ማዕደ ሰማይ/ Heavenly Meat


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


#በፀጋ ነው
#ፀጋው ብቻ
#የታደገን ከዓለም ጡጫ።
#በፀጋ የዳነ
#ያለፀጋ አይፅፍም
#ያዳነው እያለ
#የዳነው አይነግስም፤
#ባለፀጋው #ባይኖር
#እኔም ችዬ አልኖርም።
እንዳለው እንድኖር
ጸጋ አለ የሚያኖር።
ለአስተያየቶ በዚህ 👇 ይላኩልኝ።
@Surtsega
@Surafeltsegamets
@heavenlymeatministry

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


#አቤት_ጌታችን 🎸

እግዚአብሔር አሰበን
እኔና ቤቴም ደስ አለን

አደረገልን ድንቅና ታምር
የቀመሰ ያውቃል ይመስክር

ቸረን የሆድን ፍሬ
ይብዛለት ከእኛ ዝማሬ

የምስጋናው ባለዕዳ አ`ድርጎናል
ያልጠበቅነው አድርጎልናል።

በክብር የሞሸረን ሲደግመን እንደምህረቱ
ነፍሳችን ፈነደቀች ዘለለች በደግነቱ

ተመስገን ከማለት በቀር
ቢጠፋን አንድ የምንለው ቃል
እንላለን እግዚአብሔር
አሰራር፤
ማስዋብን፤
ማስጌጥን፥ ብቻውን ያውቃል።

ጌታና መድኅኒታችን ይመስገን ይብዛለት ክብር
በሰማይ ከመላዕክቱ ሲቀበል፤ ከቤቴም አይቅርበት በምድር

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets


#የዳዊት_ልጅ
(ሉቃ 18÷39) (2ሳሙ 7÷ 1_29)

1. አብ የሰጠን ተስፋ
(የተነገረለት፣ የምንጠብቀው)
(ያልተዛነፈው ትንቢት መቋጫ)
(በዘመን መገባደጃ የአብ መናገሪያ)

2. ህመምን የሚያውቅ
(እህ ብሎ የሚያደምጥ)
(ዝም በሉ ለሚባሉ ጯሂዎች የሚቆም)

3. መማርን የሚያውቅ
(ምህረት ለሮጠ አይደለም።)
(ምህረቱም ከህይወት ይሻላልና።)
(እርሱ ከዘላለምም መለኮት ነው።)

የተባረኩበት ቃል ነውና ተባረኩበት።

(የዳዊት ልጅ የናዝሪቱ ኢየሱስ በክብር በደመና ይመጣል።)

ለእኔ ቀኑ ጨልሞ መስማት እንጂ ማየት አልችል
ጥዋት ልለምን የወጣሁ መሽቶ በሰው ነው ምገባው
ትንሽ ትልቅ መሪዬ
የሰው ፍቃድ ማደሪያዬ
የእድሜዬን ግማሽ ቆጠርኩ
ጨለማውን ለመድኩ

#መጣ_ኢየሱስ
ይሄ የአለም ብርሃን
ዓይኖቼን ከፈተ በእውርነቴ ሃገር
ታሪኬ ተለወጠ (2x)

#የዳዊት_ልጅ ማረኝ ብዬ ተከፈተ ብርሃኔ
መልካምነቱን አየሁት በዚህች በአጭሯ ዘመኔ

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega @elgraceministry


የተወደድክ ዘማሪ በረከት ተስፋዬ ጌታ በቤተክርስቲያችን ጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን የተጠቀምከውን ስላጋራኸን እናመሰግናለን።

እርግጥ ጸጋ ቃለህይወት ቤተ ክርሰቲያን ማንን አፈራች፤ የማንንስ ጸጋ አቀጣጠለች፤ ለማንስ ክህነት ቅዱስ ስፍራ ሆነች?

እርግጥ ነው ብዙዎችን ያስጠለለች የታላላቅ ፍሬዎች መጠለያ ናት።

ለብዙዎች የተረፈች፤ የተቸገሩትን የረዳች፣ የታረዙትን ያለበሰች፣ ደካሞችንም የደገፈች፣ የታሰሩትን የጠየቀች፣ ያዘኑትን ያጽናናች፣ መበለቶችን የጠየቀችና ወላጅ አልባ ልጆችን ያሰበች የሰማይ መንግስት የምድር ወካይ/አምባሳደር ነች።

ጌድዮን እውነቱ፤ ዳንኤል እውነቱ፣ ክርስቲያን ግርማ በ90's የደመቁ የመዝሙር አቀናባሪዎችና ሙዚቀኞችን ያፈራች ቤተክርስቲያን ናት።

''አማኑኤል አማኑኤል
ከእኛ ጋራ ያለው
ስሙ ድንቅ መካር
ኤልሻዳይ የሆነው
ኢየሱስ ነው''

የሚለውን ዝማሬን ያበረከቱልንን ''ለ'' መዘምራንን

እና

''በእኛ ላይ ታላቅ ምህረትህ ጥበቃህ ስለበዛ
ጌታ ሆይ ልንልህ ቻልን ልንጠራህ በምስጋና
ዛሬም እንደገና''

የሚለውን ዝማሬ ያበረከቱልንን ''ሀ'' መዘምራን ህብረትን ያበረከተችልን ቤተክርስቲያን ናት።

ለመቁጠር የሚያዳጎቱ የቤተክርስቲያን አባቶችና እናቶች ያሏት ቤተክርስቲያኒቷ በጉብዝናቸው ወራት የቤተክርስቲያን ተከላ በአራቱም አቅጣጫ የሮጡና የተሰካላቸውን አባቶችንና እናቶችን አፍርታለች።

ተስፋዬ ጫላ ፣ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል፣ በረከት ተስፋዬ፣ ለምለም ንጋቱ ፣ ርኆቦት አለማየሁ እና የመሳሰሉ አንጋፋ ዘማሪዎችን ላፈለቀው አቤኔዘር (ጂሲኤ) የተማሪዎች ህብረት አዳራሽዋን ዛሬም ድረስ ከፍታ ታስተናግዳለች።

ቤተክርስቲያናችን እንደቃሉ ያሉ ልምምዶችንና ትምህርቶችን አንጥራና መዝና የምታስተምር አጥቢያ ስትሆን ከአቤኔዘር የተማሪዎች ህብረት ጋራ ቤተክርስቲያናችን ወንጌልን ዛሬም በትጋት የምታገለግልና የወንጌል ታላቅ ተልዕኮነቱን ሳትዘነጋ ለመዘርጋት የምትጥርና የምትታትር የጥንት ቤተክርስቲያን ናት።

በነገራችን ላይ GCA ከሚለው ውስጥ G stand for Grace (ጸጋ) መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናውቅ ይሆን? የት/ት ቤቱ አመሰራረት ከቤተክርስቲያኗ ጋራ መቆራኘቱስ?

ለወንጌል ተልዕኮ ከውጪው ዓለም ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጡት ሚሽነሪዎች ት/ቤቱ መስርተው ተልዕኳቸውን ሲወጡ ሳሉ፥ በተፈጠረው የመንግስት ለውጥ ከሀገር ሲወጡ፥ መሬቱን ለቤተክርስቲያኒቷ ቢሰጡም በሰዓቱ የነበረው አብዮታዊ መንግስት ስሙን ከመቀየረ የጀመረ ንጥቂያ አድርጎ ቤተክርስቲያኒቷ እንድትዘጋ አድርጎ ነበረ።

ነገር ግን ሳትዘጋ በሌላ ስፍራዎች የቀጠለችና እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በብዙ ውጣውረዶች ያለፈችና የተነጠኩትን መሬት መልሱልኝ ስትል ጆሮ ዳባ የተባለች ብትሆንም፤ ለሁሉም ዕምነት ተቋም መሬት በተሰጠ ጊዜ  የመሬት ልማት የሰጣትን ስፍራ አሁንም በአንድ ስፍራውን በያዘ #ግለሰብ ምክንያት ቤተክርስቲያኒቷ ዛሬም መብቷን እየተገፈፈች ትገኛለች።
ቅዱሳን ፍትህ ለጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስትያን እንድትጠይቁልን እና አጥብቃችሁም እንድትጸልዩ አደራ እንላለን።

ጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን (የብዙዎች እናት ቤተክርስቲያን) አሻራዋ ያለባችሁ ሁሉ በጸጋችሁ መጥታችሁ አብረን እንድናገለግል ቤተክርስቲያኒቷ ጥሪዋን ታሰማለች።

ቤተክርስቲያኒቷም ዛሬም ከወትሮ ጠንክራና አብልጣ አምልኮን የጨመረች ሲሆን የአምልኮ ኘሮግራሞቿም
ሰኞ ማለዳ ፦  የእናቶችና እህቶች ኘሮግራም
ማክሰኞ ማለዳ ፦ የጾም ጸሎት ኘሮግራም
ሐሙስ አመሻሽ ፦ የቃል እና የትምህርት ጊዜ
ቅዳሜ አመሻሽ ላይ ፦ የወጣቶች ኘሮግራም
እሁድ ማለዳ ፦ የዘወትር የሰንበት ኘሮግራም

ኑ በጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን በሚመቻችሁ የአምልኮ ኘሮግራም ተሰባስበን ከቃሉ ማዕድ እንቋደስ።

በጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን (ጸጋ) የተጠቀመ ሌላ ምስክርነት ካለ አጋሩን🙏

አድራሻችን ከጂሲኤ ት/ት ቤት አልያም ከጎተራ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጀርባ

@surafelgrace




"የወንጌልን እውነት ያልተረዱ ሰዎች በድፍረት “መስቀል ቤዛነ” እንዲሁም "መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ" ይላሉ!!" ዲያቆን ኤርሚያስ ኪሮስ

(AmlekoTube - አምልኮቲዩብ እንዳጋራው)

መስቀል ትልቅ ኃጢአት የሰሩና የተረገሙ ሰዎች መቀጫ ነው። ጌታ ኢየሱስ ኃጢአታችንና መርገማችንን ተሸክሞ በመስቀል ላይ ተቀጣ። መስቀሉ እኛና ኢየሱስን የተቀያየርንበት ቦታ ነው። የኛን ኃጢአት ወስዶ ጽድቁን፤ ፍርዳችንን ወስዶ ምህረትን፤ መርገማችንን ወስዶ በረከትን፤ ሞታችንን ወስዶ ህይወቱን ሰጠን። ውርደታችንን ተቀብሎ ሰማያዊውን ክብር አጎናጸፈን። "በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤" ገላ - 3፥13 መስቀል ይህ ድንቅ ነገር የተፈጸመበት ቦታ ነው። ስለዚህ መስቀሉ ይሄን ታላቅ እውነት ድንቅ ፍቅር የምናስታውስበት ምልክት (Symbol) ነው።

ከዚህ ውጪ መስቀሉ ምንም አይነት ሚና የለውም። የወንጌልን እውነት ያልተረዱ ሰዎች በድፍረት “መስቀል ቤዛነ” እንዲሁም "መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ" ይላሉ። ቤዛ ማለት እኮ ምትክ ማለት ነው። ምትካችን የሞተው  ኢየሱስ እንጂ የሞተበት መስቀል አይደለም። ይቀጥሉና "ንሰግድ ለመስቀለ እግዚዕነ ኢየሱስ” ኢየሱስ ለተሰቀለበት መስቀል እንሰግዳለን" ይላሉ። ይሄ ታላቅ ስህተት ነው። እንዴት ግኡዝ ለሆነ ነገር ይሰገዳል ብላችሁ ብትጠይቁ የምታገኙት መልስ ደሞ "ጌታ በደሙ ስለቀደሰው" የሚል ይሆናል። ነገር ግን ጌታ መስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰው ሰውን ለመቀደስ እንጂ መስቀሉን ለመቀደስ አይደለም። ቃሉ መቼ መስቀሉን ቀደሰው ይላል? ከተሰቀለበት የተሰቀለልን እንበልጣለንና ለመስቀል አይሰገድም!

የተሰቀለበት የተሰቀለውን ኢየሱስን ብዙዎች እንዳያዩ  ጋርዶታል። አይናችንን ዋጋ በከፈለው ላይ እንጂ ዋጋ በከፈለበት ቦታ ላይ አናድርግ። የወንጌል ስብከት ስለ ኢየሱስ እንጂ ስለ መስቀል አይደለም። በመስቀሉ አዳነን ማለት መስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ እንጂ መስቀሉን እንደ ማዳኛ ተጠቀመው ማለት አይደለም። መስቀል የተከፈለልኝን ዋጋ የሚያስታውሰኝ ሲሆን መዳኔ ግን በኢየሱስ ብቻ ነው እንበል። መስቀሉን ስናይ የተከፈለልንን ዋጋ እናስብ።

"በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና" 1ኛ ቆሮ - 2፥2
                ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega    
@elgraceministry
@Elgracebot          
@surtsega
         @surafeltsegamets


አንተ እግዚአብሔር
ስትመለክ የምትኖር(×፪)

ቅዱስ ቅዱስ እያሉህ
መላዕክት ቀንና ሌት የሚጠሩህ
ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች
ወድቀው ፊትህ ሚሰግዱልህ
አንተ እግዚአብሔር አልፋ ዖሜጋ
በእርግጥም አንተ ነህ
የምትከፍት የምትዘጋ
የሲዕልና የገነት ቁልፍ በእጁ ያኖረ።

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets


#የማይመስል_ነገር

የማይነጋ እንዳልመሰለን ጭጋጉ የማይገፈፍ
ማዕበሉ አውራቂስ ሱናሚ ሲመስል የማይታለፍ

ጌታ
በደጋግ አይኖቹ አየን፤ ምልጃችንን ጆሮው አደመጠ
እጆቹ አጽንተው ያዙን፤ ያራወጡንን እርሱ አናወጠ።

ራርቶ የተሸከመን፤ ጉልበቱ የማትዝል ጌታ
እንሻገር ብሎን፤ ቢመስለን ረስቶን የተኛ
እንቆቅልሻችንን፤ ቋጠሯችንን ችሎ የማይፈታ
ግድየለም
እርሱ ማን ነው
የሚያሰኝ መጎብኘትን ይጎበኘናል
የዘገየ በመሰለን ማዕበል ላይ ይደርስልናል።

#ይደርሳል
                  ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets


Forward from: ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️
አዲሱን አስረጅተሃል!
(ድንቄም አዲስ)😊
----◉-----
ከበርናባስ በቀለ

አንተ እግዚአብሔር "እዚያ" የምትለው ስፍራና "ወደፊት" የምትለው ጊዜ የለም። ለአንተ ለኢ-ውስኑ አምላኬ ሥፍራዎች ሁሉ እዚህ፣ ጊዜያትም ሁሉ "አሁን" ናቸውና ያልኖርኳቸው ዘመኖቼ ሁሉ በፊትህ "እዚህና አሁን" ናቸው።

አዲስ ያልሁት ዓመት (2017) በዘንድህ ያረጀ፣ ይመጣል ያልሁትም ዘመን በፊትህ ያለፈ ነው። ምጡቅ ነህና ከጅማሬው ፍጻሜውን ተናግረሃል፣ ረቂቅ ነህና ከቀኖቼ ቀድመህ ኖረሃል፣ ከዘላለም ነህና አዲስ ያልሁትን አስረጅተሃል!

ድንቄም አዲስ!
አዲስስ አንተው ራስ ነህ!


ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊


እንኳን አምላክ ተሸክሞ የ2016ዓ.ም የጠላቶቻችንን አሻጥሮችን በድል አሻገረን።
ለመውረስም ዓመት በጤናና በድል አዘለቀን።

የተወደደውን የአዲሲቷን ከተማ መብራት የጽድቅ ፀሐይ የምስራቅ ኮከብ የሆነውን ኢየሱስን የምናይበት ይሁንልን።

የተነገረልንን ማቀፍ ይሁንልን።
የተናገርነው ቃል የተወደደ ይሁንልን
ሞገስን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንጥገብ።
እንሰማ፤ እንደመጥ።
ከሰሙን ሁሉ ጋር ያለአንዳች ቋንቋ መደበላለቅ መረዳዳት ይሁንልን።

ልባችንን በቅንነት አምላክ ይጠብቅ።
እግዚአብሔር ቀኙን ይስጠን።
እጁም ከእኛ ጋር ትሁን።
ድንበራችን ይስፋ።
እግዚአብሔርን እንዳንበድለው ጸጋ ከትላንት ዛሬ ይልቁም ይብዛልን።

የሰማነውና የምንሰማውን ሁሉ የምንቋቋምበትን ጸጋ ይብዛልን።
የጠላቶቻችን በትር በራሳቸው ላይ ይዙር።

የእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ዘወትር ይከተሉን።
ዘወትር ስለሁላችን የሚታየውን ሊቀ ካህንን ምናልቅበትን መንፈሳዊ መረዳትን በመሞላት እንባረክ።

በአብርሃም በይስሃቅ በያዕቆብ አምላክ ዘንድ #መታሰብ ይሁንልን።

"ዮሴፍም ወንድሞቹን አለ፦ እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም #መጎብኘትን_ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር #ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር #ያደርሳችኋል።
ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፦ #እግዚአብሔር_ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ አማላቸው።”

ዘፍጥረት 50፥24 - 25

ዓመቱ
#የመታሰብ (የመውጣት የመድረስና የመውረስ) ዓመት ይሁንላችሁ።

           ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets


#መዳኛ_ነህ_መዳኛ

📍 የኃጥኤ መንገድ ቢመስልም የሰመረ 📌
📍ከፍጻሜው ማማ ሞት እንደ ተቀበረ 📌
📍 ቢበራለት አዳም እንዲህ ባለሰከረ ‼️

ይበራለት ዘንዳ እንማልድለት አሁን
መዳኑን እንዲያቀና በክርስቶስ በኩል።

ተጻፈ ©በሱራፌል (ጸጋ)


Forward from: ሱራፍኤል ወርቁ ፀጋ
━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets


Moto of my soul too;

I Believe In a Sun Even When It Is Not Shining
I Believe In Love Although I'm Alone.
I Believe In God Even When He Is Silent.

#I_never_lose_Faith



              @elgraceministry
              ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega 
@surtsega
@surafeltsegamets




#መልካም_ልደት

#ህያቤ
#እያ
#ከላይ
#እናት
#ውዴ
ምን ስልሽ የሚያንስብሽ ስጦታዬ
የእናት ምትክ የሚስትነት መለኪያዬ።

ቃልኪዳን ነሽ ዳግም አለም
የመረቀሽ መድሃን የአለም።

በክፉ ቀን ደስታን አስታጣቂ
ቸር መሆንን የምትፈነጥቂ
ልባሟ ሴት የቤትሽ መርከበኛ
የባልሽ ዘውድ የትውልድሽ ነሽ መጽናኛ።

መወለድሽ በረከትን ያዘለልኝ፤
ለዕድለኛሽ ለማፈቅርሽ፤ ዕልፍ ኑሪልኝ፤
ሰንብቺልኝ።

ክፉ አይንካሽ በክፉ ቀን
ይረከብሽ ያዛለቀን

ወልደሽ ሳሚ፤
ፍሬዎችሽ በማዕድ ዙርያ ይቀመጡ
ፈልገው አንዳች ነገር ከአንቺ አይጡ።

ኑር ሰንብቺ ራዕይሽ መሬት ይንካ
ሳቅ ደስታሽ በሰው ልስዓን አይለካ

በወደደሽ በአምላክሽ ተቀጠሪ፤
ጥቂት ዘርተሽ ዕልፍ አፍሪ
ከዘለቁት ተቆጠሪ።

አሜን ለአንቺ።



©ሱራፌል ለማፈቅርሽ ውድዋ ባለቤቴ


🤔🤔🤔 #መገረሚያዬ_ነው። 🤔🤔🤔
(በመገረም በመደነቅ በመሸነፍ ልሳን አልባ ሆኜ ቀረሁ
እርሱ መሳይ ስላላየሁ። 😭😭)

🤔
ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።

ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?

አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።

ኢሳይያስ 40 ፥ 26 - 28
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

(ኧረ ኡኡ ልሳን አልባ ፥ ቃላት ዕጦት፤
ያለኝ ሁሉ ፥ መቼ ገልጾት።
ምንም እርቃን አምልኮዬ መጥኖ አንተን አይለካህም
የኔ ቅኔ ለአንተ በቅቶ ጨርሶ አንተን አይስልህም።)

               ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets


😍😍 #የሞትም_አለቃ 😍😍

የምስጋና ቅኔ እንዳጎድል ከአፌ
በከንቱ ላትረክስ
ለውዳሴ ቀስቃሽን ላትሻ
የወድድካት ነፍሴ
የዘወትር ትውስታዬን
አድርገው በሞትህ መትረፌ፤
አንተ መቃኔ ላይ ታይተህ
በሞት መታለፌ።

ሞት ሆይ መውጊያህ የታል
ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህሳ??
ብዬ ምጮህበት የድል ቀን ችቦዬ
የማይቋረጠው የማይደበዝዘው ዜማዬ
ኢየሱስ ክርስቶስ
የዘላለሙ ባለድል ይሁን ትዝታዬ።

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets


#አብዶ_ነው_የሞተው

"እግዚአብሔር ሞቷል፤
እንደሞተም ቀርቷል፤
እኛም ገድለነዋል"
ብሎ የተፈላሰፈው
ኒቼ የተባለ ሰው
አብዶ ነው የሞተው።

ግጥም
በ'ሐንኤል

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry


#መልካም_የመለየት_በዓል

ለመላው ቤተሰብና ወዳጆቻችን በሙሉ፥
ይህ የተወደደው ቀን ከብዶን የከረመው የተንከባለለበት፤ ያስፈራን የተገፈፈበት፤ የለም ብለን ያስደነገጠንን ደግሞ ህያው ሆኖ ያገኘንበት  ታላቅ ዕለት ነውና ዛሬም እንደገና ትንሳኤ ይሁንልን።

“ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥” ሉቃስ 24፥2

“እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።”
  — ማርቆስ 16፥6

ሱራፌል እና ቃልኪዳን(እያ)
            ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets
            ━━━━⊱✿⊰━━━━━


*             ━━━━⊱✿⊰━━━━━              *
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets
*             ━━━━⊱✿⊰━━━━━              *


Part two.

17. As the six hours of the #Crucifixion wore on, Jesus was less and less able to bear His weight on His legs, as His thigh and calf muscles became increasingly exhausted. There was increasing dislocation of His wrists, elbows and shoulders, and further elevation of His chest wall, making His breathing more and more difficult Within minutes of crucifixion Jesus became severely dyspnoeic (short of breath).

18. His movements up and down the Cross to breathe caused excruciating pain in His wrist, His feet, and His dislocated elbows and shoulders.

19. The movements became less frequent as Jesus became increasingly exhausted, but the terror of #imminent_death by asphyxiation forced Him to continue in His efforts to breathe.

20. Jesus’ lower limb muscles developed excruciating cramp from the effort of pushing down on His legs, to raise His body, so that He could breathe out, in their anatomically compromised position.

21. The pain from His two shattered median nerves in His wrists exploded with every movement.

22. Jesus was covered in blood and sweat.

23. The blood was a result of the Scourging that nearly killed Him, and the sweat as a result of His violent involuntary attempts to effort to expire air from His lungs.
Throughout all this He was completely naked, and the leaders of the Jews, the crowds, and the thieves on both sides of Him were jeering, swearing and laughing at Him. In addition, Jesus’ own mother was watching.

24. Physiologically, Jesus’ body was undergoing a series of catastrophic and terminal events.

25. Because Jesus could not maintain adequate ventilation of His lungs, He was now in a state of hypoventilation (inadequate ventilation).

26. His blood oxygen level began to fall, and He developed Hypoxia (low blood oxygen). In addition, because of His restricted respiratory movements, His blood carbon dioxide (CO2) level began to rise, a condition known as Hypercapnia.

27. This rising CO2 level stimulated His heart to beat faster in order to increase the delivery of oxygen, and the removal of CO2

28. The Respiratory Centre in Jesus’ brain sent urgent messages to his lungs to breathe faster, and Jesus began to pant.

29. Jesus’ physiological reflexes demanded that He took deeper breaths, and He involuntarily moved up and down the Cross much faster, despite the excruciating pain. The agonising movements spontaneously started several times a minute, to the delight of the crowd who jeered Him, the Roman soldiers, and the Sanhedrin.

30. However, due to the nailing of Jesus to the Cross and His increasing exhaustion, He was unable to provide more oxygen to His oxygen starved body.

31. The twin forces of #Hypoxia (too little oxygen) and #Hypercapnia (too much CO2) caused His heart to beat faster and faster, and Jesus developed #Tachycardia.

32. Jesus’ heart beat faster and faster, and His pulse rate was probably about 220 beats/ minute, the maximum normally sustainable.

33. Jesus had drunk nothing for 15 hours, since 6 pm the previous evening. Jesus had endured a scourging which nearly killed Him.

34. He was bleeding from all over His body following the Scourging, the crown of thorns, the nails in His wrists and feet, and the lacerations following His beatings and falls.

35. Jesus was already very dehydrated, and His blood pressure fell alarmingly.

36. His blood pressure was probably about 80/50.

37. He was in First Degree Shock, with #Hypovolaemia (low blood volume), #Tachycardia (excessively fast Heart Rate), #Tachypnoea (excessively fast Respiratory Rate), and #Hyperhidrosis (excessive sweating).

38. By about noon Jesus’ heart probably began to fail.

39. Jesus’ lungs probably began to fill up with Pulmonary Oedema.

40. This only served to exacerbate His breathing, which was already severely compromised.

41. Jesus was in Heart Failure and Respiratory Failure.

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets
━━━━⊱✿⊰━━━━━

20 last posts shown.