የተወደድክ ዘማሪ በረከት ተስፋዬ ጌታ በቤተክርስቲያችን ጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን የተጠቀምከውን ስላጋራኸን እናመሰግናለን።
እርግጥ ጸጋ ቃለህይወት ቤተ ክርሰቲያን ማንን አፈራች፤ የማንንስ ጸጋ አቀጣጠለች፤ ለማንስ ክህነት ቅዱስ ስፍራ ሆነች?
እርግጥ ነው ብዙዎችን ያስጠለለች የታላላቅ ፍሬዎች መጠለያ ናት።
ለብዙዎች የተረፈች፤ የተቸገሩትን የረዳች፣ የታረዙትን ያለበሰች፣ ደካሞችንም የደገፈች፣ የታሰሩትን የጠየቀች፣ ያዘኑትን ያጽናናች፣ መበለቶችን የጠየቀችና ወላጅ አልባ ልጆችን ያሰበች የሰማይ መንግስት የምድር ወካይ/አምባሳደር ነች።
ጌድዮን እውነቱ፤ ዳንኤል እውነቱ፣ ክርስቲያን ግርማ በ90's የደመቁ የመዝሙር አቀናባሪዎችና ሙዚቀኞችን ያፈራች ቤተክርስቲያን ናት።
''አማኑኤል አማኑኤል
ከእኛ ጋራ ያለው
ስሙ ድንቅ መካር
ኤልሻዳይ የሆነው
ኢየሱስ ነው''
የሚለውን ዝማሬን ያበረከቱልንን ''ለ'' መዘምራንን
እና
''በእኛ ላይ ታላቅ ምህረትህ ጥበቃህ ስለበዛ
ጌታ ሆይ ልንልህ ቻልን ልንጠራህ በምስጋና
ዛሬም እንደገና''
የሚለውን ዝማሬ ያበረከቱልንን ''ሀ'' መዘምራን ህብረትን ያበረከተችልን ቤተክርስቲያን ናት።
ለመቁጠር የሚያዳጎቱ የቤተክርስቲያን አባቶችና እናቶች ያሏት ቤተክርስቲያኒቷ በጉብዝናቸው ወራት የቤተክርስቲያን ተከላ በአራቱም አቅጣጫ የሮጡና የተሰካላቸውን አባቶችንና እናቶችን አፍርታለች።
ተስፋዬ ጫላ ፣ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል፣ በረከት ተስፋዬ፣ ለምለም ንጋቱ ፣ ርኆቦት አለማየሁ እና የመሳሰሉ አንጋፋ ዘማሪዎችን ላፈለቀው አቤኔዘር (ጂሲኤ) የተማሪዎች ህብረት አዳራሽዋን ዛሬም ድረስ ከፍታ ታስተናግዳለች።
ቤተክርስቲያናችን እንደቃሉ ያሉ ልምምዶችንና ትምህርቶችን አንጥራና መዝና የምታስተምር አጥቢያ ስትሆን ከአቤኔዘር የተማሪዎች ህብረት ጋራ ቤተክርስቲያናችን ወንጌልን ዛሬም በትጋት የምታገለግልና የወንጌል ታላቅ ተልዕኮነቱን ሳትዘነጋ ለመዘርጋት የምትጥርና የምትታትር የጥንት ቤተክርስቲያን ናት።
በነገራችን ላይ GCA ከሚለው ውስጥ G stand for Grace (ጸጋ) መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናውቅ ይሆን? የት/ት ቤቱ አመሰራረት ከቤተክርስቲያኗ ጋራ መቆራኘቱስ?
ለወንጌል ተልዕኮ ከውጪው ዓለም ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጡት ሚሽነሪዎች ት/ቤቱ መስርተው ተልዕኳቸውን ሲወጡ ሳሉ፥ በተፈጠረው የመንግስት ለውጥ ከሀገር ሲወጡ፥ መሬቱን ለቤተክርስቲያኒቷ ቢሰጡም በሰዓቱ የነበረው አብዮታዊ መንግስት ስሙን ከመቀየረ የጀመረ ንጥቂያ አድርጎ ቤተክርስቲያኒቷ እንድትዘጋ አድርጎ ነበረ።
ነገር ግን ሳትዘጋ በሌላ ስፍራዎች የቀጠለችና እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በብዙ ውጣውረዶች ያለፈችና የተነጠኩትን መሬት መልሱልኝ ስትል ጆሮ ዳባ የተባለች ብትሆንም፤ ለሁሉም ዕምነት ተቋም መሬት በተሰጠ ጊዜ የመሬት ልማት የሰጣትን ስፍራ አሁንም በአንድ ስፍራውን በያዘ #ግለሰብ ምክንያት ቤተክርስቲያኒቷ ዛሬም መብቷን እየተገፈፈች ትገኛለች።
ቅዱሳን ፍትህ ለጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስትያን እንድትጠይቁልን እና አጥብቃችሁም እንድትጸልዩ አደራ እንላለን።
ጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን (የብዙዎች እናት ቤተክርስቲያን) አሻራዋ ያለባችሁ ሁሉ በጸጋችሁ መጥታችሁ አብረን እንድናገለግል ቤተክርስቲያኒቷ ጥሪዋን ታሰማለች።
ቤተክርስቲያኒቷም ዛሬም ከወትሮ ጠንክራና አብልጣ አምልኮን የጨመረች ሲሆን የአምልኮ ኘሮግራሞቿም
ሰኞ ማለዳ ፦ የእናቶችና እህቶች ኘሮግራም
ማክሰኞ ማለዳ ፦ የጾም ጸሎት ኘሮግራም
ሐሙስ አመሻሽ ፦ የቃል እና የትምህርት ጊዜ
ቅዳሜ አመሻሽ ላይ ፦ የወጣቶች ኘሮግራም
እሁድ ማለዳ ፦ የዘወትር የሰንበት ኘሮግራም
ኑ በጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን በሚመቻችሁ የአምልኮ ኘሮግራም ተሰባስበን ከቃሉ ማዕድ እንቋደስ።
በጸጋ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን (ጸጋ) የተጠቀመ ሌላ ምስክርነት ካለ አጋሩን🙏
አድራሻችን ከጂሲኤ ት/ት ቤት አልያም ከጎተራ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጀርባ
@surafelgrace