"የወንጌልን እውነት ያልተረዱ ሰዎች በድፍረት “መስቀል ቤዛነ” እንዲሁም "መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ" ይላሉ!!" ዲያቆን ኤርሚያስ ኪሮስ
(AmlekoTube - አምልኮቲዩብ እንዳጋራው)
መስቀል ትልቅ ኃጢአት የሰሩና የተረገሙ ሰዎች መቀጫ ነው። ጌታ ኢየሱስ ኃጢአታችንና መርገማችንን ተሸክሞ በመስቀል ላይ ተቀጣ። መስቀሉ እኛና ኢየሱስን የተቀያየርንበት ቦታ ነው። የኛን ኃጢአት ወስዶ ጽድቁን፤ ፍርዳችንን ወስዶ ምህረትን፤ መርገማችንን ወስዶ በረከትን፤ ሞታችንን ወስዶ ህይወቱን ሰጠን። ውርደታችንን ተቀብሎ ሰማያዊውን ክብር አጎናጸፈን። "በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤" ገላ - 3፥13 መስቀል ይህ ድንቅ ነገር የተፈጸመበት ቦታ ነው። ስለዚህ መስቀሉ ይሄን ታላቅ እውነት ድንቅ ፍቅር የምናስታውስበት ምልክት (Symbol) ነው።
ከዚህ ውጪ መስቀሉ ምንም አይነት ሚና የለውም። የወንጌልን እውነት ያልተረዱ ሰዎች በድፍረት “መስቀል ቤዛነ” እንዲሁም "መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ" ይላሉ። ቤዛ ማለት እኮ ምትክ ማለት ነው። ምትካችን የሞተው ኢየሱስ እንጂ የሞተበት መስቀል አይደለም። ይቀጥሉና "ንሰግድ ለመስቀለ እግዚዕነ ኢየሱስ” ኢየሱስ ለተሰቀለበት መስቀል እንሰግዳለን" ይላሉ። ይሄ ታላቅ ስህተት ነው። እንዴት ግኡዝ ለሆነ ነገር ይሰገዳል ብላችሁ ብትጠይቁ የምታገኙት መልስ ደሞ "ጌታ በደሙ ስለቀደሰው" የሚል ይሆናል። ነገር ግን ጌታ መስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰው ሰውን ለመቀደስ እንጂ መስቀሉን ለመቀደስ አይደለም። ቃሉ መቼ መስቀሉን ቀደሰው ይላል? ከተሰቀለበት የተሰቀለልን እንበልጣለንና ለመስቀል አይሰገድም!
የተሰቀለበት የተሰቀለውን ኢየሱስን ብዙዎች እንዳያዩ ጋርዶታል። አይናችንን ዋጋ በከፈለው ላይ እንጂ ዋጋ በከፈለበት ቦታ ላይ አናድርግ። የወንጌል ስብከት ስለ ኢየሱስ እንጂ ስለ መስቀል አይደለም። በመስቀሉ አዳነን ማለት መስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ እንጂ መስቀሉን እንደ ማዳኛ ተጠቀመው ማለት አይደለም። መስቀል የተከፈለልኝን ዋጋ የሚያስታውሰኝ ሲሆን መዳኔ ግን በኢየሱስ ብቻ ነው እንበል። መስቀሉን ስናይ የተከፈለልንን ዋጋ እናስብ።
"በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና" 1ኛ ቆሮ - 2፥2
━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega
@elgraceministry
@Elgracebot
@surtsega
@surafeltsegamets