አካባቢ፣ እስላም መቃብር ፣ ሎሚ ሜዳ ፣ ጠሮ መስጊድ፣ አማኑኤል ቤ/ክ፣ አማኑኤል ሆስፒታል፣ ሻወል ደማ ት/ቤት፣ ብርጭቆ፣ አስኮ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ እህል በረንዳ ፣ አውቶብስ ተራ፣ አዲስ ከተማ ት/ቤት፣ ገነሜ ት/ቤት፣ አማኔኤል ቤ/ክ ፊትለፊት፣ ሰብስቴሽን አካባቢ፣ ማሳለሚያ ፣ እሳት አደጋ፣ ሳንባ ነቀርሳ ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ታይዋን፣ ሆላንድ ኤምባሲ፣ ቀራንዮ መድሃኒዓለም ቤ/ክ ፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል እሳት አደጋ፣ ወይብላ ማርያም፣ አውጉስታ፣ አንፎ፣ ወይራ ሰፈር፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕ የነበረው፣ ተዘንአ፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢያቸው የሃይል አቅርቦቱ በ8:00 ልዩነት ጊዚያዊነት በፈረቃ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን በኃይል ማከፋፈያ ፓወርትራንሰፎርመሩ ላይ የተፈጠረው ብልሽት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

7.1k 0 59 26 20

ለመጪው የኢድ አል-ፈጥር በዓል የተደረገ ቅድመ-ዝግጅት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመጪው የኢድ አል-ፈጥር በዓል ሊኖር የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ተቋማችን በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ የኃይል መቆራረጥናመዋዥቅ ችግር ሳይፈጠር ለተጠቃሚው ለማቅረብ ከተከሰተም በአፋጣኝ የአስቸኳይ ጥገና ሥራ ለመሥራት በየደረጃው ግብረ-ሃይል በማዋቀር ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ግብረ-ሃይሉም በተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግር የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በመለየት በመካከለኛና በዝቅተኛ መስመሮች ላይ ጭነት የማመጣጠንና ሌሎች የቅድመ-ጥገና ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሆኖም መሰል ዝግጅቶች ቢደረጉም የሃይል መቆራረጥ ችግር በከፊልም ቢሆን ሊያጋጥም ስለሚችል የኃይል ጭነት በማይበዛባቸው ሰዓታት በተለይ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ባሉት ጊዚያት መጠቀምን እንመክራለን፡፡

የቅድመ-ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቻችንም በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ እንግልት ለማስቀረት ከወዲሁ የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድማችሁ እንድትሞሉ /ካርድ እንድትሞሉ/ እየጠየቅን፤ በዋዜማውና በዕለቱ ካርድ ማስሞላት የምትፈልጉ ደንበኞችም በተመረጡ ማዕከላት ይህንን አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ውድ ደንበኞቻችን በቤት ውስጥ የምትገለገሉባቸው የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆን ይገባቸዋል፡፡

በመጨረሻም ድንገት የኤሌክትሪክ አደጋ ቢያጋጥም፣ ተቋሙን የሚመለከቱ ሌሎች መረጃዎች ለመጠየቅ እንዲሁም ጥቆማዎችና አስተያይቶች በአቅራቢያ ለሚገኙ ማዕከል በአካል ማቅረብ ወይም በ905ና 904 ነፃ የጥሪ ማዕከል ስልክ በመደወል ማሳወቅ እንደሚቻል እንገልፃለን፡፡

19 last posts shown.